ፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ እንደዘገበው ኢትዮጵያ ውስጥ የቴሌኮም አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት የወያኔ ሀብት የሆነው ኢትዮ-ቴሌኮም የተባለ አንድ ድርጅት ብቻ ይገኛል፡፡ አንድ ድርጅት ብቻ በመሆኑ ሕዝብ አማራጭ በማጣት የግዴታ ውዴታ የዚህ ድርጅት ደምበኛ መሆን ተገዷል፡፡ አብዛኛው አገልግሎቶቹ ስልክ፣ ኢንተርኔትና ፋክስ በሚያስደነግጥ ሁኔታ ቀርፋፎችና የሚቆራረጡ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በዚህም ሳቢያ ሕዝቡ አገልግሎቱን ሳያገኝ ገንዘቡን ይበዘበዛል፡፡ በዚህ በቴሌኮም ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያ ከዓለም ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካም የመጨረሻው ጠርዝ ላይ እንዳለች የታወቀ ነው፡፡ የወያኔ ትኩረት በእንዲህ የመቆራረጥና የመንቀርፈፍ ችግር ባለበት ሁኔታ የሚደረጉ የስልክና የኢንተርኔት ግንኙነቶችን በመጥለፍ የሕዝቡን የእለት ተእለት ግንኙነቶች መሰለል ላይ ነው፡፡
የአሜሪካና አብዛኛው የአውሮፓ አገራት ኤምባሲዎች ከወያኔው ቴሌኮም ውጪ በሳተላይት እንደሚገናኙ የታወቀ ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት በቴሌኮም ማጭበርበር ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች መኖራቸው ይነገራል፡፡ ከእነዚህ ውስጥም በወያኔ ተደርሶባቸው እንደታሰሩም እንደሆነ ተነግሯል፡፡ በዚህ ሥራ ላይ የሚሰማሩት አብዛኛዎቹ የትግራይ ተወላጅ የወያኔ አባላት መሆናቸው ታውቋል፡፡ ይህ ውስልትና ጎልቶ የታየባቸው አካባቢዎች አዲስ አበባ፣ ጅግጂጋ፣ ሐረርና ድሬዳዋ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ በዚህ ውስልትና ተግባር ወያኔ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ለኪሳራ እንደተዳረገ ማወቅ ተችሏል
No comments:
Post a Comment