Tuesday, October 21, 2014

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ችሎት ትናንት እና ዛሬ ቀጥሎ ዋለ

የመከላከያ ምስክሮች በዋና ዋና ጭብጦች ላይ የኮሚቴዎቹን ንጹህነት እየመሰከሩ ነው!
ድምፃችን ይሰማ እንደዘገበው:-
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ችሎት ትናንት እና ዛሬ ቀጥሎ ውሏል፡፡ ችሎቱ ባለፈው ዓመት ጀምሮት የነበረውን የመከላከያ ምስክሮች ሂደት አቋርጦ በዚህ አመት ዳግም ቢጀምርም ከጥቅምት 3/2007 ጀምሮ ‹‹ኤሌክትሪክ ሄዷል፣ ኤሌክትሪክ ተቆረጠ››፣ እንዲሁም ‹‹ካርድ አልተሞላም›› በሚሉ ምክንያቶች ችሎቱ ከሳምንት በላይ ለሆነ ጊዜ ድጋሚ እንዲቋረጥ ሆኖ ነበር፡፡ ዛሬ ችሎቱ ዳግም ሲጀመር ባለፈው የመከላከያ ምስክርነታቸውን ጀምረው መስቀለኛ ጥያቄ ሳይቀርብላቸው በቀሩት አቶ አህመድ ኡመር ሲጀምር ምስክነርት በሰጡበት በጭብጥ 10 ላይ አቃቤ ህግ ለመከላከያ ምስክሩ አቅርቦ ያልጨረሳቸውን መስቀለኛ ጥያቄዎች አቅርቦ አቶ አህመድ ኡመር በቂ ምላሽ ሰጥተዋል።
muslim dim
አቶ አህመድ ኡመር 53ኛ ምስክር በመሆን በጭብጥ 11 ላይ ትናንት ምስክርነት ሲሰጡ በሐምሌ 2004 የመንግስት ታጣቂ ኃይሎች በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የፈፀሙትን ጭፍጨፋ የገለጹ ሲሆን በታላቁ አንዋር መስጂድ በተደረገው የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደጉት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ሕገ ወጥና ኹከት ቀስቃሽ፣ እንዲሁም ጸረ ሰላም ንግግር ሳይሆን ሰላማዊና ለህዝቦች የጋራ መኗኗር ጠቃሚ ሐሳብ ለህዝቡ ማስተላለፋቸውን ለችሎቱ አስረደትዋል፡፡ 54ኛ የመከላከያ ምስክር ሆነው የቀረቡት አቶ ጀማል ሽኩር ደግሞ በጭብጥ 7 ላይ ሰፊ ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡ በእማኝታቸው እሳቸው በሚኖሩበት ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የመጅሊስን ምርጫ አጠቃላይ ሂደት ሲመሩትና ሲያቀናብሩት የነበሩት የአካባቢው የወረዳ ሀላፊዎችና የፖለቲካ ሹመኞች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የቤት ለቤት ቅስቀሳውን ጨምሮም ሂደቱ በሙሉ በመንግስት አስፈጻሚዎች ይዘወር እንደነበርም ገልጠዋል፡፡
ዛሬ በቀጠለው ችሎትም የ3 መከላከያ ምስክሮች መከላከያ ምስክርነቶች የተደመጡ ሲሆን በ2004 ከተሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አህባሽ ስልጠናዎች ትልቁ በነበረውና በኢትዮ-ቻይና የሙያ ኮሌጅ በተካሄደው የጠመቃ ስልጠና ከሰልጣኞቹ አንዱ የነበሩት አቶ ሰኢድ ኢብራሂም በስልጠናው ሂደት ላይ የነበሩትን የመንግስት እጆችና ሕገ ወጥ አካሄዶች ሲያስረዱ ቀጣዩ ምስክር አቶ ሙሐመድ በሐምሌ 2004 የመንግስት ታጣቂዎች አንዋር መስጂድ ውስጥ ይገኙ በነበሩ ምእመናን ላይ የፈጸሙትን ጭፍጨፋ በጭብጥ 11 ማእቀፍ መሰረት ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡
ጋዜጠኛ አቡበከር አለሙ በተከሰሰበትና በፒያሳው ኑር መስጂድ ሰላማዊ ውይይት እንዳይካሄድ በማድረግና በማደናቀፍ ለተመሰረተበት ክስ አቶ አብዱልሃኪም አስፋው የመከላከያ ምስክርነት ሰጥዋል፡፡ በምስክርነታቸውም በወቅቱ አቡበከር ኹከት ፈጣሪ ንግግር እንዳልተናገረና የመንግስት ክስ ከሚለው በተቃራኒ በወቅቱ ሌሎች ሰዎች የተሰጣቸውን ጥያቄ የመጠየቅ መብት ሁሉ ተነፍጎ መድኩን ጥሎ ለመውጣት መገደዱን አስታውሰዋል፡፡ የዛሬዎቹ ምስክሮች በሰጡት ምሰክርነት ላይ ችሎቱ መስቀለኛ ጥያቄ አቅርቦላቸው በተገቢው መልኩ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ችሎቱ በነገው እለትም ሂደቱን ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በሌላ በኩል በአቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ ተከሰው በነጻ የተለቀቁት ሸኽ አብዱህራማን ኡስማን ከሊል እና አሊ መኪ በድሩ ዳግም ወደ ወህኒ እንዲገቡ በፌደራሉ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እንደተወሰነባቸው ታውቋል፡፡ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍ/ቤት 4ኛው ወንጀል ችሎት በታህሳስ 3/2006 በሰጠው ብይን ሁለቱን ተከሳሾች ጨምሮ 8 ሙስሊሞች አቃቤ ህጉ ካቀረበባቸው ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ አቃቤ ህጉ ባቀረበው ይግባኝ መሰረት ጉዳያቸው ሲታይ የቆዩት ሸኽ አብዱራህማን እና አሊ መኪ ድጋሚ እንዲታሰሩ ወሳኔ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ከህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጋር ተከሰው ፍርዳቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በነጻ የተሰናበቱት ሸኽ አብዱረህማን ኡስማን ከሊል እና አሊ መኪ በድሩ በፍርድ ቤት ድጋሚ እንዲታሰሩ በመወሰኑ ሸኽ አብዱረህማን አሁን በቂሊንጦ ወህኒ ቤት የሚገኙ ሲሆን ሌላው ወንድም አሊ መኪም በተገኘበት እንዲያዝ መባሉ ታውቋል፡፡ በዚህም መሰረት የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የሰጠባቸውና በችሎቱ ተገኝተው የነበሩት ሸኽ አብዱረህማን ኡስማንም ችሎቱ እንደተጠናቀቀ በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸውና አሁን በቂሊንጦ ዞን 3 እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ጫናው በርትቷል “ሰላማዊ ትግል የሚባል ነገር አይሰራም፤ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን›› -የብአዴን አመራሮች

