Thursday, December 4, 2014

የወቅቱ የኢትዮጵያ ወጣት እና ህወሓትን የማስወገድ ትግል

ታደሰ ብሩ

መግቢያ

አገራችን ኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛት ከአፍሪቃ ሁለተኛ ስትሆን በተባበሩት መንግሥታት መመዘኛ “ወጣት” ተብሎ በሚጠራው የኅብረተሰብ ክፍል ብዛት ግን አንደኛ ነች። እርግጥ ነው ወጣነት በእድሜ ብቻ የሚገለጽ የኅብረተሰብ ክፍል አይደለም።  የሚከተለው የወጣት ትርጉም ሰፋ ያለ  ተቀባይነት ያለው ይመስለኛል።
0,,17657086_303,00
የኢትዮጵያዉያን ሰሚ ያጣ ጩኸት
ወጣት፣ በማኅበረሰቡ አንኳር ጉዳዮች ላይ እየወሰነ ባለው “አዋቂ” ተብሎ  በሚጠራው የኅብረሰተሰብ ክፍል እና ማኅበራዊ ፋይዳ ያላቸውን ውሳኔዎች ለመስጠት ገና ባልተዘጋጀው ሕፃን መካከል ያለ የኅበረተሰብ ክፍል ነው።
በዚህ ትርጓሜ መሠረት ወጣትነት የማኅበራዊ ግኑኝነት መገለጫ ጽንሰ ሀሳብ ነው። ይህ ማኅበራዊ ግኑኝነት ወደ እድሜ እንመዝረው ስንል ችግር ውስጥ እንገባለን፤ ምክንያቱም ወጣቱ ወደ አዋቂነት የሚሸጋገርበት ጊዜ እንደየአገሩ ባህሉና እንደ እድገቱ ይለያያል። በዚህም ምክንያት ነው የወጣትነት የህግ ትርጓሜዎች በየአገሩና ባህል የተለያዩ የሆኑት። ለምሳሌ፣ የተባበሩት መንግሥታት ወጣት ማለት “እድሜው 15 እስከ 24 ዓመታት ድረስ ያለው ሰው ነው” ሲል ይተረጉማል፤ ይሁን እንጂ የራሱ አካል የሆነው  UN Habitat “ወጣት ማለት እድሜው 15-32 ዓመት ያለው ሰው ነው” ይላል።  በአገሮች ትርጓሜ መካከል ያለው ልዩነት ደግሞ በጣም የተዘበራረቀ ነው። ዩጋንዳ ውስጥ እድሜው 12-30 የሆነ ዜጋ ወጣት ሲሰኝ ጎረቤትዋ ኬንያ ውስጥ 18-35 ነው። ስለዚህም አንድ የ16 ዓመት ወጣት ዩጋንዳዊ  ድንበር ተሻግሮ ኬኒያ ሲገባ ሕፃን ይሆናል፤ አንድ የ 32 ዓመት ኬንያዊ ወጣት ዩጋንዳ ሲሻገር ጎልማሳ ይሆናል።  ከአፍሪቃ ዝብርቅርቅ የወጣት ትርጓሜዎች ለአብነት ጥቂቶቹን ላንሳ: ሞውሪሸስ 14-29፣ ደቡብ አፍሪቃ 14-29፣ ናይጄሪያ 18-35፣ ጂቡቲ 16-30፣ ኬኒያ 18-35።
በ2004 ዓም የወጣው የኢትዮጵያ መንግሥት የወጣቶች ፓሊሲ ከ15 -29 ዓመታት ውስጥ የሚገኝን ኢትዮጵያዊን ዜጋን ወጣት ብሎ ይተረጉመዋል። በወጉ የሚያስተናግደው አላገኘም እንጂ ይህ ፓሊሲ በወጣበት ወቅት የኢትዮጵያ የወጣት ትርጓሜ እንደ ኬኒያና ናይጄሪያ 18- 35 መሆን ይገባዋል የሚል ሀሳብ ቀርቦ ነበር። የወጣቱ ከፓለቲካና ማኅበራዊ ውሳኔዎች መገለል መብዛትን በማጤን የላይኛው ጣራ እስከ 39 ከፍ ማለት አለበት የሚል ክርክርም ነበር። በበኩሌ ሥራአጥነትና ዘረኛ የህወሓት ፓሊሲ ያስፋፋው መድልዎና መገለል የወጣት የእድሜ ማዕቀፍ እንዲሰፋ አድርጓል ብዬ አምናለሁ። አርባ ዓመት አልፏቸው ከወላጆቻቸው ጥገኝነት ያልወጡ “ወጣቶች” ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ነው። እኔ በዚህ አጭር ጽሁፍ ውስጥ ስለወጣት ስናገር እድሜው በ 18 እና 39 ዓመታት መካከል ያለውን ዜጋ እያሰብኩ ነው።

የዘመናችን ወጣት

0,,17014545_404,00የዘመናችንን ወጣት የሚተቹ በርካታ ጽሁፎች የወጡ ቢሆንም እኔ ብዙዎቹ ትችቶች አግባብ መስለው አይታዩኝም። በአንድ በኩል ወጣቱ የማኅበረሰቡ አካል በመሆኑ በወጣቱ ውስጥ የሚታየው ክፉም ሆነ ደግ ከማኅበረሰቡ የወረሰው ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ነገሮች ሁሉ ወጣቱ ላይ ይጎላሉ። በሌላው ዓለም ያለው የመብቶች መከበር እና የኑሮ ሁኔታ ከራሱ እውነታ ጋር ሲያመዛዝን የአንዳንዱ ወጣት ልብ በረሀ ለማቋረጥ፣ ባህር ለመሻገር እንዲደፍር ያደርገዋል፤ የአንዳንዱ ወጣት ልብ ደግሞ የማዕከላዊ እስር ቤትና በውስጡ ያለውን ቶርቸር እንዳይፈራ ያፀናዋል። የዘመናችን ወጣት ሊወደስባቸው የሚገቡ በርካታ ነጥቦች ቢኖሩም የሚከተሉት ግንባር ቀደም ናቸው ብዬ አምናለሁ።

