Monday, September 28, 2015

ሑመራ የገበያ ማእከሏ በእሳት ጋየ

fhumera

አምዶም ገብረሥላሴ እንደዘገበው ሑመራ ከተማ የ150 ነጋዴዎች ንብረት የሆነው የገበያ ማእከል በእሳት ቃጠሎ ሙሉ ወድሟል። ቃጠለው ሓሙስ 13/ 01 / 2008 ዓ/ም ሌሊት ያጋጠመ ሲሆን የ150 ነጋዴዎች ንብረት የሆነ ከ50 ሚልዮን ብር በላይ ንብረት በቃጠለው መውደሙ ታውቋል። ህብረተሰቡ ቃጠለው ለማጥፋት የተቻለው ቢጥርም ሊሳካ እንዳልቻለ ኑዋሪዋሪዎች ገልፀዋል። ከሁሉም በላይ ሒመራን የምታክል ትልቅ ከተማ የእሳት ማጥፍያ መኪና መንግስት ባለማዘጋጀቱ ቅሬታቸው ኣሰምተዋል። የቃጠለው መነሻ እስካሁን ከመንግስት የተሰጠ መግለጫ የለም። መንግስት ለተለያዩ ምክንያት መሬቱ ሲፈልገው እሳት የማስገባት ልምድ እንዳለው ይታወቃል። ለምሳሌ በመቐለ ኢንዳስትሪ ቀበሌ በተነሳው ቃጠሎ ሱቃቸው የወደመባቸው ሰዎች መልሰው ለመገንባት ሲሞክሩ መንግስት ቦታው ለሌላ ስራ ስለፈለገው መስራት ኣትችሉም ተብለው ተከልክለዋል። ሑመራ እነሞላ ኣስገዶም የገቡበት መንገድ ስለሆነ የጣሉት ወይም የተንጠባጠበ ቢሆንስ ማን ያውቃል። ንብረታቸው ቃጠሎ ያወደመባቸው ዜጎቻችን ፅናት እንመኝላቸዋለን። ህዝባችን በስንት ይ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46975#sthash.slAxFZJ2.dpu


Sunday, September 27, 2015

እምቢኝ በል ወያኔን

ተጨፈኑና ላሞኛችሁ የሚለውን የወያኔን ደባ ለመቃወም አለበለዚያም የጎሳና የሃይማኖት ፖለቲካን ለማራመድ በወያኔና ሻዕቢያ አጋፋሪነት አብረው አሸሸ ገዳሜ መቼ ነው ቅዳሜ እያሉ የኢትዮዽያን ህዝብ ሲገሉና ሲያስገድሉ የነበሩ አሁን ደግሞ በውጭ በመሆን ስማቸውን በመቀያየር የሻዕቢያ ተለጣፊ በመሆን እንደ ሸማኔ ዕቃ ወዲያና ወዲህ እያሉ በሌላ በኩል ትላንት የኢትዮዽያን ህዝብ ሲገልና ሲያስገድል ሲዘርፍና ሲያዘርፍ የነበረው፣ የኢትዮዽያን ወጣት ለስደት የዳረገውና በሞት የቀጣውን መለስ ዜናዊ በማጀብ ኢትዮዽያን ሲዘርፉ የነበሩና ዛሬ ከሞት ተርፈው በውጭ ያሉ የሀገራችንን ልጆች የአበሳና የመከራ ጊዜ ለማራዘም ተንኳሽ ፖለቲካን የሚያራምዱትን ካንተ የኔ ይበልጣል አንተ በኔ ስር ዕደር በኔ ጥላ ተጠለል በማለት ከኢትዮዽያ ህዝብ ሊለያየን እየሞከረ ያለውን ይህን የወያኔ እና የሻዕቢያ ቅጥረኛ እንቢ እንበለው። በተሻለ መልኩ ኢትዮዽያዊና የኢትዮዽያ ህዝብ ዓይኑን የጣለበትን አንጋፋ የፖለቲካ ድርጅትን በየምክኒያቱ እያራከሱና ስም እያጠፉ የማድቤት ፖለቲካን በመጀመራቸው ለተጠናከረ ድጋፍ ማጣት ምክኒያቶች እየሆኑ ያሉትን እንቢኝ አሻፈረኝ እንበላቸው። በትውልዴ ነብይ ወይም የነብይ ልጅ አይደለሁም ጆሮዬ ካዳመጠው ዓይኔን ካፈዘዘው የግፍና የጣር ማስታወሻ ጨልፌ ሀገር ወዳድ ለሆኑ ኢትዮዽያዉያን ወገኖቼ የሚከተለውን ለማሳሰብ እወዳለሁ። ህይወት ተሻጋሪ ናት ለአፍታ ደስታ ትሰጠና ሳይታሰብ ደግሞ ሀዘንን ከመከራ ለቅሶ ጋር ታላብሰናለች በዚህ ዓለም የምናሳልፈው ዘመንም እጅግ ጥቂት ነው። ትላንት በሀገራችን አውራ ጎዳናዎች ክፉኛ የኢትዮዽያ ህዝብን ሲያሰቃይና ሲገድል የነበረ የወያኔ አለቃ የነበረው ዛሬ በህይወት የለም፡ አውራው ቢሞትም በሀገራችን በኢትዮዽያ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ የመከፋፈልና የማፈራረስ ዘመቻውን ወያኔ አሁንም ተያይዞታል። ህዝባችን በአንድነትና በህብረት እንዳይኖር የተቃጣበትን ጥቃት በጋራ እንዳይመክት በዘር በቋንቋ በሃይማኖት በተሰመረ የአስረሽ ምችው የፖለቲካ ዘይቤ አለቅጥ ይታመሳል። ታዲያ አንባቢ እንዲረዳልኝ የምሻው የዚህ ሁሉ ሴራ መሠሪ እራሱ የወያኔው ዘረኛ ቡድንና አሽከር ሆድ አደሮቹ በኢትዮዽያ ህዝብ ውስጥ ተሰግስገው ያሉትን ሲሆን ግብራቸው ሰይጣናዊ ስለሆነ ወያኔን በሁለገብ ትግል እንቢኝ አሻፈረኝ ልንለው ይገባል። ወያኔና ሻዕቢያ የኢትዮዽያ የውስጥ መዥገር ናቸው። አሁንም በስልጣን ላይ አለሁ የሚለውም ወያኔ የኢትዮዽያ ህዝብን ሊወክል አይችልም!! እንደሚታወቀው