 ‹‹ሰላማዊ ትግል የሚባል ነገር አይሰራም፤ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን፡፡››
የብአዴን አመራሮች
በምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ከገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት የሚደርስባቸው ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ጸሃፊ የሆነው ጠበቃ ሳሙኤል አወቀ በእሱና በሌሎች የፓርቲው አመራሮችና አባላት ላይ ዛቻ እንደሚፈጸምባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
blue party
የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ ቢሮ በ2006 ዓ.ም የእቅድ ግምገማ እና የ2007 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም እቅድ በተወያየበት እና የሁሉም ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የስራ ሂደት ባለቤቶች በተገኙበት፣ ‹‹ሳሙኤል አወቀ የሚባል በጥብቅና ሽፋን የመሬት ፖሊሲውን የሚታገል፣ ለተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊ አርሶ አደሮች ጥብቅና የሚቆም፣ ከአሸባሪ ጋር ግንኙነት ባለው ድርጅት አመራር የሆነን ግለሰብ በህግ ሽፋን እስር ቤት እንዲወርድ ያላደረገ አቃቤ ህግ አቃቤ ህግ አይደለም›› ተብሎ በህግ ስም እርምጃ እንዲወሰድበት ትዕዛዝ መተላለፉን ጠበቃው ገልጾአል፡፡
በተለይ የደብረማርቆስ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አቃቤ ህጎች ዋነኛ ችግራቸው ጠበቃ ሳሙኤልን በህግ ስም ማስቀጣት አለመቻላቸው እንደሆነ ተገምግመዋል ተብሏል፡፡ ጠበቃው ወዲያውኑ የፈጠራ ክስ እንደተመሰረተበት፣ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ‹‹ለፍትህ ስርዓቱ አጋዥ ባለመሆኑ›› በሚል መከሰሱንና ባልተከራከረበት ፍርድ ሂደትም 8000 ብር ቅጣት እንዲከፍል እንደተወሰነበት ገልጾአል፡፡
ጠበቃው በ28/1 እናርጅ እናውጋ ለቀጠሮ ባቀናበት ወቅትም የእናርጅ እናውጋ አስተዳደርና ጸጥታ ኃላፊ አቶ ስራው በረኩ እና የብአዴን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ መኳንንት አበበ እና ሌሎችም ከፖሊስና ከጸጥታ የመጡ አመራሮች ‹‹ምን ልታደርግ ነው? ልትቀሰቅስ ነው?›› በሚል እንዳዋከቡትና አቶ ስራው በረኩ ‹‹አንጠልጥዬ ነው እስር ቤት የማስገባህ፡፡ ማንም ሊያድንህ አይችልም›› ብለው እንደዛቱበት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
‹‹የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሆነህ በፍትህ ስርዓቱ መገልገል አትችልም፣ ጥብቅናህን መልቀቅ አለብህ፣ ነገረ ኢትዮጵያ ላይ ትጽፋለህ፣ የፍትህ መምሪያ ሃላፊውን (ጸጋየ መንግስቴ) ችግር እንደሚፈጽምብህ በነገረ ኢትዮጵያና በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ጽፈህበታል፣ እንዲህ እያደረክ መኖር አትችልም፣ አንተን ገሎ መጣል ቀላል ነው፣ ለነፍስህ የምታዝን ከሆነ አገር ልቅቅ›› ብለው እንደዛቱበት ገልጾአል፡፡
ሌሎች ጠበቃ ጓደኞቹ ከእሱ ጋር እንዳይሄዱ ‹‹እሱ ማለት ሰማያዊ ነው፡፡ ሰማያዊ ደግሞ የአክራሪ ሙስሊም ፓርቲ ነው፡፡ እናንተ ለምን ከእሱ ጋር ትሄዳላችሁ?›› ብለው እንደሚያስፈራሯቸውና ደንበኞቹ ከእሱ ጋር እንዳይሰሩ ማስጠንቀቂያ እንደሚደርሳቸው ጠበቃው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
ጠበቃውን ጨምሮ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባል ሆነው ማደራጀት መብታቸው መሆኑን ሲገልጹ የብአዴን አመራሮች ‹‹እናንተ እኛን ስለማትረዱን ነው፡፡ እኛ ጋር ሰላማዊ ትግል የሚባል አይሰራም፡፡ ወንድ ከሆናችሁ ጫካ ገብታችሁ ሞክሩን›› በሚል ለህግ የማይገዙና ለሰላማዊ ትግል ቁርጠኝነት እንደሌላቸው አሳይተውናል ብለዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የሰማያዊ ፓርቲና አመራር የሆኑ ነጋዴዎች ከፓርቲው እንዲለቁ ለማድረግ የንግድ ድርጅታቸውን እንደሚዘጉ እያስፈራሩ እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ለአብነት ያህልም አቶ ይኸይስ ቀጸላ የተባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ‹‹ሻይ ቤት ከፍተው እያደራጁ ነው፡፡ የንግድ ድርጅቱን እንደ ጽ/ቤት ይጠቀሙበታል፡፡ በመሆኑም ካላረፉ ሻይ ቤቱን እንዘጋዋለን›› እያሉ እንደሚያስፈራሩ ታውቋል፡፡
የዞኑ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የገዥው ፓርቲ ዛቻና ማስፈራሪያ እንዲሁም እርምጃዎች እየተጠናከሩ ቢሆንም እርምጃው እነሱ ተጽዕኖ በመፍጠራቸው የመጣ በመሆኑ ይበልጡን እንደሚያበረታታቸውና የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
አቶ መኳንንት አበበን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችን የእጅ ስልካቸው ላይ በመወደል ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡

Hiber Radio: ኢትዮጵያ የኢቦላ ተጠርጣሪዎችን ናሙና ወደ ኬኒያ እንደምትልክ አንድ የአገሪቱ ባለስልጣን ገለጹ; * ካራቱሪ በኪሳራ ሳቢያ መሬቱን አሳልፎ እየሸጠ መሆኑ ተጋለጠ

የህብር ሬዲዮ ጥቅምት 9 ቀን 2007 ፕሮግራም !
<... የተሰደድነው ጋዜጠኞች ደህንነታችን ዛሬም ስጋት ላይ ነው...ገደኛህን አስታመህ ሞቶ እሱኑ ሬሳውን እንኳን ለመሸኘት ለስንብት ዕድል ስትነፈግ ያሳዝናል። አገዛዙ ያው የለመደወን ነው ያደረገው ውሸት ስራቸው ነው። ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹርቤ እንደማናችንም በጫና ነው ስራውን ያቆመው እና የተሰደደው እነሱ ግን በአስከሬኑ እንኳን ፕሮፖጋንዳ ሊሰሩበት ነው። ይህ ያሳዝናል።ወቅታዊ ምላሽ ለሰጡ ወገኖቻችን ግን... >>
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ኤልያስ ጉዲሳ የቃል ኪዳን መጽሔት ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር በስደት ካለበት ኬኒያ የአገዛዙ ሰዎች እንዴት በሞት የተለየውን የሙያ አጋሩን እንኳን መሰናበት እንደከለከሉት ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)
<... በምርጫ አሁን ያለው ስርዓት ይወርዳል የሚል ዕምነት የለኝም። በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ተቃዋሚዎችን ተስፋ እያስቆረጥኩ አይደለም። ግን ምርጫ እንገባለን አንገባም ሳይሆን አስቀድመው የሁኔታዎች ትንተና ጥናት መስራት አለባቸው ። የምርጫ ህጎቹን ስታይ ፣የምርጫ አስፈጻሚውን ስትመለከት ሁኔታው ግልጽ ነው።...በምርጫ 2002 ሕዝቡ ሳይመርጥ 99.6 በመቶ አሸነፍን ተብሏል አሁን እንደውም የመለስን ራዕይ እናሳካለን በሚል መቶ በመቶ ለመጠቅለል ነው የሚሰሩት ። በዕኔ ዕምነት ከጠየከኝ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በምርጫ ከስልጣን ማውረድ አይቻልም...>
አቶ ኤርሚያስ ለገሰ የቀድሞ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ(ሙሉውን ያዳምጡት)
ኢቦላ እና ዛሬም ያልተቀረፈው ስጋት በአሜሪካ (ልዩ ዘገባ)
ዜናዎቻችን
ኢትዮጵያ የኢቦላ ተጠርጣሪዎችን ናሙና ወደ ኬኒያ እንደምትልክ አንድ የአገሪቱ ባለስልጣን ገለጹ
ሰፊ መሬት በኢትዮጵያ ያለው ካራቱሪ በኪሳራ ሳቢያ መሬቱን አሳልፎ እየሸጠ መሆኑ ተጋለጠ
በኢትዮጵአ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በምርጫ ማውረድ እንደማይቻል የስርዓቱ የቀድሞ ሚኒስትር አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ገለጹ
አቶ ሌኒጮ ለታ ምክትላቸውን ተከትለው አዲስ አበባ በቅርብ ቀን እንደሚገቡ ድርጅታቸው አስታወቀ
የዶ/ር ዲማ ነጎ ኢትዮጵአ መግባት አነጋጋሪ ሆኗል
ኤርትራ ውስጥ የመንግስት ለውጥ ያስፈልጋል ያሉ አንድ የተባበሩት መንግስታት ኤክስፐርት ስልጣናቸውን ለቀቁ
ኤርትራ አልሸባብን ሳይሆን የኢትዮጵያን ትጥቅ ያነሱ ተቃዋሚዎች እንደምትረዳ ተገለጸ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
-- Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.--

“በጋምቤላው ግጭት በተሳተፉት ላይ እርምጃ አልተወሰደም” መኢአድ

“አስፈላጊው እርምጃ ተወስዷል፤ ወደፊትም ይወሰዳል” መንግስት
በቅርቡ በጋምቤላ ክልል ጎደሬ ወረዳ፣ በዜጎች መፈናቀልና ግድያ ላይ ተሳትፈዋል በተባሉ ባለስልጣናትና ካድሬዎች ላይ መንግሥት ምንም አይነት እርምጃ አለመውሰዱን የመላ ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የገለፀ ሲሆን መንግስት በበኩሉ፤ ድርጊቱን በፈፀሙት ግለሰቦች ላይ የማጣራት ስራ ተከናውኖ አስፈላጊው እርምጃ መወሰዱንና ወደፊትም እንደሚወሰድ አስታውቋል፡፡
(ጋምቤላ ክልል)
(ጋምቤላ ክልል)

