Monday, July 27, 2015

ፕ/ት ባራክ ኦባማ አዲስ አበባ ሲገቡ ቀስተ ደመና መታየቱ ነዋሪውን አነጋገረ፣ ሕዝቡ ፕሬዝዳንቱ ቶሎ በሄዱልን የሚል ምሬት ውስጥ መግባቱ ተገለጸ፣ኦባማ አዲስ አበባ ገብተውም አገዛዙ በተቃዋሚዎች ላይ የሚያደርገውን ጫና መቀጠሉ፣አርበኞች ግንቦት ሰባት የህዝብ ንብረት የማውደም ዓላማ የለኝም ማለቱ፣የዶ/ር አክሎግ ቢራራ በኦባማ አማካሪ ሲሳን ራይስ መግለጫ ላይ የተሰጠ ቃለ መጠይቅ፣የሳንባ ካንሰር፣የኦባማ ጉዞ ዳሰሳ፣ሁበር የፈጠረው ጫናና የታክሲ አሽከርካሪዎች ስጋት እና ሎሎችም -

የህብር ሬዲዮ  ሐምሌ 19 ቀን 2007 ፕሮግራም <…በኢትዮጵያው አገዛዝ የይስሙላ ምርጫ ላይ የፕሬዝዳንት ኦባማ አማካሪና የህወሃት ወዳጅ ሲዛን ራይስየመቶ በመቶ ምርጫው ዲሞክራሲያዊ ነው ማለታቸውና  እሳቸው እንደሳቁት እኔም ስቄያለሁ የሳቸው ሳቅና የኔሳቅ የተለያየ ነው። የመቶ በመቶ ምርጫው  እንዳሉት ሳይሆን በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ፍሪደምሀውስን ጨምሮ ምርጫው የድሮ የሶቪየትን ምርጫ ነው ፣የሰሜን ኮሪያን ምርጫ ነው የሚያስታውሰውብለዋል። አምባሳደር ሱሳን ራይስ የጎዱት የኢትዮጵያን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለአሜሪካ በኢትዮጵያ ሕዝብ በኩልየሚኖረውን አክብሮትም ጎድተውታል።ምክንያቱም  …>    ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በፕ/ት ኦባማ የኢትዮጵአ ጉዞና የፕሬዝዳንቱ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ የሆኑት ሱሳንራይስ በጉብኝቱ ላይ የሰጡትን መግለጫ በተመለከተ  ተጠይቀው ከሰጡን ሰፋ ያለ ማብራሪያየተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)   <…በአዲስ አበባ አራት አይነት ዩኒፎርም የለበሱ ፖሊሶች ሕዝቡን በከፍተኛ ሁኔታ እያስጨነቁት ነው ነገ(ሰኞ)ሕዝቡ በአብዛኛው በዚህ ተማሮ፣የታክሲው ወረፋ ስራ የሚሄድ አይመስለኝም …ፕ/ት ኦባማ እዚህም እያሉሕጋዊው የመኢአድ አመራሮች እየታደኑ እየታሰሩ ነው ግማሾቹ የደረሱበት አልታወቀም። ፕሬዝዳንቱምተቃዋሚዎችን የሚያናግሩ አይመስለኝም…>  አቶ አበበ ውቤ የህጋዊው መኢአድ የጭርቆስ ቀጠና ሀላፊ በእስርስጋት ውስጥ ሆነው ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት) የፕሬዝዳንት ኦባማ የኬኒያና የኢትዮጵያ  ጉዞን ተከትሎ የተከሰቱ ተቃውሞና ድጋፎች ፣አስገራሚ ክስተቶች ሲዳሰሱ “ከ አሜሪካ ጋር እንደምነወዳጅ ሁሉ ከአሜሪካ ጋር ልዮነቶች እንዳሉን ማወቅ አለብን “ የኬነያው ፕ/ት ኡሁሩኬኔያታ ( ልዩ ጥንቅር) የሳምባ ካንሰርና  ሐኪም ለሞቱ ቀን የቆረጠለት ግለሰብ በስራው ቦታ ባልደረቦቹን ሊሰናበት የሄደበት አስደንጋጭ ሁኔታና የጓደኞቹ ምላሽ( ልዩ ዘገባ)     <… የቬጋስ አሽከርካሪዎች የሁበርን እየመጣሁ ነው ማለት ተከትሎ የመጣ ስጋት፣ የታክሲ ኩባንያዎቹ ተጨማሪ ታክሲ የማግኘት ሩጫና ስራው ላይ የሚያመጣው ተጽዕኖ …> (ውይይት ከታክሲ አሽከርካሪዎች ጋር)   ሌሎችም ዜናዎቻችን ፕ/ት ባራክ ኦባማ  አዲስ አበባ ሲገቡ ቀስተ ደመና መታየቱነዋሪውን አነጋገረ ሕዝቡ ፕ/ት ኦባማ ከኢትዮጵያ ቶሎ የሄደው ከዚህ አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ በተገላገልን የሚል ምሬት ውስጥ መግባቱ ተገለጸ “ ባራክ ኦባማ ይሄ ኢትዮጵያ እንጂ አሜሪካ ወይም ኬኒያአይደለም” የኦባማን ወደ አ/አ መምጣት ከተቃወሙነዋሪዋች መካከል ያስማው ተቃውሞ የግንቦት 7አርበኞች ግንባር ንቅናቄ የሕዝብ ንብረትየማውደም  ዓላማ የለኝም አለ በኢትዮ–ኤርትራ ድንበር ላይ መጠነ ሰፊ ጦርነትሊቀጣጠል እንደሚችል አንድ ምሁር አስጠነቁቁ ኦባማ ኢትዮጵያው ገብተው የተቃዋሚ አመራሮችና አባላት በደህነቶች እየታፈኑ መወሰድ መቀጠሉን አንድ የተቃዋሚ አመራር ገለጹ ታዋቂዋ አሜርካዊት የሲኒማ ተዋንያት እና ዳይሬክተርአንጄሊና ጆሊ ከኢትዮጵያ የወሰደቻት ልጇን ልታጣትነው ቴኤ የኡበርና ሊፍትን ወደ ቬጋስ መምጣት በመቃወም ከ320 በላይ ታክሲ ፈቀደ ገደብ የነበረባቸውን ታክሲዎች ገደቡን አነሳላቸው ኡበር በኒዮርክ የገጠመውን ጠንካራ ተቃውሞ በድልመወጣቱ ተዘገበ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45370#sthash.9UvlmrHL.dpuf

No comments:

Post a Comment