Friday, July 11, 2014

ሶስተኛዉ የረመዳን የጁመዓ ተቃዉሞ ተደረገ



“ለከፈልነዉ መስዋእትነት አቻ ዉጤት እናመጣለን!” በሚል ጽኑ መንፈስ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ዛሬም በተለያዩ ከተሞች ታላላቅ ሰላማዊ ሰልፎችን አድርገዋል። ይህ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተሳተፉበት ሰልፍ በተሳካ መልኩ የተጠናቀቀ መሆኑን ሰላማዊዉን ንቅናቄ የሚመራዉ ድምጻችን ይሰማ አስታዉቋል። በባለፈዉ ሳምንት በተደረገዉ ተቃዉሞ እስከ ሰላሳ የሚደርሱ የሰልፉ ተሳታፊዎች ተይዘዉ መታሰራቸዉን፤ ብሎም ፍርድ ቤት በአዉቶቢስ ተጭነዉ መቅረባቸዉን ለማወቅ ተችሏል። ህገ መንግስታዊ መብታችን እስኪከበር ድረስ እስር፣ግድያ፣መገረፍ፣መደብደብ እና መሰደድ ትግላችንን አይገታዉም፤እስከ ድል ደጃፎች ድረስ በጽናት መትመማችንን እንቀጥላለን ይላሉ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች።
‹ግፉ እንዲያበቃ የ1 ብር ሰደቃ›› በሚል መሪቃል የተካሄደው የዛሬ ጁሙዓ ሐምሌ 4/2006 የሰደቃ እና የዝምታ ተቃውሞ 
2
45631
-- Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.--

Monday, July 7, 2014

የካምብሪጅ ጠበቆች ቡድን ከእንግሊዝ ውጪ ጉዳይ ባለስልጣናት ጋር ነገ በአንዳርጋቸው ዙሪያ ይሰበሰባል። እንግሊዝ ከፍተኛ የሚኒስቴሮች ቡድን ከማስጠንቀቂያ ጋርወደ አዲስ አበባ ትልካለች



 አንድአርጋቸው ቴዲ አፍሮ ወይንም ብርቱካን ሚደቅሳ አይደለም !!!

573C78C ወያኔዎች አንዳርጋቸውን አስረው የፖለቲክ ትርፍ የሚያገኙ መስሏቸዋል። አንዳርጋቸው ሳይታሰር ከሚፈጥረው ተጽእኖ ይልቅ ታስሮ የሚፈጥረው ተጽእኖ ቀላል አይደለም ፡ በውጪ ከሚታገለው ኤጥፍ በላይ በወህኒ በሚከፍለው መስዋትነት በወያኔ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ይፈጥራል። አንዳርጋቸውን በማሰራቸው የሚጸጸቱበት ቀን ሩቅ አይደለም ። ወያኔ ዝም ያለው የህዝብ ቁጣ በመፍርት ስኢሆን በሚስጥር የተብተኑ ደህንነቶች የሕዝቡን ትኩሳት እየለኩ መሆኑን ታውቅውል፤ ሃይለማርያም ደሳለንም ሆነ ሌሎች የወያኔ ባለስልጣናት የ አንዳርጋቸውን መታፈን የሰሙት ከግንቦት ስባት መግለጫ መሆኑ ተረጋግጧል። የወያኔ ድህረ ገጾች ላለፍት2 ሳምንታት ዝምታን መርጠዋል፡ ይህ የሚያመለክተው ወይኒ በራስ መተምመኑን ምን ያህል እንዳጣ ነው፡ ይህ ማለት ፕሮፌሰር አስራትን የያዙበት ግዜ አይነት አይደለም ዘመኑ አሁን የበሰለ ነው ሲሉ መረጃውን ያመጡት ተናግረዋል።
ነገ የሚሰበሰበው የካምብሪጅ የጠበቆች ቡድን ለ እንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ከባድ እና ህጋዊ ማስጠንቀቂያ በመስጠቱ ይህንን እንደሚያደርግ የሚጠብቀው ቢሮው የጠበቆቹን ቡድን አስከትሎ ክፍተኛ ሚኒስትርን ወደ አዲስ አበባ ይልካል ፤ በ እንግሊዝ የሚገኘው ታዋቂ የካምብሪጅ የጠበቆች ቡድን ከባድ ማስጠንቀቂያ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰጥቷል።
በመላው አለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እስከድል ጫፎች ድረስ ጫናችንን መቅጠል አለብን ።
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