መኢአድ ሰሞኑን በፅ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ፤ በጋምቤላ ክልል በተከሰተው የዜጎች መፈናቀልና ግጭት ከ540 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንደተሰደዱ ጠቁሞ፤ በድርጊቱ የመንግስት ባለስልጣናት መሳተፋቸው ሁኔታውን በጣም አስፈሪና አስደንጋጭ ያደርገዋል ብሏል፡፡ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ዜጎችን ማፈናቀልና የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲቆም በተደጋጋሚ ሲጠይቅና ሲያሳስብ መቆየቱን ያመለከተው ፓርቲው፤ በመንግስት በኩል ተገቢ እርምጃ ባለመወሰዱ ችግሩ እየሰፋ መሄዱን ገልጿል፡፡
የዛሬ ሁለት ዓመት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉራፈርዳ ወረዳ ተመሳሳይ ድርጊት የፈፀሙትን ካድሬዎች መንግሥት በቁጥጥር ስር ማዋሉን ሲገልፅ እንደነበር ፓርቲው አስታውሶ፤ ነገር ግን የፖለቲካ ፍጆታ ከማድረግ ባለፈ እርምጃ ሲወስድ አለመታየቱንና አሁንም በጋምቤላው ድርጊት በተጠረጠሩት ላይ እርምጃ ይወስዳል የሚል እምነት እንደሌለው አስታውቋል፡፡ ባለፈው ሰኞ በክልሉ ቴፒ እና ጎደሬ ወረዳ ባገረሸው ግጭት የ5 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን የጠቆሙት ምንጮች በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል ብለዋል፡፡ ከረቡዕ ጀምሮም አካባቢው በፌደራል የመከላከያ ኃይል አባላት ከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥር እየተደረገበት መሆኑን ምንጮች ጨምረው ጠቁመዋል፡፡
ከትናንት በስቲያ ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዜጎችን ከመኖርያ ቀዬአቸው ማፈናቀልን አስመልክቶ ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ በአገሪቱ ያለው ስርአት የግለሰቦችንና የቡድን መብትን በእኩል የሚያከብርና የሚያስከብር መሆኑን ጠቁመው በጋምቤላ በተፈፀመው ማፈናቀል ላይ መንግስታቸው ጉዳዩን መርምሮ ድርጊቱን ፈጽመዋል በተባሉት ላይ እርምጃ መውሰዱንና ለወደፊትም እንደሚወስድ አስረድተዋል፡፡
ከመንግስት በኩልም ሆነ ከተቃዋሚዎች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ብሔረሰቦችን ለማጋጨት የሚጥሩ እንዳሉ የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚህ ድርጊት በሚሳተፉት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ህጋዊ መስመር እንደሚያሲዟቸው፣ ጥላቻን የሚዘሩ ኃይሎችንም ሆነ በጠባብነትና በትምክህት የተለከፉ አካላትን አደብ ለማስገዛትም መንግስት ጠንክሮ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንዘገበው ዘጠኝ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ ጥቅምት 11/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
semayawi party
ፓርቲዎቹ ለረዥም ጊዜ ስለ ትብብር ሲመካከሩ የቆዩ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፣ ዛሬ ሰባት ገጽ ያለው ሰነድ ላይ የትብብር ፊርማቸውን በማኖር ትብብሩን ሊመሩ የሚችሉ አመራሮችንም መምረጣቸው ታውቋል፡፡
ዘጠኙ ፓርቲዎች የትብብር ስምምነቱ ያስፈለገበትን ምክንያት በሰነዱ ላይ ገልጸዋል፤ በዚህም ‹‹ነጻ አሳታፊና ታአማኒ ምርጫ እንዲካሄድ በትብብር ለመስራት፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና የዜጎችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ በጋራ መታገል››ን በተመለከተ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
በዚህም መሰረት ፈራሚዎቹ ፓርቲዎች የሚከተሉትን አመራሮች ትብብሩን እንዲመሩ መርጠዋል፡-
1. ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከሰማያዊ ፓርቲ
2. ምክትል ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርጌሎ ከከንባታ ህዝቦች ኮንግረንስ
3 ዋና ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ ከኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
4. ምክትል ፀኃፊ አቶ ካሳሁን አበባው ከመኢአድ
5. ገንዘብ ያዥ አቶ ኑሪ ሙደሂር ከመኢዴፓ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
በትብብር ለመስራት ሲወያዩ ከነበሩት 14 ፓርቲዎች መካከል አንድነትና መድረክ ውስጥ የታቀፉት ፓርቲዎች ትብብሩን ለመፈረም በየ ድርጅቶቻቸው ውሳኔ ባለመተላለፉ ያልፈረሙ ሲሆን ትብብሩ እስከ ቅዳሜ እንዲጠብቃቸው ጠይቀዋል፡፡ በመሆኑም በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ትብብሩ ስለ ቀጣይ የትግል ሂደትና ስለ ትብብሩ አጠቃላይ ሂደት ላይ ነገ ጥቅምት 12/2007 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሰዓት በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

“አንዳርጋቸውን አስገድደው በማናገር ሌላ የፊልም ቅንብር ለመስራት ተፍ! ተፍ! እያሉ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል” – ታማኝ በየነ