  1. የዘመናችን ወጣት ማሰብ ተከልክሎ ያደገ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ማሰብና መመራመርን የሚያበረታቱ ሁኔታዎች የሉም ማለት ሁኔታዉን አቅሎ መመልከት ይሆናል። ምርምር የሚጀምረው ከመጠራጠር ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ሥርዓቱ ትክክል ናቸው ያላቸውን ነገሮች መጠራጠር ወንጀል ነው። ኢትዮጵያዊ ወጣት “የምነግርህን ሳትጠራጠር አምነህ ተቀበል” ተብሎ ያደገ ነው። በዛሬቷ ኢትዮጵያ ውስጥ መረጃዎችን ማፈላለግ፣ ማንበብ፣ ማዳመጥ፣ ሀሳብ መለዋወጥ ወንጀል ነው። ወሳኝ በሆነ የፓለቲካና የፍልስፍና ጉዳዮች ላይ አቋም ይዞ መከራከር አይቻልም።  በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም የሚሰጠው ትምህርት እንደ ርዕዮተ ዓለም ቅስቀሳ ሁሉ “ያለቀለት እውነት” እንጂ ተማሪዎች በራሳቸው መንገድ ሊያረጋግጡት የሚገባ ጥሬ ሀሳብ ተደርጎ አይደለም። እንዲህ ዓይነቱ የአዕምሮ ውርጅብኝ የወረደበት ትውልድ ሆኖ እያለ ፈጽሞ  አለመደንዘዙ፤ ዛሬም በየእውቀት ዘርፉ ጎበዞች የሆኑ ወጣቶች መኖራቸው ድንቅ ነው። የዛሬ ወጣት አስተማሪም ትምህርት ቤትም ሳይኖረው – ያለ አስተማሪ እና ያለ ትምህርት ቤት – አሁን እደረሰበት ደረጃ ላይ መድረሱ ሊያስመሰግነው ይገባል።
  2. ከሰማንያ በመቶ በላይ የሆነው ወጣት ከኢህአዴግ ሌላ መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ ኖሮ አያውቅም። እድሜውን በሙሉ ኢህአዴግ እና መንግሥት አንድ ሆነው ነው ያደገው። ስለአገራዊ አንድነት ከሰማው ስለ “ብሔር”፣ “ብሔረሰቦች” የሰማው በእጅጉ ይበልጣል። የአሁኑ ወጣት የኢትዮጵያ ታሪክ ተብሎ እየተነገረው ያለው የቂምና የበቀል ታሪኮችን ነው። አንድ የሃያ አምስት ዓመት ወጣት ዛሬ ያሉት ክልሎች ከጥንት ጀምሮ የነበሩ ቢመስሉት እንኳን ልንፈርድበት አይገባም። ከሬድዮና ከጋዜጣ ብቻ ሳይሆን ከወላጆቹ ጭምር ሲሰማው የኖረው ይህንኑ ነው። ዘረኝነት መንግሥታዊ ፓሊሲ በሆነበት፤ “አዋቂ” የሚባሉት ታላላቆቹ ራሳቸው ዘረኞች አሊያም በፍርሀት ተሸብበው ዝምተኞች በሆኑት አገር አድጎ ኢትዮጵያዊነትን ፈጽሞ አለመርሳቱ ይህንን ትውልድ በእጅጉ ያስመሰግነዋል።
  3. የዛሬ ወጣቶች በተለምዶ “ያ ትውልድ” የሚባለው ትውልድ ልጆች ናቸው። “ያ ትውልድ” ደግሞ ብዙ አልሞ የትም ያልደረሰ፤ ሊያጠፋው ከተነሳው አውሬ የባሰ ጭራቅ – ህወሓትን – ያነገሰ ነው። የዛሬ ወጣት ወላጆች በወጣትነታቸው የነቃ የፓለቲካ ተሳትፎ የነበራቸው ሊሆን ይችላል፤  ምናልባትም ማርክሲስትና ሌኒኒስቶች ሆነው ለላብ አደራዊ ወይም ወዛደራዊ ዓለም ዓቀፋዊነት ሲታገሉ ኖረው ይሆናል፤ አሊያም ነፃ አውጭዎች የነበሩ ሊሆኑ ይችላሉ። እርግጥ እነሱ በጽናትና ቆራጥነት ታግለው ሊሆን ይችላል። ያንን ስሜትና ጽናት ግን ወደ ወጣቱ አላስተላለፉትም። እንዲያውም “እኛም በጊዜዓችን ሞክረን አልቻልነውም” እያሉ የአዲሱን ትውልድ ሀሞት የሚያፈሱ ሆነዋል።  እንደ “ያ ትውልድ” ሁሉ ዛሬም እስርና ግርፋትን የማይፈሩ ወጣቶች መኖራቸው የሚያስመሰግናቸው ነው። እንደ “ያ ትውልድ” አየር ላይ ለተንሳፈፈ ርዕዮተ ዓለም ሳይሆን ለራሳቸውና ለሀገራቸው ክብርና ነፃነት ሕይወታቸውን ለመስጠት የቆረጡ ወጣት ወንዶችና ሴቶችን ስናይ ተስፋችን ይለመልማል። እርግጥ ነው እንዲህ ዓይነት ወጣቶች ቁጥራቸው ጥቂት ነው፤ የታሪክን ቦይ የሚቀዱት ግን እነዚህ ጥቂቶች መሆናቸው ጥርጥር የለውም።
  4. ስለዛሬው ወጣት ምግባረ ብሉሽነት ብዙ ይወራል። እኔ ይህ ትክክል አይመስለኝም። የሥራ አጥ ብዛት እንደ አሁን የተስፋፋበት ጊዜ የለም።  ዘጠና በመቶ ያህሉ ሥራ አጥ በወጣትነት የእድሜ ክልል ያለ ነው። “ትምህርቱን ጨርሶ” የሙሉ ጊዜ ሥራ አጥ ሆኖ የተቀመጠ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የከተማ ወጣት አለ። ሥራ አጥነት ከኢኮኖሚ ችግርነቱ የባሰው ማኅበራዊ ችግርነቱ ነው። ሥራ አጥ ሆኖ ኃላፊነት የሚሰማው እና በማኅበረሰቡ የሚደመጥ ዜጋ መሆን ከባድ ነው። ሥራ አጡን ወጣት ወደ አጓጉል ልማዶች የሚስቡት ክሮች ብዙ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ስናይ ግን ሁኔታው በሚወራው መጠን ተስፋ አስቆራጭ አይደለም። ዛሬም ሥጋ ቤቶች በሽቦ አጥር አልታጠሩም፤ ወርቅ ቤቶች አርቲፊሻል ሳይሆን እውነተኛ ወርቅ በመስታወት ውስጥ ዘርግተው ይሸጣሉ፤ ብዙ ምግብ ቤቶች ዋጋ ሳይቀበሉ ያስተናግዳሉ። እነዚህ ነገሮች ስናስተውል የኢትዮጵያዊውን ወጣት ሥነምግባር ማድነቅ ይገባናል ብዬ አስባለሁ።
  5. በከተሞች ተቀጥሮ የመሥራት እድል እየጠበበ ከመምጣቱ በላይ ያች ጠባብ እድልም በህወሓትና አጫፋሪዎቹ መዳፍ ውስጥ ናት። ህወሓት እና አጋፋሪዎቹ እያንዳንዱን የሥራ እድል “ሰው መግዣቸው” ሆኗል። በመንግሥት ሥራ ለመቀጠር ከትምህርትና ሙያ ይበልጥ የኢህአዴግ አባልነት ወሳኝ መሆኑ አገር ያወቀው ሀቅ ነው። ወጣቶች የራሳቸውን የግል ሥራ የሚፈጥሩበት ሁኔታም የለም። ነፃ አስተሳሰብ፣ ነፃ የንግድና የፍትህ ተቋማት በሌሉበት ስለ “ኢንተርፕሪነርሺፕ“ መስበክ ባዶ ዲስኩር ነው። በአንድ በኩል የወጣቱ የፈጠራ ተነሳሽነት እንዲላሽቅ ተደርጓል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከመንግሥት ሥራ ያልተናነሰ የወያኔ ጥቃት በግሉ የሥራ ዘርፍ ውስጥም አለ። አፍቃሪ ወያኔ ያልሆኑ ነፃ ዜጎች የግል ቢዝነስ ቢጀምሩ እንኳ ሳንካዎች ይበዙባቸዋል፤ ሳንካዎችን ተቋቁመው አንገታቸውን ብቅ ካደረጉ በግብር እና በቫት ይኮረኩሟቸዋል፤ አቤቱታ ማሰሚያ ቦታ የለም።
በገጠር ያለውም ሀቅ ተመሳሳይ ነው።  የህወሓት የመሬት ፓሊሲ ግንባር ቀደም ሰለባ የሆነው የገጠር ወጣት ነው። መሬት ተሸንሽኖ አልቋል፤ ዛሬ ግማሽ ሄክታር መሬት ያለው ቤተሰብ ሀብታም ነው። በብዙ የአገራችን ክፍሎች ወጣት ገበሬዎች ከሩብ ሄክታር ያነሰ መሬት ይዘው ነው የራሳቸውን ትዳር የሚጀምሩት። ሩብ ሄክታር ለጓሮ አትክልት መትከያነት ቢሆን እንጂ ለሰብል አይበቃም። በአንፃሩ ደግሞ ግብርናንና ገበሬን የሚጠሉ “ኢንቬስተሮች” የሚይዙት መሬት የሚለካው በ10 ሺዎች ሄክታር ነው። ድሮ የማይታወቀው የገበሬ ሩቅ አገር መሰደድ አንዱ ምክንያት ይህ ነው። በገጠር ዘርን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች ከሚያባብሱ ነገሮች አንዱ ይህ የመሬት እጥረት ነው።
በገጠርም በከተማውም ያለው ሀቅ ይህ ሆኖ እያለ ዛሬም አገሩን ከልቡ የሚወድ ወጣት መኖሩ የሚገርም ነው።
  1. አብዛኛው አዲስ ስደተኛ፣ ወጣት ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ ስደተኛ ዓይነትና ስብጥር (demography) እና የስደተኛው  መዳረሻ አገሮች ተቀይረዋል። ወደ ደቡብ አፍሪቃ፣ ሱዳን እና አረብ አገሮች ያለው ስደት “ፍልሰት” በሚባል መጠን ነው። ወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች የማይታዩባቸው የገጠር መንደሮች ሞልተዋል፤ ወደ አረብ አገሮች አሊያም ደቡብ አፍሪቃና ሱዳን ነጉደዋል። አሜሪካ፣ አውሮፓና አውስትራሊያ የሚደርሰው ከስደተኛው ብዛት አንፃር ከቁጥር የማይገባው በጣም ትንሹ ነው። ታድያ በፓለቲካውም በኢኮኖሚውም ተደብድቦ፣ ተገፍቶ የወጣው ስደተኛ ወጣት ለአገሩ፣ ሕዝቡ፣ ባህሉና ታሪኩ ያለው ፍቅር የሚደንቅ ነው።
  2. የኢትዮጵያ ፓለቲካና ኢኮኖሚ አንድ መለያ ባህርይ “እጦት”  deprivation ነው። የፍትህ እጦት፣ የነፃነት እጦት፣ የመረጃ እጦት፣ የሚዛናዊ ትምህርት እጦት፣ የመሠረታዊ የጤና አገልግሎት እጦት፣ የመብራት ኃይል እጦት፣ የማገዶ እጦት፣ የመኖሪያ ቤት እጦት፣ የሥራ እድል እጦት፣ የኔት ዎርክ እጦት፣ የታክሲ እጦት፣ የእለት ጉርስ እጦት …. እጦት … እጦት  …  እጦት … ። ህወሓት እጦቶችን ተጠቅሞ ነው ወጣቱን እመዳፉ ውስጥ ለማስገባት እየጣረ ያለው።  (ህወሓት እና እጦት የረዥም ጊዜ ወዳጅነት እንዳላቸው የታወቀ  ነው፤ በድርቅ ለተጎዳው ሕዝብ በመጣ እርዳታ ራሱን ያደራጀ እጅግ ክፉና መሠሪ ድርጅት ነው) በእጦቶች የተጎዳ ሕዝብ ለእጦቶቹ ደረጃ ያወጣላቸዋል። መሠረታዊ እጦቶችን (ለምሳሌ የእለት ጉርስ፣ ኮንዶሚኒየም) ለማሟላት “ትላልቅ” እጦቶች (ለምሳሌ የፍትህና የመብት እጦቶችን) ይታገሳል።
0,,17658698_404,00አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ግን እጦቶችን በመሣሪያነት የሚጠቀም ፋሽስታዊ አገዛዝ ውስጥ አድገው እያለ ስለፍትህ፣ ስለነፃነት፣ ስለእኩልነት፣ ስለመብቶች የሚያሰላስሉ፣ የሚጽፉ፣ የሚታገሉ ብሩህ አዕምሮ ያላቸው ወጣቶች ያሉን መሆኑ መታደል ነው። ዛሬ ይህንን ማስታወሻ በምጽፍበት ወቅት በቃሊቲ፣ በቂሊንጦ፣ በዝዋይ እና በማይታወቁ በርካታ እስር ቤቶች ውስጥ በርካታ ወጣቶች ለፍትህ፣ ለሰብዓዊ ክብርና ነፃነት ዋጋ እየከፈሉ ነው።  እነሱን የመሰሉ በርካታ ወጣቶች ከእስር ቤቶች አጥሮች ውጭ በከተሞችም በገጠሮችም መኖራቸውን ሳስብ ደግሞ በዚህ ትውልድ ወጣቶች እኮራለሁ። ከዚህ አልፎ በእጦቶች መታሰር መሯቸው ወደ ተራራዎች ያቀኑ ወጣቶች መኖራቸው እና ቁጥራቸውም እያደር እየበዛ መሆኑ ስሰማ በዚህ ትውልድ ላይ መቅናት ያምረኛል።
  1. ኅብረት መፍጠር ቀላል የሚሆነው በቃላት ነው። “ተባበሩ” ብሎ መስበክ እና “እንዴት መተባበር አቃታችሁ” ብሎ መዝለፍ በጨለማ ሌሊት ወደ ሰማይ አንጋጦ ከዋክብትን የመቁጠር ያህል አዝናኝ ነው። መተባበር የትም አገር ቢሆን ከባድ ነው። እኛ አገር ደግሞ ይበልጥ ከባድ የሚያደርጉት ሁኔታዎች አሉ። (በነገራችን ላይ ህወሓት፣ ኢህአዴግ ላይ እንዳደረገው ዓይነት የአፈና ጥርነፋን “ኅብረት” ብለው የሚጠሩ ሰዎች አሉ) የመተባበር ችግራችን ዛሬ የተጀመረ አይደለም። መተባበር ያስቸገረን በፓለቲካው መስክ ብቻም አይደለም። ሌላው ቀርቶ ስለ ኅብረት ሲሰብኩ ውለው ሲሰብኩ የሚያድሩ የሃይማኖት አባቶችም እርስ በርሳቸው መተባበር አልቻሉም።
የመተባበር ችግር ለህወሓት ምቹ ሁኔታ ፈጥሮለታል፤ ልዩነቶችን እያራገበ፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ እየተሳለቀ ተዝናንቶ ይገዛል። ዉጣ ውረድ የበዛበት አስቸጋሪ መንገድ ቢሆንም እንኳን በዚህም ረገድ የተስፋ ጭላንጭል እየታየኝ ነው። ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ወጣቶች ወደ ፓለቲካ አመራር እየመጡ ነው። ከሰሜን፣ ከደቡብ፣ ከምሥራቅ፣ ከምዕራብና ከመሀል አገር የተወጣጡ ወጣቶች ለጋራ ኢትዮጵያ ሲሰለፉ፤ ያንንም ትግል በጋራ ሲመሩ ማየት የሚያኮራ ነው። የተለያዩ እምነቶች ተከታዮች የሆኑ ወጣቶች በፓለቲካ ድርጅት አመራርነት ተመርጠው በጋራ ሲሰሩ ማየት ተስፋ ሰጪ ነው። ለአንድ የጋራ ዓላማ ጉልበትን በማስተባበር ረገድ ብዙ ይቀረናል፤ ተግዳሮቶቹ በርካታ ናቸው፤ ያም ሆኖ ግን በወጣቱ በኩል እየታየው ያለው መናበብ ተስፋ ሰጭ ነው። የዛሬ ወጣት ውብ ኢትዮጵያን ከምናቦቻችን አውጥቶ በእውን ሊፈጥራት የታደለ ትውልድ ነው፤ ይህን ለማድረግ ደግሞ ብቃት አለው ብዬ አምናለሁ።

ቁጭት

ከላይ የዘረዘርኳቸው ስምንት መልካም ነገሮችን አዳብረናቸው፤ የወጣቱን ጉልበትና ተነሳሽነት በሚገባ ተጠቅመንበት ቢሆን ኖሮ እስካሁን የት በደረስን?
እነዚህን ስምንት አበረታች ነገሮች በሚገባ አሳድገናቸው ቢሆን ኖሮ:
  • ሰዎች ለመናገር፣ ለማንበብ፣ ለመስማት፣ ለመፃፍ የሚሸማቀቁበት አገር ዜጎች ባልሆንም ነበር፣
  • በራስ መተማመንን ያዳበሩ በርካታ ድንቅ የተፈጥሮና የማኅበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች፣ የፈጠራ ሰዎች በሕዝብ የተወደዱ ወጣት መሪዎች፣ በጥረታቸው የተሳካላቸው የቢዝነስ ሰዎች፣ … ወዘተ በኖሩን ነበር፣
  • ትምህርት፣ አዕምሮን ማደንቆሪያ መሆኑ ቀርቶ የምርምን አድማስን ማስፊያ፣ አዕምሮን ማበልፀጊያ እና ሙያ መቅሰሚያ ይሆን ነበር፣
  • ኢትዮጵያችን እንደአሁን የተማረው የሚሸሻት ሳይሆን የወጣው የሚመለስባት አገር ትሆን ነበር፣
  • የኢትዮጵያ ሕዝብ የህወሓት መጫወቻ፤ የአገሪቱ ሀብት ደግሞ የሹማምንቱ መድለቢያ ባልሆነ ነበር፣
  • የዘር ፓለቲካ መንግሥታዊ ፓሊሲ ሆኖ እርስ በርሳችን መግባባት እስከሚያቅተን ድረስ ለራሳችን ወንድሞችና እህቶች ባዕዶች ባልሆንም ነበር፣
  • ገበሬው ከማሳው ባልተፈናቀለ፤ በድህነት፣ በስደተኛና በእስረኛ ብዛት ብዛት ዓለምን መምራታችን ይቀርልን ነበር፣
  • በሀገራችንም በውጭ አገራትም ወጣቶቻችን አንገታቸውን ቀና፣ ደረታቸውን ነፋ አድርገው በሄዱ ነበር፤  እህቶቻችን በአረብ ጎረምሶች ከሚደርስባቸው ስቃይ በተገላገሉ ነበር፣
  • አገሪቱን የሚመሯት እኛው ፈልገንና ፈቅደን የመረጥናቸው፤ ካልተስማሙን የምንሽራቸው፤ የምናከብራቸው እንጂ የማንፈራቸው፤ በፓሊስና በወታደር የማያስደበድቡን “የኛ” የምንላቸው ሰዎች በሆኑ ነበር፣
  • ሌሎችም ብዙ መልካም ነገሮችን ባየን ነበር፣

ምልከታ

ባለፈው መቆጨት መልካም የሚሆነው ለወደፊቱ ምልከታ ሲያገለግል ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ አዎንታዊ ለውጥ በፍጥነት እንዲመጣ የወጣቱ ተሳትፎ አሁን ካለበት በጣም መጨመር ይኖርበታል። ይህን ማድረግ ደግሞ ይቻላል፤ ወጣቱ፣ አቅም፣ ችሎታውና ተነሳሽነቱ አለው። ወጣቱ በራሱና በአገሩ የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ አዎንታዊ ሚና  እንዲኖረው በራሱ ላይ ያለውን መተማመን ማዳበር ይኖርበታል፤ አፈናን በሚሰብር መልኩ ራሱን ማደራጀት ይጠበቅበታል። እንዲህ በተጠና መንገድ የሚንቀሳቀስ ከሆነ ትናንንሽ የሚመስሉ ጥረቶች ተብላልተው ትልቅ ሕዝባዊ ማዕበልን መፍጠር ይችላሉ።  ይህንን ትግል አሁን በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ በተለያዩ ስልቶች በሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ድርጅቶች ውስጥ በአመራር ጭምር በመሳተፍ ሊደረግ ይችላል። ይህ በማይመችበት ጊዜ ደግሞ የተለያዩ የአደረጃጀት ስልቶችን መጠቀም ይገባል።
የኢትዮጵያ ወጣት ሁሉ አንድ ዓይነት አመለካከት ወይም የተቀራረበ አመለካከት ይኖረዋል የሚል ብዥታ የለብኝም። ሆኖም ግን ከዚህ በታች ያለው ጽሁፍ የሚያተኩረው ተስፋው በህወሓት የተነጠቀው አብዛኛውን ወጣት እያሰብኩ ነው።
የኢትዮጵያ ወጣትን ትግል ለማገዝ ሶስቱ የመዳረሻ (tipping point) ህግጋትን በሚገባ መረዳት እና በሥራ ላይ ማዋል ይጠቅማል ብዬ አምናለሁ። ሶስቱ የመዳረሻዎች ህግጋት (1) የአናሳዎች ህግ  (Law of the Few)፣  (2) መጣበቅ (Stickiness Factor) እና (3) የሁኔታዎች ህግ (The Law of Context) ናቸው።
  1. የአናሳዎች ህግ፣ በሚገባ የተደራጁ ጥቂት ሰዎች ትልቅ ሕዝባዊ ማዕበልን ማስነሳት ይችላሉ የሚለው መርህ ነው። ይህ በማኔጅመንት ውስጥ “መርህ 80/20” (The 80/20 Principle) ከሚባለው ጋር ይዛመዳል። ለምሳሌ በ 20% ጥረት 80% ውጤት እንደሚገኘው ማለት ነው። በአንድ የሥራ ቦታ 100 ሠራተኞች ቢኖሩ አብዛኛውን ጊዜ 80% ያህሉ የሥራ ሸክምና ኃላፊነት የሚወድቀው ከ 20 ባልበለጡ ሠራተኞች ላይ ነው። እነዚህ 20 ለይቶ ማወቅ፣ መሸለም፣ ማሰልጠንና ማበረታታት የጥሩ ማኔጀር ሥራ ነው። በማኅበራዊ ንቅናቄዎችም እንደዚሁ ነው። ጥቂቶች ናቸው ወሳኙን ሥራ የሚሰሩት – ወሳኝ ጥቂት ሰዎች (the vital few).

