(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) በጎንደር የሚገኙት የህወሓት አገዛዝ ከፍተኛ ባለስልጣናት በአሁኑ ሰዓት ለሁለት ተከፍለው ወደ መተማ ሸዲና አርማጭሆ አቅንተው ህዝቡን በመማፀን ላይ ናቸው፡፡
በትናንትናው ዕለት በጎንደር ጎሃ ሆቴል በነበረው ስብሰባ ላይ ገዱ አንዳርጋቸው የጎንደር ህዝብ በስርዓቱ ላይ ማመፁን ባፋጣኝ የማያቆም ከሆነ የክልሉ ልዩ ኃይል እና ፌደራል ፖሊስ ጦር ተቀናጅተው የማያዳግም የኃይል እርምጃ እንደሚወስዱ እሱ የሚመራውን ክልል አስተዳደር አቋም አስታውቋል፡፡
በዛሬው ዕለት አባይ ፀሐዬ፣ ደመቀ መኮንን እና አምባቸው /የክልሉ ምክትል አስተዳዳሪ/ ወደ መተማ ሸዲ አምርተው በቦታው ያገኙትን ጥቂት ህዝብ ከአንገት በላይ የሆነ ጉንብስ ለመዋረድ እየጣሩ ይገኛሉ፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታም እንዲሁ በረከት ስምዖን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ሙሉጌታ ወርቁ /የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር/ እና የክልሉ ልዩ ሃይል አዛዥ የሆነው ሰው ወደ አርማጭሆ ዘልቀው ከህዝብ ጫማ ስር በመውደቅ ላይ ናቸው፡፡
No comments:
Post a Comment