Monday, October 3, 2016

ሕዝባዊው አመጽ በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋና በሌሎችም ከተሞች ተቀጣጠለ

carscarswmeki
(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ትናንት በቢሾፍቱ የ እሬቻን በዓል ለማክበር በወጡ ንጹሃን ላይ በሂሊኮፕተር እና በመትረየስ የታጀበ የዘር ማጥፋት ከፈጸመ በኋላ በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ አመጹ እንደገና ተቀጣጠለ::
ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች እንደጠቆሙት በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋና በሌሎችም ከተሞች ተቃውሞው ተቀጣጥሏል::
በተለያዩ ከተሞች በተነሱት በነዚሁ ሕዝባዊ አመጾች የመንግስት መኪኖች ሲነዱ ታይተዋል::
በአምቦ፣ በጊንጪ፣ በሸኖ፣ በመቂ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደንቢ ዶሎ፣ በቄለም ወለጋ፣ በም ዕራብ ሸዋ ሕዝብ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን እያሰማ ሲሆን በመንግስት ንብረቶች ላይ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይም ይገኛል::
በተለይ የሕወሃት ንብረት የሆነው ሰላም ባስ በሃረርጌ ጥቃት እንደተፈጸመበት የደረሰን መረጃ ያመልከታል::
በቄለ ወለጋ ጂማ ሆሮ ወረዳ ኑኑ ከተማ ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ተቅስቅሶ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እንደሆኑ ሲታወቅ በባሌ ሮቤ ደግሞ ሁሉ ነገር መዘጋጋቱ ተሰምቷል::
በደምቢ ቦሎ ኢንተርኔት በጠቅላላ መቆረጡ ሲታወቅ ተቃውሞውም እንደበረታ ምንጮች ገልጸዋል:: በአምቦም እንዲሁ ተመሳሳይ ተቃውሞዎች ዳግም እንደተቀሰቀሰ የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ

No comments:

Post a Comment