የጉዳያችን አጭር ዘገባ
”Ethiopian diplomat flees US to dodge prosecution” ”ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ከአሜሪካ ፍትህ ፊት ሸሽቶ አመለጠ ከአሁን በኃላ ወደ አሜሪካ በማንኛውም ጊዜ መምጣት አይችልም ከመጣ ግን ክሱ ይጠብቀዋል” ”ዘሂል” በአሜሪካ የምክርቤት እና የዋይት ሃውስ ጉዳይ ላይ በማተኮር የሚዘግበው ጋዜጣ መስከረም 22/2007ዓም (ኦክቶበር 02/2014)
”ዘሂል” (The Hil) የተሰኘው እ አ አቆጣጠር ከ1994 ዓም ጀምሮ በአሜሪካ የምክርቤት እና የዋይት ሃውስ ጉዳይ ላይ በማተኮር የሚዘግበው ጋዜጣ ዛሬ መስከረም 22/2007ዓም (ኦክቶበር 02/2014) ”Ethiopian diplomat flees US to dodge prosecution” ”ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ከአሜሪካ ፍትህ ፊት ሸሽቶ አመለጠ” በሚል ርዕስ ስር ባወጣው ዘገባ በኤምባሲው ውስጥ የተኮሰው ሰው የዲፕሎማሲ ከለላ እንዲነሳ እና አሜሪካ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ የኢትዮጵያን መንግስት ጠይቆ እንደነበር ይገልፃል።
ዘገባውም አያይዞ ”የስቴት ዲፓርትመንት”ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ”ግለሰቡ የዲፕሎማሲ ከለላው እንዲነሳ እና በአሜሪካ ሕግ እንዲዳኝ” ለኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልፀዋል።ጄን ሳኪ አያይዘውም ”ከሀገር ከወጣ በኃላ ተመልሶ ወደ አሜሪካ የመምጣት ዕድል የለውም ከመጣም ዕድሉ ሕግ ፊት መቅረብ ብቻ ነው ” ብለዋል።
እዚህ ላይ ”The Hill” በዘገባው ”የዲፕሎማሲ ከለላውን አንሱ እና ፍርድ ቤት ላቁመው አለበለዝያ ከሀገር መባረር ነው እጣው”የሚለውን የሕግ ትርጉም አክሎበታል።ስለሆነም የመጀመርያው ስላልሆነ ሁለተኛው መባረሩ ዕውን ሆነ።መባረሩን ግን አሁንም ከፍትህ አመለጠ የሚል ዘገባ ሰሩበት እንጂ መባረሩን ዘገባዎቹ ከሕጉ ጋር ማለትም የዲፕሎማሲ ከለላ ካልተነሳ መባረር እንደሚከተል ”ዘ ሂል” በዘገባውም ላይ ቃል በቃል እንዲህ ይላል ”Diplomats are expelled from the United States when their host country declines to waive diplomatic immunity” ”በአሜሪካ ማንኛውም ዲፕሎማት የዲፕሎማሲ ከለላውን ለማንሳት የሀገሩ መንግስት ፈቃደኛ ካልሆነ (በወንጀል እየተፈለግ ሳለ ማለት ነው) ከአሜሪካ ወድያውኑ ይባረራል”ማለት ነው። ስለዚህ ግለሰቡ በትክክል ተባርሯል።
ከዋሽግተኑ ክስተት ወዲህ የኢህአዲግ ደጋፊዎች በማኅበራዊ ድረ ገፆች ላይ በአሜሪካ ላይ የዛቻ ፅሁፎችን እያወጡ ሲሆን አቶ ግርማ ብሩ ግን አንድ አሜሪካን ሀገር ለሚተላለፍ ራድዮ በሰጡት መግለጫ ተቃዋሚዎችን ከመሳደባቸውም በላይ ከአሜሪካን ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዳይበላሽ ”ሁሉም ሊንከባከበው ይገባል” ቀረሽ ንግግር ሲማፀኑ ተሰምተዋል።ነገሩ እያመራ ያለው ግን እርሳቸው እንዳሰቡት አይመስልም።አሁን የሚጠበቀው ከሁለቱ አካላት አንዳቸው የሚሰጡት ጠንከር ያለ የቃላት ልውውጥ ብቻ ነው።ብዙዎች አሜሪካ ከፍተኛ ትዕግስት ማሳየቷ እና ከእዚህ በኃላ ግን ልትታገጽ እንደማይገባት ያሰምሩበታል
No comments:
Post a Comment