በምንሊክ ቤተመንግሥት ተወሽቆ ኢትዮዽያንና ኢትዮዽያዊነትን ከህዝባችን ልብ ለመፋቅና በምትኩ የጎጥንና የጎሳን ፖለቲካ የሚያራምድ ድርጅት ነው። ነገር ግን የትግራይ ህዝብ ወኔና ኢትዮዽያዊነትም በዚህ ስንኩል ድርጅት ሴራ አይለካም። የትግራይ ህዝብ ወያኔ ከደገነበት አፈሙዝ ውጭ በራሱ የሚያስብ የሀገር ፍቅር የሚያንገበግበው ቆራጥና አስተዋይ ህዝብ ነው። ለዚህም ነው የዚህ ኩሩ ህዝብ ብርታትና ኢትዮዽያዊነት በወያኔ ነኝ ባዩ ዘረኛ ድርጅት ልንለካው የማይገባን። አንዳንድ በወያኔ ጠረጴዛ ስር ፍርፋሪ ለመልቀም ጎንበስ ቀና በሚሉ ከዚህ ብሔር መካከል ወጥተው ብሎም የራሳቸውን ህሊና የሸጡና ለወያኔ ጊዜያዊ መገልገያ በሆኑ ሰዎች ምክኒያት የትግራይ ህዝብ ተወቃሽ አይሆንም። ወያኔንና የእሱ ተላጣፊዎች የሆኑትን አንተ የትግራይ ህዝብ እንቢ ልትላቸው ይገባል። እኛ የትግራይ ህዝብ ከኢትዮዽያ ህዝብ ጋር ነን በማለት የወያኔ ምፀት ልታወግዝ ይገባል። ይህን ህዝብ የፈጠራ ፕሮፓጋንዳ ለጊዜው ቢያደናግረውም ኢትዮዽያዊነቱንና አሁን በወያኔ የተያዘው አፍራሽ የፖለቲካ ዘይቤ ልክ አለመሆኑን እውነት ራሷ ትመሰክርለታለች። ከዚህም ባሻገር ሀገር በጎሳና በቋንቋ ስትከፋፈል የሚያስከትለውን መዘዝ የአካባቢ ክስተቶች ይመሰክራሉ። ጥቃት ደግሞ አመፅን ይወልዳል ግፍ በቀልን ያመጣል መከፋፈል ለውጭ ጠላት አጋልጦ ይሰጣል። አንዱ በሌላው ላይ የሚያደርሰው በደል ምንም ጊዜ ቢቆጥርም መመለሱ አይቀርም። ለጥቃት አሜን ብሎ የሚኖር ሰው አንዴ ሳይሆን በየዕለቱ ነው የሚሞተው በሌላ አባባል ህይወት የባለቤቷን ቆራጥነት ትፈታተናለች። ስለዚህ እንቢኝ በል አንበሳ ፀጉሩን ዝንብ አያስነካም። የኢትዮዽያ አንድነትን ለማስከበር ሆነ የህዝባችንን ውህደት ለማፋጠን በቅድሚያ የወያኔን ሴራ የምናከሽፈው እንቢ ስንልና ብሎም ለህዝባዊ አመፅ ስንነሳሳ ብቻ ነው። ተራ በተራ እጅና እግርህ እየታሰረ ቤትህ ተዘርፎ ሀገርህ ፈርሳ ዓይንህ እያየ ዳግመኛ ሞትን ከመሞት የሁሉንም ዘር ሃይማኖትና ቋንቋ ባቀፈ የፖለቲካ መርህ በመመራት ህዝባዊ በሆነ ድርጅት ታቅፈን ስንታገል ብቻ ነው የምናቸንፈው። በአገር ውስጥም ሆነ በየዓለማቱ ተበትነን የምንገኝ ኢትዮዽያዊ/ት የጎሳንና የቋንቋን ክልል በተሻገረ አመለካከት በመሰለፍ የኢትዮጵያ ህዝብ ስልጣን ባለቤት ለማድረግ የሚበጀን ሐዋርያው እንደመከረን እንቢ ለጋኔን እንዳለው እኛም ደግሞ እምቢኝ አሻፈረኝ ብለን ጸረ ወያኔ ትግላችንን እናፋፍም ስል ጹሑፌን በዚሁ እቋጫለሁ። ይዋል ይደር እንጂ በህዝብ ደም እና እንባ የሚሳለቁ አምባገነኖች ሁሉ በህዝብ አመፅ ተገርስሰው ህዝባዊ ፍርድ የሚቀበሉበት ጊዜ ፀሐይ በምስራቅ እንደ መውጣቷ ያለና አይቀሬ የተፈጥሮ ህግ ነው። የወያኔን አምባገነን አገዛዝ በተባበረ ትግላችን እናስወግዳለን። የኢትዮዽያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት እስከሚሆን ድረስ ትግላችን ይቀጥላል እናቸንፋለን!

ነገ ሽሮሜዳን ያድርገኝ… አለች ቦሌ – አቤ ተኮቻው

Demera - satenaw
ንግዲህ ዛሬ ደመራው በድምቀት ተለኮሰ አይደለ… (ለመሆኑ ወዴት ወደቀ… አወዳደቁስ ምን ተናገረ…. እስቲ ቅርብ የነበራችሁ አጣሩና ንገሩን….) ታድያ ደመራው በተለኮሰ በነጋታው አዲሳባ ላይ ከሆኑ፤ ማይትስ ሽሮሜዳን ነው… መኖርስ ሽሮሜዳ ላይ ነው… የምንል እኛ፤ መስቀል እና ሰኞ ሲገጥሙ ደግሞ በቃ ሽሮሜዳ አለሟ ነው፤ እና እነ ቦሌ ሳይቀሩ ምነው እርሷን ባደረገኝ እያሉ በጉምዥት ነው የሚያዩዋት… ስንል ምስክረነታችንን እንሰጣለን።

ድሮም ሽሮሜዳ ሰኞ ቀን እጣ ፈንታዋ ነው… ፈታ የሚባልበት ላንቺም ጠጪ ለኔም አምጪ ተግባራዊ የሚሆንባት…. ቸበር ቻቻ የሚነግስበት እቁብ የሚጣልበት እቁብ የሚበላበት ጠጅ እንደ ጮማ የሚቆረጥበት…. ዘገየ ዘለግ ባለ ድምጹ ”የዝናዬ…. አንቺ የዝናዬ….የዝናዬ ማሬ ወለላዬ….” ብሎ እየዘፈነ የሰፈሩን ሰው የሚያስደምምበት… እነ አቡሌ በግሩፕ ”ዴንዳ ዴንዲኪ”ን የሚያቀልጡበት… ሰኞ ለሽሮሜዳ በቃ ምን ልበላችሁ ሰኞ ነው!!!