አሻራ፦ ጤና ይስጥልኝ አርቲስና አክቲቪስት ታማኝ በየነ፤ በቅድሚያ ስለ ጊዜህ በአንባቢያን ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ። አቶ አንዳርጋቸውን ለምን ያህል ጊዜ ታውቃቸዋለህ ? እንዴትስ ትገልጻቸዋለህ?
andargacew ashara magazine cover page
ታማኝ፦ አንዳርጋቸውን የማውቀው ከምርጫ 97 ጀምሮ ነው።በምርጫ 97 ቅንጅትን ተቀላቅሎ በሚንቀሳቀስበት ወቅት ማለት ነው። ያኔ መቼም ሁላችንም ልባችን የምርጫው እንቅስቃሴ ላይ ስለ ነበር በየእለቱ እየደወልን ሁኔታውን እንከታተል ነበር። እኔም ራሴ ሃገሬ ገብቼ እንደልቤ በነጻነት ለመኖር የምችልበት ጊዜ አሁን ነው ከሚል እምነት የመግባት እቅድ ነበረኝ። አንዳርጋቸውን የማውቀው እንግዲህ በዛ ግዜ በነበረን የስልክ ግንኙነት ነው። እስኪታሰር ድረስ ማለት ነው። በነገራችን ላይ ከመታሰሩ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ያናገረኝ እኔን ነበር። ከኔ ጋር አውርተን ስልክ እንደዘጋ ነው የታሰረው።
ከንግግራችን የማስታውሰው እኔ እዚህ ሆኜ በስልክ ብቻ ከምከታተል ልምጣ እያልኩት ነበር። እሱ ደግሞ በዚህ ደረጃ መምጣት የለብህም እዛው ብትሆን ነው የምትጠቅመን እያለኝ ተነጋግረን እንደጨረስን ታሰረ። ከዚያም ተፈቶ ወደ እንግሊዝ አገር ተመለሰ። በኋላም በቅንጅት ኢንተርናሽናል ተመርጦ ሲሰራ በስልክም በአካልም እንገናኝ ነበር። ከአንዳርጋቸው ጋር የነበረን ትውውቅ ይህን ይመስል ነበር፡፡
እንዴት ትገልጸዋለህ? ላልከኝ፦በጣም አስቸጋሪ በሆነበት ጊዜና መንገድ ህልሙን ሊያሳካ የደከመ ሰው ነው!። በተማሪዎች እንቅስቃሴ ወቅት የውጭውን ዓለም ዘመናዊ ህይወት የለመዱ ከአውሮፓና ከአሜሪካ እየሄዱ የኢህአፓን ትግል ተቀላቅለው በርሃ የቀሩ ወጣቶች እንደነበሩ አንብቢያለሁ። በንባብ የምታውቀውን ታሪክ በአካል የምታውቀው ሰው ሲያደርግ ስታይ ደግሞ በጣም ከባድ ነው። በአውሮፓና አሜሪካ ህይወት ፤ ምግብ፤ አልባሳት፤መኝታ፤ መዝናኛ፤
ብቻ እያንዳንዷን ነገር በምርጫና በፍላጎት የምታደርግበትን ህይወት ለምደህ በርሃ ገብተህ፤ ድንጋይ ለመንተራስ፤ አሸዋ ለመልበስ፤ ላለመታጠብና ያልታጠበ ለመልበስ መወሰን እጅግ በጣም ከባድ ነው። አስበው ከእንግሊዝ አገር ከንግስቲቷ ከተማ ሄዶ አሸዋ ላይ መተኛት ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ!።
ባጠቃላይ አንዳርጋቸው ከልጅነቱ ጀምሮ ከራሱ ህይወት አልፎ ቤተሰቡ የከፈለውን መስዋዕትነት ሳይ የሚሰማኝ ስሜት ሃዘን ሳይሆን ይህን ሥርዓት በተለያየ መልኩ እንታገላለን ለምንል ወገኖች ትልቅ ምሳሌና አርአያ የሆነ ሰው መሆኑን ነው።
አሻራ፦ የወያኔ መንግስት አንድን ግለሰብ ለመያዝ ይህን ያህል ተጨንቆና ተጠቦ፤ ቀደም ሲል የግድያ ሙከራ ማድረጉ አሁን ደግሞ ከፍተኛ ወጪ አፍስሶ፤ ሁለተኛ አገር(የመን) የተሳተፈችበት ድንበር ዘለል አፈና መፈጸሙ ምን የፖለቲካ ፋይዳ አገኝበታለሁ ብሎ ይመስልሃል?
ታማኝ፦ በመጀመሪያ የአንዳርጋቸውን የዓላማ ጽናት (ኮሚትመንት) አብሯቸው በሰራ ጊዜ አይተውታል። ያውቁታል። ከወጣትነት ዕድሜው ጀምሮ በኢ.ህ.አ.ፓ በኋላም ከነሱ ጋር ሲሰራ ለራሴ የሚል ሰው እንዳልሆነ፤ ስልጣን ይዞ ለመንደላቀቅ፤ ቤት ለመስራት፤ መኪና … የመሳሰሉት ቁሳዊ ፍላጎት የሌለው ሰው እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቁታል። የአንዳርጋቸው የዘወትር ቁጭት ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ብዙ ያልተሟሉ ጉዳዮች ስላሏት እነሱን ለማሟላት መሆኑንም ያውቃሉ። ከቅርብ ጊዜው ብናይ እንኳ በምርጫ 97 ቅንጅትን ተቀላቅሎ በአጭር ግዜ ውስጥ ምን ያህል ህዝብን የማሰባሰብና የማደራጀት ስራ እንደሰራ እናስታውሳለን።
ባለፈው አስመራ ድረስ ቅጥር ነፈሰ ገዳይ ልከው ሊያስገድሉት መሞከራቸውን ኢሳት በዘገበበት ጊዜ እንዴት ሊሆን ይችላል?ይሄ የኢሳት ወሬ ነው ያሉኝ ሰዎች ነበሩ። እነሱ(ወያኔዎች) ግን በየት በኩል ጉዳት ሊመጣ እንደሚችል በደንብ ገብቷቸዋል።በኔ ግንዛ አንዳርጋቸው የማስተባበሩን ስራ ጥሩ አድርጎ እንደሚሰራ ስላወቁ ይመስለኛል ይህን ያህል ክትትል አድርገው ሊይዙት የቻሉት።
Tamagn
አሻራ፦ እንዳልከው አቶ አንዳርጋቸውን መያዝ ማለት የተቃዋሚውን አከርካሪ እንደመስበር ሳይቆጥሩት የቀሩ አይመስልም።ይሁንና አቶ አንዳርጋቸውን የመን ላይ ይዘው መውሰዳቸው ለግዜው ጮቤ ቢያስረግጣቸውም፤ ውጤቱ ግን “ አሳ ጎርጓሪ….” ሆኖባቸዋል የሚሉ ብዙ ናቸው፡፡ አንተስ በዚህ ሃሳብ ትስማማለህ?
ታማኝ፦ በጣም እንጂ የምስማማው።እኔ እንግዲህ ህወሃት አገሪቷን ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ በተቃዋሚነት አብሬ ኖርያለሁ። በውጭው ዓለምም አውሮፓ ፤ አውስትራሊያ ፤ አሜሪካ …ያለውን የተቃዋሚውን ወገን እንቅስቃሴ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን አውቃለሁ እላለሁ። እናም ከቅንጅት በኋላ “የምን ፖለቲካ?…ፖለቲካ በቃኝ!” እያለ የሸሸው ሰው ሁሉ በፈቃደኝነት “ምን እናድርግ?” ብሎ የመጣበት ወቅት ነው አሁን።
የአንዳርጋቸውን ነገር የተለየ የሚያደርገው ደግሞ፦ አንዳርጋቸው በየመድረኩ የሚታይ ሰው አይደለም። ከሱ በበለጠ እኔ በብዙ መድረክ እታያለሁ።
እሱ ግን የሚሰራ እንጂ የሚታይ ሰው አልነበረም፡፡ ይሁንና ህውሃት ይህን ያህል ሊያጠፋው የፈለገው አንዳርጋቸው ምን አይነት ሰው ቢሆን ነው? የሚለውን ነገር እንድት ጠይቅና እንድታገናዝብ ያደርግሃል። ለዚህም ይመስለኛል በውጭም በሃገር ቤትም የሚገኘው ህዝብ በሚያስደንቅ መልክ የተንቀሳቀሰው።
በዚሁ ጉዳይ ላይ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ምሁር ጋር ስንወያይ “በታሪክ ውስጥ አንዳንድ ሰዎች ለለውጥ ምክንያት ይሆናሉ” ነበር ያለኝ። እኔም አንዳርጋቸው የለውጥ ምክንያት እንደሆነ ነው የሚሰማኝ። በርግጥ በዚህ መልክ መሆኑና እየደረሰበት ያለውን ስቃይ ስታስብ ቢያምህም በህዝብ ውስጥ የፈጠረው የመተሳሰብና የአብሮነት ስሜት ግን ቀላል አይደለም። ፊት ለፊት የማይተያዩና መነጋገር የማይፈልጉ ተቃዋሚዎች ያወጡትን ተመሳሳይ ቁጭት፤ እልህና ንዴት የተንጸባረቀበትን መግለጫ ስታየው ህወሃቶች እራሳቸው ምነው በቀረብን ሳይሉ የሚቀሩ አይመስለኝም። አንዳርጋቸውን መያዛቸው በርግጥም “አሳ ጎርጓሪ..” ሆኖባቸዋል በሚለው ሃሳብ እስማማለሁ።
አሻራ፦ አሁን ደግሞ በቅርቡ ለእይታ ወዳቀረብከው “ተላላኪው ማነው?” ወደሚለው የምስል ዘገባ ልመልስህ፦ ይህን ስራ ለማቅረብ ምክንያት የሆነህ ወይም መነሻ ሃሳቡን ያጫረብህ ጉዳይ ምንድነው?
ታማኝ፦ እእ …! ሁሌም በአይምሮዬ የሚመላለሱ ጥያቄዎች አሉ፦ የህወሃት መሪዎች ከሟቹ ጠ/ሚንስትራቸው ጀምሮ “እነዚህ የሻቢያ ተላላኪዎች” የሚሉት ነገር አለ። እናም ሁሌ እነኝህ ሰዎች እውነት ሰው አያውቅብንም ብለው ያስባሉ? እያልኩ እራሴን እጠይቃለሁ። አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር “እነኚህ የሻቢያ ….” ሲሉ እየቀለዱ ነው? እላለሁ።
አሁን ደግሞ አንዳርጋቸውን ከያዙ በኋላ ይህንኑ አባባላቸውን ደጋግመው ሲጠቀሙበት …. አልበዛም? የሚል ስሜትና የነሱ መሬት የለቀቀ ውሸት ነው ለሥራው ያነሳሳኝ።
አሻራ፦ አቶ አንዳርጋቸውን ለሁለተኛ ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮ ያቀረቧቸው “ተላላኪው ማነው?” የሚለው የታማኝ የምስል-ዘገባ በኢሳት እንደሚቀርብ ከማስታወቂያው በማወቃቸው ሳይቀደሙ ለመቅደም አስበው ነው ሲሉ ብዙዎች አስተያየት ሰንዝረዋል። በተለይ ያቀረቡት የፊልም ዘገባ የሚጀምረው “የሻቢያ ተላላኪዎች” በሚሉ ቃላት መሆኑ የአስተያየቱን ትክክለኝነት ያጎላዋል ይላሉ…በዚህ መልክ ታይቶሃል?
