Monday, July 27, 2015

አጭር ጥያቄ ለእነ ኦባማ አጭር ማስገንዘቢያ ለእነ ወያኔ! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

  • 352
     
    Share
ከአምሳሉ ገ/ኪዳን
ከአምሳሉ ገ/ኪዳን
አቶ ኦባማ እንደፈከሩ አደረጉት አይደል! ጥሩ አንዴ ልብ ብለው ያድምጡኝ? እኛ ኢትዮጵያዊያን በአሁኑ ጊዜ የራሳችን የሆነ ሉዓላዊ መንግሥትና ሀገር ቢኖረን እናንተም በሀገራችን የውስጥ ጉዳይ ላይ የማትገቡ ብትሆኑና ወያኔን አስታግሱልን አደብ አስገዙልን መብቶቻችንን አስጠብቁልን፤ እንቢ ካላቹህ የምታደርጉለትን ሁሉ አቀፍ ድጋፍ አቁሙ! አታርጉ! አትስጡ! አስጨረሳቹህልን! አስፈጃቹህን! እያልን ነጋ ጠባ ወደናንተ አቤቱታ የማናቀርብ ብንሆን ምንኛ መልካም በነበረ ምንኛ ደስ ባለን ነበር፡፡ ምክንያቱም እኛ ይሄንን በማለታችን ሉዓላዊነታችንን ማስደፈር እንደሆነ ስለምናስብ፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን የሉዓላዊነት የነጻነት የክብር ጉዳይ በእጅጉ ስለሚያንገበግበን ነው፡፡
ነገር ግን ምን ዋጋ አለው የሀገር ነጻነት ሉዓላዊነት ክብር የሚባል ነገር የማያውቅ የማይገባው ያለ ራሱ ጥቅም የማይታየው “ወያኔ” የሚባል የእፉኝት ልጅ መጥቶ አስደፈረን አዋረደን፡፡ ካለበት ከባድ በራስ ያለመተማመንና የአቅም ውስንነት የሚመነጭ የጥገኝነት ችግር የተነሣ በረሀ እያለ ጀምሮ እናንተንም ሆነ ሌሎቹን ምዕራባዊያን በውስጥ ጉዳያችን ዘው ብላቹህ እንድትገቡ በማድረጉ “ግንቦት 7 አሸባሪ ቡድን ነው፣ ዲሞክራሲያዊውን (መስፍነ ሕዝባዊውን) የወያኔን አገዛዝ ማንም እንዳይነካው፣ ዝንቡን እንኳን እሽ እንዳይልብን፣ በእሱ ላይ እጁን የሚያነሣ ቢኖር ጠላታችን ነው!” እያላቹህ እንደ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብነታቹህ በምንጋራቸው ጥቅሞች ላይ ጥብቅና በመቆም የኢትዮጵያ ሕዝብ የሰብአዊና ፖለቲካዊ መብቶችን ማጣቱ መገፈፉ አሳስቧቹህ እንደ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አካልነታቹህ መውሰድ ያለባቹህን እርምጃዎች አንዲትም ሳትወስዱ ከየራሳቹህና ዓለም ዓቀፍ ሕጎችና ስምምነቶች በተጻራሪ ለዚህ አንባገነናዊ አገዛዝ ጠበቃና አለኝታ ሆናቹህ አገዛዙ ሉዓላዊነታችንን እንድትጥሱ እንድትዳፈሩ አድርጎ በውስጥ ጉዳያችን እንድትገቡ እንድትፈተፍቱ በማድረጉ ነው እኛ ኢትዮጵያዊያን “እባካቹህን?” እያልን ዘወትር የምንዘበዝባቹህ የምንማጸናቹህ የምንለምናቹህ እንጅ ምንም ስለሆናቹህ አልነበረም፡፡