ከእነዚህ ጥቂት ሰዎች መካከል በወጣቱና በማኅበረሰቡ ተሰሚነት ያገኙ፤ ሲናገሩ የሚደመጡ፤ ንቅናቄውን ወደ በጎ ነገር ይመሩታል ብለው ተከታዮቻቸው እምነት የሚጥሉባቸው “አውራዎች”  ወይም የኔታዎች (Mavens) ያስፈልጋሉ። በእድሜ ከወጣትነት የዘለሉ ዜጎች አንዱ ገንቢ ሚና ይህንን ቦታ መሙላት ነው። ሌላው እጅግ አስፈላጊ ነገር የግኑኝነት መረብ (Network) መዘርጋት ነው። እያንዳንዱ የትግሉ ተሳታፊ ከበርካታ ሰዎች ጋር በመገናኘት አድማሱን ማስፋት ይገባል። ግኑኝነት ለመፍጠር ወጣቱ የሚወዳቸውንና የሚያዘወትርባቸው መስኮች ማወቅና አክብሮት ለሚገባቸው አክብሮት መስጠት ያስፈልጋል። ስፓርት፣ ኪነ ጥበብ፣ የእምነት ተቋማት፣ ት/ቤቶች …  ሊዳሰሱ ይገባል። አንዳንድ ወጣቶች በተፈጥሮዓቸው ብዙ ኔትዎርክ አላቸው። እንዲህ ዓይነቶቹን ወጣቶች የንቅናቄው አካል ማድረግ በጣም ጠቃሚ ነው፤ ያለ ብዙ ድካም ወጣቱን የማገናኘቱን ሥራ ያቀላጥፉታል። በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ የቀስቃሾች መኖር እጅግ አስፈላጊ ነው። ቀስቃሾች ንግግርን፣ ሙዚቃን፣ ስዕልን … ወዘተ በመጠቀም ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ ሕዝብን በአንድ መስመር ውስጥ ማስገባት ዋነኛው ሥራቸው መሆን ይኖርበታል።

“መሰብሰብ ወንጀል በሆነበት አገር እነዚህ ‘ጥቂቶች’ እንዴት ይገናኛሉ? እንዴትስ ይደራጃሉ?” የሚል ጥያቄ እንደሚነሳ እገምታለሁ። ስለወጣት ድርጅቶች ስናስብ በሃሳባችን መምጣት ያለባቸው አባላትን መዝግበው፣ መዋቅር አዘጋጅተው ተመዝግበውም ሆነ ሳይመዘገቡ የሚሠሩ መደበኛ ድርጅቶችን ብቻ አይደለም። አፈና በበዛበት ሥርዓት ውስጥ ኢመደበኛ ድርጅቶች (informal organisations) ከመደበኛዎቹ የተሻለ ሊያገለግሉ ይችላሉ። የስፓርት ቡድን ደጋፊዎች፣ የመፃህፍት አፍቃሪያን ስብስቦች፣ የአገርህን እወቅ ክበባት፣ የአካባቢ ጥበቃ ማኅበራት፣ የቴኳንዶና ማርሻል አርት ክበባት፣ የሙዚቃ ክበባት፣ የማርያም፣ የሥላሴ፣ የገብሬል … ጽዋ ማኅበራት፣ ደብተሮች፣ እርሳስና እስክሪብቶዎችን ለድሆች ተማሪዎች አሰባሳቢ ክበባት፣ በረንዳ አዳሪዎችን አልባሽ ማኅበራት፣ እቁቦችና ትናንሽ እድሮች እና የመሳሰሉት ሁሉ የመደበኛ የወጣት ድርጅት ምትክ ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ።

  1. መጣበቅ (Stickiness Factor)፤ ይህ ህግ የመልዕክቱ ይዘትና አቀራረብን የሚመለከት ነው። መልዕክቱ በቀላሉ መዳረስ ብቻ ሳይሆን ከተቀባዩ ጋር “መጣበቅ”  አለበት።  መልዕክት በብዛት ቢዳረስም ሆነ በተከበሩ ሰዎች አንደበት ቢነገርም እንኳን አድማጩ አዕምሮ ውስጥ የማይቀር ከሆነ ማዕበል የማስነሳት አቅም አይኖረውም። የመልዕክቱ ይዘት ደግሞ ቀላልና ግልጽ ብቻ ሳይሆን ወደሌሎች  ለማዳረስም የሚያጓጓ መሆን ይኖርበታል።

ወጣቱ የትግሉን ግብ በግልጽ ቢያስቀምጥ ይጠቅማል ባይ ነኝ። መልዕክቶች አጭርና ቀላል ሆነው ወደ ተግባር የሚመሩ መሆን ይኖርባቸዋል። ለምሳሌ የወጣቱ እንቅስቃሴ ዓላማ በሚከተለው አኳኋን በአጭሩ ማቅረብ ይቻላል።

ህወሓት በሕዝባዊ እምቢተኝነትና አመጽ ይወገዳል፤ ሰፊ ውክልና ያለው የሽግግር መንግሥት ይመሠረታል። የዜጎች፣ የሃይማኖቶች፣ የብሄር/ብሄረሰቦች፣ የቋንቋዎች እኩልነት ይከበራል፤ ገለልተኛ ተቋማት ተመሥርተው በሁሉም እርከኖች የመንግሥት ሥልጣን በነፃ የሕዝብ ምርጫ ይወሰናል። አዲሱ ሥርዓት ለሁላችንም የሚበጅ ስለሆነ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎናችን ይቁም። በተለይ የመከላከያ ሠራዊትና ፓሊስ ከሕዝብ ጋር ወግኑ፤ የኢህአዴግ አባላትም በሕዝብ ጎን በመቆም ታሪክ ስሩ።

መልዕክቶችን በምስል፣ በተረት፣ በምሳሌ፣ በቀልድ ወዘተ ማስተላለፍ መለመድ ይኖርበታል። !!

  1. የሁኔታዎች ህግ (The Law of Context)፤ አካባቢያዊ ሁኔታዎች በእንቅስቃሴዎቻችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ  እንዳላቸው ማመን ተገቢ ነው። የትግል ስትራቴጂና ስልት በአብዛኛው የሚወሰኑት በሁኔታዎች ነው። እኛ በሁኔታዎች ላይ ሙሉ ቁጥጥር የለንም። በዚህም ምክንያት ከአንድ ዓይነት የትግል ስልት ጋር “መቁረብ” በጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ወጣት መሪዎች ሁኔታዎችን እያጠኑ ተስማሚ ስትራቴጂዎችንና ስልቶችን መቀየስ መልመድ ይኖርባቸዋል። በአንዱ ቦታ የሠራው በሌላ ቦታ ላይሰራ እንደሚችል፤ የነጠረ፣ ብቸኛ የሚባል ስትራቴጂ እንደሌለ መገንዘብ ይጠቅማል።

አጣዳፊ ሥራዎች

ሁሉንም  ሥራዎች በአንድ ጊዜ  መፈፀም የማንችል በመሆኑ  ቅደም ተከተል ማውጣት ግድ ነው። በኔ ግምት አሁን የለውጥ ዋዜማ ውስጥ እንገኛለን። በዚህ ወቅት በስፋት መሠራት ያለባቸው ሁለት ነገሮች ወጣቶችን ማንቃትና ለለውጥ ማዘጋጀት እና ኔትዎርኮችን ማስፋት ናቸው። በሌላ አነጋገር መቀስቀስ እና ማደራጀት የወቅቱ ሁለት አጣዳፊ ሥራዎች ናቸው።

ወጣቱን ለመቅስቀስ ያሉት የመቀስቀሻ መሣሪያዎችን ሁሉ – ቴሌቪዥን፣ ሬድቶ፣ ጋዜጣ፣ ማኅበራዊ ሚዲያዎች፣ በራሪ ጽሁፎች፣ ስብሰባዎች፣ የሰው ከሰው ንግግሮች እና ሌሎችም መንገዶች ሁሉ መጠቀም አለብን። ለማደራጀት ደግሞ  ከላይ እንደተገለፀው መደበኛ ድርጅቶችን ብቻ ሳይሆን ኢመደበኛ ድርጅቶችን መጠቀም መልመድ አለብን።