Saturday, July 5, 2014

“ትግሉ የተጀመረው አሁን ነው” – ሻምበል በላይነህ (ከአቶ አንዳርጋቸው ለኢትዮጵያ መሰጠት በኋላ)

የኢሳት 4ኛ ዓመት በሳንሆዜ በአሁኑ ወቅት እየተከበረ ይገኛል። የአቶ አንዳርጋቸውን ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ መሰጠት ተከትሎ በአዳራሹ ያለው ሕዝብ እንዳዘነ ይነበባል። ሁሉም ተቆጥቷል። አርቲስት ሻምበል በላይነህ ለታዳሚው አንድ ሽለላ ያቀረበ ሲሆን ትግሉ የተጀመረው አሁን ነው ብሏል።
ሽለላውን እና ቪድዮውን ተመልከቱ።
አሁን ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እየተናገሩ ነው፤ ቪድዮው እንደደረሰን እናቀርባለን ይመለሱ።

አቶ አንዳርጋቸው “ለኢትዮጵያ መንግሥት ተሰጡ” ሲል ግንቦት ሰባት አስታወቀ (VOA Amharic)

00:00
00:00
የየመን መንግሥት የግንቦት ሰባትን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፎ ሰጥቷል ሲል ግንቦት ሰባት አስታውቋል፡፡
ግንቦት ሰባት በዌብ ሳይቱ ላይ ባሠፈረው መግለጫ “የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ለሥራ ጉዳይ በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት ሰንዓ ከተማ እያለ በየመን መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ ታግቶ መቆየቱ ማስታወቃችን ይታወሳል።” ብሏል፡፡
ግንቦት ሰባት ይቀጥልና “የየመን መንግሥት በህገወጥ መንገድ ያገተብንን የንቅናቄዓችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም – ይልና – የአገሩን የረዥም ጊዜ ጥቅም ማየት የተሳነው የየመን መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቅ አምባገኑን ወያኔ መርጦ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል።” ብሏል፡፡ “በዚህም ሳቢያ – ይላል የግንቦት ሰባት መግለጫ – የየመን መንግሥት ይቅርታ የማያሰጥ፤ ዘመን የማይሽረው ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወዳጅ ጎረቤት ትሁትና ቀና ቢሆንም ጥቃት በሚያደርስበት የቅርብም ሆነ የሩቅ ጎረቤት ላይ ግን ቁጣውን የሚመጥን የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ያውቅበታል።”
ግንቦት ሰባት ያወጣውን ሙሉውን መግለጫ ለማየት ከሥር የተያያዘውን ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ፡፡
DEA54BEE-2996-4145-A17A-2842A121CD0E_w640_r1_s
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

