ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ መቼስ የማንሰማው ነገር የለም 25 አመት ሙሉ በትግዕስቱ ታግሶዋቸው የተቀመጠውን ህዝብ በየተራ እየተነሱ ማንቋሸሽ፣ መስደብ አላቆሙም። አሁንም እንኳን ሞት በራፋቸው ላይ ቆሞ መጥፊያቸው ግቢያቸው ገብቶ ስድባቸውን ቀጥለዋል። ይሄ የሚያሳየው ደግሞ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያላቸው ጥላቻ ካልጠፉ በስተቀር እንደማይተውት የሚያሳይ ነገር ነው።
የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር የኢትዮጵያን ወጣቶች ቦዘኔ፣ ፍንዳታ፣ በማለት ሲያጥላሉ እና ሲሳደቡ አሻንጉሊቶቹ የፓርላማ አባላት ያጨበጭቡና ይስቁ ነበር። የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ባገኘው አጋጣሚ እንደማይፈልጋቸው ሲነግራቸው ኖሯል። ህዝቡ እንዳልመረጣቸው ቢያስውቃቸው ምን ታመጣላችሁ በሚል እያንቋሸሹ፣ እየሰደቡ የጭቆና አገዛዛቸውን ቀጥለውበታል። ህዝብን የሚያክል ነገር መሪ በተባሉት አካል ቦዘኔ እየተባሉ በአደባባይ ሲሰደቡ የሚያሳፍር ቢሆንም ህዝቡ ግን ቦዜኔ ያለው ቤተ መንግስት ነው በማለት የቦዘኔ ጥርቅም ያለው ያለ እውቀታቸው እና ያለ ህዝብ ፍላጎት ተመርጠናል በማለት የተሰገሰጉበት መሆናቸውን ይነግራቸው ነበር።
በ97 የቅንጅት ሰልፍ ግዜ አጋዚ በሰላማዊ ሰው ላይ በወሰደው ኢሰባአዊ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ወያኔዎች የተወሰደው እርምጃ ትክክል ነው ባንክ ሊዘርፉ ሲሉ የነበሩ እና የተለያየ የሽብር ስራ ሊሰሩ የነበሩት ናቸው እርምጃ የተወሰደባቸው በማለት ከመጸጸት ይልቅ ያልተገባ ስም እየሰጡ መግደላቸውን እንደ ትክክለኛ ስራ አድርገው ሲነግሩን ህዝባችን ጥርሱን ነክሶ ዝም ከማለት ውጪ ምንም ያደረገው ነገር አልነበረም። ወያኔዎች የኢትዮጵያ ህዝብን በማንቋሸሽ እና በመስደብ የታወቁ ናቸው። በተቃራኒው ደግሞ የትግራይ ህዝብ ደግሞ በወያኔዎች አገላለጽ ወርቅ ትውልድ እንደሆኑ ይነግሩናል። ይሄ ደግሞ አንደኛ ዜጋ እና ሁለተኛ ዜጋ እንደሆንን አልገባን ከሆነ በግልጽ ነግረውን እየሰሩበት ይገኛሉ።ለዚህ ነው ህዝባችንን ወራዳ፣ ፍንዳታ፣ ቦዘኔ ሌላም ሌላም እያሉ የሚሰድቡት። ዛሬ ደግሞ በለመደው የስድብ አፋቸው አጋንት፣ጠንቋይ ብለው ህዝባችንን በግልጽ በአደባባይ ሰድበውታል። ይሄ የሚያሳየው ለወያኔዎች የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ሰው አለመቁጠራቸው ነው። የሰው ልጅን አጋንት ተብሎ መሳደብ ያስቀጣል ወደፊትም ተጠያቂም ያደርጋቸዋል። ዛሬ ስልጣን ላይ ነይ ብለው በስልጣናቸው ተጠቅመው የፈለጉትን መናገርና መስራት እንችላለን ተብሎ ህዝብን የሚያል ማዋረድ ህዝብን ማንቋሸሽ አቋማቸው ሁሌም የማይለወጥ መሆናቸውን አሳውቀውናል እኛም ካወቅን ሰነበትን። ህዝቡ ሲነሳ ነደድ እሳት እንደሆነ አልተገነዘባችሁ ይሆንን? ህዝብ ሆ ብሎ ተነስቶ እንደሚያጠፋችሁ ዘንግታችሁታል። ህዝብን ንቆ፣ አዋርዶ፣ አንቋሾ መኖር እንችላለን ብላችሁ ካሰባችሁ ዶክተር መራራ ጉዲና እንደተናገሩት እነሱ ከጫካው ወጡ እንጂ ጫካው ከነሱ አልወጡም የሚለው አገላለጽ ይገልጻችኋዋል። ዛሬም ከ25 አመት በኋላ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያላችሁ ጥላቻ አለመጥፋቱን በግልጽ ነግራችሁናል። ዛሬም የኢትዮጵያን ህዝብ ለመስደብ እና ለማጥፋት እንደማይመለሱ በእርገጠኝነት አሳይታችሁናል።
እንግዲህ ዛሬ ያልነቃህ ካለህ ንቃ ያልተነሳህ ካለህ ተነስ። ኦፒዲኦ፣ ብአዴን፣ ደህዴን የሚባሉት ድርጅቶች ቀድመን እንደተናገርነው ደግመንም ደግመንም እንዳሳሰብነው የወያኔ መጠቀሚያ እንጂ ምንም የማይሰሩ በአገሪቷ ላይ ስልጣን የሌላቸው የሆድ አደር ጥርቅም እንደሆኑ ብዙሃኖቹ አስረግጠው ተናግረዋል። በየትኛውም አካባቢ ትዕዛዝ የሚያስተላልፉት ውሳኔ የሚሰጡት የክልሎች መንግስት ተብዬዎች ሳይሆን ወያኔዎች ናቸው። ከዚህ መስመር በኋላ ኦፒዲኦ ነው የሚመለከተው ከዚህ መስመር በኋላ ብአዴን ነው የሚመለከተው ከዚህ መስመር በኋላ ደህዴን ነው የሚመለከተው በማለት ሁሉም አንድ ሆነው እንዳይሰሩ ለመለያየት የተጠቀመበት እንጂ ምንም የማይፈይዱ የወያኔ መጠቀሚያ የሆኑ አጥር እና ድርጅቶች ናቸው። ይሄንን አጥር እና የወያኔ ሴራ ለአንደ እና ለመጨረሻ ግዜ መሰበሪያው ሰአት አሁን ነው። በአጥር ከልሎ አንዱ ወደ ሌላው እንዳይመጣ አንዱ ለአንዱ አጋር እንዳይሆን እናንተ አይመለከታችሁም ሁሉም የራሳቸው አስተዳዳሪ ስላላቸው ማንም ከራሱ ክልል ውጪ አይመለከታችሁም በሚል ሰበብ አራርቆ ወያኔ ግን ሁሉም ክልሎች ውስጥ በዋነኝነት እየሰራ ህዝባችንን አለያይቶ በተነጠል እያጠፋን ስለሆነ ነገሮችን በጥልቀት እና በብልጠት የምናይበት ግዜ ነው። ወያኔ ያስቀመጠው አጥር በማፍረስ ፍቅር አሸናፊ ነው አንድነት ሃይል ነው የኛ ጠላት ወያኔ ነው ብለን የከፋ ነገር ሳይመጣ አንድነታችንን በግልፅ እናውጅ። በአገር ቤትም በውጪም የምትኖሩ የተቃዋሚ ኃይሎች አንድ ነን ብላችሁ በአንድነት ተሳሰሩ በአንድነት ቁሙ ስለ አንድነት ዘምሩ ያኔ በአንድነት የተሳሰረ ህዝብ በአንድነት የፍቅር መዝሙርን ሲያሰሙ የወያኔ ምሶሶዎች ይፈርሳሉ ዛሬ አጋንት ብሎ ህዝባችንን የሰደቡ በፍቅር እና በአንድነት ስንቆም የእግዚአብሔር ኃይል ለብሰን የተሳዳቢዎችን አፋቸውን የመዝጋት ስልጣን እናገኛለን። የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ንቁ እንንቃ ሁሉም ህብረተሰብ አንዱ ለአንዱ ዘብ ይቁም አንዱ ለአንዱ መከታው ይሁን። ሁላችንም ሳንለያይ በመደጋገፍ ለወያኔ ሴራ ክፍተት ባለመስጠት ብንሰራ በአጭር ግዜ ድሉን በእጃችን ማስገባት ይቻላል ሰላምን ለኢትዮጵያ ማስፈን ይቻላል።
የወያኔን ፉከራ ባዶ ፉከራ ማድረግ የምንችለው ሳንከፋፈል ስንታገል ብቻ ነው። ስድባቸውን ማጥፋት የምንችለው በአንድነት ስንነሳ ብቻ ነው። ይሄ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ መልዕክቴ ነው። ህዝባችንን ለጭፍጨፋ አናጋልጥ ለህዝባችን ነጻነትን ለማምጣት በረሃ የወረዱትንም አሰልቺ ትግል እንዲጋፈጡ አናድርጋቸው። ነጻነት ማግኘት የምንችለው በረሃም ያሉት ከተማም ያሉት በውጪም ያሉት የአንድነት ድምጽ ሲኖረን ነው። ይሄ ካልሆነ ግን ትላንትና በአደባባይ ቦዘኔ፣ ፍንዳታ፣ ወራዳ ተብለን ተሰድበንና ተገድለን በመከራ እንዳለፍን ሁሉ ዛሬም አጋንት፣ ጠንቋይ ብለውን እየሰደቡን እየገደሉን እያዋረዱን ነው። በአደባባይ እየተሰደብን በአገራችን እየተገደልን ከቄአችን ላይ እየተፈናቀልን እንዳንኖር ሰላማችንን ማምጣት የምንችለው እኛው ነን። ወያኔ እንደሆነ መቼም መለወጥ የማይችሉ ናቸው። መለወጥ ያለብን እኛው ለውጥን ፈላጊ ሰላምን ናፋቂዎቹ ነን።
No comments:
Post a Comment