Friday, July 24, 2015

በአፋር ክልል በኤርትራ ድምበር አካባቢ የህወሓት መከላከያ ሰራዊት ህዝብን ከቀዬው እያፈናቀለ በስጋት እና በፍርሃት ቆሟል -

* ምናልባት ሰሞኑን የአርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ስርዓት ላይ ያወጀው ጦርነት ከህዝብ ለመደበቅ ሲባል የሚወስዱት እርምጃ ይሆን?
* ሴቶችን አስገድዶ ከመድፈር ባለፈ በአፋር ህዝብ አኗኗር የተለመደ ከሆነው ከቦታ ወደ ቦታ እየተንቀሳቀሱ እንስሶቻቸውን የመመገብ ነፃነታቸው ላይ ገደብ ተጥሏል
* ቁጥራቸው 5 የሚሆኑ ሴቶች በተለያየ ርቀት ፍየሎቻቸውን እየጠበቁ በነበረ ሰአት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ድብደባ ደረሰባቸው

Photo File
Photo File
አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው
በኢትዮጵያ አፋር ክልል የዔሊ ዳዓር ወረዳ ከኤርትራ ጋር ድምር ናት። በዔሊ ዳዓር ወረዳ ቡሬ ላይ ትልቅ የመከላከያ ሰራዊት ካሞፕ ይገኛል። በዚህ ካምፕ የሚገኙ የመላከያ ሰራዊት አባላት በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የተለያዩ ጥቃቶች እያደረሱ ቆይቷል። ለምሳሌ ሴቶችን አስገድዶ ከመድፈር ባለፈ በአፋር ህዝብ አኗኗር የተለመደ ከሆነው ከቦታ ወደ ቦታ እየተንቀሳቀሱ እንስሶቻቸውን የመመገብ ነፃነታቸው ላይ ገደብ ተጥሏል። አሁን ደግሞ ሰሞኑን ከምንጊዜም በባሰ ሁኔታ መከላከያ ሰራዊቱ ህዝብን መውጫና መግቢያ አሳጥቷል። በትናንናው ዕለት በዔሊ ዳዓር ወረዳ በዓድገኖ እና በታሙክሌ ቀበሌ አካባቢዎች ህዝብ እንደ ነፃ ነዋሪ መንቀሳቀስ እንዳልቻለ ለምንጮቻችን ተናገሯል።
«እኛ ስንኖርበት የነበረው ቀዬችን የመከላከያ ሰራዊት አዲስ ካምፕ ሆነ። እኛ ከዛ በአሰቸኳይ እንድንነሳ ተነገረን፣ እኛ የምንኖረው በግብርና ስለሆነ ለእንስሶች ውኃ በቀላሉ ማግኘት አንችልም። ለውኃ ስንጠቀምበት ወደነበረው አካባቢዎች ድርሽ እንዳንል ተከልክለናል። ሴቶቻችን ይደፈሩብናል፣ ይደበደቡብናል፣ ወጣቶች ይታሰሩብናል፣ ከብቶች እና ፍየሎች በማን አለብኝነት ይዘርፉብናል ምንስ ያልደረሰብን በደል አለ?» ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች።
በተለይ ትናንት በአካባቢው ቁጥራቸው 5 የሚሆኑ ሴቶች በተለያየ ርቀት ፍየሎቻቸውን እየጠበቁ በነበረ ሰአት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከዚህ በፊት አስጠንቅቋቸው እንደነበረ በመናገር ባደረሱባቸው ከፍተኛ ደብደባ እና የተወሰኑ ሰዓታት እስራት ሴቶች ላይ ከደረሰው የአካል ጉዳት ባለፈ ፍየሎቻቸው ጠፍቶባቸዋል። በእርግጥ በዔሊ ዳዓር በቡሬ አካባቢ ይሄ ነገር የተለመደ ቢሆንም የሰሞኑን ነገር ለየት የሚያድረገው የመከላከያ ሰራዊቱ በአዳዲስ ቦታዎች ህዝብን ማሸበር መጀመራቸው ነው።
ምናልባት ሰሞኑን የአርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ስርዓት ላይ ያወጀው ጦርነት ከህዝብ ለመደበቅ ሲባል የሚወስዱት እርምጃ ይሆን?
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45304#sthash.p4CQ88Rr.dpuf

No comments:

Post a Comment