Friday, July 24, 2015

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት – ክፍል አንድ

tigrai
ታላቋንና ገናናዋን ምድር ኢትዮጰያ ሲያስተዳድር እና ሲመራ ለሺህዎች ዓመታት የዘለቀው የዘውድ ስረዓት ህልፈቱን ዓይቶ ግብዓተ መሬቱ ተፈፅሞ 225ኛው ንጉሰ ነስት ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ከዙፋናቸው ወርደው ደርግ በትረ ስልጣኑን ጨብጦ የአገሪቱ ፖለቲካዊ መፃኢ ሁኔታ በአምባገነናዊና ዴሞክራሲያዊ መንታ መንገድ ላይ ቆሞ ወደ የትኛው አቅጣጫ እንደ ሚሄድ ሳይታወቅ ከአያቶቻቸው ክህደትን እየተማሩ ያደጉት አባቶቻቸው አገርና ወግናቸውን ለነጭ ሸጠው የሚያገኙትን እና አያቶቻቸው ገላቸውን ለጣሊያን ቸርችረው የሚለቅሙትን ሶልዲ እየበሉ ያደጉ የባንዳ ልጆች በህዝብ ላይ ጭምር በቀል አርገዘው ደደቢት በርሃ በመውረድ ሸፈቱ፡፡
አረጋዊ በርሄ፣ ስዮም መስፍን፣ ግደይ ዘርዓፅዮን፣ ዘርኡ /አጋአዚ/ ገሰሰ፣ አስፍሀ ሀጎስ በጥር ወር 1967ዓ.ም ደደቢት በርሃ ወርደው ከዚያም ወደ ሳህል በርሃ በማቅናት ከኤርትራ ህዝብ ነፃነት ግንባር ወታደራዊ ስልጠና በመውስድ እንዲሁም ገንዘብ፣ ትጥቅ እና ስንቅ በመመፅወት ድርጅት ለማቋቋም እውቀትና ልምድም ጨምሮ በመዋስ ህወሓትን መሰረቱ፡፡ ከእነዚህም የህወሓት መስራች በአንፃራዊነት ከአረጋዊ በርሄ በስተቀር ሁሉም በወታደራዊ እና በፖለቲካዊ የእውቀት ደርጃቸው ትምህርታቸውን ያላጠናቀቁ እዚህ ግቡ የማይባሉ ነበሩ፡፡
meles
በመሆኑም ህወሓት ገና ከጅምሩ መስረቱ የተናጋ በመሆኑ ውሎ አድሮም ልምድ ያላቸውን ሊያገኝ ወይም ሊያፈራ ባለመቻሉ ለ17 ዓመታት በኤርትራ ህዝብ ነፃነት ግንባር ጀርባ ታዝሎ አዲስ አበባ ምኒሊክ ቤተ መንግስት ሊገባ ችሏል፡፡ የእውቀት፣ የልምድ እና የአስተሳስብ ድህነቱም ዛሬ በእጅጉ ፅንቶበት ይገኛል፡፡
ነገር ግን ህወሓት ዛሬ በገዥነት ዙፋን ላይ ሆኖ በኤርትራ መንግስት የሚደገፉ የነፃነት ሀይሎችን “የሻዕቢያ ተላላኪዎች” እያለ አፉን ሞልቶ ሲናገር ይደመጣል ፡፡
“ብሔረ ትግራይ በጨቋኝዋ የአማራ ብሄር የሚደርስባት ተህጽኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎላ እና እየተባባሰ በመሄዱ የብሄረ አማራ ሶሻሊስቶች፣ ትምክተኞችና አድር ባዩች ሆነው ስለሚገኙ የትግራይ ህዝብ ለርጅም ዘመን ሰብዓዊና ፖለቲካዊ መብቱ ተነፍጎ ሲጠላና ሲናቅ እንዲሁም አድሎ ሲፈጸምበት በመቆየቱ ይህም በደል ጭቋኝዋ የአማራ ብሄር ሆነ ብላ እንደ መንግስት መመሪያዋ አድርጋ ስትስራበት ቆይታለች፡፡
ጭቋኝዋ የአማራ ብሄር የምታደርገው የኢኮኖሚያዊ ብዝበዛና ፖለቲካዊ ጭቆና ታክሎበት ከዚህም በላይ የሚያኮራው የህዝባችን ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ እንዲዳከምና እንዲጠፋ በማድረጓ የሦስት ሺህ ዓመታት ታሪክና ባህላችን መመኪያቸውና መፎከሪያቸው ሆኖ ስለሚገኝ ይህ የታሪክ ስርቆት በአንድ በኩል የአማራው ብሄር መፎከሪያ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሰፊው የትግራይ ህዝብ ታሪክ እንደሌለው በመቆጠሩ ምክኒያት ብሔረ ትግራይ ይህን የትጥቅ ትግል አርነት መንገድ መርጣለች፡፡ በመሆኑም ጨቋኝዋ የአማራ ብሄር ጭቆናዋን እስካላቆመች ድርስ ህብርተሰባዊ እረፍት አታገኝም…”
በማለት ህወሓቶች ከአንድ ዓመት በኋላ በየካቲት 1968 ዓ.ም ባወጡት የፖለቲካ ሰነዳቸው በርሃ ወርደው ነፍጥ ያነሱባቸውን ምክኒያቶች ይዘርዝራሉ፡፡
በ1968 ዓ.ም ባቀርቡት የፖለቲካ ሰነዳቸው ዓላማቸው ቁልጭ ባለ መንገድ በገፅ 18 ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡
“የትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ትግል ፀረ አማራ ብሄራዊ ጭቆና ነው፡፡ ስለዚህም የአብዮታዊ ትግል አላማ ከባላባታዊ ስርዓትና ከኢምፔረያሊዝም ነፃ የሆነ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ማቋቋም ይሆናል፡፡”
ህወሓቶች በዚህ በ1968 ዓ.ም ባወጡት የፖለቲካ ሰነዳቸው መግቢያ ላይ የትግራይ ህዝብ ሀቀኛ ወኪል እንደሆኑ ይገልፁና የትግራይን መሬት ወሰን በተመለከተ እንዲህ ነበር የፃፉት፡፡
“የትግራይ መሬት በድቡብ ኤሊውሃ በሰሜን መረብ ሲያካልሉት በምዕራብ በኩል ደግሞ ወልቃይትና ፅለምትን ያጠቃልላል፡፡”
ስለሆነም ህወሓት ከጎንደር እና ከወሎ መሬት ቆርሶ ወደ ትግራይ ለምን እንደወሰደ ሲጠየቅ በህገ መንግስቱና በፊድራሊዝም አስተዳደር አወቃቀር መሰረት እንደሆነ የሚገልፀው ፈፅሞ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ ሙሉ በሙሉ ያሳካው የበረሃ ህልሙን ነው ማለት ነው፡፡
ህወሓቶች ዝጎ በተሰነጣጠቀው የታሪክ መነፅራቸው ትግራይን ተመልክተው እንዲህ በለው ፃፉ፡፡
“ትግራይ አክሱም እስከ ወደቀችበት ጊዜ ድርስ የአክሱም መንግስት እየተባለች ትጠራ ነበር፡፡ አክሱም ከወደቀች በኋላ እራሷን በማስተዳደር ለብዙ ጊዜ ብትኖርም ቅሉ አልፎ፣ አልፎ በአካባቢዋ ለነበሩ መንግስታት ግብር መክፈሏ አልቀርም፡፡ በአፄ ዮሃንስ ዘመነ መንግስት ኃይሏ በርትቶ በአካባቢዋ የነበሩትን ነገስታት በቁጥጥሯ ስር አውላ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አፄ ዮሃንስ ከሞቱ በኋላ በዳግማዊ ምኒልክ አማካኝነት ትግራይ በማዕከላዊ ግዛት ስር ወደቀች፡፡”
ህወሓቶች ቆይተው ደግሞ ስልጣን ላይ እንደወጡ “ኢትዮጵያ የ100 ዓመት ታሪክ ነው ያላት” ሲሉ በድፍርት ተናገሩ፡፡ ህወሓቶች የአያቶቻቸውን የሀገር ክህደት ሳት ዳር ጨዋታ እየሰሙ ያደጉ ባንዳ የባንዳ ልጆች የታሪክ አተላዎች በመሆናቸው፤ ማንነታቸው ግራ ቢያጋባቸው፤ የማንነት ጥግ ፍለጋ ሲሯሯጡ ብናያቸው፤ በልካቸው ያልተሰፋ የማንነት ሱሪ አጥልቀው ሲሮጡ እየወለቀባቸው መለመላቸውን ብንመለከታቸው፤ ታሪክን ክደው ሊያስክዱን ሲሞክሩ ብንሰማቸው የሚያስደንቅ አይደለም፡፡
ህወሓት ምድረ ደናቁርት በዘር ነጋሪት ከየቦታው ተጠራርተው በረሃ በመውረድ የነጭ አምላኪ ባንዳዎች የክህደት ማህበር በመሆኑ የፖለቲካ ዓላማና ፕሮግራሙ ሌኒን እንዳለው፣ ማርክስ እንደተናገረው፣ ስታሊን እንደፃፈው… በሚሉ ሀሳቦች ብቻ የታጨቀ ነው፡፡
ህወሓቶች ሽፋናቸውን በእጆቻቸው ከዳበሷቸው ነገር ግን ካልገለጧቸው ከእነዚያ ቀያይ መፅሀፍት የቅዠት ባሀር ውስጥ ገብቶ በመስጠም የጠፋውን ማንነታቸውን ዛሬም ድረስ ፈልገው ሊያገኙት አልተቻላቸውም በእርግጥም አያቶቻቸው በሶልዲ የቀየሩትን ማንነታቸውን ሊፈልጉት አልሞከሩም፡፡ ሙሉ በሙሉ ረስተውታልና፡፡ ማንነታቸውን ፍሪዳ ጥለው ቅርጫ እያደረጉ ያደጉት የህወሓት አባላት…
ህወሓቶች በድርጅታቸው የፖለቲካ ፕሮግራም እገሌ እንዳለው እያሉ የሚፅፉት በማህፀን እያሉ የተጣባቸው ክህደት አመላቸው ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ከማንነታቸው ጋር ሙልጭ ብሎ አብሮ ስለጠፋ የራሳቸው የሆነ ሀሳብ ስለሌላቸው ጭምር ነው፡፡ ከአሸዋ ላይ ተዘርተው የበቀሉ በመሆናቸው በራሳቸው መቆምና መተማመን ስለማይችሉ የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ሀሳብ እንኳ ቢኖራቸው ትክክል መሆናቸውን የሚያረጋግጡልን እገሌ ብሎታል በሚል ብቻና ብቻ ነው፡፡
በገፅ 8 ሰፍሮ የሚገኘው ፅሁፍ የህወሓቶችን ጭንቅላት እርቃን መቅረት በግልፅ ያሳየናል፡
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45324#sthash.gZb3Km2u.dpuf

No comments:

Post a Comment