Saturday, December 27, 2014

እየተደረገ ያለዉን በዘርኝነት ላይ የተመሠረተ የጥፋት ቃለ መሃላ ማክሸፍ የእያንዳንዱ እትዮጵያዊ ነኝ ባይ ሁሉ ግዴታ ነው ፤

ከአየነው ብርሃኑ
ኢትዮጵያዉያን የዉጭ ጠላት ሲነሳባቸዉ የዉስጥ ልዩነታቸዉን ወደ ጎን በመተዉ ጠላትን ድባቅ የመምታት አቅሙ እንዳላቸዉ የሩቅም ሆነ የቅርብ ታሪካችን ነዉ።
ከቅርቡ እንኳን ብንነሳ በሻቢያና ወያኔ የጥቅም ግጭት ምክንያት በተነሳ ጦርነት ሮጠዉ ያልጠገቡ ወጣቶች የፈንጅ ማምከኛ እየሆኑ ዉድ ህይወታቸዉን አሳልፈዋል።
ወያኔ ለራሱ ህልዉና ማጠናከሪያ ቢጠቀምበትም የጦርነቱ የመጨረሻ ዉጤት ለኢትዮጵያ ያደላዉ  ከኢትዮያዊነት ስሜት በመነጨ ወኔ መሆኑ አይዘነጋም።
አዎ ወያኔ እና ጀሌዎቹ ከኋላ ፤ በሺህዎች  የተቆጠሩ ወጣቶች ግን በግንባር ቅደምትነት ተሰልፈዉ የቦንብ ማምከኛ በመሆናቸዉ የጦርነቱ አቅጣጫ ተቀየረ። በዚህ እልቂት ኢትዮጵያዉያን እናቶች የሃዘን ማቅ ለበሱ። ወያኔም በሥልጣን መንበሩ ላይ መቆየቱን አረጋገጠ።
ጭር ሲል አልወድም የሚለዉ ወያኔ ዛሬም የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ ነው። የማይደፈር ሃይል መሆኑን ለማሳየትም በርጥባን ከጌቶቹ ያገኘዉን የጦር መሳሪያ ከቦታ ቦታ በማንቀሳቀስ ህዝብን በማሸበር ላይ ነዉ።
በጦር ሃይሉ ዉስጥ ያሉ የሌላ ብሄር የጦር መሪዎችን በማባረር በአንድ ዘር ላይ የተመሠረተ የግድያ እና የጥፋት ሃይሉን በማዘጋጀት ላይ ዪገኛል።
ለዚህ ተግባር የሚዉል  አዲስ ወታደራዊ ቅጥር  ጥሪ እያደረገ መሆኑ ዪታወቃል።
የኢትዮጵያ መሰረታዊ ጠላት ከሆነችዉ ሱዳን ጋር ወታደርዊ ስምምነት አደረኩ የጋራ ጦርም መሠረትኩ በሚል ለጥቂት ቀናት አደነቆረን።

ተጠቅሞ የጣላቸዉን የቀድሞ ሰራዊት አባላት ተመልሰዉ እንዲቀላቀሉት በተለያየ መንገድ ጥሪ እያደረገ ነው። ሁሌ እኔ ብቻ ላሞኛችሁ የሚል የደንቆሮዎች ዘይቤ። መልሱ ግን ሞኚህን ፈልግ ሆነ  !!
ለመሆኑ ይኸ ሁሉ የጦርነት ነጋሪት መጎሰም ከምን መጣ ? ይህ የድረሱልኝ ጥሪ መነሻዉ ምንድን ነዉ፡የዉጭ ጠላት አልወረረን!!!!!
የወንድ ልጅ ሞቱ የሚጀምረዉ ያደረገዉን የረሳ ጊዜ ነው ይላሉ አበዉ ሲተርቱ።
ሃብት አደንቁሮአቸዋልና !! ወያኔን ለማጥፋት አዲስ አበባም ጫካ መሆኑን ለመገንዘብ የዕዉቀት አድማሳቸዉ አልፈቀደላቸዉም ።
ያም ሆነ ይህ ግን ምኞታቸዉ የተሳካ ጥያቂያቸዉም በአግባቡ እየተመለሰላቸዉ ባለበት ጊዜ ላይ ደርሰዋል። የስብሃት ነጋ የዘር ጥላቻ፡ የአባይ ጸሃየ የዕምነት ተቋማትን የማፈራርረስ ሴራ፤የአዲሱ ለገሰ ከጡረታ መመለስ ከውዲያ ወዲህ መፈራገጥ፤ የበረከት በስብሰባ ላይ ራሱን ጥሎ ከመዉድቅ  ዉጭ ፋይዳ ያለዉ ሥራ ለመከወን  ከማይችልበት ደረጃ ላይ መድረስ  ወይም ደግሞ ብአዴን በግንቦት ሰባት  ኦህዴድንም በኦነግነት መፈረጅ ከዉድቀት አያድናቸዉም ።
የእነ ደብረጽዮን እና ጌታቸዉ አሰፋ ድንበር ዘለል የዉንብድና ተግባር አልፈየደም ። የህዝብ ወገኖችን እያደኑ መያዝ፡ በአለም ላይ አለ የተባለ የማሰቃያ መንገድ ሁሉ በታጋዮች ላይ እንዲፈጸም ማድረግ በተጠናወታቸዉ የዘር ጥላቻ  እየተወጠሩ ለመኖር እና ያለ አግባብ በተካበተ  የሀገር ሃብት እየተንደላቀቁ ለመኖር  መፍትሄ አልሆነም።
በሌላ መልኩ  የመሃል አገር ህዝብ የወያኔን የከፋፍለህ ግዛ ዘይቤ በመበጣጣስ አንድነቱን አጠናክሮ ወያኔን ጥግ ማስያዝ ከጀመረ ሰነባበተ ። የህዝብ ጉልበትም መጎልበትና መፈርጠም ጀምሮአል ።
ሰላሙና ተቻችሎ መኖሩ ይበጃል በሚል እንጂ ለሌላዉማ ከእናንተ በተሻለ  እኛም እናዉቅበታለን የሚሉ አንበሶች ብቅ ብቅ ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል።  አንድነታቸዉንም  አጠናክርው ለመጨረሻዉ ፍልሚያ በትጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ ።
ለዚህም  የትግራይ ረመጦች በአንድ በኩል የግንቦት 7 ፤ የአርበኖች ግንባርና ሌሎችም አንበሶች በሌላ በኩል ለዎያኔ እኩይ ተግባር ምላሽ ለመስጠት ዝግጅታችንን ጨርሰናል በሚል የድል ችቦ እየለኮሱ ያሉት ህያዉ ምስክር ነው።
ወያኔ አንድ አርጋቸዉንና ሌሎችንም በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ያዘ፤ አሰቃየ ፤ የአካልም የመንፈስም ጉዳት አደረሰ ይህን ሲያደርግ ግን ያለኪሳራ አይደለም። መቃብሩን እየቆፈረ መሆኑን  ራሱ ወያኔም ያዉቀዋል ።
ለትግራይ ረመጦችና  ለግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል መጠናከር መሠረት የሆነዉን  አንዳርጋቸዉ ነዉና ። አንዳርጋቸዉን መያዝና ማሰቃየት ዉድቀቱን እያፋጠነለት መሆኑን ወያኔ ራሱ ከተረዳዉ ቆይቶአል።
በሌላ በኩል እስኪ የዘርኝነት መሃንዲሶቹን አንድ አንድ ጥያቄዎች እንጠይቅ፡
ይኸ የህዝብ ትግል  የጦርነት ነጋሪት በመጎሰምና የድረሱልኝ ለቅሶ በማላዘን ወደ ኋላ ይቀለበስ ይሆን እንዴ አቶ ስብሃት?
የስንት ቀን ፋታ የምታገኙ ይመስልሃል አቶ አባይ?
በርግጥ የአንተና የስዩም መስፍን ማገገም፡ ወደ ሥራ መመለስና  መንፈራገጥ መፍትሄ  ይሆን እንዴ አቶ አዲሱ ለገሠ?
ሃዉልትህ  ምትሃታዊ ሃይል ኖሮት የልቀቁኝ በቃኝ ጥያቄህን  ወደ ኋላ እንድትል ይረዳህ ይሆን ጀኔራል ሳሞራ?
በአፈናና በስቃይ ተግባራችሁ ግለሰቦችን ከማሰቃየት በዘለለ የህዝብን ትግል አፍናችሁ  ከዛሬ  ነገ ምን ይከሰት ይሆን ከሚለዉ የፍርሃት ቆፈናችሁ የምትላቀቁ ይመስላችኋል እነ ደብረ ጽዮን ፤ ጌታቸዉ በላይ እና የአፈና ቡድናችሁ?
በጭራሺ ከንቱ ድካም። ከንቱ ልፋት። የኢትዮጵያ ህዳሴ መቃረቡን የህዝብ የነጻነት ጮራ እየፈነጠቀ መሆኑን ምነዉ ያኔ የሱዳኑ አባታችሁና የአምልኮት ጣኦታችሁ ሲሞት በቀብር የተገኙት እነስዩም መስፍን አልነገሯችሁም ነበር እንዴ?
ኢትዮጵያዉያንን እርስ በርስ ለማገዳደል እያሰባችሁ ያላችሁት የጥፋት ድግስ የማይሳካ ጊዜዉ ያለፈበት ዘዴ ነው። የተበላ እቁብ !!!
በሀገራዊ ስሜትም ሆነ በግል የኢኮኖሚ ችግርህ አሁን ያለዉን የመከላከያ ሠራዊት የተቀላቀልክ ጭቁን የኢትዮጵያ ሠራዊት አባል ቆም ብለህ አስብ። እነዚህ የቀን ጅቦች ለጥፋት እያዘጋጁህ መሆኑን ለአንዲት ደቂቃም ቢሆን መዘንጋት የለብህም።
የባህር በር እጠብቃለሁ እንዳትል ወያኔ አገርህን የባህር በር አልባ አድርጎልሃል። ድንበር አስከብራለሁ እንዳትል ወያኔ የአገርህን ድንበር እየቆራረጠ ለአገራችን ጠላቶች ለገጸ በረከትነት እያቀረበልህ ነው።
ወያኔ ወኔህን ሰልቦ ብሄራዊ ወኔህን ገፎታል። እንድ ለአምስት እንድትደራጅ ፡መሪህ ከወርቁ ዘር የወጣዉ  ብቻ እንዲሆንና አንተ አንድ ካርታ ጥይት ብቻ እንዲኖርህ መሪህ ግን እስካፍንጫዉ እንዲታጠቅ እየተደረገ ያለዉ ለምን ይመስልሃል። በዚህ አይነት ጥርነፋ ከወገኖችህ ጋር እንድትዋጋ ከኋላ ሆነው ሊነዱህ እንደሆነ ግን ተገንዝበኸዋል?
ይኸን ከንቱ የወያኔ ምኞት ለማክሸፍ ከነጻነት ታጋዮች ወገኖችህ ጋር ጊዜ ሳትሰጥ ተቀላቀል።
ይህን በማድረግህ አገርህን ከነዚህ የባንዳ ዉላጆች ነጻ ታወጣለህ ። በስቃይ ላይ የለዉን ወገንህን እንባ ትጠርጋለህ።
በዘር ማንነት ፖለቲካ ተሰብካችሁ ከሌላዉ በበለጠ ጀግንነት የእናንተ ብቻ እንደሆነ እየተሰበካችሁ ያደጋችሁ የመሪነት ቦታዉን የያዛችሁና እኛ ከኋላ ሆነን ሌላዉን ኢትዮጵያዊ ከፊት በማሰለፍ የጌቶቻችንን የስልጣን ዕድሜ እናራዝማለን ብላችሁ  በዘር ላይ የተመሠረተ  ቃለ መሃላ የፈጸማችሁ ። ይህ መሃላ ግን መፈራረሱን ወደ ህዝብና ወደ ህሊናቸዉ ተመልሰዉ ወደ ዕዉነታዉ ዓለም በተቀላቀሉት ሻምበል ግደይ ሳሙእል እና ቴክኒሺያን ፀጋብርሃን ግደይ ላይ ያዎረዳችሁት የከሃዲነት ዉንጀላ አብይ ምስክር ነው።
በከንቱ ዉዳሴ ተወጥራችሁ ህዝብን አሸንፈን በሥልጣናችን እንቀጥላለን ብላችሁ የምታስቡ የጦር መሪ ነን ባዮች ወደ ህሊናችሁ ተመለሱ። የኢትዮጵያ ህዝብ ከእናንተ ጋር ምንም ችግር የለበትም። ታሪኩ፡ ባህሉ ወጉና ልምዱ በአብሮ መኖር በኩል ችግር እንደሌለበት ምስክሮች ናቸዉና!!!
በሌላ በኩል ግን የትግራይ ረመጦችም ሆኑ የግንቦት ሰባት አንበሶች ለአንድ አላማ  ለኢትዮጵያዊነት እና በሰላም ተቻችሎ ለመኖር ነዉ እየዘመሩ ያሉት።
ይህ ሲባል ግን ስብሃት ነጋ ከዘር ጥላቻዉ እንዲላቀቅ ሱባኤ እንዲገባ አይደረግም ማለት አይደለም።
አባይ ጽሃይም ላለበት ሃይማኖትን የማፍረስ አባዜ በአርባ ቀን ጥምቀት ለመንጻት ቄስ አያጠምቀም ወይም ሼህ እይጎበኘዉም ማለት አይደለም። የትኛዉ እንደሚፈዉሰዉ ምርጫዉ የራሱ ነው።
የነ ደብረጽዮን ፤ ጌታቸዉ አሰፋና አምስቱ የአፈና ቡድናችዉ  የመሰረቷቸዉን ድብቅ ያማሰቃያ ቦታዎች ይፋ እንዲያደርጉ ፤ ያጠፏችዉን ኢትዮጵያዉያን  ዝርዝር እንዲያቀርቡ  ህዝብ አይጠይቃቸዉም ማለትም አይደለም።
ሳሞራ የኑስ ምን ኣልባት ለዚያ ከደረሰ የጀኔራልነት ሃዉልቱን ተሸክሞ በአደባባይ በመዞር ለዚህ ያበቃዉን ገድል እንዲተርክለት ህዝብ ይጠቅ ይሆናል ።
የብአዴን፤ ኦህዴድና ኦህዴድ ፈረሶችም ቢሆኑ በሀገር ላይ ክህደት ከፈጸመዉ ደመቀ መኮነንና በንጹሃን ደም እጁ ከተጨማለቀዉ ሃይለ ማርያም ደሳለኝ እና ከመሳሰሉት በስተቀር ሌሎቹ የማስመሰያ የዘር ጭምብላቸዉን አዉልቀዉ ለአጠፉትም ጥፋት ይቅርታ ጠይቀዉ ወደ እዉነተኛ ማንነታቸዉ እንዲመለሱና የ 24 ዓመት ድራማዉን እንዲተርኩለት የኢትዮጵያ ህዝብ መጠየቁ የሚቀር አይመስለኝም።
የትናት ሺፍቶች የዛሬ ሚሊዮነር ጀኔራሎች የሃብት ምንጫቸዉን እንዲነግሩን መጠየቅ የኢትዮጵያዊነት መብታችን  መሆኑም መዘንጋት ያለበት አይመስለኝም።
ዕዉነት ዕዉነት እላችኋለሁ ። ዛሬ ወገኖቻችን እየታደኑ በተገኙበት እርምጃ የሚወሰድባቸዉ ፤ ወደ ወህኒ የሚወረወሩት  እና ሁሉም ስቃይ በህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለዉ ወያኔ በጣዕር ላይ በመሆኑ እርምጃዎቹ ሁሉ የደመነፍስ በመሆናቸዉና  በዚያዉ ከዘር ጥላቻ በመነጨዉ ጥላቻዉ  ነው።
እናም እላችኋለሁ ግንቦት ወር  የወያኔ የምርጫ ድራማ  የምናደምቅበት አይሆንም። በሌላ በኩል ግን ወያኔን አሽቀንጥረን ጥለን ለመቻቻል አብሮ ለመኖርና  ያገራችንን የወደፊት አካሄድ የምወስንባት ወር ነው መሆን ያለባት ግንቦት ወር።
ይህን ዕዉን ለማድረግ በጥቅማ ጥቅም ተገዝተህ ለዘረኛዉ ቡድን ሰግደህ ያደርክ ሁሉ  ወደ ህሊናህ ተመልሰህ ከህዝብ ተቀላቀል።
ለግል  ጥቅምህ ተገዥ በመሆን ከዚህም ከዚያም አይደለሁም እያልክ ሌላዉ ሳይሆን ራስህን እያታለልክ የምትኖር  የወገንህን ብሶት አስብ ከጎኑም ለመሰለፍ ጊዜ አትዉሰድ።
ባጋጠማችሁ መልካም አጋጣሚ ሥልጣን ላይ ተኮፍሳችሁ ያካበታችሁት ያገር ሃብት የማሰብ ህሊናችሁን ለሸፈነው ዘረኞች የእስካሁኑ ይበቅል ። የያዛችሁትን ለመብላት ከበቃችሁ ከበቂም በላይ ሁሉንም አድርጋችኋል። ይህ ግን እንዳይቀጥል ህዝብ በቃ ብሎአል እና ለሁሉም አይንት ጥፋት ብላችሁ ከምርጥ ዘራችሁ ዉስጥ ያዘጋጃችሁት የጥፋይ ሃይል አያድናችሁምና ለንስኃ ሞት የምትበቁበትን መንገድ ፈልጉ የምነት ድሃዎች ። ህዝብ  በቃ ብሎአልና!!!
የጥፋቱን መጠን መቀነስ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነኝ ለሚል   የሆነ ሁሉ ሃላፊነት ነዉ።
ከዚህ በተረፈ  ግን ሁሉንም ሥራዉ  ያዉጣዉ !!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!

ኢትዮጵያዊውን የገደለው ቻይናዊ ‹‹ለሁለቱ አገራት መልካም ግንኙነት›› ሲባል ክሱ መቋረጡ ተጋለጠ

በነገረ ኢትዮጵያ
በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን አቸፈር ወረዳ ውስጥ ኢትዮጵያዊውን የገደለው ዠንግ ቢንዥንግ የተባለ ቻይናዊ ‹‹በቸልተኝነት ሰው በመግደል›› ወንጀል ክስ ተመስርቶበት የነበር ቢሆንም ‹‹ለሁለቱ አገራት መልካም ግንኙነት›› በሚል ትዕዛዝ ክሱ መቋረጡን ከክልሉ ፍትህ ቢሮ የተገኘው ሰነድ አጋለጠ፡፡
negere ethiopiqየአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ለአቸፈር ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ተከሳሹ ካሳ ከፍሎ መውጣቱ ለሁለቱ አገራት መልካም ግንኙነት እንደሚበጅ በጻፈው ደብዳቤ ክሱ እንዲቋረጥ መደረጉን ‹‹በአማራ ፍትህ ቢሮ የምዕራብ ጎጃም ዞን የፍትሕ መምሪያ የወንጀል መዛግብት መርምሮ መወሰንና ተከራክሮ ማስወሰን የስራ ሂደት›› ለሰሜን አቸፈር ፖሊስ ጽ/ቤት በጻፈው ደብዳቤ ተመልክቷል፡፡ በትዕዛዙ መሰረትም ክሱ ቀሪ ሆኖ የምርመራ መዝገቡ ተመላሽ መደረጉን በደብዳቤው ላይ ተገልጾአል፡፡

ከድንበር ጋር በተያያዘ በአማራና በትግራይ ክልል ከፍተኛ ውጥረት ነግሶአል

ethiopia-map
ታኀሳስ ፲፯(አስራ ሰባትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ታህሳስ 16 ቀን 2007 ዓም በሶረቃ ከተማ ከ70 ያላነሱ ከትግራይ ክልል የመጡ ታጣቂዎች፣ ከምስላል ወደ ስላንዴ በረሃ የሚሰራውን መንገድ ለማስቆም ተኩስ በመክፈታቸው 2 አርሶ አደሮች ሲቆስሉ፣ በአብራጅራ ወረዳ የሚገኙ ጸረ ሽምቅ እየተባሉ የሚጠሩ ሃይሎች ከህዝቡ ጋር በመሆን የአጸፋ ተኩስ በመክፈታቸው ታጣቂዎች ከአካባቢው ተሰውረዋል።
ፌደራል ፖሊስ ወደ አካባቢው በመሄድ ህዝቡን ለማነጋገር ሙከራ በማድረግ ላይ ሲሆን፣ በአማራ ክልል በኩል ያሉ የአራት ወረዳ ህዝብ እስከ ታህሳስ 30 ድንበራችን ካልተከለለ እና የታሰሩ ሰዎች ካልተፈቱ እርምጃ እንወስዳለን በማለት ማስጠንቀቃቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል .
ሌሎች ወገኖች እንደሚሉት ደግሞ የትግራይ ክልል እያስታጠቀ የሚልካቸው ታጣቂዎች በአማራ ክልል ያሉ ብአዴኖችን እያስቆጣ ነው። ግጭቱንም የሁለቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ግጭት አድርገው የሚወስዱት ወገኖች አሉ። ሁለቱም ክልሎች የድንበር ችግሩን እስካሁን ለመፍታት አለመቻላቸው በአካባቢው ለሚነሳው ተደጋጋሚ ግጭትና ለሚጠፋው የሰው ህይወት ምክንያት መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ህወሃት ስልጣን በያዘባቸው የመጀመሪያዎቹ አመታት ከአማራ ክልል መሬት በመውሰድና ወደ ትግራይ በማካለል የቀድሞ የህወሃት ታጋዮችን አስፍሮበታል በሚል በተደጋጋሚ እንደሚተች ይታወቃል።

ከድንበር ጋር በተያያዘ በአማራና በትግራይ ክልል ከፍተኛ ውጥረት ነግሶአል

ethiopia-map
ታኀሳስ ፲፯(አስራ ሰባትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ታህሳስ 16 ቀን 2007 ዓም በሶረቃ ከተማ ከ70 ያላነሱ ከትግራይ ክልል የመጡ ታጣቂዎች፣ ከምስላል ወደ ስላንዴ በረሃ የሚሰራውን መንገድ ለማስቆም ተኩስ በመክፈታቸው 2 አርሶ አደሮች ሲቆስሉ፣ በአብራጅራ ወረዳ የሚገኙ ጸረ ሽምቅ እየተባሉ የሚጠሩ ሃይሎች ከህዝቡ ጋር በመሆን የአጸፋ ተኩስ በመክፈታቸው ታጣቂዎች ከአካባቢው ተሰውረዋል።
ፌደራል ፖሊስ ወደ አካባቢው በመሄድ ህዝቡን ለማነጋገር ሙከራ በማድረግ ላይ ሲሆን፣ በአማራ ክልል በኩል ያሉ የአራት ወረዳ ህዝብ እስከ ታህሳስ 30 ድንበራችን ካልተከለለ እና የታሰሩ ሰዎች ካልተፈቱ እርምጃ እንወስዳለን በማለት ማስጠንቀቃቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል .
ሌሎች ወገኖች እንደሚሉት ደግሞ የትግራይ ክልል እያስታጠቀ የሚልካቸው ታጣቂዎች በአማራ ክልል ያሉ ብአዴኖችን እያስቆጣ ነው። ግጭቱንም የሁለቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ግጭት አድርገው የሚወስዱት ወገኖች አሉ። ሁለቱም ክልሎች የድንበር ችግሩን እስካሁን ለመፍታት አለመቻላቸው በአካባቢው ለሚነሳው ተደጋጋሚ ግጭትና ለሚጠፋው የሰው ህይወት ምክንያት መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ህወሃት ስልጣን በያዘባቸው የመጀመሪያዎቹ አመታት ከአማራ ክልል መሬት በመውሰድና ወደ ትግራይ በማካለል የቀድሞ የህወሃት ታጋዮችን አስፍሮበታል በሚል በተደጋጋሚ እንደሚተች ይታወቃል።

