Tuesday, January 26, 2016

በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች ግድግዳዎች ላይ የተቃውሞ ጽሑፎች ተጽፈው አደሩ


(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ ግድግድዎች ላይ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት የሚቃወሙና ጥያቄም የሚጠይቁ መፈክሮች ተጽፈው አደሩ:: በተለይ መንግስት ያሰራቸውን የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ፍርድ የሚቃወም; በሃገሪቱ በተቃዋሚዎች ላይ የሚሰጡ ፖለቲካዊ ፍርዶችን የሚቃወሙ; በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ የሚያወግዙና ሌሎችም መፈክሮች በትላልቁ በግድግዳዎች ላይ ተጽፈው አድረዋል::
ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ መንገዶች ተቃውሟቸውን በስርዓቱ ላይ ቢያሰሙም በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የሕዝቡን ጥያቄ ወደ ጆሮ ዳባ ልበስ በሚል አሁንም በርካታ ጋዜጠኞችን; የሃይማኖት መሪዎችን; የፖለቲካ ሰዎችን አስሮ በማሰቃየት እንዲሁም በመግደልም ላይ ይገኛል::
በአዲስ አበባ ግድግዳዎች ላይ ተጽፈው ያደሩ ተቃውሞዎችን በፎቶ ይመልከቱ::

addis ababa1addis ababaaddis ababa 3addis ababa2

ፍ/ቤቱ በአቶ ዮናታን ተስፋየ ላይ ለ2ኛ ጊዜ 28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሰጠ



‹‹ነጻነት ይሰማኛል›› ዮናታን ተስፋየ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ማዕከል በእስር ላይ የሚገኘው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለ2ኛ ጊዜ የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶበታል፡

yonatan Tesfaye
ዛሬ ጥር 17/2008 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት የቀረበው አቶ ዮናታን ፖሊስ ምርመራየን አልጨረስኩም በሚል የጠየቀበትን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለየካቲት 15/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ አቶ ዮናታን ተስፋየ የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡
ፖሊስ በአቶ ዮናታን ላይ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ሲጠይቅ ‹‹የቴክኒክ መረጃዎችን መሰብሰብ ይቀረናል፤ ያልተያዙ ግብረ አበሮችንም አሉ›› የሚል ምክንያት ማቅረቡን የተጠርጣሪ ጠበቃ ገልጸዋል፡፡
አቶ ዮናታን ተስፋየ በጠበቃ እና በቤተሰቦቹ እንዳይጎበኝ እንደተከለከለና ከታሰረበት ክፍል መታፈን የተነሳ የጤና እከል ቢገጥመውም ህክምና እንዳላገኘ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም አቤቱታውን አድምጦ በጠበቃውም ሆነ በቤተሰቦቹ እንዲጎበኝ እንዲፈቀድለትና ህክምናም እንዲያገኝ ትዕዛዝ መስጠቱን ከጠበቃው ለማወቅ ተችሏል፡፡
አቶ ዮናታን ከችሎት ሲወጣ በስፍራው ለነበሩት ቤተሰቦቹና ወዳጆቹ ያለውን ፍቅር ገልጾ ‹‹ነጻነት ይሰማኛል›› በማለት ጮክ ብሎ ሲናገር ተደምጧል፡