ታማኝ፦ እንዳልከው የተሰነዘሩ አስተያየቶችን ሰምቻለሁ። ምንድነው ከባዱ ነገር መሰለህ ? የኔ ስራ ከመውጣቱ በፊት ለመቅደም ሲሉ አዘጋጁት ብል የኔ ከፍታ ሊጨምር ነው፤ መንጠራራት ሊሆንብኝ ነው። ከኔጋ እየተከራከሩ ነው ማለት በጣም በጣም ይከብዳል። ከተለያዩ ሰዎች የተሰነዘሩ አስተያየቶችን ስትመለከት፤ የቪዲዮው ያለ ጥንቃቄ ተከታትፎ (በአግባቡ ኤዲት ሳይደረግ) በችኮላ መቅረብ፤ የተጠቀሙበት ቃልና ከኔ ሥራ ጋር በአንድ ቀን መልቀቃቸው እነኚህን ነገሮች እንድታስብ ያደርግሃል። ጥድፊያቸው ደግሞ ከአንዳርጋቸው ቃል ጀርባ ያለውን የጣር ድምጽ እንድንሰማ እስከማድረግ ያደረሳቸው ነው። ይህን ይህን ደማምረህ ስታይ አንተ ከምትለው ጋር ይቀራረባል ። እኔ ግን ለኔ መልስ ሰጡ ብዬ ማለት ይከብደኛል።
አሻራ፦ እንደ መንግስት አስበሃቸው ይሆን ለኔ መልስ እየሰጡኝ ነው ማለት ይከብደኛል ያልከው?
ታማኝ፦ በጭራሽ!! እንደ መንግስት ቢያስቡና እኔም እንደ መንግስት ባስባቸውማ በወደድኩ ነበር። ዋናው ችግር እንደ መንግስት አለማሰባቸው ፤ እንደ መንግስት አለመስራታቸው አይደል እንዴ?እንዴት አድርጌ ነው እንደ መንግስት የማስባቸው? እኔ ይህን የምለው ሕዝብን ከማክበር ነው። በግለሰብ ደረጃ የሰጠሁት አስተያየት ወይም ያቀረብኩት ስራ ሊታይ የሚገባው በዛው ደረጃ መሆኑን ስለማምንበትና ከዛ በራቀ እንዳይታይብኝ ነው።
Fezralizm – By Tamagn Beyene Part 2
አሻራ፦ በቅርቡ በጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና አወያይነት አንተ፤ አቶ ኤርሚያስ ለገሰና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ወንድማገኝ ጋሹ በኢሳት ቀርባችሁ ባደረጋችሁት ውይይት ብዙዎችን ያስገረመ ነገር አስደምጠሃል። ያስደመጥከው ነገር፦ ጥቂት የወያኔ ባለስልጣናት በተገኙበት ውይይት ላይ አቶ በረከትና አቶ አዲሱ የተናገሩትን ነው። ይህ ውይይት በኢሳት መደመጡ ተቃዋሚው ወያኔ ጉያ ውስጥ ለመግባቱ አመላካች ሆኗል የሚሉ ብዙዎች ናቸው። ትግሉ የደረሰበትን ደረጃም ያሳያል የሚሉም አሉ፡፡ እንደ ጥያቄ ማንሳት የምሻው ይህን አይነት ጥብቅ ሚስጥር ኢሳት እጅ ሊገባ መቻሉ የተቃዋሚው የመረጃ ክፍል ጥንካሬ ወይስ ወያኔ ውስጡ ከመቦርቦሩ ጋር በተገናኘ እየሆነ ያለ …?
ታማኝ፦ ህዝቡ እኮ ታፍኖ የመጨረሻ ግፍ እየተቀበለ ነው ያለው። ደርግ ክፉ ነገሮችን ሁሉ ጨርሶ አድርጓቸው ሄዷል፤ ከደርግ በላይ ማንም ምንም አይነት ግፍ ሊፈጽም አይችልም የሚል እምነት ነበርን፡፡ እነዚህ ግን እኮ ሁሌም የሚሰሩት ግፍና ክፋት እያስደነቀን ነው።
ክፋታቸውን ቢያሳይ አንድ ምሳሌ ልንገርህ፦ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ፍርድ ቤት ቀርበው በነበረበት ጊዜ፤ በርሃብ ምክንያት መናገር እንኳ አቅቷቸው፤ ለዳኛው ምግብ በልተን አናውቅም ብለው ሲናገሩ፤ ዳኛው ደንግጦ ምግብ አምጡላቸው ብሎ ፍርድ ቤት ውስጥ እኮ ምግብ ተበላ! እነኚህ ሰዎች እኮ ያሰሩትን ሰው በርሃብ የሚቀጡ ናቸው ! እረ ስንቱን…… ዘርዝሬ እችለዋለሁ?
የህዝብን ስሜት በጥቂቱም ሊያሳይ ከቻለ አንድ ነገር ልንገርህ፦ በቅርቡ ለኢሳት አራተኛ አመት ወደ ጀርመን ሄጄ ነበር፡፡ በዝግጅቱ ላይ አንድ ሰው እጁን አውጥቶ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ሄጄ ነበር፡፡ በክፍለ ሃገር ቤተሰቤ በሚገኝበት አካባቢ ለሚኖሩ አንድ አዛውንት ለቡና መግዣ ብዬ 50 ዩሮ ሰጠኋቸው። ተቀብለው ካመሰገኑኝ በኋላ፤ ሰማህ ወይ ልጄ ከዚህች 50 ብር ላይ ዘርዝርና 10 ብሩን ለዛ ለታማኝ በእጁ ስጥልኝ፤ ለኢሳት ገቢ እንዲያረግልኝ ብለው ሰጥተውኛል።” ነበር ያለው፡፡ ተመልከት በዚህ አይነት የኑሮ ደረጃ ያሉ ኢትዮጵያዊ እንኳ ከተሰጣቸው 50 ዩሮ 10 ለኢሳት ይሰጥልኝ አሉ።ይሄ እኮ ሌላ ምንም ማለት አይደለም። ህዝቡ ምን ያህል ነጻነት እንደናፈቀ የሚያሳይ ነው። የሰውን ፍላጎት ነው የምነግርህ፡፡
በመረጃ በኩልም ህዝቡ ለትግሉ የሚጠቅም መረጃ ለመላክ በሚገርም መልኩ ፍቃዱና ፍላጎቱ አለው። ባገኘው ቀዳዳ ሁሉ ሳይፈራና መስዋዕትነት ከፍሎም ቢሆን መረጃዎችን ለመላክ ይፈልጋል።
ኢሳት አሁን አብዛኛውን መረጃ የሚያገኘው ከህዝብ ነው። እኔ በግለሰብ ደረጃ ነው መረጃዎቹ የሚደርሱኝ፡፡ አንድ ጠንካራ ድርጅት ተፈጥሮ በዚህ ረገድ ስራ ቢሰራ ደግሞ ምን ያህል እንደሚተባበር መገመት ከባድ አይሆንም።
አሻራ፦ ወደ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ልመልስህ፦ አቶ አንዳርጋቸው ላይ አፈናው በተፈጸመበት ሰሞን በለንደን በተደረገ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተህ በነበረበት ወቅት አቶ አንዳርጋቸው የአንበሳ ምስል በልዩ ሽልማት መልክ ሲሰጡህ ከሚያሳይ ክሊፕ ጋርአዳብለህ “ አንዳርጋቸው አንበሳውን መልሰህ ተቀበለኝ፤ ለኔ አይገባኝም!” የሚል መልዕክት አስተላልፈሃል። ይህን ያዩ ሰዎች ለአንድ ሃገር አንድ አንበሳ ብቻ ነው የሚያስፈልጋት እስካልተባለ ድረስ ታማኝም አንዳርጋቸውም ለሃገራችን አንበሶች ናቸውና ታማኝ ለምን ያንን አደረገ? ሲሉ ይጠይቃሉ። በርግጥ ለአቶ አንዳርጋቸው ያለህን ክብር ለመግለጽ የተጠቀምክበትን አገላለጽ ብዙዎች ወደውታል ። እስቲ ይህን ልትል ያስቻለህን …. ግለጽልን፡፡
ታማኝ፦ ያንን ያልኩት በስሜታዊነት ወይም በግብታዊነት አይደለም። ከልቤ የተሰማኝንና የሚሰማኝን ነው የተናገርኩት። አንዳርጋቸው አንበሳውን ለኔ ሲሸልም ስለኔ የተናገረው ራሱ በጊዜውም ከብዶኛል። እኔ ቀደም ሲል እንደ ገለጽኩልህ ራሴን የማየው እንደ አንድ ለህዝብ ነጻነትና ለሃገሩ ሰላም ፤ ….የሚናፍቅ ዜጋ ነው። አንዳርጋቸው በዚህ እድሜው ለህዝቡና ለሃገሩ ሲል የወሰደው እርምጃ በጣም ያስደንቀኛል። ሊከፍል የተዘጋጀው መስዋእትነት ሳያንስ እንደገና አፈናው ሲፈጸምበት ልንላቸው ይገባል፡፡
እነሱ (ገዢው ፓርቲ) በፍርሃት ዓለም ውስጥ ስለሆኑ ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር ነው ሩጫቸው፡፡ ወደፊት መቼም ቻይና የማትሰራው ነገር የለምና አገር ስትገባ ኤርፖርት ላይ ለመንግስት ክፉ -ልብ ያለውን ስካን የሚያደርግ መሳሪያ ሁሉ ሊያሰሩ ይችላሉ ….(ሳቅ)። ምርጫውንም ቢሆን ከዚህ በተለየ አይደለም የማየው። ፍርሃት ውስጥ ያለ አካል እውር ድንብሩን ብዙ ነገር ሊያደርግ ይችላል።
አሻራ፦ አንዳንድ ሰዎች ታማኝ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝን የራራላቸው ይመስላል። አቶ መለስን የተነፈሷትን ቃል ተከትሎ ወዲህ ወዲያ ያደርጋቸው እንዳልነበር ለአቶ ሃይለማሪያም ምነው ዝም አለ ይላሉ?
ታማኝ፦ ሳቅ…………! ይህን የሚሉ ሰዎች እውነት ከልባቸው እኔ በአቶ ኃይለማሪያም ላይ ግዜ እንዳጠፋ ፈልገው ነው? አይመስለኝም፡፡ አቶ መለስ እኮ የራሳቸው ተረት ፤የራሳቸው ስድብ ፤የራሳቸው፤ ውሸት የራሳቸው ምናምን…የነበራችው ሰው ነበሩ። አቶ ኃይለማሪያም ደግሞ ሳይዛቸው አልሆን ብሎ እንጂ የአቶ መለስን ልብስ ሊለብሱ የሚፈልጉ ነው የሚመስለኝ።
የአገር መሪዎች ከስራ ውጭ መጽሄት ማገለባበጥ፤ የአለም ዜና መከታተል …. እንዲህ እንዲህ አይነት ነገር እደሚያደርጉ ነው የማስበው፡፡ አቶ ኃይለማሪያም ግን ሌሊት ሁሉ ቁጭ ብለው የአቶ መለስን ቪዲዮ የሚያዩ ነው የሚመስለኝ፡፡ “ እስኪ የ 94ቱን አምጪልኝ የ93ቱን ጨርሻለሁ እያሉ…” እና በእኝህ ሰው ላይ ነው ግዜ እንዳጠፋ የሚፈለገው? ለሳቸው የሚሆን ግዜ እንኳ የለኝም፡፡ በቁምነገር ልወስዳቸው አለመፈለጌ እንጂ አቶ ኃይለማሪያም እንዴት ያለ ኮሜዲ ሊሰራባቸው የሚችሉ መሰሉህ?
አንተ ኮ! ስትኮርጅ የሰውን ሃሳብ፤ ወይም ሻል ያለ ነገር ትኮርጃለህ ። ማዛጋት ትኮርጃለህ?…..(ሳቅ) እሳቸው እኮ የአቶ መለስን ማዛጋት ሁሉ እየኮረጁ ነው! (ሳቅ)……! እኔ እንደ መዝናኛና ኮሜዲ ሾው ነው የማያቸው። ከዚህ ባለፈ አላያቸውም። አይ የግድ ይሰራባቸው ከተባለም ለቁምነገር ሳይሆን ለትርፍ ግዜ መዝናኛ ሊሰራባቸው ይችላል፡፡ከዚያ ውጭ ግን በሳቸው ላይ ግዜ ማጥፋት ያለብኝም ያለብንም አይመስለኝም።
ደግሞ ምን መሰለህ..? እኔ ጠ/ሚ/ር ስትለኝ የሚመጣብኝ ምስል እንደ አክሊሉ ሃብተወልድ አይነት ሰው ነው፡፡ ….እና በዚህ ስም ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሲጠራበት ……(ፋታ) ልክ አይሆንም፡፡
አሻራ፦ የወያኔን ከፍተኛ ባለስልጣናት በስልክም ቢሆን ለማግኘት ሞክረህ አታውቅም? ሞክረህ ከሆነ ውጤቱ ምን ነበር?
ታማኝ፦ እምምም.. አዎ! አንድ ሶስት ግዜ ሞክርያለሁ፡፡ አንዴ የቤንሻንጉል መፈናቀል ጊዜ …ሌላው ደግሞ አርሲ ውስጥ ሙስሊሞች የተገደሉ ጊዜ ይመስለኛል…አንዱን ዘነጋሁት። ብቻ ለ3 ጊዜ ያህል አቶ በረከት ጋ ደውዬ ነበር።መጀመሪያ የደወልኩ ጊዜ አነሳ፤ ጤና ይስጥልኝ ከአሜሪካ ነው የምደውለው አልኩት። “ማን ልበል? ” አለኝ። አይ እኔ የመንግስትዎ ተቃዋሚ ነኝ፤ ነገር ግን አሁን እየሆነ ባለው ጉዳይ መረጃ ይሰጡኝ እንደሁ ብዬ ነው የደወልኩት አልኩት።
እሱም “ማንነትክን ካልገለጽክልኝ ምንም መረጃ መስጠትም ሆነ ማውራት አልችልም” አለኝ።
መልሼም፦ማንነቴን ከነገርኩዎት አያናግሩኝም አልኩት። “ግዴለህም አናግርሃለሁ!” አለኝ።
ታማኝ በየነ ብዬ ሳልጨርስ ስልኩ ላዬ ላይ ተዘጋ፡፡በሌላም ጊዜ የሆነው እንዲሁ ነው፡፡ ታማኝ በየነ ነኝ ስለው ስልኬን ይዘጋዋል።
አሻራ፦ ለማነጋገር ፈቃደኛ ቢሆን ኖሮ በምን አይነት ስሜት ነበር የምታናግረው? ምንስ ነበር የምታናግረው?
ታማኝ፦ ለነገሩ በተለይ በመጀመሪያ የደወልኩለት ጊዜ አልተዘጋጀሁም ነበር፡፡ አሁን ስልኩን ሲያነሳ እንዴት ብዬ ነው የማናግረው? ንዴትም ቁጣም ፤ እልህም ይኖራል እና እንዴት እንደማናግረው አላውቅም ነበር፡፡ ሰዎችም አብረውኝ ነበሩ። ለማንኛውም የምለውን ሳልል እሱም ስልኩን ዘጋው። ሁለተኛ ስደውል ግን አስቤበት ነበር፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው ስልኩ ይነሳና ራሴን ሳስተዋውቅ ይዘጋል።
አሻራ፦ ምን ትለው ነበር ?
ታማኝ፦ሁሌ ራሴን የምጠይቀውን ነገር ነበር ልጠይቀው የፈለኩት። እንደው መጨረሻችሁ ምንድነው? እውነት እናንተ ሰዎች የምታደርጉትን ነገር ሁሉ የምታደርጉት የምር!! ለሃገርና ለህዝብ ጥሩ እየሰራን ነው ብላችሁ አምናችሁበት ነው? ልጆቻችሁን ትወዳላችሁ? ልጆቻችሁ ከሌሎች ልጆች ጋር በፍቅር እዲኖሩ አስባችሁ ታውቃላችሁ? ብዬ ጠይቄ ከራሳቸው አንደበት ብሰማው ፈልጌ ነበር አልሆነም ዘጋብኝ፡፡
አሻራ፦ ወደ ወቅቱ ጉዳይ ልመልስህ፦ የአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ኢትዮጵያዊውን ሁሉ አስቆጥቷል፡፡ በወያኔ መንግስት ላይ ያለው ተቃውሞና ለለውጥ ያለው ተነሳሽነት ከመቼው ጊዜ በተለየ ጠንክሯል። ይህን ተነሳሽነት ወደ ውጤት ለመለወጥ ምን መደረግ አለበት ትላለህ?
ታማኝ፡- አንድ ነገር አለ! በአሁኑ ሰአት በሃገራችን እየሆነ ያለው ነገር በጣም የሚያስፈራ ነው፡፡ እኛ የምንቃወማቸው ስለምንጠላቸው አይደለም፡፡ የምንቃወማቸው እያደረጉ ያሉት ነገር በጣም የሚያስፈራ፤ ሃገራችን እንደ ሃገር ህልውና እንዳይኖራት፤ ህዝባችንም አብሮ መኖር እንዳይችል የሚያደርጉ ሥራዎችን እየሰሩ በመሆኑ ነው። በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በተደጋጋሚ የዘር ቅራኔዎችን እያየን ነው። እገሌ ከዚህ ክልል እገሌ ከዚህ ክልል ውጣ እየተባለ ህዝብና ህዝብ እየተቂያቂያመ እንዲሄድ እየተደረገ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ያስፈራል፡፡
የህክምና ባለሙያ ባልሆንም አንድ ዶክተር ወደ ካንሰር ሊለወጥ የሚችል በጣም ከባድ የጤና ችግር ያለበትን በሽተኛ ፡ በአግባቡ መርምሮ ዘለቄታዊ መፍትሄ ይፈልግለታል እንጂ ህመም አስታጋሽ (ፔይን ኪለር) የሚሰጠው አይመስለኝም፡፡ የሃገራችን ወቅታዊ ጉዳይም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው። ዛሬ አንድ ዘላቂ መፍትሄ ነገር ካላደረግን ችግሩ ሊድን ወደማይችል ካንሰርነት መለወጡ አይቀርም።
ኢትዮጵያን ሃገሬ የምንላት ሁሉ አትሌቶቻችን ባንዲራዋን ለብሰው ትራክ ላይ ሲያሟሙቁ፤ ማን በ10 ሺህ ተሰለፈ ? ማን ለወርቅ ተስፋ አለው? …. እያልን እንጨነቃለን ። በውጤቱም እንደሰታለን። አሁን ደግሞ አትሌቶቿ ወርቅ ሲያስገኙላት የምንቦርቅላት ሃገር እንደ ሃገር መቀጠሏ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። ይህ ደግሞ በኛና በኛ ትከሻ ላይ ብቻ ያረፈ ችግር ነው። ስለሆነም ከዚህ በፊት በተቃዋሚነት ሲንቀሳቀስ የቆየውም ሆነ ያልተንቀሳቀሰው ዜጋ፤ ብቻ ሁሉም ሁሉም ባመነበትና ታግሎ ያታግለኛል ባለው በአንዱ መስመር ገብቶ መታገል አለበት እላለሁ፡፡ ዛሬ አንዱ ተመልካች አንዱ ሯጭ የሚሆንበት ጊዜ አይደለም። ማንም ለምንም ጥሪ የሚያደርግበት ጊዜም አይደለም። ዛሬ አንድ ነገር ካላደረግን ለልጆቻችን የምናስተላልፈው “ነገ” የለም፡፡በዚህ ደረጃ ነው መታየት ያለበት የሚመስለኝ።
አሻራ፦ በተነሳንበት እንቋጭና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለህዝብ ነጻነት በጽናት ሲታገሉ ጠላት እጅ ወድቀዋል ፤ ህዝብስ ለሳቸውም ሆነ ለሃገር ነጻነት በመታገል ረገድ ምን ይጠበቅበታል ትላለህ?
Andargachew Tsige
ታማኝ፡- አንዳርጋቸው በወያኔ እጅ እስከወደቀበት ጊዜ ድረስ የራሱንና የቤተሰቡን ህይወት ሰውቶ፤ በርሃ ገብቶ የቻለውን ሁሉ አድርጓል። የአንዳርጋቸው የትግል ጉዞ እዛ ጋ አብቅቷል። ዓለም ላይ ያሉ ሰውን የማስቃያ ቴክኒኮችን ሁሉ በእጁ ያስገባው የወያኔ መንግስት ደህንነት ባለፉት ሁለት ወራት አንዳርጋቸው ላይ ምን ሲፈጽምበት እንደቆየ ለመገመት የካፒቴን ተሾመ ተንኮሉን ቃለ ምልልስ ማድመጡ በቂ ይመስለኛል፡፡ አንዳርጋቸው ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል። እየከፈለም ነው።
የወያኔ መንግስትን ባህሪ መለስ ብለን ብናይ ሕዝብ የሚያከ ብራቸውን ሰዎች አዋርዶና አቅልሎ ለማሳየት የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደሌለ እንረዳለን፡፡
በአቶ አንዳርጋቸው መታፈን የተቆጣውን ህዝብ ተስፋ ለማስቆረጥ በተለመደው መልክ አቶ አንዳርጋቸውን አስገድደው በማናገር ሌላ የፊልም ቅንብር ለመስራት ተፍ! ተፍ! እያሉ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል። ዋናው ቁምነገር ግን ህዝባችን ለዚህ መሰሉ የወያኔ ተደጋጋሚና አሰልቺ ህዝብን የማሳሳት፤ ጉምቱ የህዝብ ወኪሎችን የማዋረድ ሴራ አዲስ ስላልሆነ ምንም ይበሉ ምንም ይስሩ ፕሮፓጋንዳው ውጤት እንደማይኖረው አልጠራጠርም፡፡
ዋናው ቁም ነገር የነሱን ፕሮፓጋንዳ ማክሸፍ ብቻ ሳይሆን ለዘመናት ስንታገልለት የቆየነው ዘረኛውን መንግስት ከሕዝብ ጭንቃ ላይ የማውረድ ዓላማ በውጤት እንዲቋጭ ሁላችንም አንድ ሆነን መነሳት ነው!!!።
አሻራ፡ ስለ ጊዜህ በድጋሚ እናመስግናለን! ታማኝ፡ እኔም ስለተሰጠኝ እድል አመሰግናለሁ::
በአውስትራሊያ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማስታወስ ከታተመችው አሻራ መጽሄት የተወሰደ::