Tuesday, December 23, 2014

የሕወሓት አስተዳደር የአስመራው መንግስት ሄሊኮፕተሩን በሱዳን በኩል እንዲመልስለት መጠየቁ ተሰማ

(ምንሊክ ሳልሳዊ) ስርአቱን ከዱ የተባሉት አብራሪዎች ከድሬዳዋ ተነስተው በጅቡቲ ድንበር አስታከው በአሰብ ዘልቀው ኤርትራ ያሳረፉት ሄሊኮፕተር በሱዳን በኩል እንዲመለስለት ሻእቢያን መጠየቁን የሱዳን ዲፕሎማቶች ጠቆሙ::
captured-ethiopian-mi-24-by-eritrea
ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርገውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና በአየር ሃይሉ ውስጥ የሚፈጸመውን ደባ በመቃወም ከድተዋል የተባሉት 2 ፓይለቶች(ካፒቴን ሳሙኤል እና ቢሊሊኝ )እና አንድ ቴክኒሽያን(ጸጋ ብርሃን)ለኤርትራ መንግስት እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ይህንንም የወያኔው ቴሌቭዥን ጣቢያ እማኝነቱን ሰቷል::
አብራሪዎቹ ይዘውት የሄዱትን ሄሊኮፕተር እንዲመለስለት ወያኔ የሱዳን ዲፕሎማቶችን የላከ ሲሆን ሻእቢያ የማይመልስ ከሆነ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ከባድ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አንድ ለስርአቱ ቅርብ የሆነ ድህረገጽ ጽፏል::
በሃገር ውስጥ እና በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደ ፖለቲካ ድል ሲቆጥሩት አንዳንዶቹ ወያኔ የሻእቢያን አየር ሃይል በሰው ሃይል እየገነባ ሊሆን ይችላል ከጀርባ ሌላ ደባዎች በወያኔ እና ሻእቢያ ሊሰራ ይችላል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አልጠፉም::የወያኔ መክላከያ ሰራዊት አጸፋዊ እርምጃ ይወስዳል የሚል ስጋት ቢያይልም;ሃገር ወዳዶች ግን ምንም እርምጃ አይወስድም የፍርሃት ዛቻ ነው ሲሉ ተደምጠዋል:

Sunday, December 21, 2014

በባህርዳር የሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተደረገውን የጅምላ ግድያና ድብደባ እናወግዛለን

ENTCአገር በቀል የሆነው፤ የቅኝ አገዛዝና ዘረኛው የወያኔ ሰርአት በባህር ዳር የሚኖሩ ወገኖቻችንን ላይ በትናንትናው እለት ያደረገውን የጅምላ ግድያና ድብደባ አሁንም በታላቅ ቁጭትና ሀዘን ለማየት ተገደናል። በተለይ አካለ ስንኩላንና በእድሜ የገፉ አዛውንት በድብደባ ቆስለው ማየት ምን ያህል ልብ የሚያደማና የስርአቱን ኢሰብአዊነትና ጨካኝነት አሁንም ደግሞ ደጋግሞ የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በላይ ይህንን ዘግናኝ ወንጀል የፈጸሙት የስርአቱ አራማጆች አንድ ቀን ለፍርድ በሚቀርቡበት አደባባይ በመረጃነት የሚያዝ ይሆናል። ምንም እንኳን የመሳሪያና የዱላ እሩምታውን ቢያወርድበት፤ ቆራጡ የባህር ዳር ህዝብ ይህንን ተቋቁሞ ምሬቱን መግለጽ ብቻ ሳይሆን ከትግል አጋሩ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር፤ ይህንን የበሰበሰ ስርአት ከተከሻው አሽቀንጥሮ የሚጥልበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። የወያኔ ሰርአት ላለፉት 23 አመታት በተለያዩ ክልሎች ተመሳሳይና ከዚህም የከፉ የጅምላ ጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት ድርጊቶች በኢትዮጵያውያን ላይ ሲፈጽም ቆይቷል። የአንዱ ኢትዮጵያዊ ጥቃት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥቃት መሆኑን አምነን በአንድነት በመቆም ስርአቱን ለማስወገድ ካልታገልን፤ ወያኔ ስልጣኑን ለማራዘም ወደፊት ከዚህ የከፉ ድርጊቶች እንደሚፈጽም ያሳለፍነው የ23 አመት የመከራ ታሪክ ማሳያ ሊሆነን ይገባል።
ይህን አገር በቀል የቅኝ አገዛዝ፤ ዘረኛና ጨካኝ ሰርአት ለማስወገድ የኢትዮጵያን ሕዝብ መሰረት ያደረገ ሁሉንም አካላት የሚወክልና ትግሉን በአንድ ማእከል የሚመራ ጠንካራ የአንድነት ሃይል መክሮና ተስማምቶ ማቋቋም አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑን ድርጅታችን በጽኑ ያምናል። በዚህም መሰረት የሽግግር ምክር ቤቱ ይህንን የትግል አስተባባሪና መሪ አካል በጋራ ለማቋቋም ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል። በዚህ አጋጣሚ ሀገር ወዳድና ነጻነት ናፋቂ ወገን ሁሉ ተመሳሳይ ጥረትና ግፊት እንዲያደርግ ሀገራዊ ጥሪ እናቀርባለን።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሽግግር ምክር ቤት

