Wednesday, August 20, 2014

የ ኢቦላ ቫይረስ በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ያስተላለፉት ቀጭን ትዛዝ አነጋጋሪ ሆኖዓል።

ሄኖክ የሺጥላ
MSF-ebola-guinea_2872612bበምዕራብ አፍሪካ የተነሳውን የኢቦላ ቫይረስ ተከትሎ የተለያዩ ሃገራት ወረርሽኙ ወደታየባቸው ሀጋሮች የሚያደርጉትን ማንኛውም አይነት የአየርም ሆነ የየብስ፣ የንግድና የቱሪዝም ፣ የትምህርትና የስልጠና እና ሌሎችንም አይነት የንግድ ይሁን መሰል ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች አቁመዋል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ግን ፣ አይዞዋችሁ ፣ ወደተባለው አደገኛ መንደር መሄዱ አይደልም መፈራት ያለበት ፣ መፈራት ያለበት ቦሌ ላይ የምናደርገው የቁጥጥር ስርዓት ነው ፣ በዚህ ደሞ ሃሳብ አይግባችሁ እኛ እንኩዋን ኢቦላን አንዳርጋቸው ጽጌንም ቢሆን ይዘናል እያሉን ያሉ ይመስላሉ። አክለውም እንደው ባጋጣሚ ይሄ ኢቦላ የተባለው ቫይረስ ቢገኝ እንኩዋ ባ’ስር አልጋና በሃያ ዶክተሮች ታጥቀን እየጠበቅነው ነው እያሉ ነው። የዓለም የጤና ድርጅት “The World Health Organization (WHO)” ቫይረሱ ሊያመጣ የሚችለውን እልቂት እየተናገረ ፣ በይበልጥም የህክምና ጠበበብቶች በአማካይ ለ 21 ቀናት ቫይረሱ ምንም አይነት የበሽታ ምልክት ሳያሳይ በተጠቂው ግለሰብ ላይ የመቆየት እቅም እንዳለው እየተናገሩ፣ የኛ ጠቦቶች ( ማለቴ ጠበብቶች ) ግን ተጠቂውን ( ወይም ለነሱ ታጣቂውን ) የምንለይበት ልዩ ዘዴ ስላለ አትቸገሩ እያሉን ነው።
እኔ እምለው ኢቦላም ላይ ከፍተኛ ክትትል ለማድረግ በሽታው ከዔርትራ መነሳት ነበረበት ማለት ነው? መንግሥቴ ምነው ያልተጠመደ ቦንብ ከምታፈነዳብን ምናለ ይቺን ኢቦላ ከመፈንዳቱዋ በፊት ብታክሽፍልን ? ወይስ የምርጫ ታዛቢዎች ወደ ሀገሪቱዋ እንዳይገቡ ለማድረግ እየተዶለተ ያለ ነገር አለ? መቼም እናንተ እኮ ስለ ሰው ሕይወት ያላችሁ ግንዛቤ ጅብ ስለ አህያ ስጋ ያለውን ያህል ግንዛቤ እንደማይሆን እጠረጥራለሁ ። እኔን የገረመኝ ግን እነዚያ 20 ዶክተሮች እነማን ይሆኑ ? ምናልባት ስርዓቱን በመቃወማቸው የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ምስኪኖች?
ለማንኛውም ኢቦላ ክላሽንኮቭ ተሸክሞ ፣ ቦምብ ታጥቆ ፣ በጾረና በኩል የሚመጣ ዋርድያ ወይም ጀሌ ወይም ማንጁስ አይደለም ፣ የኢቦላን ምንነት ለመረዳት ቢያንስ ሚንስትሪን ማለፍ የግድ ይላል ። በአምስተኛ ክፍል እውቀት ግን እንኩዋን ኢቦላን የሆድ ድርቀትን መረዳት የሚከብድ ይመስለኛል ። ለናንተ አይነቱ ድፍን መሀይም የዚህ በሽታ ጥፋት እና ክፋት ሊታያችሁ ያልቻለው ደሞ ነገሮችን ሁሉ የምታዩት የታንክ ሰንሰለት ባያችሁበት አይናችሁ ስለሆነ ነው ። ህዝቡ ግን ዝም ብሎ እንደሚታረድ በግ የሆነ ይመስለኛል ። ማን ያውቃል መጥፍያችሁስ ቢሆን

