”ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም” ይላል ደጉ ኢትዮጵያዊ። አሁን አሁን መጪውን የመከራ ዘመን ለመቀበል እራሳቸውን ያዘጋጁ፣መካሪ ሽማግሌ ያጡ እና ጥጋብ የሚሰሩትን ያሳጣቸው በእሳት ሲጫወቱ ማየት የተለመደ ሆኗ
ከእዚህ በላይ የምትመለከቱት ፎቶ አፍቃሪ ሕወሃቱ ፋና ብሮድካስቲንግ በድረ ገፁ ላይ የሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች የአካባቢው ቀደምት ነዋሪዎች አማራ ነን ትግሬ አይደለንም በማለታቸው ብቻ ትግሪኛ ተናጋሪዎች ሰልፍ መውጣታቸውን ከዘገበበት ገፅ ላይ የተወሰደ ነው።
በፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የለም በሚባል ደረጃ ሁለት ወይንም ሶስት ብቻ ትመለከታላችሁ።የቀረው በሙሉ ከኢትዮጵያ ጡት ያደገ በማይመስል መልክ (ተገዶ መሆኑን የሚገልፁ አሉ) የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተሽቀንጥሮ በህወሓት አርማ ሰቲት ሁመራ ላይ ተሰልፈዋል።
ዜናውን ፋና እንዳለው ብቻ ላቅርበው እና ሰልፈኞቹ መንግስትን ጎረቤቶቻችንን ይግደልልን ማለታቸውን አንብባችሁ ፍረዱ።በመጀመርያ ደረጃ በሰቲት ሁመራ፣በታች አርማጮ የአማራ ተወላጅ ነን ትግርኛ ብንናገርም ባህላችን፣ለቅሷችን፣ ሁሉ በአማራ ባህል ነው።በሚል በሰላማዊ እና በሰለጠነ መልክ ለመጠየቅ አዲስ አበባ ድረስ ተወካይ የላከው የሁመራ ሕዝብ ተወካዮቹ ታፈኑበት።እንግዲህ ይህንን በሰላማዊ መንገድ ለተጠየቀ ጥያቄ ነው ሰልፍ ተወጥቶ እንደ ፋና አገላለፅ ሰልፈኞቹ እንዲህ ብለዋል ይለናል-
‘‘ህዝቡ እነዚህን አካላት እስካሁን በትዕግስት ጠብቋቸዋል ያሉት ነዋሪዎቹ፥ ከአሁን በኋላ ግን መንግስት አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወስደባቸው ጠይቀዋል።’‘
በትዕግስት ጠበቃቸው የተባሉት ስለ ሁለት ነገር ነው ማለት ነው? አንዱ ቀድመው ነዋሪ ስለሆኑ ባህላችን ይጠበቅ በማለታቸው ሲሆን ሁለተኛው ይህንን መብታቸውን ደጋግመው በሰላማዊ መንገድ መጠየቃቸው ነው።
ለጥያቄው ምላሽ የሕወሃቱ የምስራቅ ትግራይ አስተዳዳሪ አቶ ኢሳያስ በምላሹ እንዲህ አሉ ይላል ፋና :- ”የህዝቡን ጥያቄ ለማክበርም በእነዚህ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንወስዳለን”
በቀይ ሽብር ዘመን እርምጃ ወስደናል ማለት ገድለናል ማለቱ መሆኑን ማንም ያውቀዋል።በፋና ዘገባም ሕዝብ ”እርምጃ ይወሰድ” አለ ማለት ”ይገደሉልን” ማለቱ ሲሆን ”እርምጃ እንወስዳለን” አሉ ሲል ደግሞ ”እንገላለን” ማለት መሆኑ ነው።እነማንን ሲባል ጎረቤቶቻቸውን እና ቀደምት ነዋሪዎችን።ምክንያት ባህላችን ይከበር በግድ ከመሬታችን ተገፋን ስላሉ።
ይህ አይነቱ የለየለት መንግስታዊ ፋሺዝም በኢትዮጵያ ላይ ነቅሎ ሰላም ይመጣል ማለት ዘበት ነው።በኦሮምያ በመቶ የሚቆጠሩ በጥይት እረግፈው እና የአስር እና አስራሁለት ዓመት ወጣቶች አደባባይ ወጥተው ድምፅ አሰሙ ብሎ ጥይት በተርከፈከፈባቸው እና መድረክ አዲስ አበባ ላይ ሰልፍ ለመጥራት ጠይቆ በተከለከለ ማግስት ሁመራ ላይ የሕወሃትን ሰንደቅ አላማ የያዙ ሰልፈኞች ጎረቤቶቻችንን ግዴልልን ብለው መንግስትን ጠየቁ መንግስትም እሺ እንገላለን አለ።የሚል ዜና የሚገኘው ፋና ድረ-ገፅ ላይ ብቻ ነው።ሰልፈኞችም ባይሰልፉ ቢቀር መልካም ነበር።ሽማግሌዎች (ሽማግሌ ካለ) ተሰብስበው ቢነጋገሩ እና መላ ቢዘይዱም ጥሩ ነበር።ነበር ለማለት ነው እንጂ ለህወሓት ከሁሉ በላይ የሆነ ስለመሰለው ፋሽሽታዊ ልብሱን በደንብ እያጠለቀ ነው።ለነገሩ ከቁንጮ እስከ እግር ድረስ በአንድ አካባቢ ሰው የምትመራ አገር በፋሽሽት መሪዎች እጅ ብትወድቅ አይገርምም።
ይህ ስርዓት ከትናንቱ ይልቅ መጪው ፋሽሽታዊ አላማው ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን በግልፅ ታይቷል።
ጉዳያችን GUDAYACHN
No comments:
Post a Comment