Saturday, December 20, 2014

ይድረስ ለጎንደር ሕዝብ ቁ. 3

ጎንደር ተወልደን ያደግን ሁሉ እንደምናዉቀዉ ህዝባችን እንግዳ ተቀባይ፤ ሽራፊ እንጀራውን ተካፍሎ አዳሪ፤ እንዲሁም በደስታም ሆነ በመከራ አብሮ ከመቆም ባህሪው በመለስ፤ በየዘመኑ ሊያጠቁን እና እናት አገራችን ሊወሩ የመጡብንን ጠላቶቻችን፤ መሪ ሲኖረው ከመሪው ጋር። መሪ ሳይኖረው ጀግኖቹን የጎበዝ አለቃ አድርጎ በመምረጥ እራሱን በራሱ አደራጅቶ እሴት ወንድ፤ ትንሽ ትልቅ ሳይል እንደማንኛዉም ኢትዮጵያዊ የነጻነት አርበኛ ሆኖ፤ የብዙ ጀግኖችን ህይወት ሰውቶ ትልቅ ታሪክ ሰርቷል። በዚህ በፈሰሰው ደሙ እና በተከሰከሰው አጥንቱ ለዛሬ መመኪያ የሆነችንን ጎንደርንም፤ ኢትዮጵያንም አዉርሶናል። ለሶስት መቶ አመታት 27 ነገስታት ያገለገሉበትን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ኩራት የሆነውን የመጀመሪያዉን የጎንደር ቤተ መንግስት የገነባዉም ይኽው በአንድነቱ ሲወደስ የኖረው አማራዉ፤ ቅማንቱ፤ አገዉ፤ ቤተ እስራኤሉ፤ ክርስቲያኑ፣ እስላሙ እና ሃይማኖት የሌለዉም ጎንደሬ ጭምር ነዉ።
Fasil , Gonder
ስለ ኋላ ታሪካችን ከአሁን በፊት በወጡት መግለጫዎቻችን ላይ ብዙ ስላልን፤ ለዛሬ ከ“አብዮት” በኋላ የደረሱብንን ማንነታችን አንድነታችን ፈታኝ የሆኑ አሥቀያሚ ገጽታዎችን ማንሳቱ በቂ ነው። ከስልሳ ስድስት አብዮት በኋላ፤ በተፈጠረው የመሥመር ልዩነት፤ ወደ ትጥቅ ትግሉ ለመግባት ከተመረጡት ቦታዎች አንዱ በዚሁ በጎንደር ክ/ሀገር ነበር። በመሆኑም፤ ወደ ትጥቅ ትግሉ ለመግባት የወሰኑትን ከመላ ኢትዮጵያ የሚመጡ ዜጎቻችን ያሥተናገደው እና በዚሁም ሰበብ ከፍተኛውን የደርግ ቀይ ሽብር ጭፈጨፋ መራራ ጽዋ ከተጎነጩት ክፍለ ሀገራት አንዱ የጎንደር ክ/ሀገር ህዝብ ነው። የማይረሳው የቅርብ ጊዜ አሥከፊው ትዝታችን ደግሞ፤ የትግራይ ክ/ሀገሩ ተወላጅ ገብርህይወት ገ/እግዚአብሔር በፊት የወገራ፤ ሰሜን እና ጭልጋ አውራጃ የጦር አበጋዝ፤ በመጨረሻም የጎንደር ክፍለ ሃገር የደህነት ሃላፊ፤ ግን የወያኔ ሰርጎ ገብ የዉስጥ ነጻ አዉጭ፤ የደርግ ተወካይ በመምሰል ከነመላኩ ተፈራ ጋር ተባብሮ በከተማም ሆነ በገጠር እጅግ ብዛት ያላቸው ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን መጨረሱ ነው። ይህን ሁሉ የቅጣት ዋጋ ያስከፈለን፤ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ወንድማችን እህታችን ብለን ማስተናገዳችን ብቻ ነዉ። ጎንደር ሌላ ጥፋት የለዉም፤ በዘር ሳይደራጅ ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ! በማለቱ እንጂ። አሁን ግን በዛብን፤ ባበላን ተነከስን፤ ባስተናገድን ተወረርን። ፍቅራችን እና ትብብራችን ያሥደነገጣቸው ከፋፋዮች ሊያለያዩን ጎሳ ሥለታቸውን ሰነዘሩበን።
በ1991 ወያኔ አዲስ አበባ ሲገባ ዉስጥ ዉስጡንም ሆነ በይፋ ሰርቶ ባዘጋጀዉ ካርታ መሰረት የጎንደር ክልል የነበረውን የሁመራን፤ ወልቃይት ጠገዴን እና የጠለምት መሬታችንን በጉልበት በመውረር ወሰደ። ከቦታዉ የነበረዉን ለዘመናት የኖረ ህዝብ አፈናቀለ። የዘር ማጥፋት ዘመቻዉ አሁንም ቀጥሏል። በአብደራፊ፤ በመተማ እና በቋራ ዘይትና ወርቅ ብሎም የርሻ ልማት ያለበትን የጎንደር መሬት ለመዉሰድ በኢንቬስተር (INVESTOR) ስም ለወያኔ ካድሬዎች በገፍ እዬቸበቸበ ነዉ። ተወላጁ የጎንደር አራሹ ገበሬ እየተፈናቀለ፤ እየታሰረ፤ እየተገደለ፤ እየተሰደደ፤ አንዴ የትግራይ መሬት ነዉ፤ ሲያሰኛቸዉ በመተማ በኩል ያለውን ደግሞ የቤኒሻንጉል ነዉ፤ እያሉ ግማሹን ለራሳቸዉ የቀረዉን ለሱዳን ቆርሰዉ እያስረከቡ ደካማ እና ታሪክ የሌላት ጎንደርን በፈለጉት መንገድ ሊሥሏት እየተዘጋጁ ነዉ። አሁን ያመጡት የመጨረሻዉ ጥቃት ደግሞ ግማሹን የጎንደር መሬት ሲነጥቁ የቀረዉን ጎንደሬ ቅማት እና አማራ በሚል ማለያየት የጠነሰሱት እኩይ የጥፋት ሴራ ነዉ። አማራዉን በኢትዮጵያ በአራቱ ማዕዘን አዳክሞ አገር የማጥቃት እስትራቴጂ ዋንኛው አካል ነዉ። ላለፉት 23 ዓመታት መላዉ የጎንደር ህዝብ ጎንድር አንድ ነዉ፤ ጎንደር የቅማንት የአማራ፤ የቤኒሻንጉል፤ የአገዉ፤ የቤተ እስራኤል አገር ነዉ ብሎ በዘር መከፋፈልን በጽኑ ተቃዉሞ ቆይቷል። በወቅቱ ወያኔ የመለመላቸዉ በጣት የሚቆጠሩ የቅማት ተወላጆች በዋና ከተማዋ ጎንደር ሲኒማ አዳራሽ ስብሰባ ሲጠሩ ሁሉም የከተማዉ ህዝብ ቅማንት ነን ብሎ ከአዳራሹ ገብቶ ግራ እንዳጋባቸዉ ሁላችሁም ታዉቃላችሁ።
አሁን ግን እነሱ ከገቡ የተወለዱና ሲገቡ ወጣት እድሜ የነበራቸው የተወሰኑ ወጣቶችን፤ እንዲሁም ጥቂት አዛዉንት እና ምሁራንን ለሂደቱ አዳማቂ እንዲሆኑ በዘረኛነት አጥምቀዉ ጎንደርን፣ አማራ እና ቅማንት በሚል ካርታ ለይተዉ የጎሳ እሳት መለኮስ ጀምረዋል። ለበለጠ ጥፋትም ተዘጋጅተዋል። ይህን እሳት ማጥፋት አለብን። የሥራአቱ መራሽ የሆኑት ወያኔወችከጀርባ እዬሰሩት ያለዉ ሃቅ ግን እኛን እያዋጉ መሬት ለመንጠቅ እንድሆነ ግልጽና በተግባር የታየ ነዉ። እዉነተኛዉ እኛ የምናዉቀዉ ጎንደሬ የቅማንት ተወላጅ፤ ሁመራን ወልቃይት ጠገዴን ጠለምት እራስ ዳሸንን ወያኔ ወሮ ዘመቻ በከፈተበት የጥፋት ዘመን ላይ መሆናችንን እያዬ፤ ለቅማንት ጎሳ ሌላ ክልል ልፍጠር ብሎ ለአዲስ ካርታ ጦርነት ይገባል ብለን ፍጹም አናምንም። ወያኔ መራሹ መንግሥት ግን ይህን ለማስፈጸም እየሰራ እንደሆነ አንጠራጠርም። እኛ የጎንደር ተወላጆች የገንደርን አብሮነት የጎንድርን ዳር ድንበርና አንድነት ለማስከበር ሃይማኖት ጎሳ ወይም ቋንቋ ሳይለያየን እስከመጨረሻዉ መታገል የግድ ይላል። ከዚህ ያነሰ አማራጭ ጎንደርን የሚያዳክም ብሎም የሚያጠፋ ነዉ ሊሆን የሚችለው። የታሪክ ተወቃሽ እንዳንሆን ወያኔወችንም ተከታዮቻቸዉንም አምርረን ቁርጡን እንገራቸዉ። ሁሉም ጎንደሬ አማራ፤ ቅማንት፤ ቤተ እስራኤል፤ አገዉ፤ ክርስቲያን ወይም እስላም ሆኖ የመኖር ማንነት ማንም የመንፈግም ወይም የመስጠት መብት የለዉም። ይህ አብዛኛዉ የአማረኛ ተናጋሪ ህብረተሰብ ጠንካራ አይበገሬ የኢትዮጵያዊነት አቋም በመያዙ የጥፋት ማዕበል የአገራችን እምብርት በሆነችው ጎንደር ላይ የመከፋፈል ዘመቻ ከፍተዋል። የክፍፍል ማዕበሉ የወያኔን ጎጠኞች እና የዘረኛነት ማቃቸዉን ጠራርጎ እንዲወስድ የጎንደር ህዝብ ተባብሮ መነሳት አለበት።
ወያኔ ቅማንት የሚለዉን የነገድ ስም ከኢትዮጵያ ማህደር ከወረቀት እንዲፋቅ ያደረገዉ፤ ዘረኝነትን ያልተቀበለዉ ጎንደሬዉ ቅማት ዘራፍ ብሎ አምጾ አንቀጽ 39 እንዲቀበል የተጠነሰሰ ሴራ ነዉ ብለን እናምናለን። የቅማንት ምንነት ቋንቋ ወይም የስነ ልቦና ባህላዊ አኗኗር የጎንደር ታሪክ ነዉ ብሎም ተቀብሎ የቆየበት ዘመን እጅግ እረጅም ነዉ ከ፪፬፻፲ (2410) ዓመተ ዓለም ጀምሮ የኢትዮጵያ ነገዶች ቅርስ ሁኖ ቆይቷል። ይህም ኩሽ በተባለዉ ንጉስ የኢትዮጵስ አባት ዘመነ መንግስትም እረዘም ያለ ወደ አራት ሺህ ዓመታት ገደማ ያስቆጠረ ነዉ። አንዳዶች በቅርብ ቀን አንዴ ከኢሽያ፤ ሌላ ጊዜ ከግብጽ መጣ ይላሉ። ግን ኢትዮጵያ 200 ዓመታት 2335 ዓ. ዓ ግብጽን ማስተዳደራን ጠቅሰዉ አይጽፉም።
የጎንደር ህዝብ፤ በተለይም ይህ ትዉልድ የቅማንትን የምንነት መልካም ታሪክ የራሴ ነዉ ብሎ እዉነተኛ ጎንደሬነቱን ይቀበላል። የዘመኑ ዘረኛ ጎጠኞች ግዛታቸዉን ለማራዘም አንዱን ትንሽ ሌላዉን ትልቅ እያደረጉ ያለስም ስም የመስጠት አጉል እና ኋላ ቀር ባህል ፍጹም የዚህ ትዉልድ አቋም አይደለም፤ አይቀበለዉም። ይልቁንም ያለፉትም ሆነ፤ አሁን በግፍ ላይ ግፈ ሞልቶ እስኪፈሥ እየተደራረበ ያለው የመጥፎ አስተዳደር ዉጤት ነዉ ብለን ሁላችንም እናምናለን። የወያኔን የመሬት ወረራ የመስፋፋት ፖሊሲን ለማሳካት ቅማንት እና አማራ ብሎ የጎንደር ክፍለ ሃገርን ሕዝብ ከሁለት ግዛት ለመክፈል የሚካሄደዉን ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን። “ጎንደር አንድ ነዉ” በሚል ተንቀሳቅሰን እና ተደራጅተን የጎንደርን መሬት ለማስመለስ እና አንድነታችን ለማስከበር በጎንደር አንድነት (አብሮነት) ጥላ ስር ተሰባስበን ከመታገል ሌላ ምርጫ የለንም። ጎንድር እንደነበረዉ ያልተሸራረፈ ጎንደር ይሆናል። አገራችን ኢትዮጵያም እንደነበረች ለዘለዓለም በአንድነቷ ተከብራ ትኖራለች።
ይህን ዕራያችን እዉን ለማድረግ ለአንድ ዓመት ጠንክረው በኮሚቴ ደረጃ ሲንቀሳቅውሱ የቆዩት የጎንደር የቅማት ብሔረሰብ ተወላጆች እ. ኢ. አ በ 11/23/14 ዓ. ም በጠሩት የህብረት ጥሪ ተሰባሥበን እጅግ መሳጭ እና የጎንደርንም ሆነ የኢትዮጵያን ታሪክ ጠንቅቀው በሚያውቁ እውቅ ምሁራንና እድሜ ጠገብ ተወላጆችን ያካተተ ውይይቶት አድርገን እንደገና ለበለጠ መጠናከር ለሁለተኛ ጊዜ ሁሉን ጎንደሬ አቀፍ ኮሚቴ ከመሰረትን በኋላ በ12/07/14 እጅግ ብዛት ያላቸውን የጎንደር ተወላጆች ቴሌፎን ሰብሰባ (Tele conference) በመጥራት አራት ሰዓት የፈጀ ጥልቅ ውይይት አደረግን።
በነዚህ ሁለት ቀናት የሥልክ ሥብሰባዎች የተገኙት የጎንደር ተወላጆች የመነጋገሪያ አጀንዳቸው የነበረው ከወልቃይት እና ከራስ ዳሸን ወደ ትግራይ መከለል በኋላ ሌላ የጎንደርን አንጀት እንደመዘርገፍ የሚያስቆጥረውን የቅማንትን ብሔረሰብ ከሌላው ወገኑ ለይቶ ለማዋቀር የሚደረገውን አደገኛ እና ወደ ተግባር ሊቀዬር ሲሞከር ሊያመጣ የሚችለውን የሕብረተሰብ ቀውሥ በተመለከተ ነበር።
በነዚህ ሥብሰባዎች፤ የታየው ብሔራዊ ስሜት የተጠበቀም ቢሆን፤ በየአንዳንዱ ተናጋሪ አንደበት ይወጣ የነበረው ፍቅር የተላበሰ፤ ከአንድነት እና ከአብሮነት የተወረሰ ወኔ ቀሥቃሽ ሐሳብ በሲቃ እና በሃዘን የተቀላቀለ ነበር። በተለይም፤ ከታች አርማጭሆ እና ከላይ አርማጭሆ የቅማንት ተወላጅ ካልሆኑ የእድሜ ብቃት ካላቸው አዛውንቶች የተሰማው ልብ የሚበላ ሃሳብ እንዲህ የሚል ነበር፤ “እነ ፊታውራሪ አየለ አባ ጓዴ፤ እነ ደጃዝማች ጣሹ፤ አገራቸው ሲደፈር አሻፈረኝ ብለው፤ ሰላቶን ለረዥም አመታት የተዋጉት የቅማንትን ተወላጅ ብቻ ይዘው አልነበረም። አገሬን ለሰላቶ አላሥደፈርም፤ ለነጭም አልገዛም ያለውን ኩሩ ኢትዮጵያዊ በመምራት እንጂ። በዘመነ ኃይለሥላሴም ዘመነ መንግሥት፤ እነ ሹምዬ በቀለ፤ እንደሻው ቦጋለ፤ ግራዝማች ካሰኝ አለማዬሁ፤ ልጅ ደምረው ጣሹ፤ ተፈሪ ንጉሴ እና የመሳሰሉት ለፓርላማ አባልነት በጎንደር ከተማ እና የተለያዩ አውራጃዎች ተወዳድረው ሲያሸንፉ የነበሩት፤ በቅማንትነታቸው ፤ በቅማንቱ ሕዝብ ብቻ ተመርጠው ሳይሆን፤ ሁሉም የጎንደር ሕዝብ የዘር ሃረጋቸውን ሳይመዝ በእውቀታቸው እና በችሎታቸው ይወክሉኛል፤ ጉዳዬን ያሥፈጽሙልኛል በሚል መርጧቸው እንጂ” በማለት የአንድነት ኩራታችን የሆነውን የሩቅ ጊዜ ትዝታ ታሪክ በመጥቀሥ፤ በዚያን ዘመን የነበሩትን ታሪክ ሰሪዎች በማወደሥ፤ አንድነታችን ዛሬም በሚያልፍ መንግሥት፤ የማያልፍ ሥም እንዳንፅፍ፤ በሚል ለዚህ ትውልድ አደራነታቸውን አሥተላልፈዋል።
በአጠቃልይ፤ በነዚይ ሁለት ቀናቶች በተደረገው የሥልክ ስብሰባ (Teleconference) በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ በመሥማማት፤ አገር ውሥጥ ለሚገኙ ወገኖቻችን እንደሚከተለው የውሳኔ ሃሳባቸውንን አሥተላልፈናል።
1. በአገራችን ኢትዮጵያ ለሃያ ሦስት ዓመት የአገሪቱን ሰላም እያመሰ ያለው የጎሳ ክልል፤ ወደ ጎንደር ሲመጣ ደግሞ እጅግ የከፋ እንደሚያደርገው ተገንዝበው፤ የቅማንት ማንነትን ከማሥከበር በመለሥ፤ ራሥን በራሥ የማሥተዳደር ጥያቄን ያነሱ ወገኖች፤ እንደገና ዓላማችውን እንዲመረምሩ።
2. በሰሜን አሜሪካ የደላ ኑሮአቸውን እየኖሩ፤ ከዬትም ዓለም የተሰባሰቡ ህዝቦች፤ ያለ ልዩነት ሲኖሩ፤ የሰው ልጅ በዘሩ ሳይሆን፤ በሰባዊነቱ መከበሩን መረዳት አቅቷቸው፤ ተግባር ላይ ሊውል የማይችለውን የወገኖቻችን የወሰን ጥያቄ እንቅሥቃሴ በገንዘብ የሚያግዙ ሰሜን አሜሪካ ያሉ፤ የቅማንት ተወላጅ ወገኖቻችን፤ የአገር ቤቱ እንቅሥቃሴ ወደ ፈራነው አቅጣጫ ሄዶ የደም መፋሰሥ ችግር ቢፈጥር፤ በታሪክ እንደሚያሥጠይቃቸው አውቀው፤ የያዙትን አቋም እንደገና እንዲመረምሩ እና ከእኛ ጋርም ተቀራርበው እንድንመካከር በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እናደርጋልን።
3. የቅማንት እና የአማራ ብሔረሰብ በልማድ በየጎሳቸው ተዋውቀው ቢኖሩም፤ በእምነት፤ በባህል፤ በቋንቋ፤ በታሪክ እንዲሁም በቦታ የተሳሰሩ በመሆናቸው፤ ለያይቶ ለማሥቀመጥ የማይቻል ከምሆኑም በላይ ሙከራው ራሱ የከፋ ታሪክ ጽፎ ከማለፍ በሥተቀር፤ በተግባር ላይ ሊውል የማይቻል መሁኑን የሁለቱ አካባቢዎች ተረድተው አሥቸኳይ መፍትሔ እንዲፈልጉለት።
4. የኢትዮጵያ ገዥው መንግሥትም ሆነ የክልል መሪዎች፤ ይህን ራሥን በራሥ የማሥተዳደርን ጥያቄ ያሥነሳውን የቅማንት ብሔረሰቦች ብሶት በቀናነት ከመፍታት አልፈው፤ ብሶቱን እውነት የክልል ጥያቄ አሥመሥሎ ማሥተናገድ፤ እጅግ ለአካባቢው
4 አለመረጋጋት ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው ተገንዝበው በሁለንተናዊ መልኩ የተዋህደውን ህብረተሰብ ሰላም፤ በራሥ አሥተዳደር ሥም ከማደፈረሥ እንዲቆጠቡ።
5. መላው የጎደር ህዝብ፤ በቅማንት ብሔረሰብ ወገኖቻችን የተነሳውን፤ የራሥን በራሥ የማሥተዳደር ጥያቄ አደገኛነት ተገንዝቦ፤ ለዚህ ጥያቄ ያነሳሳቸውን በደል በጋራ እንዲመረምር እና ችግሩን በጋራ ለመፍታት በጋራ እንዲቆም።
6. ሁለቱም የቅማንት እና የአማራ ቤተሰቦች፤ በዚህ በሰለጠነው ዘመን፤ ኋላ ቀር የሆኑ፤ የሰውን ልጅ እንደ ሰው የማያስቆጥሩ አፈ ታሪኮች አሥወግደው፤ የመናናቅ እና ያለመከባበር አጉል ባህል ተላቀው፤ ሥድብ እና ዛቻ፤ ጠብ እና ጥላቻን፤ ብሎም እስከ መገዳደል ከሚያደርሱ ፉክክሮች ተቆጥበው፤ ይህ ሥራዓቱ ያመጣባቸውን የዘር ጣጣ፤ በብልሃት ይዘው ጊዜውን እንዲሻገሩ።
7. ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው በሰላም ያለ ወሰን ለረዥም ምዕተ ዓመታት የኖሩትን ህብረተሰቦች እሥከ ወዲያኛው እንዲለያዩ ከሁሉም አቅጣጫ የውጡልኝ ጥያቄ ያነሱ ቡድኖች፤ እየሰሩ ያሉትን እጅግ ትርጉም የሌለው እንቅሥቃሴ አቁመው፤ በዚህ ምክንያት በአካልም ሆነ በህሊና የበደሏችውን ወንድሞቻቸውን፤ በአካባቢው በተመረጡ ሽማግሌዎች አማካኝነት ይቅርታ ጠይቀው፤ የአካባቢውን ሰላም እንዲያረጋጉ።
8. እጅግ አሳዛኝ እና ከሰባዊ ተፈጥሮ ውጭ በሆነ መልኩ፤ ዛሬ የሰው ህይዎት ቀርቶ፤ የእንሰሳት ህይዎት ክብር እያገኘ በመጣበት ዘመን፤ በኮምፒተር ጀርባ፤ በፌሥ ቡክ፤ “የማን አባት ጎበጠ” አይነት ፉክክር የሳይበር ጦርነት የከፈቱ የቅማንት ተወላጆች ነን የሚሉ ጥቂት ግለሰቦች፤ ወደ ህሊናቸው ተመልሰው፤ ጦርነት ጥፋትን እንጂ ልማትን እንደ ማያመጣ ተረድተው፤ ወደ ሰላማዊ ህሊናቸው እንዲመለሱ።
የሚሉትን እና የመሳሰሉትን የውሳኔ ሃሳቦች ከተሰነዘሩ በኋላ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን በመላ አገሪቱ እያመሰ ያለውን ጊዜው ያለፈበት የጎሳ ፖለቲካ ፋሽን በመተባበር አውልቆ እንዲጥል እና ሁሉም በጎሳ በረት ሳይዘጋ፤ በመላው የኢትዮጵያችን ክልል ተከባብሮ እና ተፋቅሮ በፈለገበት ቦታ በኩራት የሚኖርበትን ሥርአት እንዲፈጥር የትግል ጥሪያችን እናሥተላልፋለን።
እንዲሁም መላ የጎንደር ተወላጆች፤ ይህን የሕዝባችን አንድነት የመጠበቅ ቅዱሥ ዓላማ፤ ያላችሁን የአገርቤት ግንኙነት መሰመር በመጠቀም፤ የበኩላችሁን ድርሻ በመወጣት እንድትተባበሩ አደራ እንላለን።
በጎንደር ክ/ሀገር እየተለኮሰ ያለው የጎሰኝነት እሳት ያሳሰበን በውጭ አገር የምንተኝ የጎንደር ክ/ሀገር ተወላጆች ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ።

