(ዘ-ሐበሻ) በአሜሪካም ውስጥ ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሶ የሰነበተው የዶናልድ ትራምፕ አዲሱ የኢሚግሬሽን ትዕዛዝ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከታገደ በኋላ የአሜሪካው የአገር ጥበቃና ደህንነት ባለስልጣን (ሆምላንድ ሴክዩሪቲ) የትራምፕን የቪዛ እገዳ መቀልበሱን አስታውቋል::
ዶናልድ ትራምፕ በሶማሊያ፣ በሱዳን፣ በኢራን፣ በሊቢያ፣ በሶሪያና በየመን ዜጎች ላይ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የሚያግድ ከ90 ቀናት ህግ ከፈረሙ ወዲህ የሃገሪቱ ፖለቲካ ሲታመስ ቆይቷል:: ሕዝብ በየኤርፖርቱና ይመለከታቸዋል በተባሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች አካባቢ ሰላማዊ ሰልፎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል::
የተለያይ አየር መንግዶችም የነዚህን ሃገራት ዜጎች ሲመልሱ ቆይተዋል:: ሆኖም ግና ይህን አጨቃጫቂ ፊርማ ዶናልድ ትራምፕ ካኖሩ በኋላ በርካታ የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ሲጨቃጨቁበት ቆይተው ትናንት ማምሻውን የዋሽንግተን ፍርድ ቤት ዳኛ ውሳኔውን በማገዳቸው ሆምላንድ ሴክዩሪቲም የትራምፕን ውሳኔ አጥፎ የተከለከሉ ዜጎችን ወደ አሜሪካ ማስገባቱን ዛሬ ጀምሯል::
ትራምፕ ስልጣን ላይ በወጡ በ2 ሳምንታቸው ደከመኝ ብለው ለ እረፍት ወደፍሎሪዳ ያመሩ ሲሆን እዚያም ተቃውሞ ጠብቋቸዋል::
No comments:
Post a Comment