Monday, October 13, 2014

Hiber Radio: በአሜሪካ አንድ ሐበሻ ኢቦላ ይኖረዋል በሚል ተጠርጥሮ ተያዘ፤ ኢቦላ አለብኝ ብሎ የቀለደው አሜሪካዊ ከአውሮፕላን ለመውረድ ተገደደ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ጥቅምት 2 ቀን 2007 ፕሮግራም !
<... የዓለም ባንክ የሚሰጠው ገንዘብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለልማት ጥቅም አይውልም። ጥቂቱም ፍትሃዊ በሆነ መንገድ አይደለም የሚውለው ኢትዮጵአ ትግራይ ብቻ አይደለችም ። ገንዘቡ ለጭቆና ሕዝብ ለማፈናቀል እየዋለ መሆኑን ከ78 አገሮች ከመጡ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ባሉበት ጉባዔ ተገኝቼ ባንኩ የሚሰጠው ብድር ለሰብዓዊ መብት ጥሰት መዋሉን ገልጫለሁ ትልቅ መድረክ ነበር ጉዳያችን ትኩረት አግኝቷል ።የተለያዩ አገራት ጋዜጠኞችም የኢትዮጵያን ጉዳይ አንስተው... >>
አቶ ኦባንግ ሜቶ በዓለም ባንክና አይ.ኤፍ.ኤም ዓመታዊ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ስላቀረቡት ተቃውሞ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)
<<...የኢቦላ መተላለፊያን በደንብ ማወቅ የጥንቃቄ እርምጃ መውሰድ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ። እስካሁን የሞቱት በኢቦላ የተያዙና የህክምና ሰዎችም ቢሆን በቀጥታ ከኢቦላ ጋር ግንኙነት ያላቸው ጋር የተገናኙ ያስታመሙ ናቸው ...የኢቮላ ጉዳይ ለአገሬም ለኢትዮጵያ ያሰጋኛል ። እንደ አሜሪካ በቂ አቅም ስለሌለ...>>
ዶ/ር ኤፍሬም መኮንን ኢቦላና ትኩረት ሊያገኙ የሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃ አስመልክቶ ከሰጡን ሙያዊ ማብራሪያ(ሙሉውን ያዳምጡት)
በዳላስ ከቤቷ ወጥታ ዛሬም ድረስ ዱካዋ ስላልተገኘው ኢትዮጵያዊቷ ወ/ሮ አልማዝ ጉዳይ (ልዩ ቃለ መጠይቅ ከጋዜጠኛ ዘውገ ቃኘው ጋር ከዳላስ ሙለውን ያዳምጡት)
የኬኒያው ፕሬዝዳንት የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ውሎ (ልዩ ዘገባ)
ዜናዎቻችን
በአሜሪካ አንድ ሐበሻ ኢቦላ ይኖረዋል በሚል ተጠርጥሮ ተያዘ
ኢቦላ አለብኝ ብሎ የቀለደው አሜሪካዊ ከአውሮፕላን ለመውረድ ተገደደ
የኢቦላ በሽተኞች በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ላይ መገኘታቸው ተገለጸ
አገዛዙን የፈሩ የህክምና ባለሙያዎች በይፋ አልናገርም ብለዋል
መኢአድ በጋምቤላ ፣በሱማሌ እና በጉራ ፈርዳ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት አስመልክቶ የተቃውሞ ሰልፍ ሊጠራ መሆኑን ገለጸ
በሱማሌ ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ ሰራዊት የሆኑ የጦር መሳሪያዎች በሕገወጥ እየተሸጡ ነው
አልሸባብ ከሽያጩ ሰፊ ትርፍ ማግኘቱ ተገለጸ
የቀድሞው መንግስት ባለስልጣን ሌ/ኮሎኔል ደበላ ዲንሳ <<ሞቶ መኖር>>(ዱአኒ ጂራቹ) መጽሐፍ ተመረቀ
ኢ/ር ግዛቸው ከአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንትነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ
አቶ በላይ ፈቃዱ አዲሱ የአንድነት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል
በደቡብ ኢትዮጵያ ኑሯቸውን በአደን ያደረጉ 24 ሰዎች ሰሞኑን በተከፈተባቸው ጥቃት ተገደሉ

Breaking News: ቴዲ አፍሮ ታሰሮ በ30ሺ ብር ተፈታ

teddy afrio
አሁን በደረሰን መረጃ የ30000 ሺ ብር ዋስ ድምፃዊው በማቅረቡ ከእስር ተለቁዋል::
ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ በፌደራል ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በቀረበበት ክስ ምክንያት ዛሬ ታስሮ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ድምፃዊው የቀረበበት ክስ ከስምንት ዓመት በፊት ከቀረጥ ነፃ ወደ ሃገር ውስጥ የገባችን ቢኤምደብሊው መኪና ገዝቶ ተገቢውን የቀረጥ ክፍያ ሳያጠናቅቅ ወደ ስሙ አዛውሯል የሚል መሆኑን የኢትዮጲካሊንክ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ድምፃዊው በዚሁ ክስ መሰረት ዛሬ ረፋድ በአራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ ክሱ ከታየ በኋላ ቀርቦ የዕለቱ ዳኛ 30 ሺህ ብር በማስያዝ በዋስ እንዲፈታ ትዕዛዝ ሰጥተዋል

Breaking News: ቴዲ አፍሮ ታስሮ ፍርድ ቤት ቀረበ

teddy afro
ዝነኛው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ በፌደራል ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በቀረበበት ክስ ምክንያት ዛሬ ታስሮ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ድምፃዊው የቀረበበት ክስ ከስምንት ዓመት በፊት ከቀረጥ ነፃ ወደ ሃገር ውስጥ የገባችን ቢኤምደብሊው መኪና ገዝቶ ተገቢውን የቀረጥ ክፍያ ሳያጠናቅቅ ወደ ስሙ አዛውሯል የሚል መሆኑን የኢትዮጲካሊንክ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ድምፃዊው በዚሁ ክስ መሰረት ዛሬ ረፋድ በአራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ ክሱ ከታየ በኋላ ቀርቦ የዕለቱ ዳኛ 30 ሺህ ብር በማስያዝ በዋስ እንዲፈታ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም የዋስ ሂደቱን ለመጨረስና ድምፃዊውን ለማስፈታት የቢሮ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ለቴዲ አፍሮ መከሰስ ምክንያት የሆነችው ይህች መኪና ከዚህ ቀደም በተቀጣበት የሰው ገጭቶ ህይወት ማጥፋት ወንጀል የተከሰሰባት ነበረች፡

Sunday, October 12, 2014

የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ቀጠና ኃላፊ በደህንነት ሰዎች ተደበደቡ

ፍኖተ ነፃነት
10710933_711118828973054_6184937440487717547_nየአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የሰሜን ቀጠና ኃላፊ የሆኑት አቶ አዕምሮ አወቀ ሐሙስ ዕለት ከሥራ ወደ ቤታቸው ሲጓዙ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለፍኖተ ነፃነት ገለጹ፡፡ እንደ አቶ አዕምሮ ገለፃ ይህ ድርጊት በየጊዜው እንደሚከሰትና በሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት እንቅስቃሴ በደሴ ከተማ በመኪና ለማፈን በተደረገው ግብግብ መኪና ውስጥ አስገብተው እንደተደበደቡ ራሳቸውን ለመከላከል በሚታገሉበት ወቅትም ጋቢና የተቀመጠውን ሹፌር መኪናውን ለማስነሳት ቁልፍ እንደያዘ እጁን ሲረግጡት በመጎዳቱ፣ ሁለቱ ከኋላ የያዟቸውን ደህንነቶች ለመከላከል ባደረጉት ግብ ግብ ስላየሉባቸው ገፍትረው ከመኪናው እንደጣሉዋቸውና ወደ አዲስ አበባ ከመጡም በኋላ ወንድማችንን ደብድበሃል የትም አታመልጥም በሚል ለገሃር አካባቢ በቡድን ድብደባ እንደፈጸሙባቸው ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ ከሰሜን የሚመጡ የፓርቲው አባሎችን ለመቀበል ዝግጅት በሚያደርጉበት ታህሳስ 17/2006 ዓ.ም ቤታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተሰብሮ ንብረቱ በሙሉ ከቤት ተጭኖ ተወስዷል፡፡ ሐሙስ ዕለትም ከሥራ ወጥተው በትራንስፖርት ወደ ቤታቸው በሚሄዱበት ወቅት አየር ጤና አካባቢ ከአውቶቡስ ሲወርዱ ሁለት ደህንነቶች ግራና ቀኝ እጃቸውን በመያዝ እንዳይንቀሳቀሱ ካደረጉዋቸው በኋላ ሦስተኛው ደህንነት በድንጋይ ከጉልበታቸው በታች ደጋግሞ በመምታት ቀኝ እግራቸው ላይ ጉዳት አድርሰው ሦስቱም ከአካባቢው እንደተሰወሩ ገልጸዋል፡፡ ይህ ህገ ወጥ ድርጊት በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እንዲመጣ መታገሌን እንዳቆም እንደማያደርገኝ ሊያውቁት ይገባል በማለት ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገልጸዋል፡፡