እስማኤል አሊ ስሮ ለረዥም ጊዜ በክልል ፕረዝድንትነት የቆዩ ብቸኛ የኢህአዴግ አገልጋይ የሆኑበት ምክንያት ምንድነው ?

አኩ ኢብን ከአፋር
የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕረዝደንት የነበሩት አቶ ገብሩ አስራት በ 2006 ዓ.ም በጻፉት ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጲያ በተሰኘው መጽሀፍ ላይ ሰለ እስማእል ዓሊ ሲሮ ሲገልፁ እንዲህ ይላሉ….
(አፋር ክልልን ፍልሥሥ ብሎ የሚመራው ኢስማኤል አሊስሮ ይህ ነው)
(አፋር ክልልን ፍልሥሥ ብሎ የሚመራው ኢስማኤል አሊስሮ ይህ ነው)

በ1993 በኢህአዴግ ውስጥ ቀውስ በተፈጠረበት ወቅት የአፋር ብሔራዊ ዴሞራሲ ፓርቲ ሊቀመንበርና የክልሉ ፕረዝድነት የነበሩ ዓሊ ሲሮ አፈንጋጮችን ደግፎ ለተወሰኑ ቀናት የመለስን ቡዱን ተቃውሞ ነበር።
መለስ ድል አድረግያለሁ የባለንጣዎች ጃኬትም አውልቀያለሁ ካለ በኃላም ዓሊ ሲሮ ደስተኛ አልነበረም።
ሰለሆነም ከክፊፊሉ በኃላ ዓሊ ሲሮ መገምገም ነበረበት ከመገምገምም አልፎ ላሳየው ተቃውሞ መቆንጠጥ ነበረበትና በወቅቱ የፈዴራል ሚኒስትር የነበረው አባይ ፀሐዬና የክልሎች ዴስክ ኃላፊ የነበረው ዘርኣይ አሰገዶም የአፋር ዴሞክራሲ ፓርቲን አመራር ዓሊ ሰሮን ጠርተው ቁም ስቅሉን አሳይተውት ነበር።
ዓሊ ሲሮም ከአፈንጋጮች ጎን ተሰልፈው እንደነበረ እንዲያምን ብዙ አስለፍልፈውታል።
ሁለት አወያዮች ይህን ካደረጉ በኃላ ዓሊ ሲሮ ከስልጣን እንዲወርድ ለመለስ ሀሳብ ቢያቀርቡም አለቃ ፀጋይ በአቆራጭ መለስን ተማጽኖ ከመባረር አድኖታል።
የአለቃ ፀጋይ ዓሊ ሲሮ በስልጣን እንድቆይ መማጸን ከማናውቀው ማላእክ የሚናውቀው ሰይጧን (ሸይጣን) ይሻለናል ከሚል እንደነበረ ምንጮቻችን ነግሮናል።
እውነትም ሁኔታዎች በተለዋወጡበት ሁኔታ እንኳን አብዴፓና መሪው ሌላም አፋር ለውጥ ለማምጣት የሚቸገር ነበረና ዓሊ ሲሮ ባለበት እንድቆይ ተወስኖ ኢህአዴግን ከአስራ ሁለት አመታት በላይ ሊያገለግል ችሏል ይላል መጽሀፉ።
እዚህ ለይ እኔም የራሴ ትንሽ ልጨምረበትና በእርግጥ የእስማእል ዓሊ ሲሮ የአገልግሎት ላይ መቆየት ምክንያት አለቃ ፀጋይ ነው።
ይህም በ1993 ባደረገለት ተማጽኖ ብቻ ሳይሆን መለስ ከሞተ በኃላም ያልተቆረጠ ድጋፍ ከአለቃ ፀጋይ አላቸው።
ይሁን እንጂ መለስ ከሞተ በኃላ አለቃ ፀጋይ እራሱ ይህ የሚባል ስልጣን ባይኖረውም አቆያህለሁ እያለ ከአቶ እስማእል ብዙ ሚሊዮን ብሮች እንደሚያገኝ ይነገራል።
አለቃ ፀጋይ የትግራይ ክልል ፕረዝደንት በነበሩበት ጊዜ ዓሊ ሲሮ መቀለ ሳይዘይሩ (ሳይሳለሙ) ሳምንት አያሳልፉም ነበር።
አሁን ግን ሁለቱም መሀይሞች የሚገናኙት አዲስ አባባ ወይም ሰመራ ቢሆንም አቶ ሲሮ ስልጣን ላይ ለመቆየት ከአለቃ ፀጋይ ሌላ አዲስ ሽማግሌ የቀጠሩ የመስላሉ።
እርሱም የጀቡት ፕረዝደንት የሆኑት እስማእል ኡማር ገሌ ስሆኑ ካለፉት ሦስት ሳምንታት በፊት አቶ እስማእል አሊ ስሮ በማያገባቸው የሁለት አገር ድምበር ከተሞች የፀጥታ ኃላፊዎች በተጠሩበት ሰብሰባ ምክንያት በማድረግ ወደ ጀቡቲ ሄደው ነበር።
በዛን ጊዜ ሁለት እሰማእሎች ተገናኝተው የበሩ መሆኑን ኦና ኢህአዴግ ከእስማእል ኡመር ገሌ የሚፈለገው ብዙ ነገሮች ሰላለው ኢህአዴግን እንዲማጸኑለት እስማእል ዓሊ ሲሮ ጠይቀው ነበር።
ያነ የኢትዮጲያ ኢሳ ጎሳ ተወላጅ የሆኑት ገሌ እስማኤል ዓሊ ሲሮ ለኢሳዎች ልዩ ቀበለዎች እንዲሰጡ ወይም የኢሳ ጎሳ በአፋር ክልል በሰላም እንዲኖሩ እንዲያመቻቹ ጠይቀው አቶ ሲሮ የሁለቱም ጥያቀዎች መልስ ያለው በኢህአዴግ እጅ ውስጥ እንደሆነና እርሰዎ እንድጠይቁ በማለት በሚስጥር ከተሰማሙ በኃላ ወደ ሰመራ ተመልሷል።
ከሳምንት በኃላ የጀቡቲ ፕረዝደንት በአሶሳ በተከበረው የበሔር በሔረሰቦች ቀን ላይ ተግኝተው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
ከዛም ከሳምንት በኃላ የፈደራል ሚኒረስትር በአፋር ክልል በአዋሽ ከተማ በሁለት ክልሎች ጣልቃ ገብተው የአፋር መሬት ለኢሳ አሳልፈው ስጥተዋል።