ከዚህ ዐውድ አንጻር አሁንም እንለምናቹሀለን እንማጸናቹሀለን እጃቹህን አንሡልን! የእኛን ጉዳይ ለእኛው ተውልን! የእናንተ እጅ ከወጣልን ነገሩ ሁሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በጣም ቀላል ነው፡፡ እንቢ ካላቹህና አንሰማቹህም የምትሉ ከሆነ ደግሞ ወያኔን ለሥልጣን ካበቃቹህበት ጊዜ ጀምሮ ወያኔ በሀገራችን በኢትዮጵያና በሕዝቧ ላይ ለፈጸመብን ግፍ፣ ሰቆቃ፣ ጥቃት፣ ጥሰት፣ የዘር ማጥፋትን ጨምሮ ለበርካታ የወንጀል ዓይነቶች ኃላፊነትን ውሰዱልን ወይም ተጠያቂ እንደሆናቹህ እወቁት የሚለው ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንገብጋቢ ጥያቄና ማሳሰቢያ፡፡
ወያኔ ሆይ! ለእነዚህ ጌቶችሽ ለሞግዚቶችሽ ከአንድ ያውም ነጻነቷን ጠብቃ ከኖረች ከሉዓላዊት ሀገር ኢትዮጵያ መንግሥት ነኝ ከሚል አይደለም ከሰፈር ኩሊዎች እንኳን ፈጽሞ በማይጠበቅ ደረጃ ወርደሽ “ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት” ባይ አሽከርና ባሪያ ሆነሻቸው እያገለገልሻቸውም እንኳ በየዓመቱ በሚያወጧቸው የሀገራት የሰብአዊ መብት አያያዝን በሚተነትነው መግለጫቸው የፈጸምሻትን ወንጀል ሁሉ ልቅም አድርገው እየጠቀሱ ምን ያህል እንደሚያዋርዱሽ እንደሚያሸማቅቁሽ እንደሚያሳጡሽ ዓይተሻል ሰምተሸል፡፡ እነሱ ይሄንን የሚያደርጉበት ምክንያት 1. የዓለም ፖሊስ (ጸጥታ አስከባሪ) ነን ብለው እያለ ስንት ወንጀልና ጥሰት እየፈጸምሽ ምንም እንዳላደረግሽ ዝም ቢሉሽ ለነሱም ጥሩ ስለማይሆን ቢያንስ ካላወገዝንማ እንሳጣለን ከሚል ሲሆን 2ኛው ደግሞ ወንጀሎችሽን ሁሉ እየዘረዘሩ አንችን በማሸማቀቅ “ዋ! አርፈሽ ትገዥልን እንደሆነ ጸጥ ብለሽ ተገዥ አለበለዚያ ግን በዚህ ሁሉ ወንጀልሽ ተጠያቂ አድርገን እርምጃ እንወስድብሻለን መቀመቅ እናወርድሻለን!” እያሉ ለማስፈራራትና አሁን ካለሽው የበለጠ ተገዣቸው ባሪያቸው አሽከራቸው ሎሌያቸው ታማኛቸው እንድትሆኝ ለማድረግ ነው፡፡ መግለጫዎቻቸው ከእነዚህ ከሁለቱ ውጪ ምንም ዓይነት ዓላማ የለውም፡፡ ምክንያቱም ሌላው ሁሉ ቀርቶ እነሱ በሚጠቅሱት ወንጀሎችሽ ብቻ እንኳን አንቺን ተጠያቂ አድርገው ሲቀጡሽ እርምጃ ሲወስዱብሽ ታይተው ተሰምተው አይታወቁምና፡፡
እንደምናየው ዓላማቸውም የተሳካላቸው ይመስላል ምክንያቱም እንደዚያ እያሉ በየዓመቱ መግለጫዎቻቸው እንደዚያ እያሉ ሲኮንኑሽ ሲያብጠለጥሉሽ “እዚህ ድረስ ወርጀ አሽከር ባሪያ ሆኘ እናንተን እያገለገልኩ እንዴት እንዲህ ብላቹህ ታዋርዱኛላቹህ? እንዲህ እማ ከሆነ በቃኝ!” ሳትዪ ወገብሽን አስረሽ በኩሊነትሽ እየተገዛሽላቸው እያገለገልሻቸው “ሲጠሩሽ አቤት ሲልኩሽ ወዴት” በማለት ከበቀደም ትናንት ከትናንት ዛሬ የበለጠ ባሪያና አሽከር ሎሌ በመሆን ተዋርደሽ ሀገሪቱንም አዋርደሻል፡፡ ለተወሳሰበ ችግር ለጣጣም ዳርደሻል፡፡ ይሄንን እያወቅሽም እራስሽን ነጻ ልታወጭ አልቻልሽም ጨርሶም አልሞከርሽም ከነአካቴውም አታስቢምም ታስረሻልና ልትሞክሪም አትችይም፡፡ ከመጀመሪያውም በፈጸምሽብን ግፍና በደል ባሸከምሽን ውርደት የኢትዮጵያን ሕዝብ አንጀት እንደቆረጥሽ ጠንቅቀሽ ታውቂዋለሽና “ይቅርታ ምሕረት አያደርግልኝም” ብለሽ ተስፋ በመቁረጥሽ አሁንም የመጨረሻ ዋስትናሽ እነሱው እንደሆኑ ታስቢያለሽ ታምኛለሽ፡፡ ይህ ውርደትሽ በዓለማችን “መንግሥታት” ታሪክ ልዩ ሥፍራ የሚይዝልሽ ይሆናል፡፡
