በሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ የሚኖሩ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አባሎች የሆኑት
- አቶ ሞላ ገረመው
- አቶ ብርሃኑ ገረመው
- አቶ ካሳሁን እንዳለ ከረቡዕ ሰኔ 18 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ የተቃዋሚ አባል
በመሆናቸው ብቻ የሚያርሱትን መሬት ቀምተው አሳርሰውባቸዋል፡፡ ለምን እንቀማለን ዜጎች አይደለንም ወይ ብለው ተቃውሞ
ሲያሰሙ ከፓርቲው ለቃችሁ ካልወጣችሁ መሬታችሁ አይመለስም በማለት የቀበሌው ሊቀመንበር አቶ ፀጋዬ ጎሹ አስፈራርተዋቸዋል፡፡
እንዲሁም በምዕራብ ጎጃም በይልማና ዴንሳ ወረዳ (አዴት) የሚገኙ የመኢአድ አባላት ላይ እስርና አፈና የተፈጸመ ሲሆን አቶ በቃሉ
ደፋሩ የተባሉ የወረዳው አባል ከሳምንት በፊት በፖሊስ ተይዘው እስካሁን ፍ/ቤት አልቀረቡም፡፡
በዚሁ ወረዳ – አቶ አትገኝ እምሬ እንዲሁም
- ቄስ ይሁን ዘለቀ ከሐሙስ ሰኔ 19ቀን 2006ዓ.ም ሌሊት ጀምሮ የደረሱበት አይታወቅም ሲሉ የመኢአድ
የህ/ግንኙነት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አለምነህ ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገልጸዋል፡
No comments:
Post a Comment