ድንበር ዘለሉ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች አፈና እና የጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እጣፈንታ !

nebyu sirak
ነብዩ ሲራክ ላለፉት አስርት አመታት በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ድምጽ በመሆን በአረቡ ዓለም ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን መረን የለቀቀ ስቃይ እና በደል መቋጫ እንዲበጅለት በድህረ ገጹ በማስተጋባት ላይ የሚገኝ ጋዜጠኛ ነው ። ይህ ጋዜጠኛ በተለይ ያለምንም ቅድመዝግጀት እና ሁለትዮሽ፡ስምምነት በቤት ሰራተኝነት በደላሎች ተወናብደው ቁም ስቅላቸውን እያዩ ሰለሚገኙ እህቶቻችን አሰቃቂ ተእይንት በማለዳ ወጎቹ በማስቃኘት በአጭር ግዜ ውስጥ የአያሌ ወገኖችን ትኩረት መሳብ የቻለና የጉዳዩ ባለቤት በሆነው ህዝብ ዘንድ አንድናቆትና ክበርን ያተረፈ መሆኑም ይነገራል።
በሌላ አቅጣጫ በጋዜጠኛው ዘገባዎች ያልተደሰቱ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ካድሬዎች እና አንዳንድ የሰራተኛ እና አስሪ ኤጀንሲ ባለቤቶች አይን የሚደረግበት ክትትል የጋዜጠኛው ን የስደት አለም ህይወት ውስብሰብ እና የከፋ አድርጎታል ። ጋዜጠኛው በስደት አለም ከሚገኝበት ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ በግሉ ተከራይቶ ከሚኖርበት የመኖሪያ ቤቱ በተለያዩ ምክንያቶች እንዲፈናቀል ከሚሸረብበት ሴራ እና ኮሚኒቲ አካባቢ እንዳይደርስ እይተደረገበት ካለው ተጸኖ ባሻገር የመንግስት ካድሬዎች እና ፡ደላሎች በህይወቱ ላይ የሚሰነዘረውን ዱላ በመጋፈጥ መራራውን ጽዋ በአደባባይ ለመቀበል ተገዷል። ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክን ለማጥፋት በተለያየ አቅጣጫ መልኩን እየለዋወጠ የሚሰነዘረው ጥቃት ፍጹም ወገናዊ ርህራሄ የጎደለው በመሆኑ የጋዜጠኛው ደህንነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ፡ መግባቱን ብዙዎች ይናገራሉ። በተለይ ጋዜጠኛው የሚከተለውን ሃይማኖት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው የአባራኩ ክፋይ ከሆነው ሙስሊም ወገኑ ጋር ለማጋጨት እነዚህ ወገኖች በድህረ ገጻቻቸው ከሚያሰሙት ሴጣናዊ ጩሀት ባሻገር ከአመት በፊት ነብዩ ሲራክ የሳውዲ አረቢያን ህግ በመተላለፍ በጥብቅ የተከለከሉ የአልኮል መጠጦች እና መስል አይምሮ አደንዛዥ እጽ ንግድ ላይ የተሰማራ አስመስለው በሃሰት ወንጀላ ለወህኒ በመዳረግ ጋዜጠኛው የስይፍ ሰለባ እንዲሆን በጋዜጠኛው ህይወት ላይ የተቃጣው ሙከራ ድፍን የኢትዮጵያን ህዝብ አስደንግጧል በጅጉም አሳዝኗል ።
የዚህ ጋዜጠኛ የብዕር ጩሀት እንቀልፍ የነሳቸው የመንግስት ካድሬዎች እና ደላሎች ጋዜጠኛው ለረእፍት ወደ ሃገር ሲያቀና ለማፈን የነበራቸው እቀድ ይዚሁ እርኩስ ተግባራቸው አንዱ አካል እንደነበረም ይነገራል። ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ሳውዲ አረቢያን ጨምሮ በአረቡ ዓለም እንደ ጨው ተበትነው በሚገኙ ወገኖቻችን ዙሪያ በሚያቀርበው መረጃ በዲፕሎማቶቻችን ስራ ላይ ተጸኖ ፈጥሯል በሚል ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ከጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ካድሬዎች በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢደርሰውም ጋዜጠኛ ነብዩ ግን በወገኖቹ ላይ የሚደርሰውን አሰቃቂ ትዕይንት እያየማለፉ ሊከፍለው የማይችለው እዳ ሆኖበት ከህሊና ጸጸት ለመዳን በሙያው ያስተማረውን ህዝብ ውለታ ለመክፈል ዛሬም የሚመጣውን ሁሉ ለመጋፈጥ እውነታዎችን መዘገቡን ቀጥሎሏ ።
ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ሰሞኑንን ለፓስፖርት እድሳት ወደ ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት አቅንቶ እንደነበር የሚናገሩ ምንጮች ጋዜጠኛው የነዚህ ካድሬዎች እና ምስለኔዎች ሰለባ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ይገልጻሉ ። ጋዜጠኛው ቀደም ሲል በወገኖቹ ዙሪያ በድሀረ ገጹ ሲያቀርባቸው በነበሩ መረጃዎች ያልተደሰቱ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ.መንግስት ካድሬዎች እና ደላሎች ነብዩ ሲራክ በጃችን ገባ ሲሉ መደመጣቸውን የሚገልጹ ምንጮች የጋዜጠኛው ፓስፖርት እድሳት በ ድርጅታዊ ውሳኔ በገወጥ ሊታገድ እንደሚችል ስጋታቸውን አክለው ገልጸዋል።
በዚህ ዙሪያ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክን በአካል አጊቷ ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም ይህ ጋዜጠኛ ከተለመደው የእንገለሃልን እና በጃችን ትገባለህ ተራ የስልክ ማስፋራሪያ ባሻገር እስካሁን ምንም አይነት ችገር እንዳልገጠመው የሚገልጹ ምንጮች ፡ ጋዜጠኛው በጀመረው በጎ ተግባር እንደሚቀጥል እና እስከ ዛሬ ሲያቀርባቸው በነበሩ ዘገባዎቹ በየትኛውም አቅጣጫ የሚመጣውን መከራ እና ስቃይ በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ይናገራሉ።

በአዲስ አበባ በኑር (በኒ) መስጅድ ህዝበ ሙስሊሙ ድንገተኛ ተቃውሞ አደረገ

bbn
(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ በኑር (በኒ) መስጅድ ህዝበ ሙስሊሙ ድንገተኛ ተቃውሞ በማድረግ አስገራሚ ተቃውሞውን ገለጸ::
ድንገት በተደረገው በዚህ ተቃውሞ ላይ የተለያዩ መፈክሮችን የያዙ ፊኛዎች ወደ ተውለብለበዋል ያሉት ዘገባዎች ፊኛዎቹ የተለያዩ መፈክሮች የተጻፈባቸው ሲሆን ከነዚህም መካከል : -” ትግሉ ይቀጥላል ፍትህ ነጥፏል ፤ሂጃብ መለያችን፤ኒቃብ ውበታችን ፤ትግላችን ቀጥሏል ፍትህን ማዘግየት ፍትህን መንፈግ ነው ፤ትግላችን እንደቀጠለ ነው” የሚሉ እንደሚገኙበት ዘግበዋል;;
በተጨማሪም “ፍትህ ፍትህ ፍትህ ;We Need Justice ፤Hijab Is Beauty ፤ justice Is Denied የሚሉት መፈክሮች ይገኙበታል፡፡” ያሉት ዘገባዎቹ በርካታ ፊኛዎች የተውለበለቡና ወደ ሰማይ የተለቀቁ ሲሆን ተቃውሞው በከፍተኛ ድምቀት ተከናውኗል ሲሉ ገልጸዋል::
የዛሬው የበኑር መስጅድ ተቃውሚ መንግስት በሴኩላሪዝም ሽፋን እየፈጸመ ያለውን የሂጃብ ገፈፋ የሚያወግዝ ሲሆን በተጨማሪም በህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ እጸፈጸመ ያለውን የፍትህ መዛባት ፤ በማረሚያ ቤቱ የሚፈጸሙ ግፎችን ለማውገዝ ነው የሚሉት አስተባባሪዎቹ መንግስት ሙሉ በሙሉ ተቋሞውን በሃይል አስቁሚያለሁ ሲል የነበረ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ ግን ድንገተኛ ተቃውሞ በማድረግ አስገራሚ ተቃውሞውን ገልጹዋል፡፡
ስለዛሬው ስልፍ ቢቢኤን በሰበር ዜናው ያስደመጠውን ያድምጡ