አዜብ መስፍን በጠና ታመዋል፤ የአባዱላ ገመዳ ልጅ አረፈ – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ከባለቤታቸው ህልፈት በኋላ ከፖለቲካው መድረክ እየተገለሉ የመጡት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በጠና መታመማቸውን ቅርበት ያላቸው ታማኝ ምንጮች አስታወቁ። በስኳር ህመምና በደም ግፊት እየተሰቃዩ የሚገኙት አዜብ መስፍን የሰውነት ክብደታቸው እንደቀነሰና የመጎሳቆል ሁኔታ በገጽታቸው እንደሚታይ የጠቆሙት ምንጮቹ ለስኳር በሽታ በየእለቱ ከሚወስዱት መድሃኒት በተጨማሪ ለደም ግፊትም እንክብሎችን እንደሚወስዱ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። አዜብ በመኖሪያቸው አብዛኛውን ቀናት እንደሚያሳልፉ የጠቆሙት ምንጮቹ በፖለቲካው የደረሰባቸው ኪሳራ ብስጭት ውስጥ እንደከተታቸውና ለበሽታ እንደዳረጋቸው አያይዘው ገለጸዋል።
ቦሌ ከሳይ ኬክ ቤት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የሚገኘውና አቶ ስዩም መስፍን ለ19ዓመት የኖሩበት እንዲሁም አቶ ሙክታር ከድር ለሁለት አመት የኖሩበት መኖሪያ ቪላ ውስጥ የሚኖሩት አዜብ መስፍን ከዚህ በተጨማሪ ቦሌ ሩዋንዳ መታጠፊያ ላይ የሚገኘውን የቀድሞ የደህንነት ቢሮ ለአዜብ በቢሮ መልክ እንደተሰጣቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል።
azeb
ቀን ቀን በዚህ ቢሮ ለብቻቸው ያሳልፉ የነበሩት አዜብ መስፍን በጠና ከታመሙ ወዲህ ላለፉት አምስት ሳምንታት ወደዚህ ቢሮ ገብተው እንደማያውቁና በቤታቸው እንደሚያሳልፉ ያስታወቁት ምንጮቹ አክለውም ፓርቲው በሚያካሂዳቸው ስብሰባዎች መገኘት እንዳቆሙና ለመጨረሻ ጊዜ የተገኙት ከሁለት ወር በፊት ኢህአዴግ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ላይ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚሁ ጉባኤ ከተሰብሳቢው ኋላ ለብቻቸው ተቀምጠው የታዩት አዜብ ምንም ሳይናገሩና አስተያየት ሳይሰጡ ስብሰባውን ከመጨረሳቸው ባሻገር ከስተውና ተጐሳቁለው እንደነበር ምንጮቹ አስታውሰው ከዚያ ወዲህ ህመሙ እየጠናባቸው እንደሄደ አያይዘው ገለፀዋል። አዜብ የባለቤታቸውን ቦታ በመተካት የጠ/ሚ/ርነቱንና ፓርቲውን የመምራት እቅድና ምኞት በተቀናቃኛቸው ስብሃት ነጋ ከከሸፈባቸውና የሚተማመኑባቸው የደህንነት ባለስልጣናትና የፓርቲው ቁልፍ ሰዎች እስር ቤት መወርወርና መባበረር ለከፍተኛ የሞራል ድቀትና ለበሽታ እንደዳረጋቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። አዜብ የኤፈርት ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር ተብለው ቢሰየሙም ምንም አይነት የአመራር ሚና እንደሌላቸው የጠቆሙት ምንጮቹ በነስብሃት ተመድበው ተቋሙን ሲመሩ የቆዩት አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ወደ ራዲዮና ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ እንደሆኑና ከርሳቸው በኋላ ደግሞ የአርከበ እቁባይ ታናሽ ወንድም ጌታቸው እቁባይ እየመሩት መሆኑን አያይዘው ገልፀዋል።
ከአዜብ ጋር በተፈጠረ ያለመግባባት ከኤፈርት ለቀው የቆዩት ጌታቸው እቁባይ የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ እንዲመለሱ መደረጉን አመልክተዋል። አዜብ ወደ ትግራይ -መቀሌ ከተጓዙ 6 ወር እንዳለፋቸው አክለዋል። በኤፈርት ውስጥ የአዜብ ደጋፊዎች በነስብሃት ተለቅመው መውጣታቸውን ያስታወሱት ምንጮቹ በቅርቡ ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር የሚለውን የአዜብ ስልጣን በመግፈፍ ሊያባርሯቸው መሆኑን አረጋግጠዋል። …ይህ በእንዲህ እንዳለ የአባዱላ ገመዳ ልጅ ወጣት ኮሚያስ አባዱላ ከዚህ አለም በሞት እንደተለየ ታውቋል። የ26 አመቱ ወጣት ኮሚያስ አባዱላ በጉበት በሽታ ምክንያት ወደ ታይላንድ- ባንኮክ ተልኮ ለአንድ አመት ሲታከም ከቆየ በኋላ ሊድን ባለመቻሉ ከአራት ሳምንት በፊት ህይወቱ አልፏል። በባንኮክ ለአንድ አመት የሆስፒታል ቆይታው ለህክምና ብቻ ከ880ሺህ ዶላር ወጪ እንደተረገለት ታውቋል። በተመሰሳሳይ ሶስተኛ ታናሽ እህቱ (የአባዱላና ራሄል ልጅ) ከአምስት አመት በፊት በገጠማት የሳንባ፣ የአንጀትና የአእምሮ በሽታ በባንኮክ ሆ/ል ለሁለት አመት ህክምና የተከታተለች ሲሆን፣ ለህክምናው ጠቅላላ የወጣው 2.5ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ከዚህ ቀደም ይፋ በተረገው መረጃ መገለፁ ይታወሳል። ይህ ሁሉ ገንዘብ ከህዝብ የተዘረፈ ለመሆኑ አያጠያይቅም። ይህቺ ናት አገሬ! ..ለማንኛውም የአባዱላ ወንጀል ልጁን አይመለከተውም። ወጣት ኮሚያስ በአባቱ ድርጊት ነፃናነት ስለማይሰማው – በየእለቱ አልኮል ይጠጣና ይበሳጭ እንደነበረ ቅርብ የሆኑ ጓደኞቹ ተናግረዋል። የጉበት በሽታውም መንስኤ ይኸው ነው። ነፍስ ይማር

