Friday, September 9, 2016

የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች በቢሾፍቱ 3 ወጣቶችን ገደሉ | እናት በአደባባይ ሲያለቅሱ የሚያሳይ ቪዲዮ ተለቋል


(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች 4ኛ ቀኑን የያዘውን ሰላማዊውን ከቤት ያለመውጣትና ያለመገበያየት አድማ ተከትሎ ወትሮም ሰውን ለመግደል የማይራሩት የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች ዛሬ በቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ከተማ 3 ወጣቶችን በጥይት ቆልተው መግደላቸው ታወቀ::
በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ሕዝብ ሰላማዊ ትግል እያደረገ ቢሆንም የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች እና ስናይፐሮች በየከተማው ፈሰዋል:: በቢሾፍቱ ዛሬ ከተገደሉት 3 ወጣቶች መካከል ሁለቱ ታውቀዋል:: በአጋዚ ጥይት ሰለባ የሆኑቱም ተረፈ ሽብሩ እና በቀለ ዲባባ ሲሆኑ የአንደኛው ማንነት እየተጣራ ነው:: በተጨማሪም በርካታ የቆሰሉ ሰዎች እንዳሉ ይነገር እንጂ ዘ-ሐበሻ ለማረጋገጥ አልቻለችም::
ከዛሬው የቢሾፍቱ ግድያ በኋላ በተለይ የበቀለ እናት በአደባባይ ሲያለቅሱ የሚያሳይ ቪዲዮ ተለቋል ይመልከቱት:: የእናቶች ለቅሶ የሚያበቃው መቼ ነው??

No comments:

Post a Comment