የሰሞኑ የሥልጠና ፓለቲካ

የስምኦን ልጅ በረከት ከመክተብም አልፎ የሃገሪቷን ልሂቃን ኢንዶክትሪኔት እያደረገ ይገኛል። እስከማስታውሰው ድረስ የበረከት የመጨረሻ ህልም በዩንቨርስቲ ተጋባዥ መምህር ሆኖ ሌክቸር መስጠት ነበር። እነሆ!የልብን መሻት በማየት በላቀ ደረጃ የሚሰጠው ” ልማታዊ መንግሥት ” የሌክቸረሮች ሌክቸረር አደረገው። ርግጥ የድርጅቱ ከአጠገቡ አለመኖርም ህልሙን ያለጊዜው እንዲሳካ ሳያግዘው አልቀረም ። እኔ እምለው እሱ ባይኖር ኖሮ ማን ጵፎ ማን ያሰለጥን ነበር? አደራችሁን! ዶክተር ደብረጲዬን ብላችሁ የሀይሌን ልብ እንዳታቆሟት። የሀይሌ ልብ ከቆመ ሀገሪቷ በሁለት አመት ውስጥ ሁለት ጊዜ መስቀለኛ መንገድ ላይ ስለምትቆም ማናችንም አንፈቅድም ። ከሀይሌ ጋር ያላባራ ፀብ የገጠመው በረከትም ቢሆን!
ወደ ቁምነገሩ ልመለስ ።ወዳጄ ሰነዶቹን ሲልክልኝ ከተለመደው ውጭ አዲስ ነገር አይኖረውም በማለት ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር። አላነበብኩትም ላለማለት ብቻ ስልኬን ከፈትኩ። ከሰነዶቹ ውስጥ ” የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ትግላችንና ፈተናዎቹ” የሚለው ቀልቤን ሳበው ። አንብቤ ስጨርስ ውስን ነጥቦችን መዝዤ በማውጣት ከትላንትናው አስተሳሰብ ጋር ማገናዘብ ጀመርኩ። እናም ስልኬን አውጥቼ የሚከተሉትን ቁምነገሮች ለመክተብ በቃሁ ፣
1• Paradigm Shift
bereket
ይህ ሰነድ ስርነቀል የአስተሳሰብ ለውጥ ያመጣው በስርአቱ አደጋ ላይ ነው። ድርጅቱ ከመሬት በታች ከመዋሉ በፊት በጳፉቸው ድርሳናትም ሆነ ገድሎች የስርአቱ አደጋ በዋነኛነት የሚመነጨው ከውስጥ ነበር። ቦናፓርቲዝም፣ ጥገኛ ዝቅጠት ፣ የመበስበስ አደጋ፣ እንደ አሣ ከጭንቅላቱ መሽተት ፣ ሙስና፣ ጠባብነት እና ትምክህት፣አድርባይነት… ወዘተ የውስጥ አደጋዎቹ መገለጫዎች ነበሩ።
ዛሬ የስምኦን ልጅ ምስጋና ይግባውና በዚህ ጉዳይ ላይ ስር ነቀል የአስተሳሰብ ለውጥ በማድረግ ( ” የአስተሳሰብ እድገት” አለማለቴን ልብ ይሏል) የስርአቱ አደጋ ከኢህአዴግ ውጭ እንደሚመነጭ ያበስራል። ለዚህ እማኝ እንዲሆን በገፅ 24 ላይ ፣
“… በስልጣን ላይ ሆኖ አገሪቷን የሚያምሰ የትምክህት ሀይል የለም። … በሥልጣን ላይ ሆኖ አገሪቷን የሚያተራምስ የጠባብነት ሐይል የለም።” በማለት ይገልጻል።
ለዚህ አስተሳሰብ ማጠናከሪያ የሚሆነው በዚሁ ገጵ ላይ ፣
“… ይህ መሰረታዊ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ በሥልጣን ላይ ባለው ፓርቲና በመንግሥት መዋቅሮች የትምክህትና የጠባብነት አስተሳሰብን የሚያራምዱ ግለሰቦች አሉ።” በማለት ችግሩን በግለሰብ ደረጃ የሚገለፅ እንደሆነ ያሰምርበታል ።
ታዲያ የስርአቱ አደጋ የትነው ያለው?
2• ማነው ባለሳምንት?
የበረከት ማስታወሻ በኢህአዴግ ውስጥ ሰርጐ ገቦች መኖራቸውን አምኗል ። እነዚህ ሰርጐ ገቦች ከሌሎች ጋር በመቀናጀት ስርአቱ ላይ ፈተና እንደደቀኑበት በሚከተለው መልኩ በገፅ 24 ላይ ጠቅሶታል፣
“… ውጭ ሆነው ስርአቱን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ የትምክህትና ጠባብነት ሐይሎች ጋር በመቀናጀት ልዩ ልዪ ፈተናዎችን በመደቀን ላይ ይገኛሉ።”
ይህቺ አንቀጵ በንዴት እንደተጳፈች ታስታውቃለች። የንዴቱ ምንጭ የቅርብ ግዜውን የኦቦ አዲሱን እና የራሱን ቅሌት በማስታወስ የተጳፈች ትመስላለች ።
ኦቦ በንዴት ውስጥ ሆኖ፣
” … ሁለት ሶስተኛው መምህር የእኛ አባል ሆኖ በራሳችን ላይ ይሰለፉል” ነበር ያለው። የስምኦን ልጅ ደግሞ ቁርሴን ስበላ በሚል መንደርደሪያ የቅርብ ጓደኞቹ ሳይቀሩ ” ምርጫ የማይደርስ መስሎሀል?” በማለት እንደዛቱበት ተናግሯል ።
እናም አጨዳው ይቀጥላል ። ከበረከት ሰነድ ለመረዳት እንደሚቻለው ለመጠረግ የተዘጋጁት የአማራና ኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ የኢህአዴግ አባላት ናቸው።
ጠራጊው ማን ይሆን? ጠረጋው እስከየት ድረስ ይዘልቃል?

Friday, October 3, 2014

አሜሪካ ”በኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ከአሜሪካ ፍትህ ፊት ሸሽቶ አመለጠ ከአሁን በኃላ ወደ አሜሪካ በማንኛውም ጊዜ መምጣት አይችልም ከመጣ ግን ክሱ ይጠብቀዋል” አለች

embassy shooter

የጉዳያችን አጭር ዘገባ

”Ethiopian diplomat flees US to dodge prosecution” ”ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ከአሜሪካ ፍትህ ፊት ሸሽቶ አመለጠ ከአሁን በኃላ ወደ አሜሪካ በማንኛውም ጊዜ መምጣት አይችልም ከመጣ ግን ክሱ ይጠብቀዋል” ”ዘሂል” በአሜሪካ የምክርቤት እና የዋይት ሃውስ ጉዳይ ላይ በማተኮር የሚዘግበው ጋዜጣ መስከረም 22/2007ዓም (ኦክቶበር 02/2014)
”ዘሂል” (The Hil) የተሰኘው እ አ አቆጣጠር ከ1994 ዓም ጀምሮ በአሜሪካ የምክርቤት እና የዋይት ሃውስ ጉዳይ ላይ በማተኮር የሚዘግበው ጋዜጣ ዛሬ መስከረም 22/2007ዓም (ኦክቶበር 02/2014) ”Ethiopian diplomat flees US to dodge prosecution” ”ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ከአሜሪካ ፍትህ ፊት ሸሽቶ አመለጠ” በሚል ርዕስ ስር ባወጣው ዘገባ በኤምባሲው ውስጥ የተኮሰው ሰው የዲፕሎማሲ ከለላ እንዲነሳ እና አሜሪካ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ የኢትዮጵያን መንግስት ጠይቆ እንደነበር ይገልፃል።
ዘገባውም አያይዞ ”የስቴት ዲፓርትመንት”ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ”ግለሰቡ የዲፕሎማሲ ከለላው እንዲነሳ እና በአሜሪካ ሕግ እንዲዳኝ” ለኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልፀዋል።ጄን ሳኪ አያይዘውም ”ከሀገር ከወጣ በኃላ ተመልሶ ወደ አሜሪካ የመምጣት ዕድል የለውም ከመጣም ዕድሉ ሕግ ፊት መቅረብ ብቻ ነው ” ብለዋል።
እዚህ ላይ ”The Hill” በዘገባው ”የዲፕሎማሲ ከለላውን አንሱ እና ፍርድ ቤት ላቁመው አለበለዝያ ከሀገር መባረር ነው እጣው”የሚለውን የሕግ ትርጉም አክሎበታል።ስለሆነም የመጀመርያው ስላልሆነ ሁለተኛው መባረሩ ዕውን ሆነ።መባረሩን ግን አሁንም ከፍትህ አመለጠ የሚል ዘገባ ሰሩበት እንጂ መባረሩን ዘገባዎቹ ከሕጉ ጋር ማለትም የዲፕሎማሲ ከለላ ካልተነሳ መባረር እንደሚከተል ”ዘ ሂል” በዘገባውም ላይ ቃል በቃል እንዲህ ይላል ”Diplomats are expelled from the United States when their host country declines to waive diplomatic immunity” ”በአሜሪካ ማንኛውም ዲፕሎማት የዲፕሎማሲ ከለላውን ለማንሳት የሀገሩ መንግስት ፈቃደኛ ካልሆነ (በወንጀል እየተፈለግ ሳለ ማለት ነው) ከአሜሪካ ወድያውኑ ይባረራል”ማለት ነው። ስለዚህ ግለሰቡ በትክክል ተባርሯል።
ከዋሽግተኑ ክስተት ወዲህ የኢህአዲግ ደጋፊዎች በማኅበራዊ ድረ ገፆች ላይ በአሜሪካ ላይ የዛቻ ፅሁፎችን እያወጡ ሲሆን አቶ ግርማ ብሩ ግን አንድ አሜሪካን ሀገር ለሚተላለፍ ራድዮ በሰጡት መግለጫ ተቃዋሚዎችን ከመሳደባቸውም በላይ ከአሜሪካን ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዳይበላሽ ”ሁሉም ሊንከባከበው ይገባል” ቀረሽ ንግግር ሲማፀኑ ተሰምተዋል።ነገሩ እያመራ ያለው ግን እርሳቸው እንዳሰቡት አይመስልም።አሁን የሚጠበቀው ከሁለቱ አካላት አንዳቸው የሚሰጡት ጠንከር ያለ የቃላት ልውውጥ ብቻ ነው።ብዙዎች አሜሪካ ከፍተኛ ትዕግስት ማሳየቷ እና ከእዚህ በኃላ ግን ልትታገጽ እንደማይገባት ያሰምሩበታል