ይህም አልፎ እናየው ይሆናል

ከደቂቃዎች በፊት ሠንጋተራ አካባቢ ነበርኩ፡፡ አንድ ቦታ ላይ ችምችም ብለው የተሠሩና በመጠናቀቅ ላይ ያሉ ሦስት ትላልቅ ሕንጻዎችን አየሁ፡፡ ለቀድሞው ቁጭራ ሠንጋራ ከፍተኛ ግርማ ሞገስ አላብሰውታል፡፡ ከአንድ ሰው ጋር ስለነበርኩ ወሬ ለማጧጧፍ ፈለግሁና በቀልድ መልክ “እርግጠኛ ነኝ እነዚህ ሕንጻዎች የትግሬ መሆን አለባቸው” አልኩ፡፡ ያ አብሮኝ የነበረ ሰው ለካንስ ዝርሩን ያውቅ ኖሮ ቀጣዩን ታሪክ አጫወተኝ፡፡ እኔም ይህ ዓይነቱ ነገር ቢያስጠላኝም ታሪክን እየመዘገቡ ላሉ ሰዎች አንዳች ግባት ይሆናል በሚል እሳቤ ባጭሩ ልነግራችሁ ወደድኩ፡፡ ለነገሩ ሳይመዘገብ የቀረ ወያኔዊ ቅሌት ሲኖር አይደል! ለማንኛውም ምድረ አበሻ በምቀኝነት ተንጨርጨሪ እንጂ ይህችን የሰማሁዋትን ነገር አሁኑኑ እዘረግፋታለሁ፡፡
የዚህ ሕንጻ ባለቤት ብርሃኔ ግደይ ይባላል፡፡ አበባ ግደይ የምትባል እህቱ መገናኛ ሚ/ር ከፍተኛ ባለሥልጣን ናት አሉ፡፡ ሚስቱም የሥዩም መስፍን እህት ናት፡፡ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ እዚሁ ሠንጋራ ላይ “ዮቤክ ኤሌክትሮኒክስ” የምትል አንዲት ትንሽዬ ሱቅ ነበረችው፡፡ በዚያች እየተዳደረ  እንደማንኛውም የአካባቢው አነስተኛ ነጋዴ ራሱንና ቤተሰቡን በዝቅተኛ ኑሮ ያስተዳድር ነበር፡፡ ነገር ግን ወዳለው ተጠጋ ነውና በዘሩ ከእብቁና ከንፋሹ የመሀል አገር ሣይሆን ከ“ወርቁ” ዘውግ የተገኘ ቀብራራ ወያኔ ከመሆኑም በተጨማሪ ከቱባው ወያኔ ከሥዩም መስፍን ደም ጋር ደሙን በጋብቻ በመቀላቀሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ሀብትና ንብረት  ባለቤት ሊሆን በቅቱዋል፡፡ መታደል ነው፡፡ የምን ኅሊና – የምን ማሰብና አንጎልን መጠቀም ነው፡፡ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ያለችው ፍጡር ዱሮ ለወንድሞቼና እህቶቼ የተሰጠች ልዩ መጠሪያ ነበረች፤ አሁን ደግሞ ዘመን ተገለበጠና እኔ ለወያኔዎች መጠሪያነት አዋልኳት፡፡ ይህም ሲያንሳቸው ነው፡፡ በማሰር፣ በመግደል፣ በሸርና በተንኮል ዜጎችን በማጣላትና በማናጨት፣ በጥቅም በመደለል፤ እስከ‹ጥግ›  በመጨከን … ሥልጣንንና ሀብትን እስከወዲያኛው ማቆየት ቢቻል ኖሮ ከወያኔ በብዙ ነገር ይሻሉ የነበሩት ብልጡ ራስ ተፈሪ እና/ወይም አረመኔው መንግሥቱ ኃ/ማርያም ከሁለት አንድኛቸው እሰካሁን አራት ኪሎን የሙጥኝ ብለው ባልለቀቁ ነበር – እንደዚያ ያለ ቀመር አይሠራም፤ የለምም፡፡ ግን ሰዎች ስንባል በጣት ከሚቆጠሩ ጥቂት የታደሉ በስተቀር ብዙዎቻችን በተፈጥሯችን የለየልን ደናቁርት ስለሆንን ይመስላል አንዳችን ከሌላኛችን አንማርም፡፡ የነዚህ የወያኔዎች ድንቁርናና አህያነት ደግሞ ለከት አጣ – ግን እኮ ልማድ ሆኖብን እንጂ አህያ ለመልካም ተምሣሌትነት ነበር መጠቀስ የነበረባት – በለፋችና በቅንነት ባገለገለች ለምን መሳደቢያ ትሁን፡፡ ይህም አንዱና ሌላው ሞኝነት ነው፡፡
ለነገሩ ወያኔዎች ቢ…ሩ ቢቀ…ብን እውነታቸውን ነው፡፡ ለቅጣት መምጣታቸውን ለሃይማኖታውያኑ የስብከት ፍጆታ እንተወውና – እነሱም እንደሌሎቻችን ሁሉ በሕይወት አሉ ብዬ በበኩሌ ባላምንም  – እኛም ከነሱ ከወያኔዎቹ የባስን አህዮች ነን – ከአራት ሚሊዮን የተውጣጡ የጠራራ ወንበዴዎች ዘጠና ምናምን ሚሊዮን ሕዝብ ካነሆለሉና ከፋፍለው ከገዙ “ይደልዎሙ” (ይገባቸዋል) ከማለት ውጪ ምን ሊባል ይችላል? “ወደሽ ከተደፋሽ …” ነው ነገሩ ወንድሜ፡፡ ቀኒቱ ግን አትቀርም፡፡ ሰማይ ዝቅ፣ ምድር ከፍ ብትል የፈጣሪን ፍርድ ሊያስቀር የሚችል ወያኔዊ “ጥበብ”ና ኃይል የለም፡፡ ሃያ አራት ዓመት ደግሞ በሀገር ደረጃ ሲታይ በጣም ኢምንት ዘመን ነው – ከወያኔዎች የተለዬ ጭራቃዊ አገዛዝ አንጻር እንደ 2400 ዓመታት ቢቆጠርም፡፡ ሦስት ሺህ ዘመንስ በከንቱ ነጉዶ የለም እንዴ፡፡ በነገራችን ላይ ወያኔዎች አይዟችሁ – በያዛችሁት መንገድ እንደልባችሁ ፈንጩ፡፡ ግደሉ፤ እሰሩ፤ ጠጡ ፤ ብሉ፤ ጨፍሩ፤ ተዋሰቡም፡፡ የምትኖሩት ዕድሜም ከሺ በላይ በመሆኑ ስለዕድሜ ዘመናችሁ አትጨነቁ፡፡ ብትሞቱም ትተካካላችሁ – እስከዚያው፡፡ ያቺ ክፉ ሰዓት ስትመጣ ግን …
ብርሃኔ በቀሰቀሰብኝ ቁጭት አዲስ አበባን ለቅጽበት ያህል ቃኘሁዋት፡፡ እናም እላለሁ – በተለይ አዲስ አበባ ውስጥ አሥር አዳዲስ ዘመናዊ ሕንጻዎችን ካያችሁ ካለማጋነን ዘጠኙ የወያኔ ትግሬ ናቸው፡፡ አሥር ዘመናዊ አውቶሞበሎችን አስፋልት ላይ ሲፈሱ (“ሱ”ን አጥብቁልኝ ‹ፕሊዝ›) ካያችሁ አሁንም ካለማጋነን ስምንት ያህሉ የወያኔ ትግሬዎች ንብረቶች ናቸው፡፡ አሥር ሱቆችን ካያችሁ በጣም ዝቅተኛ በሆነ ግምት ሰባቱ የወያኔ ትግሬዎች ለመሆናቸው አትጠራጠሩ፡፡ አሥር የዩኒቨርስቲ ምሩቃንን ብታዩ እጅግ ሲያንስ ስድስቱ የወያኔ ትግሬዎች ናቸው፡፡ አሥር ለማኞችን ብታዩ ከዘጠኙ ውስጥ ትግሬ ላታገኙ ትችላላችሁ፡፡ በኔ ይሁንባችና “ሠነፍ” ወይም ብልጣብልጥነት የጎደለው ‹እንከፍ› ወይም ነገን ማስተዋል የቻለ አስተዋይ ወይም ህመምተኛ ካልሆነ በስተቀር የትግሬ ለማኝ አሁን የለም ወይም ቢያንስ ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ አሃ! የሁሉ ነገር አዛዥ ናዛዥ ማን ሆነና! ትንግርት ነው ምዕመናን፡፡ በዓለም ታሪክ ቀርቶ በሲዖል እንኳ እንዲህ ያለ መድሎና ጎጠኝነት ታይቶም ሆነ ተሰምቶ አያውቅም፡፡ ያዝልቅላቸው፡፡ ግን ወዮ ለቀኑ፤ ወዮ የፈጣሪ ፍርድ ወደ ምድር በወረደ ጊዜ! ወዮ ለኢትዮጵያዊው የምፅዓት ቀን! እንዲህ ያለው ጭፍን ጉዞ ምን ሊያስትከል እንደሚችል የማያውቅ እንደብርሃኔ ግደይና እንደ‹ሐጎስ ጎይቶም› ያለ ድፍን ቅል ዜጋ ጭንቅላቱ ውስጥ ጭቃ እንጂ አንጎል የሚባል ነገር የለውም፡፡ ትንሽነት ለካንስ መድሓኒት የሌለው ክፉ ደዌ ነው፡፡ ትንሽነት ለካንስ በሰው አምሳል እንደሚንቀሳቀስ አውሬና ጭራቅ ማለት ነው፡፡ ከትንሽ አስተሳሰብ ይሰውራችሁ፡፡ በቃኝ፡፡
ግን ግን ቢበቃም ቅሉ ለነአብርሃ ደስታ፣ ለነፀጋዬ ገ/መድኅን፣ ለነጌታቸው ረዳ (የኢትዮሰማይ ድረገፅ አዘጋጅና ባለቤት)… ስንት ቆጠርኩ ይሆን? አይ፣ ደከመኝ ይቅርብኝ፤ እናም ከምር በቃኝ፡፡
አንዱ ነኝ ከአዲስ አበባ – ስም ዱሮ ቀረ!


Comment

ግርማ ሠይፉ፣ ሠራዊት ፍቅሬና ቴዎድሮስ አድሐኖም ያልመረጥናቸው የህዝብ ልዑካን (ሁኔ አበሲኒያ)

