Sunday, June 29, 2014

[የዞን 9 ጦማርያን የፍርድ ቤት ውሎ] – ‹‹ያለ ፈቃድ መሬቱንም ፎቶ ማንሳት አይቻልም›› ፖሊስ

ጌታቸው ሽፈራው ከአዲስ አበባ
የጦማሪያኑን የፍርድ ውሎ የሚከታተለው ሰው ዛሬም እንደወትሮው በጠዋት ነው የተገኘው፡፡ አራት ሰዓት ካለፈ በኋላ የጦማሪያኑ ጠበቃ ‹‹መዝገብ ቤቷ ስለሌለች ነገ ከሰዓት ተብሏል›› ብለው ሲነግሩን በርካታ ህዝብ በተገኘበት አንዲት መዝገብ ቤት በመቅረቷ ብቻ የፍርድ ውሎው እንዲራዘም መደረጉ ገርሞን ስለጉዳዩ እያወራን ለጥቂት ደቂቃዎች ግቢው ውስጥ ቆየን፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ ደግሞ እየመጡ ነው ተባለ፡፡
የውሎው ትዕይንት እዚህ ላይ ነው የተጀመረው፡፡
ሶስቱም ጦማሪያን ሲመጡ ህዝቡ በጭብጨባ ተቀበላቸው፡፡ በድንገት እዚህ እዚያ የሚራወጡት ፖሊሶች ወደተሰበሰበው ሰው እየሮጡ በመምጣት የሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ አባል የሆነችውን ምኞት መኮንንን ‹‹ፎቶ ግራፍ አንስተሻል፡፡›› በሚል ማንገላላት ጀመሩ፡፡ በኃይል እየጎተቱ ሲወስዷትም ዮናታን ተስፋዬ ‹‹እኔን ውሰዱኝ›› ብሎ ምኞትን በኃይል እየገፈተሩ የሚወስዱት ፖሊሶች መሃል ገባ፡፡ ፖሊስ ግን እሱንም ማንገላላት ጀመረ፡፡ እሱንም አብረው ወሰዱት፡፡ ምኞትና ዮናታን ጦማሪያኑን ተከትለው ችሎቱ ወደሚገኝበት ቦታ ከተወሰዱ በኋላ ፖሊሶቹ ህዝቡ እንዲበተን ማስፈራራት ጀመሩ፡zone9-e1398747809895

No comments:

Post a Comment