መስቀል እና ሰኞ ሲገጥሙ ደግሞ…. ”ዮ…..ኦ……ካ መስቀሌ… ዮ….ኦ…ኦ…ኦ..ኦ” እየተባባሉ ቤት ያፈራውን ተቃምሰው ጠጅ ቤት ያፈራውንም ድጋሚ ተቃምሰው ፌሽቲያው ይደራል፤ እለቱ መስቀል ነውና… ጠጅ ቤቶቻችን ጠጅ ቤት ብቻ ሳይሆኑ የሰርግ አዳራሽም ይሆናሉ… እግር የጣለው ሁሉ የሰርጉ ታዳሚ ነው… ሞቅ ያለው ሁሉ ሙዚቃ አውጪ ነው… ጉራግኛ ዶርዝኛ ኦሮምኛ እና ሽሮሜድኛ ይዘፈናል…
ይሄኔ እነ ሰንጋ ተራ አይቀሩ እነ ስጋ ሜዳ አይቀሩ ምነው ሸሮሜዳን በሆንኩ ባይሉ ታዘቡኝ….
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!
ምችት ይበላችሁ!
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46962#sthash.2tFAk3mT.dpuf

Saturday, September 26, 2015

የኢሕአዴግ አይቀሬ ዕጣ – አስጊው የኢትዮጵያ ጣጣ (አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ)

ዛሬ ካለንበት የፖለቲካ ሀቅ ላይ ቆመን የነገዋን ኢትዮጵያ በሃሳብ ብንመለከት፤ ሶስት እውነታዎች ገጠው ይታያሉ። የመጀመሪያው፤ አሁን በሥልጣን ላይ ባለው የገዥ ቡድን አስተዳደር፤ ምንም ቢሆን ምንም፤ ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ሊኖራት አለመቻሉ ነው። ሁለተኛው ደግሞ፤ ኢሕአዴግ፤ ውስጡ እየነቀዘ፤ ወደ አንድ ፓርቲነት ከማደግ ይልቅ፤ በየድርጅቶቹ መጎነታተል እየተወጣጠረ፤ ከውስጥ መርቅዞ ወደ መበታተኑ በመሄድ ላይ ያለ መሆኑ ነው። ሶስተኛው ደግሞ፤ አሁን በያዝነው ሂደት፤ ሀገራችን እጅግ ወደ ከፋና ልትወጣበት ወደማትችለው መቀመቅ ውስጥ እየዘቀጠች መሆኗ ነው። እኒህ ፈጠው ያደገደጉ የፖለቲካ ሀቆች፤ በዚህ ጽሑፍ ተተንትነው ቀርበዋል። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46916#sthash.2D92zAri.dpuf

eskemeche
ዛሬ ካለንበት የፖለቲካ ሀቅ ላይ ቆመን የነገዋን ኢትዮጵያ በሃሳብ ብንመለከት፤ ሶስት እውነታዎች ገጠው ይታያሉ። የመጀመሪያው፤ አሁን በሥልጣን ላይ ባለው የገዥ ቡድን አስተዳደር፤ ምንም ቢሆን ምንም፤ ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ሊኖራት አለመቻሉ ነው። ሁለተኛው ደግሞ፤ ኢሕአዴግ፤ ውስጡ እየነቀዘ፤ ወደ አንድ ፓርቲነት ከማደግ ይልቅ፤ በየድርጅቶቹ መጎነታተል እየተወጣጠረ፤ ከውስጥ መርቅዞ ወደ መበታተኑ በመሄድ ላይ ያለ መሆኑ ነው። ሶስተኛው ደግሞ፤ አሁን በያዝነው ሂደት፤ ሀገራችን እጅግ ወደ ከፋና ልትወጣበት ወደማትችለው መቀመቅ ውስጥ እየዘቀጠች መሆኗ ነው። እኒህ ፈጠው ያደገደጉ የፖለቲካ ሀቆች፤ በዚህ ጽሑፍ ተተንትነው ቀርበዋል። መግቢያ፤ በ፳፩ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ፤ ዓለም በሥልጣኔ እየገሰገሰ፤ የሳይንስ ስነ-ምርምር የእደ ጥበብ ግኝቶችን በብዛት እያዥጎደጎደና ተዓምር የሚባሉ እምርታዎችን እያስከተለ ባለበት ወቅት፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በወገንተኛ አምባገነን አስተዳደር ሥር፤ የኋልዮሽ ስትጓዝ ትገኛለች። የዚህ ገዥ ቡድን ፍላጎትና ተግባር፤ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት በተቃራኒ የቆመ በመሆኑ፤ ሰላም፣ ብልፅግናና ዕድገት ከሀገራችን ፍጹም ርቀው ሸሽተዋል። አድልዖና ሙስና አስተዳደሩን አግምተውት፤ አፍንጫ ካስያዘ ውሎ አድሯል። በጣም ጥቂት ምርጥ ዜጎች በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ሲያካብቱ፤ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠረው ደሃ ወገናችን፤ በውጪ መንግሥታትና በበጎ አድራጎት ድርጅቶች ምጽዋት፤ ቀኑን ይገፋል። የፖለቲካ ምኅዳሩ ትርጉም በማይሠጥ መንገድ፤ በገዥው ቡድን ተጠራቆ የተያዘ በመሆኑ፤ የተለዬ አቋም ያላቸው ግለሰቦችና የአስተዳደሩን ተግባር የማይደግፉ ሁሉ፤ ለእስር የተዳረጉበት፣ የሚዳረጉበት፣ የተገደሉበትና የሚገደሉበት ሁኔታ፤ የዕለት ተዕለት የኑሮ ሀቅ ሆኗል። በሕዝቡ ዘንድ፤ በተለይም በወጣቱ ውስጥ ተስፋ መቁረጥ ነግሷል። ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት ቀርቷል። ተማሩም አልተማሩም፤ የሥራ አጡ ቁጥር ሀገሪቱን ለውጥረት ዳርጓታል። አሁንም ሀገሪቱን እየጣሉ፣ ከገዥው ክፍል እየሸሹ፣ ሞትን በከበበ አስፈሪና አስጊ መንገድ፤ ወደ ውጪ የሚነጉዱት ወጣቶች ቁጥር ልክ አጥቷል። ይህን ሁሉ ምን አመጣው? ይሄስ ምን ያህል የሚሰነብት እውነታ ነው? ይህ ጉዟችን ወደየት ያመራል? ምን መደረግ አለበት? የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ይሄን ሀቅ በመመርመር፤ በግልጽ ተንትኖ ማቅረብ ነው። ላለንበት ሀቅ የዳረገን ሂደት፤ በወርሃ የካቲት ፲፱፻፷፮ ዓመተ ምህረት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዳር እስከዳር፤ ከነበረበት የጉልተኛ ሥርዓት ማነቆ ለመላቀቅ፤ ሆ ብሎ ተነሳ። በነበረው ኋላ ቀርና አፋኝ የፖለቲካ ሥርዓት ምክንያት፤ በዚያ ወቅት ብቁ የሆነና የተዘጋጀ የሕዝቡ የፖለቲካ ድርጅት ባለመኖሩ፤ የፖለቲካ ሥልጣን ክፍተት ተፈጠረ። በወቅቱ ጉልበቱን ያሳየውና የተደራጀው ክፍል የሀገሪቱ የጦር ሠራዊት ነበርና፤ አጋጣሚውን በመጠቀም፤ የወጣት መኮንኖች ስብስብ ቦታውን በጦር ሠራዊቱ ስም ወሰዱት። ይህ የወጣት መኮንኖች ስብስብ፤ ወታደራዊ ደርግን አቋቁሞ፤ በሂደቱ የአንድ ግለሰብ የበላይነትን ፈጠረ። ይህ ሰው በላው አረመኔ መንግሥቱ ኃይለማርያም፤ የግለሰብ አምባገነንነቱን ጨብጦ፤ በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ እልቂትን አስከተለ። እንዲያ ያለ አስተዳደር ዘለቄታ የለውምና፤ በሚዘገንን መንገድ አገሪቱን አፋልሶ፤ ወገን ጨርሶ፣ ብሩህና ለወገን ተቆርቋሪ፣ ሀገራቸውን ወዳድና አስተዋይ የሆኑ የአንድ ትውልድ ልጆቿን መትሮ፣ ሀገራችንን አመሰቃቅሎ፤ ለወገንተኛ አምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በሩን ከፍቶ ለቀቀለት። ሰው በላው መንግሥቱ ኃይለማርያምም ጅራቱን ቆልፎ እንደሚሸሽ ውሻ፤ እግሬ አውጭኝ ብሎ ሾልኮ ጠፋ። በዚያ በተፈጠረው ሁለተኛ ክፍተት፤ በ ፲፱፻፹፫ ዓመተ ምህረት፤ ሰተት ብሎ አዲስ አበባ የገባው ወገንተኛው አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ የሀገሪቱን ሥልጣን ከመጨበጡ በፊትና ከጨበጠ በኋላ፤ ሁለት የተለያዩ መሠረታዊ የሆኑ ግልጽ የፖለቲካ እምነቶች ነበሩት። ይህ ድርጅት ሲመሠረት፤ የትግራይን ክፍል ሀገር ነፃ አውጥቶ፤ የራሱን አንድ ሀገር ለመመሥረት ነበር። የሥልጣን ክፍተቱ ተፈጥሮ አመቺ ሁኔታ ሲያጋጥመው፤ ይህን ዓላማውን እንደያዘ፤ “ሌሎች”ን አስተባብሬ ገዥ እሆናለሁ የሚል የፖለቲካ እምነት ገዛ። ለዚህ ዓላማው፤ ከ”ሌሎች” ጋር መተባበሩ ሊያስከትል የሚችለው የባለቤትነትና የበላይነት ጥያቄ ስላላማረው፤ ራሱ ጠፍጥፎ የሚያቋቁማቸውን ድርጅቶች አጋሮቹ በማስመሰል አንኳለለ። እኒህ ድርጅቶች፤ ከ”ሌሎች” ድርጅቶች ከድተው የወጡ፣ ከደርግ በፍርሃት የሸሹ፣ ምርኮኛ እስረኞችና እነዚህን ባንድ ላይ ሰብስበው ከሚቆጣጠሩ የራሱ ድርጅት አባሎች የተዋሀዱ ነበሩ። በዚህ ስሌት የተመሰረቱት ድርጅቶችን ከራሱ ጋር በመቁጠር፤ ኢሕአዴግን አቋቋመ። አሁን ኢትዮጵያዊ ጋቢ ለበሰ። እዚህ ላይ ግን፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ “ሌሎች” እያለ የመደባቸውን ድርጅቶችና “እኔ” በማለት ያጠነጠነውን፤ ራሱን በበላይና “ሌሎች”ን በበታች አድርጎ ነው። የተነሳበት የፖለቲካ እምነቱ እንደተጠበቀ ነበር። በተለይም ከእምነቱ ውስጥ ሁለት እንደ አንገት ማተብ ያነገታቸው አሉት። የመጀመሪያው፤ “ትግራይ እስከዛሬ የበታች ሆና ተበድላለች። አሁን በኛ አማካኝነት የበላይ ሆና፤ ‘ሌሎችን’ በዳይ መሆን አለባት!” የሚለው ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር ጎን ለጎን የሚሄደው ሁለተኛው ደግሞ፤ “አማራ እስከዛሬ የበላይ ሆኖ ሁሉን ሲበድል ነበር። አሁን የበታች ሆኖ፤ በትግሬዎችና በ’ሌሎች’ ተበዳይ መሆን አለበት፤” የሚለው ነው። እንግዲህ እኒህ ከገዥና ተገዥ መደቦች ውጪ ሆነው፤ የአንድን ግለሰብ ነፃነት ለትውልድ ሐረጉ በማስረከብ፤ “የበደለህ አማራ ነው!” “የተበደልከው አማራ ስላልሆንክ ነው!” በሚል እምነቱ፤ የበዳይና ተበዳይ ወገን የሽክርክር አዙሪት አስተዳደሩን መሠረተ። ትናንት አማራ ሁሉን በዳይ፤ ትግሬ ተበዳይ ነበር። ዛሬ ትግሬ በዳይ፤ አማራ በሁሉም ተበዳይ ነው። ነገ ደግሞ . . . እያለ የሚቀጥል