“ከኦሮሚያ አንፃር፤ ከኢሕዴአግ ደርግ ይሻላል” – ዶ/ር መረራ ጉዲና

ዶ/ር መረራ ጉዲና በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፍ ላይ ምርጫ 97 እና ምርጫ 2002 በተመለከተ የራሳቸውን ግምገማ ማስፈራቸው የሚታወቅ ነው። ካሰፈሩት ነጥቦች እና መደምደሚያዎች አንፃር ቀጣዩን ምርጫ 2007 እንዴት ይመለከቱታል? ገዢው ፓርቲ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በተመለከተ ምንስ ይላሉ? የኦሮሞ ሕዝብ ትግልን በተመለከተ ምን ይላሉ? ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኃይል አሰላፍ አንፃር የኦሮሞን ሕዝብ የፖለቲካ ሂደት እንዴት ይገልጽታል? የቀኝ ኃይሎች የፖለቲካ አካሄድን እንዴት ይረዱታል? እና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን በማንሳት ተወያይተwል። ከዶ/ር መረራ ጉዲና ጋር ፋኑኤል ክንፉ ያካሄደው ቃለ-ምልልስ እንደሚከተለው ቀርቧል።
merara_gudina_vtim
ሰንደቅ፡-የኢትዮጵያን ምርጫ ሂደት “ምርጫ” እና “ቅርጫ” በሚል አባባል ሲገልፁ ይሰማል። ምን ለማለት ፈልገው ነው?
ዶ/ር መረራ፡-በሀገራችን በበዓላት የቅርጫ ሥጋ የመካፈል ባህል አለ። ቅርጫ ሲካፈል ሁሉም እንደ አቅሙ ይወስዳል። ትልቅ ብር የከፈለ ትልቅ ይወስዳል። ትንሽ ብር የከፈለ በከፈለው መጠን ድርሻውን ያነሳል። በኢትዮጵያ ምርጫ ግን አንድ ጎበዝ ሁሉንም ጠቅልሎ ይወስዳል። ይህን የተዛባ ሁኔታ ለመግለጽ ነው፤ ምርጫ እና ቅርጫ በሚል ለመግለጽ የፈለኩት።
ሰንደቅ፡- በመጽሐፍዎ፤ “በአፍሪካ ሀገር የመንግስት ጥያቄ የአቅም ጥያቄ ነው” በማለት ጽፈዋል። ፅንሰ ሃሳቡ ምንድን ነው?
ዶ/ር መረራ፡-አቅም ሲባል፣ ወታደራዊና ድርጅታዊ አቅም ነው። በተለይ ወታደራዊ አቅም። በአፍሪካ ወታደራዊ አቅም እስከሌለህ ድረስ በሕዝብ ድጋፍ ብቻ የመንግስት ስልጣን አታገኝም። ስልጣን ላይ አትወጣም። በተለይ ተቃዋሚ ከሆንክ ከእስር ቤት ወይም ከስደት አታመልጥም።
ሰንደቅ፡- ይህ የእርስዎ መሰረታዊ አስተሳሰብ ከሆነ፣ በ1997 ዓ.ም፣ በ2002 ዓ.ም አሁን ደግሞ በ2007 ዓ.ም ምርጫ መሳተፍ ለምን አስፈለጋችሁ? የፖለቲካ መጫወቻ ክፍት ቦታ እናገኛለን የሚልስ መነሻ እንዴት አገኛችሁ?
ዶ/ር መረራ፡-የምርጫ ፓርቲዎች በመሆናችን በምርጫው ገፍተናል። ወታደራዊ አቅምም ስለሌለን ከምርጫ ውጪ አማራጭ የለንም። ወደ ምርጫ የገባነው በጠቀስኳቸው ምክንያቶች እንጂ የፖለቲካ መጫወቻ ክፍተት እናገኛለን ከሚል መነሻ አይደለም።
ሰንደቅ፡- በመፅሐፍዎ ላይ፣ በምርጫ 97 እና በምርጫ 2002 የተቃዋሚውን ጐራ ያልሰራቸው የቤት ስራዎች መኖራቸውን አስፍረዋል። በተለይ የተቃዋሚው ጐራ በትብብር አንድ መሆኑንና ጠንካራ አደረጃጀት አለመያዙ ያስከፈለውን ዋጋ አንስተዋል። አሁንስ በ2007 ዓ.ም ምርጫ የተቃዋሚው ጐራ ይህን ስህተት አርሟል?
ዶ/ር መረራ፡- የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ያላለፉት የታሪክ ፈተና፣ ማሸነፍ ያልቻሉት የታሪክ ፈተና በተለይም ተባብሮ የመስራት፣ አቅም ገንብቶ የመስራት፣ ልዩነቶችን አቻችሎ አብሮ የመስራት፣ ተባብሮ ገዢውን ፓርቲ የመግፋት ፖለቲካው አሁንም ድረስ ያላለፉት ታሪክ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል። አሁንም አላለፍነውም። እንደውም ከ97 ጋር ሲተያይ ደከም ብለን የምንታይበት ሁኔታ ነው ያለው።
ስለዚህም ከአሁን ጀምሮ የተቃዋሚው ኃይሎች ቁጭ ብለው አሰላስለው ያለንበትን ሁኔታ መመልከት ተገቢ ነው። በተለይ ትግሉ ወደ ፊት እንዲገፋ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ይህን የታሪክ ፈተና ለማለፍ በምንችልበት አቅጣጫ መንቀሳቀስ አለብን። ይህን የታሪክ ፈተና ማለፍ ካልቻልን የትም መድረስ አንችልም። ኢትዮጵያም የትም መሄድ አትችልም። እየተቋሰሉ፣ እየተጣሉ፣ እየተጠላለፉ በተተበተበ ፖለቲካ ውስጥ እየዋዠቁ መኖር፣ ለራሳችንም ሆነ ለሀገራችን የተሻለ ስራ እየሰራን እንዳልሆነ ይሰማኛል። የበለጠ ወደ ኋላ ቀርተናል።
ሰንደቅ፡- በመጽሐፍዎ በቀኝ ኃይሎች መቸገርዎን አስፍረዋል። እንደሚታወቀው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ም/ቤት ከመድረክ ጋር ያለውን ግንኙነት በገመገመበት ወቅት በብሔር ከተደራጁ ኃይሎች ጋር ለመስራት እንደማይችሉ ከስምምነት መድረሳቸው መዘገቡ ይታወቃል። ከዚህ አንፃር አሁንስ መድረክ ከቀኝ ኃይሎች ጋር ያለው ልዩነት እንደቀጠለ አድርገን መውሰድ እንችላለን ወይ?
ዶ/ር መረራ፡- አንድነት ውስጥ ያሉም ሌሎች በተቃዋሚ ጐራ ያሉ ጓደኞቼን ለመምከር ሞክሬአለሁ። ወደፊት ለመሄድ፣ ወንዝ ለሚያሻግር ፖለቲካ ለመስራት፣ የታሪክ ፈተናን ለማለፍ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች፣ የዴሞክራሲ ኃይሎች ነን የሚሉት ተባብረው ካልሰሩ፣ አቅም ገንብተው ካልሰሩ፣ የመቻቻል ፖለቲካ እስካልፈጠሩ ድረስ ለብቻቸው የትም አይደርሱም። ይህ በግልጽ መቀመጥ ያለበት ጉዳይ ነው። ከዚህ ውጪ ትርፉ ልፋት ብቻ ነው።
merera_gudina
ተባብረው ካልታገሉ አንድም ገዢውን ፓርቲ አስገድደው ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲቀበል ማስገደድ አይችሉም። ገዢው ፓርቲ እንኳን በድንገት ከስልጣን ላይ ቢወርድ የተረጋጋች ኢትዮጵያን ለመምራት የሚችሉበት ሁኔታ አይፈጠርም። ኢትዮጵያን ለሚቀጥሉት ሰላሳ ዓመታት አንድ ፓርቲ ለብቻው እገዛለሁ፣ አስተዳድራለሁ የሚለው ነገር ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ላይ ማብቃት አለበት። ኢሕአዴግ ሚሊዮን ሰራዊት ይዞ፣ የሀገሪቷን ሃብት ተቆጣጥሮ ሁሉንም ነገር ይዞ፣ ኢትዮጵያን በፈለገበት መንገድ መግዛት አልቻለም። ሃያ ሦስት ዓመት ለፋ እንጂ በሕዝብ ፈቃድ በተፈለገው መንገድ ማስተዳደር አልቻለም። ለሰላምና መረጋጋት በሚል ከፍተኛ የሀገሪቷ ሐብትም እየባከነ ነው የሚገኘው።
ከዚህ መለስ ያሉ ፓርቲዎች ደግሞ የሕልም ጉዞ ከመጓዝ ውጪ ኢሕአዴግ ከስልጣን አውርዶ የተሻለች ኢትዮጵያን፣ የተረጋጋች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ከተፈለገ የግድ ተቃዋሚዎች ተባብረው መስራት አለባቸው። ልዩነቶችን አቻችለው ከወዲሁ የሞኝ ጉዞአቸውን አቁመው የተደቀነባቸውን የታሪክ ፈተና ለማለፍ መስራት አለባቸው። ይህን ማድረግ ካልቻሉ የትም አይደርሱም። ከዚህ ውጪ ያለው መንገድ አላስፈላጊ ሐብታችንን፣ ገንዘባችን እውቀታችንን ለማባከን ነው የሚሆነው። ተቃዋሚው ኃይል ከገቡበት የታሪክ እስር ቤት ሰብረው መውጣት አለባቸው። የዛሬ አርባ አመት ያልቻልነው ይሄንኑ ነው። ዛሬም ያልቻልነው ይህኑኑ ነው። ያ ቡድን… ይህ ቡድን… ነፃ ያወጣል የሚባለውን የሕልም ጉዞ መብቃት አለበት። በተባበረ ትግል ያልተመራ ተቃውሞ መጨረሻው፣ ሁሉንም ነገር በገዢው ፓርቲ በጎ ፈቃድ የሚወሰን ነው የሚሆነው። ይህን በግልፅ ማስቀመጥ ያስፈልጋል። በመጪው ምርጫ መታረም አለበት።
ሰንደቅ፡- የአረቡ ዓለም የፀደይ አብዮት ወደ ኢትዮጵያ ቢመጣም ሰፊ መሰረት ያለው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እስካልተዘረጋ ድረስ የፈለግነው ውጤት ላይ አያደርሰንም ብለዋል። ለዚህ መከራከሪያዎ የሚያነሱት ኀሳብ ምንድን ናቸው?
ዶ/ር መረራ፡- በግልፅ እየታየ ያለ ነገር ነው። ወደግራ፣ ወደቀኝ፣ ወደጎን፣ ወደላይ እየተሄደ ነው። ይህ የገመድ ጉተታ ፖለቲካም ኢሕአዴግ የልብ ልብ እየሰጠው ነው፤ በአላስፈላጊ መንገድም እንዲሄድ እያደረገው ነው፤ ራሳቸውንም ተቃዋሚዎቹን ገመድ ጉተታ ውስጥ ከቷቸዋል። ይህን የመሰለ የፖለቲካ ክፍተት ቀዳዳው ካልተሸፈነ ምንም አይነት ለውጥ ቢመጣ የትም መሄድ አይቻልም። ቀዳዳዎችን ደፍኖ ወደ አንድ መስመር መምጣት ከተቻለ መንግስትንም መለወጥ ይቻላል።
ዴሞክራሲ የሚባለው ብሔራዊ መግባባት መፍጠር ሲቻል ብቻ ነው። ሀገራችን እንዴት ትመራ? ምን አይነት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ያስፈልገናል? የፖለቲካ መቻቻል የብሔር ብሔረሰቦች መብት? የፌደራሊዝም አይነት? ቁጭ ተብሎ መነጋገር ስትችል ነው። ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ማንኛውም አይነት ለውጥ ቢመጣ ወደተፈለገው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት አንደርስም። ለውጥ ቢከሰት የተለመደው የገመድ ጉተታ ፖለቲካ መከሰቱ አይቀሬ ነው። ለዚህ ጥሩ ማሳያ የግብፅ የፀደይ አብዮት ነው። ስልጣን ላይ ያለውን መንግስት አወረዱ፤ ቢያንስ እስከ ማውረድ ተስማምተው ነበር። በዚህ መልኩ ከእኛ ይሻላሉ።
ከለውጡ በኋላ ግን እያየን ያለነው የሙባረክ ወታደሮች ናቸው፤ ሃገር እየገዙ ያለው። ይባስ ብለው ሙባረክን ነፃ አውጥተው ለለውጥ የተነሱ ኃይሎችን እየገደሉ፣ እያሰሩ ይገኛሉ። ለዚህ ምክንያቱ የለውጥ ኃይሉ ሙባረክን እስከማውረድ እንጂ ቀጣይ የግብፅ መንግስት እና ሕዝብ እንዴት መመራት እንዳለባቸው የደረሱበት ስምምነት አልነበረም። የለውጡ ኃይል ብሔራዊ መግባባት አልነበረውም። በተመሳሳይ መልኩ በዚህም ሀገር ተመሳሳይ ለውጥ ቢከሰት ኢሕአዴግን ከማውረድ በዘለለ የተደረሰ ብሔራዊ መግባባት ባለመኖሩ ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ ሊከስት የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። እንደው ጠዋት እና ማታ አንድነት፣ አንድነት ስለተባለ ብቻ ቀውስ ማቆም አይቻልም። የወደፊቷ ኢትዮጵያ ምን መምሰል እንዳለባት አሁን ላይ ነው ምላሽ መስጠት ያለባቸው፣ አሁን ላይ ነው መግባባት መተባበር የሚያስፈልገው። ቢያንስ ምን አይነት የፖለቲካ ስርዓት ያስፈልጋል? ምን አይነት ፌደራሊዝም ያስፈልጋል? የሁሉም አስተዋፅኦ ምን መሆን አለበት? ለዚህም ነው ኢሕአዴግ ተገፍቶ እንኳን ከስልጣን ቢወርድ ይህን ታሪካዊ ፈተና እስካላለፍን ድረስ የተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓት መፍጠር አንችልም የሚለውን መናገር እፈልጋለሁ። ፖለቲካ እስከገባኝ ድረስ ለውጥ ውስጥ ያሉ ኃይሎችም እንዲረዱኝ የምፈልገው ይህንኑ እውነት ነው።
እንደተባለው አንዳንድ የፖለቲካ ኃይሎች ከዚህ ቡድን ጋር፣ ከዛ ቡድን ጋር አልሰራም አሉ ነው የተባለው። ከመስራት ውጪ ምንም አማራጭ የላቸውም። ሌላው አማራጫቸው ኢትዮጵያን ማጥፋት ብቻ ነው። እድልም ቢገጥማቸው እና ወደስልጣን ቢጠጉ ኢትዮጵያን ቢያጠፉ እንጂ ከሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች ጋር ተባብረው በመሀል መንገድ ላይ ካልተገናኙ በስተቀር ኢትዮጵያን የትም አይወስዷትም። ለምሳሌ ከእኛ አይነት የፖለቲካ ኃይል ጋር ካልሰሩ፣ ከነፃ አውጪ ድርጅቶች ጋር ምን ሊሆኑ ነው? ከኦነግ፣ ከኦብነግ፣ ከጋምቤላ ነፃ አውጪ ግንባሮች ጋር ምን ሊያደርጉ ነው? ስለዚህም መሬት ላይ ያለውን የኃይል አሰላለፍ ምንድን ነው ብሎ መፈተሸ ተገቢ ነው የሚሆነው። ከዚህ ውጪ ለመብታቸው የሚታገሉትን ጡረታ ለማስወጣት ከሆነ መጀመሪያ ጉልበቱ እንዳላቸው ማረጋገጥ ነው። ጉልበት እንኳን ቢኖራቸው ደርግ የኤርትራን ጥያቄ ገፍቶ ገፍቶ አሁን ወደላበት ደረጃ እንዳደረሰው ሁሉ፤ እነዚህም የቀረችውን ኢትዮጵያ ገፍተው ለሁላችን የማትሆነውን ኢትዮጵያ ለመፍጠር ካልሆነ በስተቀር ሌላ ነገር ያላቸው አይመስለኝም። ለዚህም ነው የመተባበር፣ ሰጥቶ የመቀበል፣ የመቻቻል ፖለቲካ ውስጥ መግባት ካልተቻለ ቢያንስ ቢያንስ ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን አናገኛትም። ምን አልባትም ከዚህ የበለጠ አደጋ ሊመጣ ይችላል። ኢትዮጵያን የሚበታትን አደጋም ሊፈጠር ይችላል።
Dr merera gudina Book
ሰንደቅ፡- በመፅሐፍዎ መደምደሚያ ሶስት ምክረ ኀሳብና ወቀሳ አስቀምጠዋል። ከእነዚህ ውስጥ “የትግራይ ሊሂቃን ስልጣን ወይም ሞት የሙጥኝ” ብለዋል የሚለው አንዱ ነው። ለዚህ አገላለፅዖ ማሳያው ምንድን ነው?
ዶ/ር መረራ፡- በግልፅ ነው የሚታየው። የኢትዮጵያን ዋና የስልጣን መዘውር የያዙት እነሱ ናቸው። በየትኛውም ሁኔታ ብትወስደው በበላይነት እነሱ ናቸው የሚመሩት።