የዚህ ወራዳና አሳፋሪ ታሪክ መቸት ኢትዮጵያ መሆኗ ለዚህች ለነጻነቷ ለሉዓላዊነቷ ለክብሯ ለኩራቷ ያልከፈለችው የመሥዋዕትነት ዓይነት ለሌላት ሀገር ታላቅ ውርደት ሐፍረትና ስብራት ነው፡፡ ይሁንና ይሄንን የውርደት የሐፍረት ሸክም ያሸከምሽን ያከናነብሽን አንች ወይም በአንድ አናሳ ጎሳ አባላት የተገነባሽው በመሆንሽ ከውጪ ወደ ውስጥ ለሚያዩን ውርደቱ የኢትዮጵያ ሆኖ ቢታይም ከውስጥ ለሚያዩት ግን የዚህ ውርደት ሐፍረት ተሸካሚዎች ከአናሳ ጎሳነታቸው የተነሣ በራስ መተማመን የሌላቸውና በዚህም ምክንያት  ጥገኛነት የሚያጠቃቸው የወያኔ ደጋፊና አባላት የሆኑት የዚያ አናሳ ጎሳ አባላት በመሆኑ የተቀረነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይም በሐውርት (ብሔረሰቦች) ከዚህ መሸማቀቅና ውርደት ነጻ ነንና ልናፍር ልንሸማቀቅ የሚገባ አይመስለኝም፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለትግሬ ሕዝብ (ለትግራይ ሕዝብ ያላልኩት በትግራይ ውስጥ ከ5 በላይ የተለያዩ ጎሳዎች ያሉ በመሆናቸውና መልዕክቴ ያተኮረው ወያኔ መከታየ መሠረቴ አለኝታዬ የሚለው የትግሬ ጎሳ በመሆኑ ነው) እናም የዚህ ጎሳ ሕዝብ ይሄ ውርደት የሚያሸማቅቀው የሚያሳፍረው ከሆነ ለወያኔ ሲሰጠው የኖረውን ሙሉ ድጋፍ ቶሎ በማቆም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመሰለፍ ለነጻና ሉዓላዊት ኢትዮጵያ መፈጠር የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክት ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡
እስከ አሁን ወያኔን እንታገላለን ብለው ከተደራጁት በትግሬ ጎሳ ስም ከተደራጁት ድርጅቶች ወያኔ “ለምን የበለጠ ወያኔ ሆኖ የበለጠ ተጠቃሚ አላደረገንም” ከሚል ቅሬታ እንጅ “ወያኔ ለምን ኢትዮጵያዊ አልሆነም” የሚሉ ባለመሆናቸው ወያኔን ከድተህ እነሱን ብትቀላቀልም “ጉልቻ ቢለዋወጥ” መሆኑ ነው እንጅ የሞራል (የቅስም) እና የማንነት ተሐድሶ ማድረግህል አያመለክትም፡፡ በቅድሚያ እንደ ሕዝብ ለዚህ ወያኔ ላደረሰብህ ላከናነቡህ ውርደት የሚዳርግህን የጥገኝነትና በራስ ያለመተማመን ከባድ የሥነ ልቡና ችግር ራስህን ነጻ አድርግ፡፡ ከዚህ የሥነልቡና ችግር ነጻ ልትሆን የምትችለውም በኢትዮጵያዊነትህ በመተማመን ከኢትዮጵያ የሚበልጥብህ ምንም ዓይነት ደባል ጥቅም እንዳይኖርህ በማድረግ ነው፡፡ እንዲህ አድርገው እራሳቸውን በኢትዮጵያዊነት ጸበል መፈወስ ካልቻሉ ግን ይህ ጎሳ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የተለየና አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ካለው ፍላጎትና ይሄንን ጥቅም ለማግኘት የሚያስችል አቅም ከማጣት ከሚመነጭ በራስ ያለመተማመንና የጥገኝነት ስሜት ችግር ዘለዓለም የጠላት መጠቀሚያ በመሆን ይህችን ሀገር ሲያምስ የሚኖር ጎሳ እንደሚሆን አጥብቄ ላስገነዝብ እወዳለሁ፡፡ የትግሬ ሕዝብ ሙሉ ለሙሉ እንዲህ ዓይነት ችግር አለበት ማለቴ አይደለም፡፡ ከሽህ አንድ ቢሆንም ኢትዮጵያዊ የሆነ አስተሳሰብ ያላቸው የሚኖሩ ይመስለኛል፡፡
ከዚህ አናሳ ጎሳ ከወጡ መሪዎች እንዲህ ዓይነቱን ውርደትና ሸክም ሀገራችንንና ሕዝባችንን ሲያከናንቡን ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደምም በዐፄ ቴዎድሮስ ወይም በሀገር ላይ ክህደት በመፈጸም ለእንግሊዝ ባንዳ ሆነው በሠሩት ውለታ በምላሹ ከእንግሊዝ በተደረገላቸው እገዛ ለንጉሥነት የበቁትና ንጉሥ ከሆኑም በኋላ ለዚህ ላበቋቸው እንግሊዞች የመታዘዝ ግዴታ እንዳለባቸው ያስቡ የነበሩት የመጀመሪያው የትግሬ ንጉሥ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ (አንዳንዶች ትግሬ አይደሉም ኢሮብ ናቸው ይላሉ) እሳቸው እንደ መሪ አርቀው ማሰብ ባለመቻላቸው፣ ኃላፊነት የሚሰማቸውና በሳል ባለመሆናቸው፣ ከጎረቤት ሀገር ጋር ለባዕድ ሕዝብና መንግሥት አድሮ ተቀጥሮ መጣላቱ መጋጨቱ የማይሽር የቂም ቁስል እንደሚፈጥር፣ ወደፊት ሀገርን ዋጋ ሊያስከፍል ሰላም ሊያሳጣን የሚችል ጠንቅና ጠላት መትከል መሆኑን ባለመረዳት የእንግሊዝ አሽከርና ተቀጣሪ ሎሌ ሆነው እንግሊዝ የላከቻቸው ወታደሮቿ ድል ስለተመቱባትና ስላቃታት ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ጦር ልከው በደርቡሾች ወይም በመሐዲስቶች ተከበው መውጫ አጥተው ሊደመሰሱ የነበሩትን የደርቡሾችን ሀገር ወራሪዎች የግብጽና የቱርክ ወታደሮችን እንዲያድኗቸው እንዲታደጓቸው ወይም ነጻ እንዲያወጧቸውና በምጽዋ በኩል ወደ ሀገራቸው እንዲሸኟቸው ስለተባሉ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ለእንግሊዝ ጥቅም ሲሉ በስምምነታቸው መሠረት ጦር ልከው ለነጻነታቸው እየተጋደሉ ከድል አፋፍ ደርሰው የነበሩትን መሀዲስቶችን ወይም ደርቡሾችን በመውጋት ሊቀዳጁት የነበረውን ድል ከማስጣላቸውም ባሻገር ከባድ ጉዳትም እንዲደርስባቸው በማድረጋቸው ደርቡሾች በዚህ በደረሰባቸው ግፍና በደል ቂም ቋጥረው ለበቀል በመነሣት ሀገራችንን በተደጋጋሚ በመውረር ጎንደር ድረስ ዘልቀው እየገቡ እንድትወድም ሊያደርጓት ችለዋል፡፡