የትውልድ ሐረግ ቆጥሮ፤ በደልንና መበደልን የመረካከብ አባዜ ዘፈዘፈበት። ሌላው የፖለቲካ እርምጃ ሁሉ ከዚሁ ምንጭ ተቀዳ። በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል፤ በጥቂት የገዥው ቡድን አባላት ላይ፤ የአብዛኛው ተገዢ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነቱ መነሳት ቦታ አጥቶ፤ በኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮች፣ ላብ አደሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ነጋዴዎች መካከል ያለው የሙያና የመደብ አንድነት ተሰርዞ፤ የትውልድ ትስስሩ መነሻና መድረሻ ሆነ። ይህ ደግሞ፤ በአንድ በኩል ሰው ሁሉ በየትውልድ መንደሩ ብቻ እንዲሰፍር አስገደደ። በሌላ በኩል ደግሞ፤ አድልዖ፣ ሙስና፣ ምዝበራ፣ ለከት የለሽ ብልግና፤ የሥርዓቱና የሰዎች የርስ በርስ ግንኙነት ወሳኙና መታወቂያዎች እንዲሆኑ አደረገ። በገዥነት አሁን ቢቆናጠጥም፤ እንዳለፈው አረመኔ ገዥ ሁሉ፤ ይሄም ገዥ ቡድን ያልፋል። በርግጥ እስኪያልፍ እያለፋ ነው። አይቀሬ ዕጣው እያንዣበበበት ነው። የነገዋ ኢትዮጵያ ምን ትሆን ይሆን? ፍሬ ሃሳብ፤ የነገዋን ኢትዮጵያ በሃሳብ ስንመለከት፤ የመጀመሪያው እውነታ፤ አሁን በሥልጣን ላይ ባለው ገዥ ቡድን አስተዳደር፤ ምንም ቢሆን ምንም፤ ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ሊኖራት አለመቻሉ ነው። እንግዲህ ይህ ነጥብ፤ ለምን? የሚል ጥያቄ ማስከተሉ አይቀርም። ለዚህ መልሱ የሚገኘው ከኢሕአዴግ ማንነት ነው። አሁን ያለውን አስተዳደር፤ ማለትም የኢሕአዴግን አስተዳደር ብንመለከት፤ በመንግሥትና በኢሕአዴግ መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት የለም። መንግሥት ማለት ኢሕአዴግ ማለት ነው። ኢሕአዴግ ማለት መንግሥት ማለት ነው። መንግሥት የተለዬ አካል፤ ገዥ የፖለቲካ ፓርቲ የተለዬ ሌላ አካል፤ መሆኑ ተወርውሮ ተጥሏል። መንግሥታዊ መዋቅሩና የኢሕአዴግ መዋቅር አንድ ሆነዋል። ሕግ አውጪው ክፍል፣ ወሳኙ ክፍል፣ እና ፈጻሚው ክፍል፤ አንድ ሆኗል። አብዮታዊ ዴሞክራሲ፤ ኢሕአዴግን የበላይና ዘለዓለማዊ ያደርገዋል። በኢሕአዴግ እምነት፤ “ተዋግቶና ደሙን አፍስሶ ያገኘው ሥልጣን!” ስለሆነ፤ በምንም መንገድ በሰላም ሥልጣኑን መልቀቅ አይታሰበውም። ደሙን የከፈለው፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አይደለም። ደሙን ያፈሰሰው ለራሱ ሥልጣን ለመያዝና ዓላማውን በማራመድ ነው። ስለዚህ ከሀገሪቱ መሪ ጀምሮ እስከ ቀበሌ ዘበኛው ድረስ፤ የኢሕአዴግ አባል መሆን ግዴታ ነው። ከኢሕአዴግ ውጪ መንግሥታዊ መዋቅር የለም፤ ከመንግሥታዊ መዋቅሩ ውጪም የኢሕአዴግ አካል የለም፤ ኢሕአዴግ መንግሥት ነውና! ከዚህ ተነስቶ፤ እንዴት ያለ መንግሥታዊ አካል፤ ከኢሕአዴግ ውጪ ያለ፣ ሕግ ሊያወጣ፣ ፍርድ ሊመለከት፣ ፖሊስ ሆኖ ሥርዓት ሊጠብቅ፣ የሕዝብን አቤቱታ ሊሰማ ይችላል? እንዴትስ ያለ ነፃ የምርጫ ዝግጅት ሊያደርግ ይችላል? እንዴትስ ያለ ሕግ አውጪና ሕግ አስከባሪ ሊኖር ይችላል? ይህ የኢሕአዴግ አወቃቀር፤ ግድ የሚለው፤ ሀገር አቀፍ ድርጅት እንዳይኖር ነው። በየክልሉ ያሉ የኢሕአዴግ አባልና ተቀጥላ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ሌላ የነሱ ተቃዋሚ ድርጅት እንዳይኖር የዕለት ጉዳያቸው ነው። መገንዘብ ያለብን፤ በየክልላቸው የፖለቲካ ድርጅት ለምፍጠር የሚያመለክቱ ሰዎች፤ ፈቃድ ሠጪዎቹና ነሺዎቹ እኒሁ ድርጅቶች ናቸው። በመጀመሪያ ደረጃ፤ እነኚህን በየክልሉ ያሉ ድርጅቶች መቃወም ማለት፤ መንግሥትን መቃወም ማለት ነው። ቀጥሎ ደግሞ፤ መንግሥትን መቃወም፤ ያስከስሳል፣ ያሳስራል፣ ያስደበድባል፣ ንብረት ያስቀማል፣ ካገር ያስባርራል፣ ያስገድላል። በጠቅላላው ኢሕአዴግን ከሥልጣን ለማውረድ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ፤ መንግሥትን ለመገልበጥ የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። ስለዚህ ይህንን ለመቆጣጠርና ለመቅጣት፤ አስፈላጊ ሕጎችን ማርቀቅ፣ ካስፈለገም ያሉትን መሰረዝ፣ በተግባር ላይ ማዋል አለዚያም የማይስማማውን ሕግ አውጥቶ መጣል፤ የኢሕአዴግ ዋና ተግባር ነው። ታዲያ አሁን ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በኢትዮጵያ አሉ አይደል? ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? የሚሉ ጥያቄዎች ሊከተሉ ይችላሉ። አሁን ያሉትን በተቃውሞ የተሰለፉ ድርጅቶች ሕልውና፤ በደንብ መመርመር ያስፈልጋል። አዎ! ተቃዋሚ ድርጅቶች አሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ፤ በኢሕአዴግ እይታ፤ እኒህ አሸባሪ ድርጅቶች እንጂ፤ ተቃዋሚ ድርጅቶች ተብለው አይታመኑም፤ አይታወቁም። ማንኛውም ኢሕአዴግን የሚቃወም ወይንም ኢሕአዴግ ያላቋቋመው ድርጅት በሙሉ፤ ፀረ- ኢሕአዴግ ነው። ፀረ-ኢሕአዴግ ደግሞ፤ ፀረ-ሀገር ማለት ነው። እናም ፀረ-ሕዝብ ነው። እናም፤ አድኀሪ፤ ኋላቀር፣ ትምክህተኛ፣ ጠባብ ብሔርተኛ፣ ሀገር ከፋፋይ ጠላት ነው። ይህ የፖለቲካ ድርጅቶችን ብቻ ሳይሆን፤ የሙያ ማህበራትንና የሃይማኖት ተቋማትን ሁሉ ያጠቃልላል። የኢሕአዴግን ሰበካና ወቀሳ ደጋግሞ ላዳመጠ የፖለቲካ ሂደቱን ተከታታይ፤ እኒህ የተጠቀሱ ውንጀላዎች፤ በተደጋጋሚ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በጋዜጣ፣ በድረገጾችና በየስብሰባ አዳራሾች የሚዥጎደጎዱ ዘለፋዎች ናቸው። ስለዚህ ሌሎች ከኢሕአዴግ ነፃ የሆኑ ድርጅቶች እንዳያድጉ ተብታቢ ማሰሪያዎች ናቸው። ለምን ሲባል፤ ያልተፈለጉ ደንቃራዎች ስለሆኑ ነው። የተፈለገው፤ አጃቢ ሆኖ እሺ ጌታዬ የሚል ድርጅት ብቻ ነው። አጃቢ ያስፈለገውም፤ ለውጭ ሀገሮች መታያና የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት አለ ማስባያ የጀሮ ጉትቻዎች፣ ያንገት ማስጌጫዎች እንዲሆኑ ብቻ ነው። ያ ከሌለ ብድርም ሆነ እርጥባን አይገኝማ! ከሌሎች ጋር እኩል መሰለፍና መታየት አይገኝማ! በነገራችን ላይ፤ የዚህ የኢሕአዴግ፤ ዋናው ፈጣሪና መስራቹ አንድ ድርጅት ሆኖ፤ የበላይነቱን በሌሎቹ በፈጠራቸው ላይ ያነገሰና፤ እኒህን ተፈጣሪ ድርጅቶች በአጃቢነት የሚጠቀም መኖሩ ከታች በዝርዝር ቀርቧል። አሁን ያሉትን ተቃዋሚ ደርጅቶች ስንመለከት፤ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፤ የአንድነት ለፍትኅና ለዴሞክራሲ ፓርቲና የሰማያዊ ፓርቲ፤ ቀጥሎም መድረክ ናቸው። እኒህ ደግሞ የራሳቸውን ፈለግ እየተከተሉ ስላስቸገሩ፤ ለምርጫ ሲወዳደሩ ሙሉ እንቅፋት በመፍጠር ሕልውናቸውን ለማሳጣት ከመጣር አልፎ፤ መሪዎቻቸውን መወንጀል፣ ማሰር፣ ማስቃየት፣ ማባረር፣ ከሀገር ማስወጣትና መግደል ተፈጽሞባቸዋል። የጎንዮሽ የስም ተመሳሳይ ተለጣፊ ድርጅቶችን እያቋቋመ እንዲዳከሙና እንዲጠፉ ያላባራ ጥረቱን ቀጥሎበታል። በተጨማሪ ደግሞ ሌላው ሊከተል የሚችለው፤ ታዲያ እንዲህ ከሆነ፤ ይሄን አምባገነን መንግሥት ምን በሰላም ለመለወጥ ጥረት ይደረጋል? አጉል ድካም አይሆንም ወይ? ከንቱ ከመድከም፤ ገዥው ጠመንጃ አንግቦ ሥልጣኑን እንደነጠቀና ያለጠመንጃ ሌላ የማያውቅና የማይሰማ ስለሆነ፤ ሌሎቹስ ለምን ጠመንጃ አንግበው መታገል ብቻ አማራጫቸው አይሆንም? የሚሉ ጥያቄዎች ናቸው። ይህ ራሱን የቻለ ርዕስ ነው። ጠቆም አድርጎ ለማለፍ ያህል፤ ጠመንጃ አንግቦ ለትግል በመነሳት ሕዝባዊ ድልን ለመቀዳጀት፤ ወሳኝና መኖር ያለባቸው ግዴታዎች አሉ። መፈለግ ለብቻው ወሳኝ አይደለም። በጦርነት ማቸነፍ ይቻላል! የሚለው ብቻውን ወሳኝ አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ፤ በሰላም መንገድ እየተደረገ ያለው ትግል፤ በእውነት የሰላም ትግልን መንገድ የተከተለና፤ በትክክል ተተግብሮ ያለቀለት ነው ወይ? የሚለውን መመለስ ያስፈልጋል። ስለዚህ፤ በሰላም ወይንስ በትጥቅ ትግል የሚለውን፤ በሌላ ጊዜ እንመለከተዋለን። ከዚህ በፊት ይሄው ጸሐፊ ያቀረባቸው ጦማሮች አሉ። እነዚህን (http://nigatu.wordpress.com) ሄዶ መመልከት ይቻላል። እንግዲህ እዚህ ላይ፤ መድበለ ፓርቲና ኢሕአዴግ ሊቀራረቡና አብረው ሊሄዱ የማይችሉ መሆናቸው በግልጽ ሰፍሯል። ሁለተኛው እውነታ ደግሞ፤ ምንም እንኳን ለረጅም ጊዜ በተደጋጋሚ በኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ ድርጅቶች ወደ አንድ ፓርቲ ለመዋሐድ እየተዘጋጁ ነው ተብሎ ከበሮው ቢደለቅም፤ ይህ ስብስብ፤ በአባል ድርጅቶች መካከል ያለው ትብብር ውስጡ ነቅዞ፤ ወደ አንድ ከመሄድ ይልቅ፤ በየድርጅቶቹ የየግል ፍላጎት መጎነታተሉ የስብስብ ውህደቱን እየወጣጠረው፤ ወደ ውድቀቱ በመሄድ ላይ ያለ መሆኑ ነው። ከላይ እንደተጠቆመው፤ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባርን (ኢሕአዴግን) የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ሲመሰርት፤ የአራት “ትልልቅ” የፖለቲካ ድርጅቶች ጥምር አድርጎ ነው። እዚህ ላይ መገንዘብ ያለብን፤ በጽሑፍ ያልሰፈረ ሁለት ክፍል አለ። ይሄም፤ “እኔ” የሚለው ራሱ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርና፤ “ሌሎች” የሚላቸው ቀሪውን የኢትዮጵያ ክፍል ይወክላሉ ብሎ የመደባቸው ድርጅቶች ናቸው። በነዚህ ሁለት ክፍሎች መካከል፤ የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት አለ። ይህን በአእምሯችን እናስቀምጥና ወደ አራቱ “ትልልቅ” ድርጅቶች እንመለስ። እነሱም፤ ፩ኛ. የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ፪ኛ. የአማራዎች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ANDM) ፫ኛ. የኦሮሞዎች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (OPDO) ፬ኛ. የደቡብ ኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (SPDM) ናቸው። ሀገሪቱን ማስተዳደር ሲጀምር፤ ለመግዛት እንዲያመቸው፤ ተጨማሪ አምስት አናሳ የፖለቲካ ድርጅቶች አክሎበታል። እነሱም፤ ፩ኛ. የአፋሮች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ANDP) ፪ኛ. የኢትዮጵያ ሶማሊዎች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ESPDP) ፫ኛ. የሐረሬዎች ሊግ (HNL) ፬ኛ. የጋምቤላዎች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (GPDM) እና ፭ኛ. የቤንሻንጉልና ጉምዞች ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (BGPDUF) ናቸው። እንግዲህ እኒህ እንዴት ተዋቀሩ? በምን ተገናኙ? እና የመሳሰለውን ለመመለስ፤ ወደ ጀማሪው ድርጅት ፊታችን ማዞር ይኖርብናል። ከኢትዮጵያ ተገንጥዬ የራሴን መንግሥት እመሰርታለሁ ብሎ የተነሳው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ ከተቋቋመ በኋላ፤ በትግራይ ውስጥ ያለኔ ሌላ ድርጅት መኖር የለበትም የሚል ስሌት ይዞ፤ መጀመሪያ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባርን (TLF) ደመሰሰ። ቀጥሎ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ሠራዊትን (EPRP) ከትግራይ ወግቶ አስወጣ። በመጨረሻም የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅብረትን (EDU) በታተነ። በተጨማሪም የሁለት ነፃ አውጪ ግንባሮች መፋለሚያ ታዛ በነበረችው ኤርትራ ውስጥ በመግባት፤ የኤርትራዊያን ነጫ አውጪ ግንባርን (ሸዓብያ – EPLF) በማገዝ፤ የኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባርን (ጀብሃ – ELF) አብሮ ወግቶ ደመሰሰ። ይህ ነው አሁን ኢሕአዴግ በመባል የሚታወቀው ድርጅት። ኢሕአዴግ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የመግዣ ስሙ ነው። ይህ ድርጅት በፈጠራቸው ድርጅቶችና በራሱ ስም ሀገሪቱን ይገዛል። እያንዳንዱ የተፈጠረ የስብስቡ አባል ድርጅት፤ የራሱ የሆነ ክልል አለው። የራሱ “የተወሰነ” ነፃነት አለው። የራሱ የሆነ “ሕዝብ” አለው። እናም ሊያሳድገው ወይንም ሊያጠፋው የሚችለው፤ ተገዥ ወገን አለው። ታዲያ ይህ ሁሉ በትግሬዎች ነፃ አውጪ ሥርና ፈቃድ ነው። እዚህ ላይ መገንዘብ ያለብን፤ የኅብረተሰብ ሕልውናና የፖለቲካ ድርጅቶች ክስተት፤ በዕለት ተዕለት ግንኙነትና በፖለቲካ ገበያ ሥምሪት ልውውጥ፤ የራሱ የሆነ የእምርታ ዕድገት ሂደት ያገባና፤ ባልተጠበቀ መንገድ፤ ጉልበት ያበጃል። ትናንት የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አዛዥ ናዛዥ የነበረበት እውነታ፤ ሀገሪቱን በማስተዳደር ሂደቱ ላይ፤ ያዝዛቸው የነበሩት