በትላንትናው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ ሲከበር በነበረው አመታዊ የእሬቻ በአል ላይ ለመታደም ከመላው ኦሮሚያና ከተለያዩ የሀገራችን አባቢዎች በመጡ ተሳታፊዎች ላይ የህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ ጦር በፈፀመው አስከፊ የጦር ወንጀል ቁጥራቸውን ለመገመት የሚያዳግቱ ወገኖቻችንን ተነጥቀናል፡፡ በዚህም የወገኖቻችን ህልፈተ-ህይወት የተሰማን ሀዘን በጣም ጥልቅ ነው፡፡ የእነዚህ ኦሮሞ ወንድሞቻችን ሞት የእኛም የአማራዎች ሞት፡ የፈሰሰው ደማችውም የእኛም ደም መሆኑን እደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ በቃላት ሳይሆን አብረን በመሞትና ደማችንን በማፍሰስ አንድ መሆናችንን አረጋግጠናል፡፡ ወደፊትም በልበ-ሙሉነት እጅ ለእጅ ተጣምረን በፍፁም ወንድማማችነትና መተማመን መንፈስ ይሀንን ሰው-በላ የወንበዴ ጥርቅም ከላያችን ላይ በማሽቀንጠር ለዘለዓለሙ እንዳይነሳ በመቅበር ለሁላችንም የኢትዮጵያ ህዝቦች እኩል የምትሆን አዲስ ቤት በመገንባት በደም የተሳስረውን አንድነታችንን ዳግም የምናድስበት ቀን እሩቅ አይሆንም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ሞትና ደም መፍሰስ የአማራ ህዝብም ሞትና ደም መሆኑን በድጋሜ እያረጋገጥን ወደፊት በሚጠብቀን መራራ የነፃነት ትግል ጉዞ ትላንት የወደቁትን ዜጎቻችን በማሰብ በድል እንገሰግሳልን፡፡
ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር!!
#AmharaResistance
#AmharaResistance
No comments:
Post a Comment