ከሠሞኑ ወደግብፅ የሚያቀና ህወሀታዊ የልዑካን ቡድን ሲቋቋም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊጠብቀው በማይችለው መልኩ የልኡካን ቡድኑ ውስጥ የአንድ ሠው ስም ተሠማ “ግርማ ሠይፉ” የሚል በርካቶች ተገረሙ ወይ አንቺ ሐገር ሲሉም አዘኑ፡፡ ከዚህ ቀደም ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በፓርላማ ተብለው በተቀመጡባቸው ያለፉት 4 ዓመታት ለሐገራችን ፖለቲካ ያንን ያህል ለውጥ ባያመጡም፤ የህሊና እስረኞቹ ይፈቱ ዘንድ አሁንም ያንን ያህል ጠንከር ያለ ስረ ባይሠሩም አቶ ግርማ ሠይፉን ሌሎች አካላት ሲተቿቸው ግርማ ሠይፉን ደግፈው ከሚቆሙ አካላት መካከል አንዱ እኔ ነበርኩኝ ብዬ አስባለው፤ አስባለው ያልኩት ስለግርማ ሠይፉ ከኔ በላይም የሚያስብ ሌላ ህወሀት የተሠኘ የሠዎች ስብስብ መኖሩን ስላልተረዳሁና በቅርቡ እየታዩ ያሉትን የግርማን መንሸራተቶች ባለመመልከቴ ነበር፡፡
Renaissance-Dam-Contentበሐገራችን ፖለቲካ ማየት ከማንፈልጋቸው ነገሮች የከዳተኝነት ፖለቲካ አንዱ እና ዋነኛው ነው፤ ይህ ህዝብ ለፍቶ ከሚያገኘው የወር ገቢው ላይ ግብር ተወስዶበት ፓርላማ ለሚገኙ የህዝብ ተወካዮች በአበል እና በደመወዝ መልክ ይሠጣል ህዝቡ ይህንን የሚያደርገው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተሠኘው የሚገኙ አባላት መብቴን የሚያስከብር ህግ ያወጡልኛል፤ ስለእኔ መብት ስለቆሙ የታሠሩ የህሊና እስረኞችን የበላይ አካል እንደመሆኑ ያስፈታልኛል ብሎ አለመሆኑ እሙን ነው ምክንያቱም በህወሀት ፓርላማ ውሳኔ ችግሬ ይፈታልኛል ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ ካለ እርሱ የህወሀት አባል መሆን አለበት ሆኖም ተባራሪ ሆነው ፓርላማ ውስጥ የሚታዩ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የህዝብ ችግር ያሏቸውን ጉዳዮች ነቅሰው አውጥተው ለፓርላማው ሲያቀርቡ እንመለከት ነበር እነዚህ ሠዎችም ሲከዱ ተመልክተናል እውን ግርማ ሠይፉ ካዳ? ግርማ ሠይፉ ካዳ ወይስ አሁንም ለህዝቡ እንደቆመ ነው የሚሉትን ጉዳዮች ከማንሳታችን በፊት ከግርማ ሠይፉ ጋር የልዑካን ቡድኑ አባላት ውስጥ የሚገኙ አባላት እነማን ናቸው የሚሉትን መመልከት ተገቢ ይመስለኛል፡፡
የህዝብ ልዑካን ቡድን ሲቋቋም መታሠብ ካለበት መካከል አንደኛው እና ዋናው ነገር የልዑካን ቡድኑ አባላት በህዝብ የታመኑ፣ በመልካም ስነምግባራቸው አርዓያ የሆኑ እና ለሌሎች ምሳሌ የሚሆኑ መሆን ይኖርባቸዋል ወደግብፅ ባቀናው የልዑካን ቡድን ውስጥ የተካተቱት ግን በየትኛውም መለኪያ የህወሀት ጉዳይ አስፈፃሚ ከመሆን ውጪ የህዝብ አመኔታ ያላቸው ግለሠቦች አይደሉም፡፡ ከልዑካን ቡድኑ ውስጥ መካከል አንዱ ሠራዊት ፍቅሬ የተሠኘው ግለሠብ ነው፡፡ ይህ ግለሠብ ልክ እንደሌሎቹ የህወሀት አባላት እና አመራሮች ከወታደር ቤት ወጥቶ ሚሊየነር የሆነ ግለሠብ ነው፡፡ ሠራዊት ፍቅሬ የህዝብ ተወካይ መሆን የማይችልባቸውን ምክንያች ለማንሳት ያህል ከዛሬ ሁለት አመት በፊት በአንድ ተማሪ ላይ በማን አለብኝነት የፈፀመውን የአስገድዶ መድፈር ሙከራ ማየቱ ተገቢ ነው፡፡ ሠራዊት ፍቅሬ አስገድዶ ሊደፍረኝ ሲል አመለጥኩኝ ያለችውን ግለሠብ አዲስ አድማስ የተሠኘው ሐገር ቤት የሚታተም ጋዜጣ አነጋግሯት እንደነበረና ከጥቂት ቀናት በኋላ በሠራዊት ፍቅሬ የመድፈር ሙከራ የተደረገባት ተማሪ ሁኔታ ተደባብሶ ቀረ ወጣቷ አሁን የት እንዳለች እንኳን አይታወቅም አዲስ አድማስም ከህወሀት ሠዎች ሊደርስበት የሚችለውን ዛቻ በማሠብ ተወው ይህንን ድርጊት የፈፀመው ሰራዊት ፍቅሬ ነው አንዱ የዚህ ልዑክ አባል፡፡ ሌላኛው የልዑካኑ ቡድን አባል ቴዎድሮስ አድሐኖም ወይም እንደሱ አጠራር ቴድሮስ አድሐኖም ነው፡፡ ይህ ግለሠብ አምና በዚህ ሠዓት ሣውዲ አረቢያ ይገኙ ለነበሩ ሠዎች ሞት እና እንግልት ተጠያቂ ሊሆን የሚችል ሠው ነው፡፡ ቴዎድሮስ አድሐኖም የውጪ ጉዳይ ሚኒስተሩነቱን እና የህወሀት አባልነቱን ተጠቅሞ ለሳውዲአረቢያ የንጉሳውያን ቤተሠቦች በላከው ደብዳቤ ኢትዮጵያውያኑ ከሳውዲ ኢሠብዓዊ ድርጊት ተፈፅሞባቸው እንዲወጡ ማድረጉ ይታወሳል ይህ ግለሠብ ስለእውነት እና ስለህዝብ የቆመ ቢሆን ኖሮ የሳውዲ ንጉሶችን አሳምኖ የኢትዮጵያውያን መውጫ ቀን በማስረዘም ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ከእልቂት እና ከግፍ ያድን ነበር ሆኖም ዛሬ ይህ ግለሠብ የሠራቸው ወንጀሎች ተደብቀውለት ዛሬ የህዝብ ልዑካን ተብሎ ተሠይሞ ይገኛል፡፡ ግርማ ሠይፉም ከእነዚህ ሠዎች መካከል ይገኛል የህዝብ ልዑካን ቡድን ተብሎ፡፡ ከሠራዊት ፍቅሬ እና ከቴዎድሮስ አድሐኖም ጋር አብሮ መስራትን የመሠለ ምን ከዳተኝነት ይኖር ይሆን?
ግርማ ሠይፉ የልዑካን ቡድኑ ውስጥ መካተቱን ሳይነግረን ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ “ይህ የአሁኑ ሠንደቅ ዓላማ ለእኔ ከበፊቶቹ ይሻለኛል፤ ሁሉም የታሠሩት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ንፁህ ናቸው ብዬ አላምንም” ምናምን የሚሉ በህዝብ ላይ የተቀለዱ መጥፎ ንግግሮችን በኢንተርቪው እና በብሎጉ ላይ አሰምቶናል በተጨማሪም አምና አንድነት ጠርቶት በነበረው ሠላማዊ ሰልፍ ላይ ሠልፈኛው ሲግናል አካባቢ ሲደርስ ሲግናል ለአንድ ጎሳ አባላት ብቻ የተሠሩትን ህንፃዎች ተመልክቶ ዝም ብሎ ማለፍ ያልቻለው ሠልፈኛ ሌባ ሙሰኛ እያለ ሲጮህ ዝም በሉ እያለ ሠልፈኛውን ከሀብታሙ አያሌው ለመነጠል ሲሞክር እንኳን በግርማ ላይ ተስፋ አልቆረጥኩም ነበር አሁን ግን ከኢትዮጵያ የምንም ጊዜ ጠላቶች ጋር አበረ፡፡ የልዑካን ቡድኑ ውስጥ ያሉት ሠዎች እኮ በበደኖ እና በአርባጉ የአማራውን ጎሳ የጨፈጨፉ፤ በአምቦ ንፁሐን የኦሮሞ ተማሪዎችን የገደሉ፤ ፤ በጋምቤላ ንፁሀንን ያስፈጁ፤ ፕ/ር አስራትን እና አሠፋ ማሩን የመሳሰሉ ድንቅ የሐገራንን ምሁራን ያስገደሉ፤ እስክንድርን፤ ርዕዮትን፤ በቀለ ገርባን፤ ኤርባና ሌሊሳን፤ የሺዋስ አሠፋን፤ አብርሐ ደስታን፤ ዳንኤል ሺበሺን፤ አበበ ቀስቶን፤ ናትናኤልን፤ ሐብታሙን፤ እና ሌሎችንም ያሠሩ፤ ከጥቂት ቀናት በፊት እንኳን የሠማያዊ ፓርቲን እና የትብብሩ አባላትን ቶርች ያደረጉ፤ በትላንትናው እለት ባህርዳር ላይ ህዝብን ያስፈጁ ሠዎች ጥርቅም ውስጥ ግርማ ዘው ብሎ የገባው፡፡
ግርማ ቆም ብሎ አስቦ ህዝቡን ይቅርታ ብሎ ጠይቆ እራሱን ከፖለቲካ ከማግለል ውጪ ሌላ አማራጭ ይኖረዋል ብዬ አላስብም ፓርቲው አንድነትም ቢሆን እንደግርማ ሠይፉ ያሉ አባላትን ይዞ መቀጠሉ ለፓርቲው አደጋ መሆኑን ተገንዝቦ ህዝቡን ይቅርታ ሊጠይቅ እና ግርማ ሠይፉን ሊቀጣው ይገባል ይህ ካልሆነ ግን ለወትሮውም በሐገራችን ፖለቲካ ተስፋ ለቆረጠው ህዝባችን ጭራሹኑ ፊቱን እንዲያዞር የሚያደርግ ታሪክ ሲወቅሠው የሚኖር ተግባር ከዛም አልፎ ሌሎች እየለፉ ያሉ ፓርቲዎች ላይ ህዝቡ እምነት እንዳይኖረው የሚያደርግ አስወቃሽ ስራ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ በፊት ከግርማ እና ከፓርቲው መልስ ያስፈልጋል

ዛሬ በባህርዳር ፋሽስቱ የኢሕአዴግ መንግስት ያቆሰላቸውና የገደላቸው ክርስቲያኖች (ፎቶ በጥቂቱ)

(ዘሐበሻ) የእምነት ቦታችን ተላልፎ ለባለሃብት አይሸጥም በሚል ጥያቄ በማንሳት ኣደባባይ በወጡት ክርስቲያኖች ላይ ኣምባገነኑ የኢህኣዴግ መንግስት ጥይት ሲያረግፍባቸው ውሎ ፫ ሰዎችን አና ፯ ሰዎችን ማቁሰሉን ዘሐበሻ ቀደም ብላ ዘግባ ነበር። የሞቱት ቁጥር ወደ ፯ አንዳደገ የቆሰሉት ደግሞ ከ፳ በላይ አንደሚደርስ ኣሁን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። አርምጃ ከተወሰደባቸውና ህይወታቸው ካለፉት መካከልም ፎቶዎች ኣግኝተናል ይመልከቱት።
bahrdar 5
bahrdar 7
4
bahr dar 1
bahr dar 2
bahrdar 3

ከ3 ሳምንት እንግልት በኋላ ቴዲ አፍሮ ወደ አውሮፓ በረረ

ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከ3 ሳምንት እንግልት በኋላ ዛሬ ምሽት ከቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ተነስቶ ወደ ኦስሎ ኖርዌይ ጉዞውን ጀምሯል።
teddy afro
ኢትዮጵያዊው የፖፕ እና ሬጌ ሚዚቃ አቀንቃኝ በአውሮፓ ከተሞች የሙዚቃ ዝግጅቱን ለማድረግ ከአዲስ አበባ ተነስቶ የነበረው በወሩ መጀመርያ ላይ ነበር። ባለፈው ሃሙስ ዲሴምበር 4፣ 2014 ቦሌ አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ጣብያ እንደደረሰ የደህንነት አካላት እንዳገቱት እና ፓስፖርቱንም እንደቀሙበት በልዩ ልዩ የዜና ምንጮች መዘገቡ ይታወሳል።
አርቲስቱ ለምን ወደ ውጭ እንዳይወጣ እንደታገደና ፓስፖርቱም ለምን እንደተቀማ እስካሁን በይፋ የተነገረ ነገር የለም። አንዳንድ የዜና ምንጮች ጉዳዩን ቀረጥ ካለመክፈል ክስ ጋር አያይዘው አቅርበውታል። ይህ መላ ምት ፍጹም ስህተት ነው። ምክንያቱም ድምጻዊው በጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መርማሪ ቡድን ሙሉ ቀን ታስሮ ቢውልም ያለምንም ክስ ነበር የተለቀቀው። ቴዲ አፍሮ በዚህ ጉዳይ ቢከሰስ እንኳን አገር ውስጥ ሲገባ ታክስ ያልተከፈለበት መኪና መንዳት ፓስፖርት የሚያስነጥቅ ወንጀል አይደለም። ቴዲ አፍሮ፣ የተጠቀሰውን ተሽከርካሪ የገዛው በሕጋዊ ደረሰኝ ቀረጥ ከፍሎ መሆኑን በወቅቱ ለፍርድ ቤቱ አስረድቶ ነበር የተለቀቀው።
በጉዞ እገዳው ሳብያ ሁለት የአውሮፓ ኮንሰርቶቹ ተሰርዘዋል። ቀድሞ አውሮፓ የገባው የቴዲ አፍሮ ማናጀር ዘካርያዝ ጌታቸው እና አቡጊዳ ባንድ ስራቸው እንዲተጓጎል ተደርጓል። በአውሮፓ የቴዲ ኮንሰርት ፕሮሞተሮች ለአላስፈላጊ ወጪ ተዳርገዋል። የድምጻዊው አፍቃሪዎቹ ስሜት በእጅጉ ተጎድቷል።
ቴዲ አፍሮ ከጠበቆቹ እና ከስራ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን ላለፉት አስራ አንድ ቀናት፤ ጉዳዩን ለማጣራት እና እልባት እንዲያገኝ ለማድረግ አቅሙ የሚፈቅደውን ሁሉ ሲጥር እንደነበርም ታውቋል።
ከሁለት ሳምንታት እንግልት በኋላ በትላንት ምሽት የገዛ ፖስፖርቱን አግኝቷል።
አርቲስቱ ከሃገር እንዳይወጣ መከልከል፣ ፓስፖርቱ መቀማትና እንዲጉላላ ማድረጉ በአብዛኛው ኢትዮያዊ ዘንድ ቁጣ ማስነሳቱን እና በገዥው ፓርቲ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዚህ ከአንድ መንግስት በማይጠበቅ ድርጊት የተነሳ የገዢው ፓርቲ አባላት ሳይቀሩ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ተስተውለዋል።
ቴዲ አፍሮ በነገው እለት ማለትም ቅዳሜ – 20 ዲሴምበር 2014 ኦስሎ ላይ ዝግጅት አለው። ሌሊቱን ተጉዞ አድሮ ምሽቱን ይጫወታል። ባንዱም ኦስሎ ላይ በልዩ ዝግጅት ይጠብቃዋል። ከዚያም በሳምንቱ ማለትም በ 27 ዲሴምበር 2014 በስዊድን ከተማ፤ በ 31 ዲሴምበር 2014 ፍራንክፈርት፤ በ 3 ጃንዋሪ 2015 በሎዛን-ስዊዘርላንድ የሙዚቃ ስራውን ያቀርባል።
ከዚያም በ ጃንዋሪ 10፤ 2015(ለኢትዮጵያ ገና) አምስተርዳም ላይ ልዩ ዝግጅቱን ይዞ ከአቡጊዳ ባንድ ጋር ይመለሳል። ከአምስተርዳም በኋላ ቀጣይ ስራዎቹ ፊንላንድ እና ዱባይ ናቸው።
በዘንድሮው የቴዲ አፍሮ አውሮፓ ኮንሰርቶች ከምንግዜውም የበለጠ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያውያን የሙዚቃ አፍቃሪዎች እንደሚገኙ ይገመታል