ሰንደቅ፡- የኢትዮጵያን መንግስት የሚመራው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ነው። በዚህ ምክር ቤት ውስጥ እርስዎ ከሚሏቸው የትግራይ ሊሂቃን ከሶስት አይበልጡም። ከዚህ አንፃር ድምዳሜዎትን እንዴት ያዩታል?
ዶ/ር መረራ፡- ብዙ ዝርዝር ውስጥ ሳልገባ ቁልፍ ስልጣንም ያላቸው፣ የመወሰንም ስልጣን ያላቸው ተቋማቱንም የሚያንቀሳቅሱት የሚያስወስኑትም በዋናነት ከትግራይ የመጡ ሊሂቃን ናቸው ለማለት ነው።
ሰንደቅ፡- የአማራው ሊሂቃን አሁንም ድረስ “ከበላይነት አስተሳሰባቸው መላቀቅ አልቻሉም” ብለዋል። ከአማራው ሕዝብ የወጡ ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን በዚህ አገላለጽዎ እንዴት ያስተናግዷቸዋል?
ዶ/ር መረራ፡- የአማራ ሕዝብ ትላንትም ዛሬም ሲጨቆን አውቃለሁ። እዚህ ላይ ጠብ የለኝም። ዋናው ጉዳይ እኔ ፖለቲካ እስከገባኝ ድረስ የአማራ ሊሂቃን የበላይነት አስተሳሰቡ አለቀቀውም። ከሌሎች ኃይሎች ጋር ብሔራዊ መግባባት ፈጥሮ እናንተም እንዲህ ሁኑ እኛም መሐል መንገድ ላይ እንመጣለን ብሎ በጋራ ለመስራት እና ልዩነቶችን መሃከል ላይ አድርሶ የመታገል ፍላጎት አላይባቸውም። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በጎሳ የተደራጁ በምን የተደራጁ ቡድኖች ጋር አንሰራም የሚለው የአማራው ሊሂቃን አስተሳሰብ፣ ከማን ጋር ሊሰሩ ነው? ስለዚህም የዛሬይቱን ኢትዮጵያ ተቀብሎ በጋራ መስራት ነው የሚያስፈልገው። እኔ በግሌ ሂሳብ የማወራረድ ፖለቲካ አልፈልግም። ሆኖም ግን አንድ የተወሰነ ማሕበረሰብ ተበድያለሁ ሲል አልተበደልክም የሚል ድርቅ ያለ መከራከሪያ ከማንሳት ቢያንስ ወደፊት ማንም የማይበደልበት ሀገር እንግባ ማለት የተሻለ ነው የሚሆነው። አዲስቷን ኢትዮጵያ ለመፍጠር መስራት ነው የሚጠበቅባቸው።
ሰንደቅ፡- የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ውስጥ ያሉ የአማራ ሊሂቃን የአማራ ሕዝብ እንደማንም የተጨቆነ፣ ኋላ የቀረ ሕዝብ መሆኑን ተረድተው ከሌሎች ብሔሮች ጋር ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለመገንባት እየታገሉ እንደሚገኙ የድርጅታቸውም ሰነድ ሆነ ሊሂቃኑ በአደባባይ የሚናገሩት ነው። የአማራ የበላይነት መጠበቅ አለበት ሲሉም አይደመጡም። ከዚህ አንፃር ድምዳሜዎ ሁሉኑም የአማራ ሊሂቃን ማጠቃለሉን እንዴት ያዩታል? ብአዴን እየተጠቀመ ያለውን የፖለቲካ መጨወቻ ሜዳስ (political space) እንዴት ይገልጽታል?
ዶ/ር መረራ፡- ብአዴን የሚሰራው በዚህች ሀገር ውስጥ የበለጠ ችግር የሚፈጥር ነው። ምክንያቱም የሚያስፈጽሙት የኢሕአዴግ ፖሊሲዎችን ነው።
ሰንደቅ፡- ኢሕአዴግ ከመሰረቱት ፓርቲዎች አንዱ ብአዴን ነው። ስለዚህም ራሱ የተሳተፈበትን ፖሊሲ ማስፈጸሙ እንዴት ጉዳት ይሆናል?
ዶ/ር መረራ፡- ብአዴን ትንሽ ከኦህዴድ ይሻል ይሆናል እንጂ የተለየ ሚና የላቸውም። ከዚህ ውጪ የአንድ መንግስት አስፈፃሚዎች ናቸው። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ከዚህ የዘለለ ሚና የላቸውም።
ሰንደቅ፡- እርስዎ ካስቀመጡት መደምደሚያ መነሻነት ወስደን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ለውጦች አሉ። በማሕበራዊም በፖለቲካውም አንፃራዊ ለውጦች አሉ። በብቸኛ መንግስትነት ያስቀመጡዋቸው “የትግራይ ሊሂቃን” እነዚህን ተግባሮች በዚህች ሀገር ውስጥ መፈጸማቸው ከምን መነሻ የመጣ ነው? በእርስዎ አረዳድ የትግራይ ሊሂቃን በኢትዮጵያ ውስጥ የተለየ ተልዕኮ ወይም ራዕይ አላቸው ብለው ያስባሉ?
ዶ/ር መረራ፡- ብዙ ዝርዝር ውስጥ ሳልገባ እነዚህ ኃይሎች በሀገሪቷ ውስጥ ብሔራዊ መግባባት ካልፈጠሩ፣ ሀገሪቷን ወደ ብሔራዊ ዕርቅ ካልመሩ፣ ሀገሪቷን ወደ ብሔራዊ ስምምነት ካልመሩ መጪው ጊዜ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብሩህ ነው የሚል ግምት የለኝም።
ሰንደቅ፡- ገዢው ፓርቲ ብሔራዊ ዕርቅ ጉዳይ ሲነሳ የተለያዩ የፖለቲካ አስተሳሰቦችን ከማስታረቅ ጋር መያያዝ የለበትም። በፖለቲካ መስመርም የተጣላ የለም የሚል መከራከሪያ ያነሳል። በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
ዶ/ር መረራ፡- እንደዚህ እያሉን ኢሕአዴግ እንዲሁም በበላይነት የሚመራው ህወሓት ተጣልተው አገኘናቸው። ለምሳሌ ሕወሃት ብትወስድ አንዱን ጎኑ በልቶ ነው ስልጣን ላይ ያለው፣ የቆየው። እነአቶ ተወልደ የመለስ ሁለተኛ ሰው ነበሩ። አቶ ስዬ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ነበር። አቶ ገብሩ አስራት የትግራይ መስተዳድር ፕሬዝደንት ነበረ። ከዚህ አንፃር ግማሽ ጎኑን በልቶ ሕወሃት ስልጣን ላይ የቆየው። ብሔራዊ ርዕቅ ለራሱም ለኢሕአዴግ ያስፈልጋል። እነዚህ ሰዎች ኢሕአዴግ ከጫካ ሚኒሊክ ቤተመንግስት ድረስ ያመጡ ሰዎች ናቸው። አሁን ከሚታዩት ባለስልጣናት የበለጠ ዋጋ የከፈሉ ናቸው። ስለዚህም የተጣለ የለም የሚሉት ቀልድ ነው። ቀልዳቸውን መቀጠል ይችላሉ።
በድርጅቶች ደረጃ ከወሰድነው ላለፉት አርባ አመታት የተቋሰሉ ድርጅቶች ያለባት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለነው። በማሕበረሰብ ደረጃም ከወሰድነው ብዙ ቅራኔዎች እንዳሉም እናውቃለን። ስለዚህም የተጣለ የለም እየተባለ ግጭት በአፍጫችን ላይ ጠዋት እና ማታ እየፈነዳ ነው ያለው። ለምሳሌ በጉራፈርዳ፣ በመዠንገር፣ በጋምቤላ፣ በሱማሌ እና በኦሮሚያ አካባቢዎች ግጭቶች ተነስተዋል። ሰዎችም ተፈናቅለዋል። ነገር ግን ጉዳዩ ተዳፍኗል።
ሰንደቅ፡- የእርስዎ መከራከሪያ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ እስካሁን ካለፍናቸው መንግስታት ለኦሮሚያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን በመዘርጋትና ተጠቃሚ በማድረግ አሁን ያለው መንግስት የተሻለ መሆኑን አንስተው የሚከራከሩ ምሁራን አሉ። እርስዎ ከዚህ አንፃር እንዴት ነው የሚመለከቱት?
ዶ/ር መረራ፡- የምትላቸው ወገኖች ምን ያህል ፖለቲካ ገብቶአቸው ይሁን አልገባቸው አላውቅም። ለምሳሌ ደርግ እና ኢሕአዴግን እንውሰድ። በኢትዮጵያ ደረጃ በተለይ በሰሜኑ ክፍል ደርግ ከሁሉም የኢትዮጵያ መሪዎች የባሳ ሊሆን ይችላል፤ ለኦሮሚያ ግን አልነበረም። እኔን ብትወስደኝ በደርግ ሰባት አመታት ታስሬያለሁ። ከእኔ ጋር መኢሶን ውስጥ የተገደሉም አሉ። በተወሰነ ደረጃ በኦነግም ውስጥ የነበሩ የተገደሉ አሉ። ግን በሰፊው ሲታይ በደርግ ጊዜ ከነበረው ይልቅ ኦሮሚያ ውስጥ አሁን ያለው ቀውስ ይበዛል። አሁን ያለው እስር ይበዛል። እስር ቤት ብትሄድ የእስር ቤት ቋንቋ ኦሮሚፋ ነው የሚባለው ለዚህም ነው።
በተለይ በስፋት ከወሰድነው ደርግ እና ኢሕአዴግን አታወዳድርም። በዚህ ዘመን በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የደረሰውን በደል አታመዛዝነውም። በኢትዮጵያ ደረጃ ቀይ ሽብር ከወሰድክ የደርግ በደል ወንጀል አፈና ይበዛል። የበለጠም ነው። በኦሮሞ ደረጃ ግን ሁለቱን ስርዓቶች ስታወዳድረው በሚታሰረውና በሚገደለው ብዛትና በደረሰው መፈናቀል እና ሌሎችም ነገሮችን ስታይ የኢሕአዴግ ይብሳል የሚል እምነት አለኝ። ደርግ ምንም ይሁን ምንም የኢትዮጵያ ንቅናቄ ስጦታም ቢሆን መሬት ላራሹ በአብዛኛው ኦሮሞና የተቀረውን የደቡብ ሕዝብን ከጭሰኛነት አውጥቶታል፣ ጠቅሞታልም። በሌላ በኩል ደርግ ሁላችንንም ገድሏል። ወንድሜንም ገድሏል።
ሰንደቅ፡- ካስቀመጡት መከራከሪያ በመነሳት፣ ኦህዴድ ለኦሮሞ ሕዝብ የሰራው ስራ የለም ብሎ መደምደም ይቻላል?
ዶ/ር መረራ፡- እኔም ሆንክ በሌሎች የኦሮሞ ሙሁራን ኦህዴድ የሚታወቀው፣ የኦሮሞን ሕዝብ በማዘረፉ፣ ሕዝቡን በማሳሰሩ፣ ሃብት በማስቀማቱ ነው። አሉታዊ በሆነ መልኩ ነው የሚታወቀው። የኦሮሞን ልጆች መብት በማስጠበቅና በማጎናጸፍ አይታወቅም። ይህን ስልህ በቀድሞ የኦህዴድ ባለስልጣናት ጭምር የተረጋገጠ ነው። በተለይ ከፓርቲው ከተለዩ በኋላ የሚሰጡት ለኦሮሞ ሕዝብ ውክልና እንዳልተሳካለት ነው።
ሰንደቅ፡- በኦህዴድ ፖለቲካ አመራር ክልሉ በቋንቋው እንዲጠቀም፣ የፍትህ ስርዓቱንም በቋንቋው እንዲዳኝ፣ ክልላዊ መንግስት እንዲኖረው፣ መሬቱን የማስተዳደር ስልጣን፣ መሰረተ ልማቶችን የመገንባቱ ስራዎች በመልካም ጎኑ ሊወሰድ አይችልም?
ዶ/ር መረራ፡- ዋናው ጉዳይ የኦሮሞን መብት ጥቅም እናስከብራለን የሚሉ የኦሮሞ ኃይሎች እይታቸው ነው ችግሩ። የኦሮሞ ሕዝብ እነዚህ ኃይሎችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ፈጥረውልኛል ብሎ ይመለከታቸዋል ወይ? መብትና ክብሬን እያስጠበቁ ነው ብሎ ይመለከታል ወይ? ሕዝብ ይህን መመስከር ካልቻለ ዋጋ የለውም። በቃለ መሃላ ብቻ እናደርጋለን ማለት የትም አያደርስም። ውሃም አይቋጥርም። እነሃሰን አሊ፣ አልማዝ መኮ፣ ጁነዲን ሳዶ፣ እንዲሁም ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ጨምሮ ኦህዴድ የሚለውን የሚተገብር ሳይሆን ሕዝቡን የሚያስጠቃ ነው ብለዋል። ሕዝቡን ከመሬቱ እያፈናቀለው ነው። ሃብቱን እያዘረፈው ነው። በቀድሞ የኦህዴድ አመራሮችም በሕዝቡ ውስጥ ያለው አመለካከት ይህ ነው። ስለዚህም ኦህዴድ የሚለው ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ሳይሆን የሞግዚት አስተዳደር ነው በኦሮሚያ ያለው። ችግሩ እዚህ ላይ ነው።
ሰንደቅ፡- በመፅሐፍዎ ላይ ኦነግን በተመለከተ ካልተነካካን በስተቀር ለሶስተኛ ወገን ብለን አንጋጭም ብለዋል። ይህ ምን ማለት ነው?
ዶ/ር መረራ፡- ኦነግን በተመለከተ እኛ የተለየ አቋም እንዳለን ይታወቃል። እነሱም ያውቃሉ። ሆኖም ግን የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ መብቱ እስከሚጠበቅለት ድረስ ለምን በዚያ፣ በዚህ መስመር ሄደው ታገሉ ብለን የምናገልበት ሁኔታ የለም። እነሱን ወደመግፋት መጣላት ውስጥ አንገባም ለማለት ነው። ዋናው ጉዳይ የኦሮሞ ሕዝብ ለነፃነቱ ለክብሩ እየታገለ ነው የሚገኘው። የተለያዩ የኦሮሞ ድርጅቶች ደግሞ በተለያየ ስትራቴጂ ፖሊሲ እየታገሉ ነው የሚገኙት። ስለዚህ በተቻለ መጠን የእኛ ድርጅት ካልተነካ እነሱ እኛ ላይ ድንጋይ ካልወረወሩ ከመሬት ተነስተን ለኦሮሞ ሕዝብ እንታገላለን ስላሉ ብቻ አንጋጭም። እንደስትራቴጂም አንከተለውም።
ሰንደቅ፡- በአንፃሩ ግን በመጽሐፍዎ ላይ፣ የኦሮሞ ሕዝብ እንደኦህዴድ ለሌሎች ኃይሎች የኃይል ሚዛን መጠበቂያ መሆን የለበትም ብለዋል። የዚህስ መነሻ አመለካከቶ ምንድን ነው?
ዶ/ር መረራ፡- ደጋግሜ እንደምለው የኦህዴድ ባለስልጣናት የኦሮሞን ሕዝብ ጥቅም ከማስከበር ወደ ማስጠቃት፣ ከቤት ንብረታቸው ማፈናቀሉ፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ እንኳን በመቶ ሺዎች የሚሆኑ የኦሮሞ ልጆች ተፈናቅለዋል። በሺዎች ታስረዋል። ስለዚህም ነገ ከነገ ወዲያ አይጠቅማችሁም። የተወለዳችሁት ከኦሮሞ ልጆች ነው። የሚቀብራችሁ የኦሮሞ ሕዝብ ነው። ያደጋችሁት የኦሮሞን ሕዝብ ወተት እየጠጣችሁ ነው። ሕዝባችሁን ለጊዜያዊ ጥቅም ብላችሁ አትጉዱ። እነዚህን ሌሎችን ለመፈጸም መሳሪያ አትሁኑ ለማለት ፈልጌ ነው።
ሰንደቅ፡- አሁን ካለው መንግስት በጠንካራ ጎን የሚያነሱት ይኖርዎት ይሆን?
ዶ/ር መረራ፡- ሲመጡ የገቡት ቃል ኪዳን ጥሩ ነበር። የብሔረሰቦችን እኩልነት እናመጣለን። ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እናመጣለን። የእዝ ኢኮኖሚን አስወግደን በተሻለ መንገድ የገበያ ስርዓት እንድንመራ እናደርጋለን ያሏቸው ቃል ኪዳኖች በጣም ጥሩ ነበሩ። በኋላ ላይ የሄዱበት መስመር ነው ከኢሕአዴግ የለያየን። ኢሕአዴግ ስልጣን ላይ ሲወጣ ደጋፊው ነበርኩ። በመጸሐፌም አስፍሬዋለሁ። የተለያየነው የሽግግር መንግስት ምስረታ ላይ በተፈጸመው ቲያትር ነው። ያለፉት መንግስታት ሲሰሩት የነበረውን ድራማ አይናችን እያየ ደገመው። ከዚህ በኋላ ኢሕአዴግ የትም አይደርስም የሚል መደምደሚያ ላይ የደረስኩት ለዚህ ነው።
ቢያንስ ቢያንስ ግን ደርግን ስንታገል ለነበርነው ኃይሎች ደርግን ማስወገዳቸው በየትኛውም ሚዛን ትልቅ ድል ነው። ግን ደርግ የሰራውን ስህተት በቪዲዮ እያየ እሱኑ መድገሙ ትልቅ ወንጀል ነው። ይህን ስህተት ካላረመ ከደርግ የተሻለ የታሪክ ስፍራ ይኖረዋል የሚል ግምት ለመስጠት ያስቸግራል።

”ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች!” – ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት (የጉዳያችን ማስታወሻ)


  • 538
     
    Share
እናት አርበኞች
”ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች” ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ሰሞኑን ፓርቲው እና ዘጠኙ አጋር ፓርቲዎች በጋራ በጠሩት በመጪው ቅዳሜ እና ዕሁድ (ህዳር 26 እና 27/2007 ዓም) በአዲስ አበባ የተጠራውን የ 24 ሰዓት የተቃውሞ ሰልፍ አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት ንግግር ነው።
ይህ ንግግር አሁን ላለው ትውልድም ሆነ በኢትዮጵያዊነቱ ለሚያምነው ሁሉ ከሰማይ የገዘፈ፣ ሲያስቡት በትንሿ አእምሯችን ልንሸከመው የሚከብድ ግን ከእውነትም በላይ የሆነ እውነት ነው።
arebegnoch
ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ካቆሟት ነገሮች ውስጥ አንዱ ለዘመናት የኖረው ሕግ ነው።ዓለም እንደ ዛሬው ስለ ሕግ ብዙ ሳይናገር በቤተ መንግስቱ እና በሕዝቡ መካከል የሚያገናኙ ሕጎች ነበሩ።የተበደለ ፍትህ የሚያገኝበት፣አቤት የሚልበት ቦታ ነበረው።በዳኝነት የተቀመጠውም ህሊናውን እና አምላኩን የሚፈራበት መመዘኛ ነበረው።ፍፁምነት በእራሱ ከሰው ልጅ ባይጠበቅም እንደ ማህበረሰብ፣እንደ ሕዝብ እና እንደ መንግስት ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ለሺህ ዓመታት ሲዳኝ የኖረው ከፈረንሳይ ሀገር በመጣ ወይንም ከእንግሊዝ በመጣ ሕግ አይደለም። ሃይማኖታዊ መሰረቱን በያዘ፣ህሊናን እና ህዝብን ታሳቢ ያደረገ ሕግ እና ፍርድ ለዘመናት አኑረውናል።
ይህንን ሕግ እና በነፃነት የመኖር ፀጋን አባቶቻችን በነፃ አላገኙትም።ወጥተው እና ወርደው ደምተው እና ቆስለው ያቆዩት እኛነታችን ነው።ለእዚህ ነው ዛሬ ላይ ሆነን ለነገ ለማስተካከልም ሆነ የምናወራው ስለ ምን ዓይነቷ ኢትዮጵያ እንደሆነ ለማስታወስ ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት ሀገር መሆኗን ለአፍታም አለመርሳቱ ተገቢ የሚያደርገው።ብዙ የተደከመባት ብቻ አይደለም ብዙ ታላልቅ ሰዎች የተሰዉላት ሀገር ነች።ኢንጅነር ይልቃል ያስታወሱን እኔም በአምሮዬ ሲመላለስ የከረመው አረፍተነገር ይህ ነው።
ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች
ኢትዮጵያ ንግስት ሳባ በሴት አቅሟ በረሃ ለበረሃ ተንከራታ ኢየሩሳሌም ድረስ ሄዳ ታቦተ ፅዮንን ያመጣችላት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ ንጉስ ካሌብ እስከ የመን የሀገሩን ስም ይዞ ሄዶ በባርነት የተያዙትን ናግራውያንን ነፃ ያወጣባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ የመሐመድ ቤተሰቦች ተሰደው በክብር ተቀብላ መጠለያ ሰጥታ እስልምና ሃይማኖትን ለዛሬ አማኝ የሰው ልጆች በሙሉ ከመጥፋቱ በፊት የታደገች ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ በዘመነ ዮዲት (ጉዲት) ለአርባ ዓመት የመከራ ዶፍ ሲወርድባት ከመከራው ጋር የነደዱ፣በእሳት የተቃጠሉ፣በጦር የተወጉ ለሀገራቸው እና ለህዝባቸው ክብር በሰይፍ የተቀሉ ጀግኖች የሞቱባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ ክብር ፣ለሌሎች ነፃነት እና ለእምነታቸው ፅናት የተጉ እነ አፄ ዳዊት፣ነገስታቷ ግብፅ ያሉ ህዝቦች ተጨቆኑ ብለው በሱዳን በረሃ ተንከራተው የግብፅን ሕዝብ ከመከራ የታደጉ ሲመለሱም የክርስቶስን መስቀል ይዘው የተመለሱ በመንገዳቸው መከራ ህመምን ታቅፈው ሀገራቸው ድንበር ላይ የሞቱባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ ባዕዳን እንግሊዞች ሀገራችውን እና ወገናቸውን በከዱ ባንዳዎች እየተመሩ ሲመጡ እጅ አልሰጥም፣ኢትዮጵያን መሳቅያ አላደርግም ብለው የገዛ ሽጉጣቸውን ጠጥተው የሞቱባት አፄ ቴዎድሮስ የተሰዉላት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ ራስ አሉላ ”ፈረሴ የቀይ ባህርን ውሃ ሳይጠጣ አይመለስም” ብለው በባህረ ነጋሽ በረሃዎች ተንከራተው የሀገራቸውን ክብር ያስጠበቁ የተሰዉላት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ አፍሪካን በጠረንጴዛ ዙርያ ተሰብስበው ለመቀራመት ከተስማሙ በኃላ ሊወራት የመጣውን ጣልያንን ለመዋጋት ለወራት በእግራቸው እስከ አድዋ ድረስ ተጉዘው መስዋዕት የተቀበሉባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ ኢጣልያ ዳግም በ1928 ዓም ሲወራት ከሊቅ እስከ ደቂቅ በረሃ ለበርሃ ተንከራተው ከውስጥ አርበኛ እስከ ዓለም አቀፍ ሙግት ገብተው፣ከጳጳሳቷ እስከ ሕፃን ሰማዕት የሆኑባት፣በአዲስ አበባ በየካቲት 12 ቀን ብቻ ከአስር ሺህ በላይ የንፁሃን ደም በአካፋ እና በዶማ ጭምር የፈሰሰባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ እነ ሞገስ አስገዶም እና አብርሃም ደቦጭ በአርበኝነታቸው ተይዘው ጥፍራቸው እየተነቀለ ተሰቃይተው የሞቱላት ሀገር ነች ኢትዮጵያ።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
Ethiopians on Sunday celebrated the 118th anniversary of the Adowa battle when an untrained Ethiopian army routed a better equipped Italian invasion army. Photo Credit: Turkish Press
Ethiopians on Sunday celebrated the 118th anniversary of the Adowa battle when an untrained Ethiopian army routed a better equipped Italian invasion army.
Photo Credit: Turkish Press

ኢትዮጵያ በሮም ጣልያን አደባባይ ጎራዴ መዘው የጣልያንን ፋሽትትን የቀሉ በመጨረሻም ለሞት ሰማዕት የሆነላት ዘርአይ ድረስን ያበቀለች ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ ከጣልያን እስር ቤት አምልጦ በገዛ የጣልያን በረሃ ሸፍቶ ፋሽትን ያርበደበደ በመጨረሻም በድል የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለበ ሮም የገባ እና ከአዲሱ የጣልያን ፕሬዝዳንት የገዛ የእጅ ሰዓታቸውን አውልቀው የሸለሙት ጀግና አብዲሳ አጋን ያፈራች ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ የተሻለ አስተዳደር ያስፈልጋታል።ብለው እራሳቸውን የሰጡ ጀግና የጦር ኃይል አባላት እነ ጀኔራል መንግስቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ በስቅላት አንገታቸውን ለገመድ የሰጡላት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ አሁንም የተሻለ አስተዳደር ያስፈልጋታል፣”ሕዝባዊ መንግስት አሁኑኑ!” ያሉ በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች ለሞት እራሳቸውን የሰጡባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ የዚያድባሬ ሱማልያ ”ቁርስ ድሬዳዋ፣ምሳ አዲስ አበባ” ብላ በምትፎክርበት ወቅት ከሶስት መቶ ሺህ በላይ ወዶ ዘማች ባጭር ጊዜ ለኢትዮጵያ እሞትላታለሁ ብለው የተሰለፉላት እና ሺዎች በፈንጅ ላይ እየተራመዱ ሞተው ሀገራቸውን ለክብር ያበቁ ዜጎች የወለደች ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ አንድነቷ አይናጋም፣አትቆራረስም፣በጎሳ እና በዘር አትከፋፈልም ብለው ሰማዕት የሆኑላት እንደ ምፅዋ በነበረው የእርስ በርስ ውግያ ሳንጃ በሳንጃ እየተሞሻለቁ ከአፈር የተደባለቁላት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ አሁንም ከአምባገነናዊ አገዛዝ ትላቀቅ ብለው ተነስተው በመጨረሻ ሰንደቅ አላማዋን ተጠቅልለው በመከላከያ ሚኒስትር ቢሮ ውስጥ የተሰዉላት እነ ጀነራል መርድን፣በሰሜን እኔ ብ/ጄነራል ደምሴ ቡልቱን፣ኮለኔል ታሪኩን ያፈራች መሬት ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
አዎን ! ዛሬ በጎሳ እና በከፋፋይ አገዛዝ እጅ ወድቃ ብትቆስልም ኢትዮጵያ ብዙ ደም የፈሰሰላት፣ብዙዎች የደከሙላት ወደፊትም የሚደክሙላት ሀገር ነች።ዛሬ ኢትዮጵያን ስናስብ ይህንን ሁሉ ድካም እና እንደጎርፍ የፈሰሰው ደም ሊታወሰን ይገባል።
ይህንን ሁሉ ነው የኢንጅነር ይልቃል ንግግር ያስታወሰኝ።ይህንን ስናስብ ነው በሀገራችን ምን ያህል እንደቀለድን ሀገራችንን ለአልባሌ እዚህ ግባ ለማይባል ዘረኛ ቡድን ሰጥተን ግማሾቻችን ለስደት የቀረነው ለህሊና እስረኝነት መዳረጋችን የሚያንገበግበው።
አዎ እያወራን ያለነው ስለ ኢትዮጵያ ብዙ ስለተደከመላት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች ስለተሰዉላት ሀገር ነው።አዎን!! ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች! ይህ ትውልድ የሀገሩን ክብር ማስመለስ ያለበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ነው።ሁሉ እንጀራ ጋጋሪ አይሆንም።ሁሉም ወጥ አይሰራም።ባለን በችሎታችን ለሀገራችን ካልሰራን ከሞቱት አንሰናል።ብዙዎች የደከሙላት እና የሞቱላት ሀገር ላይ ቸል የማለት መብት የለንም

ከ5 ሚሊዮን የማያንሰው ዐማራ ዬት ደረሰ?


