Saturday, February 4, 2017

ዶናልድ ትራምፕ በሰባት የሙስሊም ሃገራት ላይ ያወጡት የቪዛ እገዳ ተቀለበሰ

(ዘ-ሐበሻ) በአሜሪካም ውስጥ ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሶ የሰነበተው የዶናልድ ትራምፕ አዲሱ የኢሚግሬሽን ትዕዛዝ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከታገደ በኋላ የአሜሪካው የአገር ጥበቃና ደህንነት ባለስልጣን (ሆምላንድ ሴክዩሪቲ) የትራምፕን የቪዛ እገዳ መቀልበሱን አስታውቋል::

ዶናልድ ትራምፕ በሶማሊያ፣ በሱዳን፣ በኢራን፣ በሊቢያ፣ በሶሪያና በየመን ዜጎች ላይ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የሚያግድ ከ90 ቀናት ህግ ከፈረሙ ወዲህ የሃገሪቱ ፖለቲካ ሲታመስ ቆይቷል:: ሕዝብ በየኤርፖርቱና ይመለከታቸዋል በተባሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች አካባቢ ሰላማዊ ሰልፎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል::


የተለያይ አየር መንግዶችም የነዚህን ሃገራት ዜጎች ሲመልሱ ቆይተዋል:: ሆኖም ግና ይህን አጨቃጫቂ ፊርማ ዶናልድ ትራምፕ ካኖሩ በኋላ በርካታ የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ሲጨቃጨቁበት ቆይተው ትናንት ማምሻውን የዋሽንግተን ፍርድ ቤት ዳኛ ውሳኔውን በማገዳቸው ሆምላንድ ሴክዩሪቲም የትራምፕን ውሳኔ አጥፎ የተከለከሉ ዜጎችን ወደ አሜሪካ ማስገባቱን ዛሬ ጀምሯል::
ትራምፕ ስልጣን ላይ በወጡ በ2 ሳምንታቸው ደከመኝ ብለው ለ እረፍት ወደፍሎሪዳ ያመሩ ሲሆን እዚያም ተቃውሞ ጠብቋቸዋል::












ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ግሪን ካርድ ለማግኘት ሲሉ የኢትዮጵያ መንግስትን ያጥላላሉ ሲሉ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ከሰሱ




(ዘ-ሐበሻ) የሃገር ውስጥ ጋዜጠኞችን ሰብሰበው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ የሰጡት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስትን የሚያጥላሉት ግሪን ካርድ ለማግኘት እንጂ እውነት መንግስትን ጠልተው ከልባቸው አይደለም አሉ::
ሚኒስትሩ በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫቸው በኢትዮጵያ በጣለው እና በመጪው መጋቢት ስድስተኛ ወሩን በሚይዘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት ዙሪያ በቀረበላቸው ጥያቄ ላይ በሰጡት መግለጫ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታሰበለት ቀን ቀድሞ አይነሳም ብለዋል:: ይህ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ሃገሪቱን እንዳረጋጋ አስታውቀዋል::
አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ዜጎች ወደ ሃገራቸው ሊመልሱ እንደሚችሉ እየተነገረ መሆኑንና በርካታ ኢትዮጵያውያንም በአሜሪካ እንደሚኖሩ ጥያቄ ያቀረበላቸው ዶ/ር ነገሪ ትራምፕ ወረቀት አልባ ኢትዮጵያውያንን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ከወሰኑ ሃገሪቱ እጇን ዘርግታ እንደምትቀበል ገልጸዋል:: በአሜሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን መንግስትን የሚያጥላሉት ወረቀት ለማግኘት እንጂ ከልባቸው ስርዓቱን ጠልተው አልመሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ነገሪ እንኳን እነዚህን ዜጎች ይቅርና በይፋ መንግስትን ሲያጥላሉ የከረሙ ተቃዋሚዎችም ሃገራቸው ገብተው በኢንቨስትመንት መሳተፍ ከፈለጉ መንግስት እንደሚተባበር ተናግረዋል::

















Monday, October 3, 2016

ሕዝባዊው አመጽ በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋና በሌሎችም ከተሞች ተቀጣጠለ

carscarswmeki
(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ትናንት በቢሾፍቱ የ እሬቻን በዓል ለማክበር በወጡ ንጹሃን ላይ በሂሊኮፕተር እና በመትረየስ የታጀበ የዘር ማጥፋት ከፈጸመ በኋላ በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ አመጹ እንደገና ተቀጣጠለ::
ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች እንደጠቆሙት በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋና በሌሎችም ከተሞች ተቃውሞው ተቀጣጥሏል::
በተለያዩ ከተሞች በተነሱት በነዚሁ ሕዝባዊ አመጾች የመንግስት መኪኖች ሲነዱ ታይተዋል::
በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋ ሕዝብ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን እያሰማ ሲሆን በመንግስት ንብረቶች ላይ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይም ይገኛል::
በተለይ የሕወሃት ንብረት የሆነው ሰላም ባስ በሃረርጌ ጥቃት እንደተፈጸመበት የደረሰን መረጃ ያመልከታል::
በቄለ ወለጋ ጂማ ሆሮ ወረዳ ኑኑ ከተማ ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ተቅስቅሶ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እንደሆኑ ሲታወቅ በባሌ ሮቤ ደግሞ ሁሉ ነገር መዘጋጋቱ ተሰምቷል::
በደምቢ ቦሎ ኢንተርኔት በጠቅላላ መቆረጡ ሲታወቅ ተቃውሞውም እንደበረታ ምንጮች ገልጸዋል:: በአምቦም እንዲሁ ተመሳሳይ ተቃውሞዎች ዳግም እንደተቀሰቀሰ የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ

ለኦሮሞ ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን(ከአማራ ተጋድሎ ግብረ ኃይል በዉስጥ መስመር የተላከ)

14355189_1776743355901679_4397046954836303499_n
በትላንትናው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ ሲከበር በነበረው አመታዊ የእሬቻ በአል ላይ ለመታደም ከመላው ኦሮሚያና ከተለያዩ የሀገራችን አባቢዎች በመጡ ተሳታፊዎች ላይ የህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ ጦር በፈፀመው አስከፊ የጦር ወንጀል ቁጥራቸውን ለመገመት የሚያዳግቱ ወገኖቻችንን ተነጥቀናል፡፡ በዚህም የወገኖቻችን ህልፈተ-ህይወት የተሰማን ሀዘን በጣም ጥልቅ ነው፡፡ የእነዚህ ኦሮሞ ወንድሞቻችን ሞት የእኛም የአማራዎች ሞት፡ የፈሰሰው ደማችውም የእኛም ደም መሆኑን እደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ በቃላት ሳይሆን አብረን በመሞትና ደማችንን በማፍሰስ አንድ መሆናችንን አረጋግጠናል፡፡ ወደፊትም በልበ-ሙሉነት እጅ ለእጅ ተጣምረን በፍፁም ወንድማማችነትና መተማመን መንፈስ ይሀንን ሰው-በላ የወንበዴ ጥርቅም ከላያችን ላይ በማሽቀንጠር ለዘለዓለሙ እንዳይነሳ በመቅበር ለሁላችንም የኢትዮጵያ ህዝቦች እኩል የምትሆን አዲስ ቤት በመገንባት በደም የተሳስረውን አንድነታችንን ዳግም የምናድስበት ቀን እሩቅ አይሆንም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ሞትና ደም መፍሰስ የአማራ ህዝብም ሞትና ደም መሆኑን በድጋሜ እያረጋገጥን ወደፊት በሚጠብቀን መራራ የነፃነት ትግል ጉዞ ትላንት የወደቁትን ዜጎቻችን በማሰብ በድል እንገሰግሳልን፡፡
ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር!!
#AmharaResistance

Sunday, October 2, 2016

ከእሬቻው ጭፍጨፋ በኋላ የአምቦ ሕዝብ ተነሳ | የተቆጣው ሕዝብ በርካታ የመንግስት መኪኖችን አቃጠለ



ambo


 (ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ኦሮሞዎችን እና አማሮችን በ እሬቻ በዓል ቢሾፍቱ ላይ ዛሬ ከጨፈጨፈና ከ500 በላይ የሰው ሕይወት ካጠፋ በኋላ በአምቦ ሕዝብ በቁጣ ተነሳ:::
በአምቦ በተነሳው ሕዝባዊ አመጽ ሕዝቡ ቁጣውን በመንግስት ንብረቶች ላይ እርምጃ በመውሰድ እየገለጸ ነው:: እንደዘ-ሐበሻ ዜና ምንጮች ገለጻ ከሆነ በአምቦ በርካታ የመንግስት መኪኖች እና አንዳንድ መስሪያ ቤቶች በ እሳት ወድመዋል:: ይህን ተቃውሞ ሊያረግቡ በመጡ የሕወሓት ወታደሮች ላይም እርምጃ መውሰድ የጀመረ ሲሆን ወታደሮች እየሸሹ መሄዳቸው ተሰምቷል::
በአምቦ መንገዶች መዘጋጋታውም ተሰምቷል::
የአምቦ ሕዝብ እጅጉን ከመቆጣቱም ባሻገር በሌሎች የኢትዮጵያ ክልል ከተሞችም እንዲሁ ይህው ሕዝባዊ ተቃውሞ እንደሚቀጥል ይጠበቃል::

Thursday, September 29, 2016

በብር ሸለቆ ወታደራዊ ካምፕ የአማራ እስረኞች በከባድና በተከለከሉ አፍዝ አደንግዝ መርፌ መድኃኒቶች እንደሚሰቃዩ መረጃዎች አመለከቱ



screen-shot-2016-09-29-at-7-07-53-am





ክሙሉቀን ተስፋው


መስከረም 19, 2009 ዓ.ም አስደንጋጭ እና አሳሳቢ
በብር ሸለቆ ወታደራዊ ካምፕ የሚገኙ ወገኖቻችን በከባድና የተከለከሉ አፍዝ አደንግዝ መርፌ መድኃኒቶች እንደሚሰቃዩ መረጃዎች አመለከቱ። ብር ሸለቆ የታሰሩ የዐማራ ወጣቶች በግዴታ በመርፌ እንዲወስዱ የተደረገውን መድኃኒት ምንነት የሚያስረዳ ምስል ትናንት ወጥቷል። በዚሁ መሠረት የዐማራ ሀኪሞች ማኅበር መድኃኒቱን በተመለከተ የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥቷል።
ሁሉም የሰውነት ጡንቻወች እንዲዝሉ ወይም አላግባብ እንዲወጠሩና የፈለጉን አሰቃቂ ድርጊት ለመከወን (አስንፎ ለመምታት፣ ለማንጠልጠል፣ ለመግደል..) የሚያስችሉ አፍዝ አደንግዝ(Sedative Hypnotic) የሆኑትን የመርፊ መድኃኒቶች በግዳጅ እየተውጉ ነው። ዲያዘፓም እና ዲልትያዘም (Diazepam Diltiazem) ጥቂቶቹ ናቸው። እነዚህ መድኃኒቶች ለሚያስፈልገውና በሃኪም ትዛዝ ብቻ የሚሰጡ፡ ከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ናቸው። ከመጠን በላይ(Over Dose)ና ለማያስፈልገው ከተወጉ የመናገር ችግር፡ የሰውነት ክፍል መዛል: አለመታዝዝ (Dyskinesias): እረፍት መንሳት(akithsia)፡መደበት(Depression) ጭንቀት እና መተንፈስ ኣለመቻል ያስከትላሉ። በብዛትና በተክታታይ ከሆነ የልብ መድከም፡ የደም ማነስ፡ ሾክ፡የሚጥል(Sezure)፡ ራስን ማሳት(Coma)ና ሞት ያመጣሉ። የሳይኮሎጅ ማስቀየር ‘Psychologic Dislocation’ ና ፍላጎት ማሳጣትም ጉዳቶች ናቸው። ቆዳ ላይ ከፈሰሱ የቆዳ ላይ ቁጣ፡መላላጥ፡ እብጠት፡እንፊክሽን፡የቆዳ ጋንግሪንና ሞት የመጨረሻወቹ ናቸው።
ናዚውና ኢሰብዓዊ ህውሃት ኣካላዊ ስቃይ ንጹሃን ላይ እንደሚያደርስ ለማንም ግልጽ ነው። ኣስደንጋጩ የህክምና ማስቃያ ግን ኣማራው ላይ የመጀመሪያው ሳይሆን ኣይቀርም። የሚያስፈራው የህክምና ሰወች (የናዚ ዶክተሮች) ለዚህ ኦፕሪሽን መሳተፋቸው ነው።


ይህ ኢሰባዊነትና አለማቅፋዊ የህክምና ሰነምግባርን የጣሰ ሆኖኣል። ሰውን በግፍ ኣለመጉዳት ’Do Not Harm’ ፡ፍቃደኛ ለሆኑ ብቻ ‘Authonomy’ ፡ የሚጠቅም ሲሆን ብቻ ‘Beneficience ’ ወዘተ የሚሉት ቃለ-ማህላ(Physicians Oath) ተክደው በ’ናዚ ሃኪሞች’ ህዝባችን እየተስቃየ ነው ። የአማራና የኢትዮጵያ ሃኪሞች ይህን ጉዳይ ባስቸኩይ ለ’ Federal Ministry of Health of Ethiopia, FMHACA, UN Human Rights ‘ ማድረስና እልባት ማግኘት ኣለበት።
መረጃውን በጥንቃቄ እየያዝን ተግጅወችን እንርዳ። መልእክቱን ለአለም አናሰራጭ









የህወሃት መከላከያ ሰራዊት እጁን እየሰጠ ወደ ኤርትራ እየገባ ይገኛል




በልኡል አለም
ሰበር መረጃ ! !
ከምእራብ ትግራይ ወደ ኡምሃጅር የተወረወረ የህወሃት መከላከያ ሰራዊት የግንባር ጦር በገጠመዉ ድንገተኛ የተኩስ ልዉዉጥ ምክንያት እጁን እየሰጠ ወደ ኤርትራ እየገባ ይገኛል።
ከሰሜኑ እዝ ከመከላከያ አባላቱ ዉስጥ ያፈተለከዉ መረጃ እንደሚጠቁመዉ ከሆነ የመዋጋት ፍላጎት የሌላቸዉ የህወሃት ወታደሮች በትናንትናዉ እለት ወደ አል-ፉሽቓ (Al fushqa) ሱዳን ድንበር በኩል አምርተዉ ለነጻነት ታጋዮች እጃቸዉን መስጠታቸዉ ታዉቋል።




ethio-soldiers





ብዛት ያላቸዉ ቀላልና ከባድ የጦር መሳሪያዎች በምርኮ መግባታቸዉንና የህወሃት መከላከያ ሰራዊት አባላትም መቀላቀላቸዉን የገለጸልን ምንጫችን በምርኮ የሚገቡትን ወገኖች የኤርትራ ወታደሮች ወደ መደበኛ ማረፊያ ማዘዋወራቸዉን ምንጮች አረጋግጥጠዋል፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !