Monday, October 3, 2016

ሕዝባዊው አመጽ በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋና በሌሎችም ከተሞች ተቀጣጠለ

carscarswmeki
(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ትናንት በቢሾፍቱ የ እሬቻን በዓል ለማክበር በወጡ ንጹሃን ላይ በሂሊኮፕተር እና በመትረየስ የታጀበ የዘር ማጥፋት ከፈጸመ በኋላ በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ አመጹ እንደገና ተቀጣጠለ::
ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች እንደጠቆሙት በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋና በሌሎችም ከተሞች ተቃውሞው ተቀጣጥሏል::
በተለያዩ ከተሞች በተነሱት በነዚሁ ሕዝባዊ አመጾች የመንግስት መኪኖች ሲነዱ ታይተዋል::
በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋ ሕዝብ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን እያሰማ ሲሆን በመንግስት ንብረቶች ላይ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይም ይገኛል::
በተለይ የሕወሃት ንብረት የሆነው ሰላም ባስ በሃረርጌ ጥቃት እንደተፈጸመበት የደረሰን መረጃ ያመልከታል::
በቄለ ወለጋ ጂማ ሆሮ ወረዳ ኑኑ ከተማ ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ተቅስቅሶ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እንደሆኑ ሲታወቅ በባሌ ሮቤ ደግሞ ሁሉ ነገር መዘጋጋቱ ተሰምቷል::
በደምቢ ቦሎ ኢንተርኔት በጠቅላላ መቆረጡ ሲታወቅ ተቃውሞውም እንደበረታ ምንጮች ገልጸዋል:: በአምቦም እንዲሁ ተመሳሳይ ተቃውሞዎች ዳግም እንደተቀሰቀሰ የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ

ለኦሮሞ ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን(ከአማራ ተጋድሎ ግብረ ኃይል በዉስጥ መስመር የተላከ)

14355189_1776743355901679_4397046954836303499_n
በትላንትናው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ ሲከበር በነበረው አመታዊ የእሬቻ በአል ላይ ለመታደም ከመላው ኦሮሚያና ከተለያዩ የሀገራችን አባቢዎች በመጡ ተሳታፊዎች ላይ የህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ ጦር በፈፀመው አስከፊ የጦር ወንጀል ቁጥራቸውን ለመገመት የሚያዳግቱ ወገኖቻችንን ተነጥቀናል፡፡ በዚህም የወገኖቻችን ህልፈተ-ህይወት የተሰማን ሀዘን በጣም ጥልቅ ነው፡፡ የእነዚህ ኦሮሞ ወንድሞቻችን ሞት የእኛም የአማራዎች ሞት፡ የፈሰሰው ደማችውም የእኛም ደም መሆኑን እደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ በቃላት ሳይሆን አብረን በመሞትና ደማችንን በማፍሰስ አንድ መሆናችንን አረጋግጠናል፡፡ ወደፊትም በልበ-ሙሉነት እጅ ለእጅ ተጣምረን በፍፁም ወንድማማችነትና መተማመን መንፈስ ይሀንን ሰው-በላ የወንበዴ ጥርቅም ከላያችን ላይ በማሽቀንጠር ለዘለዓለሙ እንዳይነሳ በመቅበር ለሁላችንም የኢትዮጵያ ህዝቦች እኩል የምትሆን አዲስ ቤት በመገንባት በደም የተሳስረውን አንድነታችንን ዳግም የምናድስበት ቀን እሩቅ አይሆንም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ሞትና ደም መፍሰስ የአማራ ህዝብም ሞትና ደም መሆኑን በድጋሜ እያረጋገጥን ወደፊት በሚጠብቀን መራራ የነፃነት ትግል ጉዞ ትላንት የወደቁትን ዜጎቻችን በማሰብ በድል እንገሰግሳልን፡፡
ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር!!
#AmharaResistance

Sunday, October 2, 2016

ከእሬቻው ጭፍጨፋ በኋላ የአምቦ ሕዝብ ተነሳ | የተቆጣው ሕዝብ በርካታ የመንግስት መኪኖችን አቃጠለ



ambo


 (ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ኦሮሞዎችን እና አማሮችን በ እሬቻ በዓል ቢሾፍቱ ላይ ዛሬ ከጨፈጨፈና ከ500 በላይ የሰው ሕይወት ካጠፋ በኋላ በአምቦ ሕዝብ በቁጣ ተነሳ:::
በአምቦ በተነሳው ሕዝባዊ አመጽ ሕዝቡ ቁጣውን በመንግስት ንብረቶች ላይ እርምጃ በመውሰድ እየገለጸ ነው:: እንደዘ-ሐበሻ ዜና ምንጮች ገለጻ ከሆነ በአምቦ በርካታ የመንግስት መኪኖች እና አንዳንድ መስሪያ ቤቶች በ እሳት ወድመዋል:: ይህን ተቃውሞ ሊያረግቡ በመጡ የሕወሓት ወታደሮች ላይም እርምጃ መውሰድ የጀመረ ሲሆን ወታደሮች እየሸሹ መሄዳቸው ተሰምቷል::
በአምቦ መንገዶች መዘጋጋታውም ተሰምቷል::
የአምቦ ሕዝብ እጅጉን ከመቆጣቱም ባሻገር በሌሎች የኢትዮጵያ ክልል ከተሞችም እንዲሁ ይህው ሕዝባዊ ተቃውሞ እንደሚቀጥል ይጠበቃል::