Friday, July 11, 2014

ሶስተኛዉ የረመዳን የጁመዓ ተቃዉሞ ተደረገ



“ለከፈልነዉ መስዋእትነት አቻ ዉጤት እናመጣለን!” በሚል ጽኑ መንፈስ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ዛሬም በተለያዩ ከተሞች ታላላቅ ሰላማዊ ሰልፎችን አድርገዋል። ይህ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተሳተፉበት ሰልፍ በተሳካ መልኩ የተጠናቀቀ መሆኑን ሰላማዊዉን ንቅናቄ የሚመራዉ ድምጻችን ይሰማ አስታዉቋል። በባለፈዉ ሳምንት በተደረገዉ ተቃዉሞ እስከ ሰላሳ የሚደርሱ የሰልፉ ተሳታፊዎች ተይዘዉ መታሰራቸዉን፤ ብሎም ፍርድ ቤት በአዉቶቢስ ተጭነዉ መቅረባቸዉን ለማወቅ ተችሏል። ህገ መንግስታዊ መብታችን እስኪከበር ድረስ እስር፣ግድያ፣መገረፍ፣መደብደብ እና መሰደድ ትግላችንን አይገታዉም፤እስከ ድል ደጃፎች ድረስ በጽናት መትመማችንን እንቀጥላለን ይላሉ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች።
‹ግፉ እንዲያበቃ የ1 ብር ሰደቃ›› በሚል መሪቃል የተካሄደው የዛሬ ጁሙዓ ሐምሌ 4/2006 የሰደቃ እና የዝምታ ተቃውሞ 
2
45631
-- Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.--

No comments:

Post a Comment