ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ሰኔ 22 ቀን 2006 ፕሮግራም
<...የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የፍርድ ቤት ውሎ ለመከታተል ነው ፍ/ቤት የሄዱት ።የፓርቲያችንን የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኦናታን ተስፋዬን ከጣቢያ ደብድበው ነው የለቀቁት የፓርቲው የሴቶች ጉዳይ አባል ምኞት መኮንንም ብሔርሽን ካልተናገርሽ ብለዋታል በአጠቃላይ ከዞን ዘጠኝ አባላት ጋር ግንኙነት አላችሁ ልትበጠብጡ ነው የመጣችሁት ብለዋቸው ነገ ተመልሰው ማዕከላዊ እንዲቀርቡ ቀጠሮ ሰትተው ነው አስረው የለቀቋቸው...> ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከፍ/ቤት ግቢ ታስረው ስለተወሰዱት ሁለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ሰዎች ለህብር ከሰጡት መግለጫ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
የዓለም ዋንጫ ሰሞነኛ ውሎ ከአስገራሚ ክንውኖችና አጓጊ ውጤቶቹ ጋር (ልዩ የስፖርት ዘገባ)
ለመንግስት ሰራተኛው ይጨመራል የተባለው ደሞዝና ተከትሎት የመጣው ኢኮኖሚያዊ ጣጣ(ልዩ ወቅታዊ ዘገባ )
<...በምህረት አዋጁ የሚካተቱ በሳውዲ እስር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እስረኞች ጉዳያቸውን የሚከታተልላቸው የጉዞ ሰነድ የሚያዘጋጅላቸው ይፈልጋሉ ። ለዚህ ቆንስላው የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት...>
ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የሳውዲ ንጉስ የሰጡትን የምህረት አዋጅ አስመልክቶ ካደረግንለት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ፌዴሬሽን እውን ለኢትዮጵያውያን በእኩል ይሰራል? የቬጋስ ቡድን አወዛጋቢ ውሳኔን አስመልክቶ ውይይት ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር(ሙሉውን ያዳምጡ)
ዜናዎቻችን
የዞን ዘጠኝ አባላትን ጉዳይ ለመከታተል ሔደው የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታስረው ተለቀቁ
የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊው ታስሮ በፖሊስ ተደብድቧል
ኦነግ በውስጡ ያለውን መከፋፈል አስወግዶ በአንድ አመራር ስር ለመታገል መወሰኑን አስታወቀ
አረና የተከለከለውን የተቃውሞ ሰልፍ በመቀሌ ደግሞ ሊጠራ ነው
ግብጻዊቷ ጋዜጠኛ በካይሮ የኢትዮጵያው አገዛዝ አምባሳደር ላይ ስልክ መዝጋቱዋ መነጋገሪያ ሆነ
የተባበሩት መንግስታት የኤርትራን የሰባዊ መብት ጥሰት እመረምራለሁ ማለቱ የአቶ ኢሳያስ መንግስትን አስቆጣ
ከአጥኚው ቡድን በስተጀርባ ኢትዮጵያና አሜሪካ አሉበት ሲሉ አገሪቱ ባለስልጣናት ይከሳሉ
በሳውዲ እስር ቤት ካሉ ኢትዮጵያውያን እስረኞች መካከል የሰሞኑ የአገሪቱ ንጉስ የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ቆንስላው አፋጣኝ ትብብር እንዲያደርግ ተጠየቀ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.