  • 511
     
    Share
moreshየትግሬ-ወያኔ ለ17 ዓመታት በሽፍትነት፣ ለ23 ዓመታት ደግሞ በገዢነት ተፈናጦ በዐማራ ሕዝብ ባደረሰው የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ምን ያህል ንፁሃን ዐማሮች እንደተጨፈጨፉ የተለያዩ አስተያዬቶች ሲደመጡ ቆይተዋል። ሞረሽ ወገኔ ባደረገው ዝርዝር የሕዝብ ብዛት ቆጠራ ትንተና መሠረት ከ1983ዓ.ም. ወዲህ ደብዛቸው ከምድረ-ገፅ እንዲጠፉ የተደረጉት ዐማሮች ብዛት ከ5 ሚሊዮን እንደማያንስ ይጠቁማል። ይህ ምንን ያመለክታል? ከጥናቱ ውጤት የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ጎልተው ይወጣሉ።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው አገር አቀፍ ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራ የተካሄደው በ1976 ዓ.ም. ነበር። በወቅቱ ኤርትራን እና የአሰብ አስተዳደርን ጨምሮ ጠቅላላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 42,616,876 ያህል ነበር። በኤርትራ እና በአሰብ አስተዳደር ኗሪ የነበሩት ዜጎች ቁጥር ሲቀነስ በቀሪዋ ኢትዮጵያ ይኖር የነበረው ሕዝብ ብዛት 39,868,572 ይሆናል። በወቅቱ በሕዝብ ብዛት አንደኛ የነበረው የኦሮሞ ነገድ ብዛቱም12,387,664 ሲሆን፤ እንዲሁም ዐማራ በሁለተኛ ደረጃ12,055,250 ያህል ተወላጆች ነበሯቸው። ስለሆነም በወቅቱ በሁለቱ ነገዶች ተወላጆች ብዛት መካከል የነበረው የቁጥር ልዩነት 332,414 ይሆናል ማለት ነው። የመጀመሪያው የሕዝብ ቆጠራ ከተደረገ ከ23 ዓመታት በኋላ፣ ማለትም በ1999 ዓ.ም. በተደረገው ሦሥተኛው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሠረት ዐማራው ቁጥሩ በአዝጋሚ ሁኔታ ወደ 19,867,817 ሲጨምር የኦሮሞዎቹ ብዛት ግን ከእጥፍ በላይ አድጎ ወደ 25,488,344 ደርሷል። ስለዚህ በኦሮሞ እና ዐማራ ተወላጆች ብዛት መካከል ያለው የቁጥር ልዩነት 5,620,527 አሻቅቧል ማለት ነው። በዐማራው እና በኦሮሞው መካከል የነበረው የቁጥር ልዩነት ተመጣጣኝነት እንዳለ እንደተጠበቀ ይቀጥል ቢባል እንኳን ከ23 ዓመታት በኋላ ሊኖር የሚችለው ልዩነት ከ664,828 አይበልጥም። በመሆኑም ከ5ሚሊዮን የማያንሰውን ዐማራ ዬት እንዳደረሱት የሚያውቁት የትግሬ-ወያኔዎች እና ሎሌዎቻቸው ናቸው።
ባለፉት 23 ዓመታት ከ4,751,333 በላይ የዐማራ ነገድ ተወላጅ የጠፋው ወያኔ ገና የትጥቅ ትግል ሲጀምር «የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ዐማራ ነው፤» « ዐማራን፣ የአማርኛ ቋንቋን እና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ማጥፋት አለብን!» ብለው የተሰለፉ በመሆናቸው የዐማራውን ነገድ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በመግደላቸው ነው። በግልፅ እንደሚታወቀው ወያኔ የዐማራውን ነገድ በሚከተሉት ሥልቶች አጥፍቷል። እያጠፋም ነው፥
  • በተለያዩ ሰበቦች በጅምላ በመግደል፦ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በሠቲት፣ በአርማጭሆ፣ በራያ ሕዝብ ላይ የፈፀሙት የግፍ ግድያ፣
  • በአሰቦት ገዳም፣ በአርባ ጉጉ፣ በወተር፣ በበደኖ በሌሎችም የሐረርጌ እና አርሲ አካባቢዎች ይኖሩ በነበሩ ዐማሮች ላይ የፈፀሙት የግፍ ጭፍጨፋ፤
  • በወለጋ፣ በኢሉባቡር፣ በጅማ ያካሄዷቸው ዐማራን በጅምላ የመግደል ዘመቻዎች፤
  • ከ1983 -1987 ዓ.ም. ድረስ በሕወሓት ሠራዊት አማካይነት በሸዋ፣ በወሎ፣ በጎጃም እና በጎንደር ኗሪ በሆኑ ዐማሮች ላይ የ«ሽፍታ ምንጠራ» እና «ብረት ማስፈታት» የሚሉ የሽፋን ዘመቻዎች በማካሄድ በፈፀሟቸው ጭፍጨፋዎች፤
  • ዐማራውን በተለያዩ ተፅዕኖዎች በማስፈራራት ዐማራነቱን ክዶ የሌላ የነገድ ማንነት እንዲቀበል በማስገደዳቸው፤
  • ዐማራውን እየለዩ ከሥራ በማባረር በርሃብ በመጨረሳቸው፤
  • «የመሬት ድልድል» በሚሉት እና ዐማራን «መሬት አልባ የትግሬ-ወያኔ ጭሰኛ» ለማድረግ በቀየሱት ፖሊሲ ዐማራው ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ተለይቶ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል አርሶ እና ሠርቶ እንዳይኖር በማድረጋቸው፤
  • ነባሩን የወባ መከላከያ ድርጅት ዘግቶ ድርጅቱን ወደ ትግራይ በማዛወር የዐማራውን ነገድ ተወላጆች የወባ መከላካያ አገልግሎት በማሳጣት አያሌ ዜጎች እንዲያልቁ በማድረጋቸው፣ በተለይም በጎጃም ሕዝብ ላይ ከ1985-1989 ዓ.ም. ያደረሱት እልቂት በምሣሌነት ይጠቀሣል፤
  • የዐማራውን ነገድ ተወላጆች በዘር ጠላትነት ፈርጀው የኤች.አይ.ቪ./ኤድስ ቫይረስን በመርፌ በማስተላለፍ በገፍ እንዲያልቁ በማድረጋቸው፤
  • የዐማራውን ተወላጆች መሠረታዊ የጤና አገልግሎት በመንፈግ በተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች እንዲያልቁ በማድረጋቸው፤
  • በወሊድ ቁጥጥር ስም የነገዱን አባሎች መካንና ታማሚ በማድረጋቸው፤
  • ከዐማራ የጸዱ ክልሎችን ለመፍጠር በተያያዙት የዘር ማፅዳት ዘመቻ «ኦሮሚያ፣ ደቡብ ብሔር-ብሔረሰቦች፣ ቤንሻንጉል-ጉምዝ፣ ጋምቤላ፣ አፋር እና ሶማሌ» ብለው በከለሏቸው «ባንቱስታን-መሠል» ግዛቶች ይኖሩ የነበሩት ዐማሮችን በግፍ እና በገፍ በማባረር፣ በመግደልና በመደብደብ ለተደራራቢ ችግሮች በማጋለጣቸው፤
ለዐማራው ነገድ ቁጥር መቀነስ ዋና እና ተያያዥ ምክንያቶች ናቸው። ስለሆነም ያለምንም ማወላወል የዐማራው ነገድ በትግሬ-ወያኔ በተከፈተበት የማያባራ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ሰለባ መሆኑን ትውልዱ ሊገነዘበው ይገባል።
በተለይ ለዐማራው ነገድ ተወላጆች እና ለሃቀኛ ኢትዮጵያውያን የቀረበ ጥሪ፦
ይህን መረጃ በማባዛት ለዓለም ሕዝብ ባሉት የመገናኛ መሣሪያዎች በመጠቀም በማሰራጨት፣ ሆን ተብሎ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለተፈጸመበት የዐማራ ነገድ ድምፅ ልንሆን ይገባል። ለተበደሉ እና የመኖር ሰብአዊ መብት ለተነፈጋቸው ሰብአዊ ፍጡሮች ድምፅ መሆን ዘረኝነት ወይም ጠባብነት አይደለም። በመሆኑም የዐማራው ተወላጆች ብቻ ሣይሆኑ፤ ለሰብአዊነት የቆሙ ሁሉ ለዚህ ነገድ ድምፅ ከመሆን አልፈው፣ በኢትዮጵያውያን ላይ ይህን ዓይነት የከፋ ወንጀል የሚፈፅሙትን ለፍትኅ አደባባይ ለማቅረብ ለተያያዝነው ትግል፥ የመረጃ፣ የምክር፣ የዕውቀት እና የገንዘብ ልገሣ እንድታደርጉልን በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!
የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ዳግም ትንሣዔ በቆራጥ ልጆቿ ተጋድሎ ዕውን ይሆናል

ብሔራዊ ደዌአችን በፈውስ ዋዜማ ላይ ይሆን?

ከሚካኤል ዲኖ
ይህ ፅሁፍ በጥልቅ ጨለማ ውስጥ ከወደቀ መንፈስ የፈለቀ ነው፡፡ በዓለሙ ሁሉ የሚከናወነው ግፍና በደል እንዲሁም የሰብዓዊነት መጣጣል እለት በእለት ወደ ጥልቁ ከሚደቀፅቃት መድረሻ ቢስ ስንኩል ነፍስ በጣር ወደህዋው የተወነጨ በህቅታ የታጀበ እውነት ነው፡፡
hana and sayat
ምስኪኗ ሀና
አንቺ የዓፉዐን ናሙና
ወግቶኛል ህመምሽ
ቆጥቀቁጦኛል እንባሽ
አምናለሁ
ፍርድ ከላይ ነው
ግምድል ነው ከታች ያለው
አምናለሁ
አካልሽ ቢዝልም በርኩሳን ሥራ
ነፍስሽ ግን ታርፋለች በቅዱሳን ስፍራ›