የኒህ ንጉሥ ድንቁርና የዐባይን ምንጭ ጣናንና አካባቢውን የመቆጣጠርና የግብጽ ግዛት አካል የማድረግ ግብ አንግቦ እየገሰገሰ የነበረውን የግብጽና የቱርክን ጦር ደርቡሾች መግታታቸው ለኢትዮጵያ ጥቅም መሆኑን በመረዳት ደርቡሾቹን መርዳት ማገዝ ሲገባቸው ምጽዋን ማግኘት ከማንም ልንቸረው የማይገባ መብታችንና የገዛ ንብረታችን ሆኖ እያለ እንግሊዝን ባለ መብት አድርጎ በመቁጠር ምጽዋን ከእንግሊዝ እጅ ለማግኘት በመፈለግ በደነቆረና በማይሆን አደገኛ ስምምነት ምጽዋን በእጅ ለማድረግ በመፈለግ የሚያስከትለውን ጣጣ ባለማወቅ ደርቡሾቹን ወግተው ተከበው የነበሩትን ግብጾችና ቱርኮች ታድገው አድነው እንደተባሉት በምጽዋ በኩል ወደሀገራቸው ሸኟቸው፡፡ ራሳቸው ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ የሞቱትም ይሄው ስሕተት ባመጣው የበቀል ጦርነት ከደርቡሾች ጋር በተደረገ ጦርነት ነው፡፡ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ በዚህ ስሕተታቸው ዐፄ ቴዎድሮስ ገና ዐፄ ሳይሆኑ በሽፍትነት ጊዜያቸው ከእንድሪስ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት መሥርተው ግንባር በመፍጠር የ11 ቀን ጉዞ ወደ ሱዳን ውስጥ በማድረግ የጋራ ጠላት የሆኑትን ዓረቦቹን እስከ መውጋት ድረስ ፈጥረውት መሥርተውት የነበረው የአንድነት የቃልኪዳን መሠረት ፈረሰ፡፡ መፍረስ ብቻ አይደለም ከዚያ በኋላ ቀንደኛ ጠላት ሊሆኑብንም ቻሉ፡፡
እንደ አባታቸው ሁሉም የዛሬዎቹ ልጆቻቸውም ያንን ታሪካዊ ስሕተት በሶማሊያ ላይ ለምዕራባዊያኑ ጥቅም ሲሉ በመድገም ለሀገራችንና ለሕዝቧ ጠንቅ ተክለውላታል የቂም ቁስል ፈጥረውላታል፡፡ ሶማሌዎች ይሄንን የተፈጸመባቸውን በደል መቸም እንደማይረሱትና አንድ ቀን አቅም በፈቀደላቸው በቻሉ ጊዜ እንደ ደርቡሽ ሁሉ ሀገራችንን እንደሚበቀሏት ዘወትር የሚዝቱት ዛቻ ሆኗል፡፡ የምዕራባዊያኑም ዓላማ ይህ ነው፡፡ ይህችን ሀገር ከውጭና ከውስጥ መቋጫ በሌለው የግጭትና የጦርነት አዙሪት ከትተው መውጫ በማሳጣት ደቅቃ ከስማ እንድትቀር ማድረግ፡፡ እንጅማ ወያኔ እራሱ መንግሥታዊ ሽብር መፈጸምን ዋነኛ የህልውናውና የአሥተዳደር ዘይቤው ያደረገ አገዛዝ እንደሆነ ጠንቅቀው እያወቁ “ለፀረ ሽብር ትግል ታማኝና ብቁ አጋር ነው” ብለው አምነው አይደለም አጋር አድርገውት ገብቶ እንዲወጋላቸው እያደረጉ ያሉት፡፡ ሲጀመር ምዕራባዊያን ሽብርንና ሽብርተኝነትን ማጥፋት ዓላማቸው አይደለም ማበራከት ማስፋፋት እንጅ፡፡ ለዚህም ነው ሊቢያን የጋዳፊን መንግሥት “አንባገነን ነው” ብለው የተረጋጋውንና ሰላም የነበረውን ሀገር አፈራርሰው ሀገሪቱን ለሽብርተኞች መናኸሪያ ምቹ አውድማ አድርገዋት ቃል የገቡትን የመልሶ ማቋቋሚያ ገንዘብም ሳይሰጡ መንግሥትም እንዲያቋቁሙ ሳይረዷቸው ጥለዋቸው የጠፉት፡
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45357#sthash.lTXWJVSa.dpuf

No comments:

Post a Comment