በአንዋር መስጊድ ብጥብጥ ታስረው የነበሩ ተጠርጣሪዎች በሙሉ በዋስ ተፈቱ

-ተጐጂዎች ከሆስፒታል ቢወጡም በደንብ እንዳልዳኑ ተገልጿል
A060C843-8BC6-416E-ABAE-9D48E9F5B7AF_w640_r1_sበአንዋር መስጊድ ብጥብጥ በፖሊስ አባላትና በተወሰኑ ሰዎች ላይ ደርሷል በተባለ ከባድና ቀላል ጉዳት ለአንድ ወር ያህል ታስረው የከረሙ ሁሉም ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው የአምስት ሺሕ ብር ዋስ በማስያዝ እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡
ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. በዕለተ ዓርብ በጁምአ ፀሎት ላይ በተነሳ ብጥብጥ፣ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ተጠርጣሪዎች በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል፡፡ በወቅቱ በነበረው ብጥብጥ ሰላም ለማስከበር በተሰማሩ የፖሊስ አባላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንና በተለይ ሁለት ፖሊሶች ኮማ ውስጥ መግባታቸው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪ ፖሊሶች ሲገለጽ ከርሟል፡፡
በጥርጣሬ የተያዙት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ታሳሪዎች በየክፍላተ ከተሞቹ በተቋቋሙ ጊዜያዊ ፍርድ ቤቶች የወንጀል ተሳትፏቸውን በማጣራት የተለቀቁ ሲሆን፣ 24 ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ኮሚሽን ሥር ሆነው ጊዜ ቀጠሮ እየተጠየቀባቸው በእስር ላይ ቆይተዋል፡፡ እስካለፈው ሳምንት ድረስ አራት ተጠርጣሪ የፖሊስ አባላትን ጨምሮ 18 ተጠርጣሪዎች በመታወቂያ ዋስትናና በአምስት አምስት ሺሕ ብር ዋስ ተለቀዋል፡፡ ቀሪዎቹ ስድስት ተጠርጣሪዎችም ነሐሴ 12 ቀን 2006 ዓ.ም. እያንዳንዳቸው የአምስት ሺሕ ብር ዋስ እያስያዙ እንዲፈቱ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነክ ሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
መርማሪ ፖሊስ ግን ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አባላትና ግለሰቦች ከሆስፒታል የወጡ ቢሆንም፣ ሙሉ በሙሉ አለመዳናቸውን በመግለጽ የሰባት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም፡፡

(Breaking News) 7 ጋዜጠኞች ሃገር ጥለው ተሰደዱ

ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው
ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው
(ዘ-ሐበሻ) መንግስት ሰሞኑን በነጻው ፕሬስ አባላት ላይ የጀመረውን ሰዶ የማሳደድ ተግባር ሰለባ የሆኑት 7 ጋዜጠኞች ሃገር ጥለው መውጣታቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው ሰበር ዜና አመለከተ::
ከሰሞኑ በፍትህ ሚ/ር ክስ የተመሰረተባቸው እነዚሁ ጋዜጠኞች የሎሚ መጽሔት, የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣና እና የጃኖ መጽሔት አዘጋጆች ሲሆኑ እነርሱም
1ኛ. ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው
2ኛ. ጋዜጠኛ ዳንኤል ድርሻ
3ኛ. ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ
4ኛ. ጋዜጠኛ አስናቀ ልባዊ
5ኛ. ጋዜጠኛ ሰናይ አባተ
6ኛ. ጋዜጠኛ ሰብለወንጌል መከተ
7ኛ. አቦነሽ
የተባሉ ሲሆን ዝርዝሩን ወደ በሁዋላ ይዘን እንመለሳለን::