በርትራንድ ረስል «ማኅበረሰብ ያለሴተኛ አዳሪ መኖር አይችልም» ይላል አስቀያሚ እውነት ነው፤ በሌላ መልኩ ሰው ሀጥያት ሳይሰራ ሊኖር አይችልም ማለትም ነው፡፡ የኛ ማህበራዊ ተራክቦም ከዚህ እውነታ አያፈነግጥም፡፡ በአስፈሪ ሁኔታ እየተንኮታኮተ ለሚገኘው የስነ- ምግባር ምሰሷችን አይነተኛ ማሳያ ለመሆኑ ምስክር የሚያሻው አይመስለኝም፡፡ ‹‹ሀይማኖተኛ ነኝ›› እያለ በሚመፃደቀው ሕዝባችን መሃል በስውር ህልውና ይንሳፈፍ የነበረው የዝሙት ተግባር ጨለማን ተተግኖ መሬት ከመርገጥ አልፎ በቀን ብርሃን በተለያየ ሽፋን ቢሮዎችን ከፍቶ፣ ከግዜ ወደግዜ ቁጥራቸው እየናረ የሚሄደውን ደንበኞቹን በትጋት እያገለገለ ይገኛል፡፡ ባሳለፍነው እሁድ ረፋድ በሸገር ካፌ በርቀት ታድሜ በዚህች ታዳጊ ቅጭት ዙሪያ የሬዲዮ ጣቢያው ጭንቅላት የሆነችው መዐዛ ብሩና ዶ/ር ምህረት ደበበ ያደረጉትን ውይይት አዳምጫለሁ፡፡
በውይይት ጠረጴዛው ከውጤቱ ይልቅ ወደፍንጩ ለማተኮር መሞከሩ ተገቢ ነው፡፡ከጭካኔና ከኋላቀርነት ጋር የተላቆጠውን ባህላችንን በርህራሄና በዕውቀት እያነጠሩ መልካሙን አጥልሎ ዝቃጩን በማስወገድ ፈንታ ሌላ ወገን ላይ ለመደፍደፍ ሲሞከር ይታያል፡፡ ከነጮቹ አለም በርካታ በካይ ነገሮች ወደ ውስጣችን መዝለቃቸው አያጠያይቅም፡፡ ይህም ሆኖ በገዛ ድንቁርናችን ያዛነፍነውንና በስንፍና ያስቀጠልነውን ባዕድ ላይ መላከክ አይጠቅምም፡፡ በዚህ መሠሉ የእሮሮ አውድ ከሚቀርቡ ልጠፋዎች አንዱ ሴተኛ አዳሪነትን ያመጣብን ጣልያን ነው የሚለው አንደኛው ነው፡፡ እንደ እውነቱ ግን ከጣልያን ወረራ በፊትም በንፅህና የኖርን ሕዝቦች አይደለንም፤ ከወረራው በፊት በነበረው ባህላችን የሰው ሚስት መወሸም፣ ባለትዳር ቢኮንም ተጨማሪ ሴትን በተጠባባቂነት ማስቀመጥ፣ የጭን ገረድ፣ በተገኘው አጋጣሚ መወስለት እንደነበር አያጠያይቅም፡፡ጣልያን በአምስት አመቱ ያልተረጋጋች ህልውናው ያደረገው ነገር ቢኖር እንዲህ ተበጣጥሶና መልክ አልባ ሆኖ የከረመውን ሀጢያት ተቋማዊነት ማላበስ ብቻ ነው፡፡
አምላኩን ከሰርክ ተግባሩ አባሮ በሃይማኖት ለበስ ድግሱ እንዲሁም በምላሱ ብቻ ቦታ የሰጠ ማህበረሰብ ሀጥያተኛ እንጂ ወንጀለኛ መሆን አልነበረበትም፤ ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ድርብ ውድቀትን ተላብሷል፡፡ አሳዛኙ እውነታም ይኼው ነው፡፡ ከእምነትም፣ ከህሊናም በመለስ ስናስብ ሴተኛ አዳሪዎች ለማህበረሰቡ ደህንነት እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ነውሩ የወጠረውን ክልፍልፍ በተረገመው መንገድ ተደራድረው ሃጥያቱን በማስፈሰስ፤ ይሄ አማራጭ ባይኖርለት ኖሮ በማህበረሰቡ ውስጥ ይፈጥር ከነበረው ትርምስ ራሱንም መንጋውንም ይታደጉታል፡፡ ይሄ ያልተጠና ድንበር፣ በሚያስደነግጥ መልኩ የሌለ ያህል እየተጣሰ ቀሪውም ማህበረሰብ ከማንና መቼ እንደሚከፈትበት የማያውቀውን ጥቃት እያሰበ በፍርሃት ይማቅቃል፡፡ አምላኩን ቸል ያለ ሃጥያተኛ፣ ህሊናውን ያዳፈነ ነውረኛ፣ ሕግን ያልፈራ ወንጀለኛ ….. የዛሬው ማንነታችን እውነተኛ መልክ ነው፡፡ ዛሬ በየትኛው ዝምድና
መተማመን ይቻላል? አባት ልጁን ይተኛል… ወንድም እህቱን ይጎዳኛል…. አያት የልጅ ልጁን ያስረግዛል … ልጅ እናቱን ይቃብዛል… በሰቀቀን እየኖርን ነው፡፡ ሁላችንም ለሰለባነት ታጭተናል፡፡ ወንድ መሆን ከጥቃት እንደማያድን አይተናል፡፡ ዳዴ ማለት በሰይጣን ክንፎች ከሚበረው ንስር እይታ
ውጪ እንዳልሆነ ሰምተናል፡፡ በእርጅና ዝሎ በዱላ ለመራድ መንገታገትም መስፈርት ሆኖ ከመቅሰፍቱ አላዳነም፡፡ በአንድ ማንነት ውስጥ ካለው ሁለትነት ጋር ተስማምቶ ለመተግበር የሚከብደውን ነውር፣ ሁለት ሶስት ሆነን በመመካከር ሰውን በቁሙ ወደ መብላት ተሸጋግረናል፡፡
በዚች ምስኪን ላይ የደረሰው ግፍ ይፋ ከሆነ በኋላ በወንጀለኞቹ ላይ ከማህበረሰቡ ከፍተኛ ውግዘት የፍርድ ሀሳብ ጭምር እየተሰነዘረ ይገኛል፡፡ የአስተያየቶቹ መግፍኤ የድርጊቱ ዘግናኝነት እና የልጅቷ ፍፃሜ አሳዛኝነት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ መረሳት የሌለበት ነገር ግን ሕግ አለ፡፡ የትኛውም ወንጀል፣ ምንም አስከፊ ቢሆን ሕጉ ካስቀመጠው የቅጣት ጣራ በላይ ሊያስቀጣ አይገባም፡፡ በስሜት ለተፈፀመ ጭካኔ የስሜት ቅጣት ለመስጠት መሞከር ለነገ አንዳች ትርፍ አይኖረውም፡፡ ለዚህም በምሳሌነት በቅርቡ ኖርዌይ ውስጥ አንድ አውቶማቲክ መሣሪያ የያዘ ወፈፌ ወደ አውራ መንገድ ብቅ ብሎ ወደሰባ አካባቢ ሰዎች የጨፈጨፈበትን ታሪክ ማንሳት ይቻላል፡፡ የሀገሪቱ ህግ ከፍተኛ የቅጣት ዘመን ሀያ ሁለት አመት በመሆኑ የተፈረደበት ይኸው ነው፡፡ ይህን ተከትሎ ግን ህጉን በመከለስ ቅጣቱን ከፍ አድርገውታል፡፡ በሌላ መልኩ በዚህ የወል ኩነኔ ውስጥ ራስን የማፅደቅ፣ እጅን በ “ከደሙ
ንጹህ ነኝ” ዘይቤ የመታጠብ ውስጣዊ አላማም ይታየኛል፡፡ “ከናንተ መሀል ንፁህ ነኝ ብሎ . . .” የሚል ተጋፋጭ እንደሌለ ተገንዝቦ ለወገራ ማሰፍሰፍም ይስተዋላል፡፡
እኛስ ግን ማን ነን? ወንድን በንጉስነት ሴትን በባርነት የበየነ ባህል ባለቤቶች አይደለንም እንዴ? ሴት ልጅን አናንቀን ወንድን ልጅ አተልቀን የምናሣድግ ቤተሰቦች አይደለንምን? ንቀት እና ጭካኔ መግበን እንዲህ ያሉ አረመኔዎችን አብቅለን ስናበቃ፣ መሠቀያቸውን ለማዋቀር ደፋ ቀና ማለት እኛን ያነፃናልን? ደፍረን መድፈር ባንችል በትዳራችን ላይ አንወሰልትም? በስሜት ተነድተን በጓደኛችን ላይ አንሄድም? ዝምድናን አንሰብርም? “በጨለማ ያደረከውን በብርሃን አወጣዋለሁ” መባሉን ዘንግተን በምሽት ሴተኛ አዳሪ አልጎበኘንም? ሌላው ቢቀር በመንገድ በምኞት ተሞልተን የቆንጆ ሴት ቀሚስን በምናብ ገልጠን አልቃዥንም? ታዲያ እኛ . . . ? ? ? ደፍሮ ከደፈረው፣ ያኮበኮበው እጅግ ይበልጣል፡፡ ዛሬም ሀናዎች እልፍ ናቸው፡፡ በእርግብ ንፅህና ገላጣ ሜዳ ላይ ይርመሰመሣሉ . . . ቁራዎችም አመቺ ወቅት ፍለጋ በላያቸው ያንዣብባሉ፡፡ በብዙ መልኩ እየዘቀጥን ነው፡፡ ይሄ
አንደኛው መልክ ብቻ ነው፡፡ ምናልባትም ለራሱ ክብር የማይሰማው፣ አምላኩ መኖሩንም ከጭርታው ይሻላል በማለት የተቀበለ ሰዋዊነቱንም ከእንስሳዊ እውነታው አሻግሮ መመልከት የማይሻ መንጋን አኗኗር በማሳያ ለማስደገፍ ሲባል ብቻ የሚጠቀስ አይነት ብቻ ነው፡፡
በሚደንቅ ሁኔታ በመገናኛ ብዙሃን ስለዚህ ጉዳይ በተነገረ መጠን ውግዘቱና እርግማኑ ተገልብጦ አንደማስታወቂያ እያገለገለ ይገኛል፡፡ መሻቱ ተዳፍኖ ለሚግለፈለፍበት ያገነፍልለታል፡፡ ጭራሽ ውጥኑ የሌለው ላይ ደግሞ ሃሳብ ያጭርበታል፡፡ በየመስኩ ያለውን የኢትዮጵያውያን ሁኔታ ጠቅለል አድርጌ ስመለከተው እጅግ ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡ በተስፋ ለማፍጠጥ የምሞክረው ድቅድቅ ያለ ጨለማማ ዋሻ ውስጥ ሆኜ ነው፡፡ በጨለማው ከማልቀስ ብዬ የምለኩሳት ሻማም ዙሪዬን በሚርመሰመሱት ዞምቢዎች ትንፋሽ ትጠፋለች፡፡ አንዳንዴ አንደውም በማይገፉት የተንሰራፋ ጨለማ ምስኪን ብርሃን መለኮስ ራስን ኢላማ ውስጥ መክተት ይመስለኛል፡፡ ሰው በመሆን መሰልቸት፣ በኢትዮጵያዊነት ችግር ሃዲድ ላይ ለዘመናት መንኳተት ሳቢያ ሙትትት እያለ ካለው መንፈሴ ውስጥ በልብ ትርታ ምት የምትመሰል ስልምልም ተስፋ ግን አንዲህ ትለኛለች . . . “ግን ምልባት ድቅድቅ ያለው ጨለማ
በንጋት ድንበር ላይ እንደሆነስ? ምናልባት ድንዛዜው ከንቃት ጥቂት ርቀት ላይ እንደሆነስ? ብሔራዊው ደዌ በፈውስ ዋዜማ እንደሆነስ….? ምናልባት …..” ትርታው ወደ ድለቃ ሲያድግ ይሰማኛል፡፡ ማን ያውቃል ለመኖር ያለኝን የፍላጎት እስትንፋስ አፍኖ ሊገድላት የደረሰው ተስፋ መቁረጥ እየተምዘገዘገ ከነበረበት የገደል መሬት ሳይላተም ነጥሮ ዳርቻው ላይ በማረፍ የህይወትን ዙሪያ ገባ በተስፋ አይን ይማትር ይሆናል፡፡ ማን ያውቃል??

መስታወት ራሱን አያይም ! ቀልዶ-አደር ክበበው ገዳና ሜሮን ጌትነት ፤ አበበ ተካ

Meron Getenet
abebe teka
መስታወት-ራሱን-አያይምይህን ፅሁፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ በቅርቡ በሁሉም ዌብ – ሳይቶች ላይ ማለት ይቻላል ፣ የወጣ አንድ የአድናቆት ፅሁፍ ነው ። ጽሁፉ አንዲት ገጣሚትን ለማድነቅ የተፃፈ ነው ። የፅሁፉ ርእስ ሐገሬ ፤ ሕዝቤ “ ፤ ክብሬ የሚል ሲሆን በእንግሊዝኛ እንዲህ ተተርጉሟል ፤ ” “My Country, My People, My Honor” :: ይህ የአድናቆት ፅሁፍ የሚያጠነጥነው ፤ ሚሮን ጌትነት በምትባል ኢትዮጵያዊት ዘመናዊ የፊልም ተዋናይ ችሎታና በግጥሙ ታክኮ ለሃገሯ ያላት ልዩ ፍቅር ላይ ነው ። ፅሁፉ ገና ሲጀምር ነው “  —--[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—–

Comment

ዲሲ የሻማ ማብራት ፕሮግራም -አንዲት ሻማ እና አንዲት ደቂቃ ለቃሊቲ እና ቂሊንጦ

አንዲት ሻማ እና አንዲት ደቂቃ ለቃሊቲ እና ቂሊንጦ
በአፋኙ እና አምባገነኑ የህውሃት ኢሃደግ ስርአት በሀሰት የአሸባሪነት ወንጀል ተፈርጀው በየእስር ቤቱ ተጥለው ለኢትዮጵያ ሀዝብ ፍትሃዊ ስርዓት ለማስገኘት ሲሉ መስዋትነት እየከፈሉ ላሉ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኛ ወገኖቻችን የአጋርነት መግለጫ ወርሓዊ የሻማ ማብራት ፕሮግራም።
አገር እና ነጻነት ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በዚህች አጭር የሻማ ማብራት ፕሮግራም ላይ በመገኘት እነዚህን ጀግና ዜጎቻችንን በምንኣብ ጉብኝት እንጠይቃቸው፣ ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ በተለይም ለምንኖርበት የአመሪካ መንግስት እነዚህ ዜጎቻችን የነጻነት ታጋዮች እንጂ ወንጀለኞች እንዳልሆኑ ምስክርነታችንን እናሰማ።
እሁድ ዲሰምበር 7, 2014
ከምሽቱ 6 ሰዐት
ሗይት ሃውስ ፊት ለፊት
3