Thursday, July 3, 2014

(ሰበር ዜና) የየመን መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፎ ሰጠ

andargachew( የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተው፣ የግንቦት ሰባቱ ዋና ጸሃፊና የድርጅቱ ሞተር የሚባሉት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ  ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፈው ተሰጥተዋል። አቶ አንዳርጋቸው ለትራንዚት ሰንዓ የመን በቆዩበት ጊዜ በየመን ደህንነት ሃላፊዎች  ከአሥር ቀናት በፊት የታገቱ ሲሆን፣ ድርጅታቸው ግንቦት ሰባት እርሳቸዉን ለማስፈታት ዉስጥ ዉስጡን በርካታ ጥረቶች ሲያደርግ እንደቆየም ከድርጅቱ የወጣዉ መግለጫ ይጠቁማል።
አቶ አንዳርጋቸውን ለመጎብኘት ጥረት ያደረገው የእንግሊዝ ኤምባሲ፣ በየመን አቶ አንዳርጋቸውን ለማግኘት እንዳልቻለ የገለጸዉ የደረሰን ዘገባ፣ አቶ አንዳርጋቸው ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፈው የተሰጡት፣ በየመን መንግስት መያዛቸው በድርጅታቸው ለሕዝብ ይፋ ከመሆኑ በፊት እንደሆነም ለማረጋገጥ ችለናል።
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከግንቦት ሰባት አባላት ዉጭ በበርካታ ኢትዮጵያዉያን ዘንድ በቆራጥነታቸውና ሐሳብ አመንጪነታቸው የሚታወቁ ናቸው። በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት ፣ በቅንጅት ዉስጥ ትልቅ ተሳትፎ ያደርጉ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው፣ ለሰላማዊ ትግሉም መጽሃፍ ጽፈው ያበረከቱ አገር ወዳድ ሰው ናቸው። በወቅቱ የኢሕአዴግ መንግስት አቶ አንዳርጋቸውን በዝዋይ አስሮ የነበረ ሲሆን፣ በዚያም በደረስባቸው ድብደባ አይናቸው ላይ ጉዳት እንደደረሰም በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል። አቶ አንዳርጋቸው አገዛዙ በሰላም አይወርድም በሚል ሁለገብ ትግል አደርጋለውሁ የሚለው የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር አባል ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ታጋይ ናቸው።