የፈጠራቸው ድርጅቶች፤ አንጻራዊ ነፃነት ማበጀታቸውና፤ ጡንቻቸውን ማፈርጠማቸው፤ አይቀሬ የኅብረተሰብ ክንውን ግዴታ ነው። እናም ዛሬ ብቅ ብቅ እያለ የምናየው የዚህን ሂደት ገጽታ ነው። እኒህ በኢሕአዴግ ስም የተካተቱ ድርጅቶች፤ በመካከላቸው፤ ከሚመሳሰሉብት የሚለያዩበት ጉዳይ ይበልጣል። በመጀመሪያ፤ ሁሉም የሚወክሉት የየራሳቸው የተለያየ ክፍል አላቸው። እናም እያንዳንዳቸው ተጠሪነታቸውም ሆነ ተቆርቋሪነታቸው ለየብቻ ለየራሳቸው ክልል ነው። እያንዳንዳቸው በውስጣቸው የሚያስተዳድሩት፤ ከፌዴራሉ ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ የራሳቸውን ክልል ነው። እናም የፌዴራል መንግሥቱ፤ በፈቃደኝነት ያሉበት የስብስብ መዋቅር ነው። ይሄ ምን ያህል ሊቆይ እንደሚችል መገመቱ ከባድ አይደለም። አንድ ሆነው ለመቆየት ምክንያቱ የለም። እስካሁን ያቆያቸው ደርግ፤ ማስፈራሪያነቱ አደፈ። አማራን ማጥቃቱ ማሰባሰቢያነቱ ሻገተ። “እኔ የበላይ ልሁን!” “የለም እኔ የበላይ ልሁን!” የሚለውና፤ “እኔ ይሄ አለኝ!” “አንተ ይሄ ይጎድልሃል!” የሚል ፉክክር በቦታው ተተካ። እስካሁን የነበረው የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር መፍራትና የታዘዙትን ማድረግ ብቻ የነበረው እውነታ፤ እያደር በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ላይ ጥላቻና ቁጭት ተተክቷል። አንድ ሊሆኑ አይችሉም። በፍርሃት የተወጠረው ረገበ። በቦታው የጥላቻ ጥርስ ተነከሰ። እስካሁን የሚደረገው ማንኛውም የፌዴራል ጉዳይ፤ በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የጉልበት የበላይነት ነበር። አሁን ተለወጠ። የክልሎችን ቦታ ወስኖ ያስቀመጠው ይሄው ፈጣሪና ፈላጭ ቆራጭ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነበር። በክልል አወቃቀር ላይ፤ ማንኛቸውም ቢሆኑ ደስተኛ አይደሉም። ትናንት የትግራይን ክልል ለማበልጸግ ብሎ በጉልበቱ ከአማራው ክልል ቆርሶ የወሰደውን፤ የወልቃይት፣ የሁመራ፣ የጠለምት፣ የጠገዴ፣ የወሎ መሬት፤ ነገ የአማራው ክልል ገዥ የኔ ነው ቢል፤ ሊገርመን አይገባም። በፍርሃት ፈንታ ድፍረት፣ በመታዘዝ ቦታ ጥላቻ ነግሷልና! ለአዲስ አበባ አስተዳደር ከኦሮሞ ክልል ቆርሶ የወሰደውን መሬት የኦሮሞ ክልል ገዥዎች እንወስዳለን ቢሉ፤ ሊገርመን አይገባም። በደቡቡ ክልል ውስጥ ያሉት የተለያዩ ወገኖች፤ በውስጣዊ የደንበር መካለል ምክንያት ግጭት ማድረጋቸው አይቀሬ ነው። ለምን ቢባል ሁሉን ያደረገው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ በላያቸው ላይ የጫነው የይስሙላ ጥብቆ እንጂ፤ ሕዝባዊ መሠረትና ድጋፍ እንዲኖረው የአካባቢውን ሕዝብ ተሳትፎና ድጋፍ ያልጠየቀ ነበርና! ደግሞም በየክልሉ ያለ አስተዳደር፤ በጉልበት ያፈተተውን በማድረግ በደል ቢፈጽም፤ ለፌዴራሉ ገዥ ክፍል፤ በውስጥ አስተዳደሬ ጣልቃ አትግባብኝ ብሎ አንገቱን ቢያቀና፤ አያስደንቅም። አክሱም ለወላይታው ምኑ ነው ተብሏልና፤ ሞያሌ ላይ የደቡቡ ክልል አስተዳደር ከኬንያ በኩል ችግር ቢገጥመው፤ ሞያሌ ለፌዴራል መንግሥቱ ምኑ ነው? ይባል ይሆን? በባጀት ቢጣሉ፣ በሕዝብ ቁጥር ቢነታረኩ፣ በክልል ደንበር ቢጋጩ፣ በፌዴራሉ ውክልናቸው፤ “እኔ የበላይ!” “እኔ የበላይ!” ተባብለው መኳረፉ፤ አይቀሬ ነው። በርግጥ በፌዴራሉ ደረጃ፤ የኔን አባል አትሰሩ፣ የኔን አባል አትክሰሱ መባባሉ ታይቷል። እስከዛሬ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አባላት ብቻ የፈለጋቸውን ሲያደርጉ፤ የሌሎቹ አባላት አንገታቸውን ደፍተው መቀበላቸው ያለ ነበር። ይህ ግን ጧፉ በርቶ፤ ሰፈፉን አቅልጦ ጨርቁን አቃጥሎ ጨርሶ፤ በርሃኑ እየጠፋ ነው። ስለዚህ፤ በፌዴራሉ ለሚደረግ ማንኛውም ውሳኔና ተግባር፤ ተፎካካሪዎች እንጂ ተደጋጋፊዎች አይደሉም። ለፌዴራል ጉዳይ ሲሰለፉም፤ “እኔ ምን አገኛለሁ?” ከሚል እንጂ፤ “እስኪ ‘ሌሎች’ ምን ቸግሯቸዋልና ልርዳቸው!” ከሚል አይደለም። ስለዚህ ተፎካካሪዎች ናቸው። እስካሁን በአንድነት ያሰለፋቸው፤ የደርግ ማስፈራሪያነት ነበር፤ አበቃለት። ቀጥሎ የተተካው ከደርግ ወጥቶ የፀረ-አማራ አቋምቸውና የዚሁ ወገን ፍራቻቸው ነበር፤ ይህን ወገን እስኪቻላቸው ድረስ አጠቁት። አሁን ምን አለ ሊያዋህድ ቀርቶ እንዲተባበሩ የሚያደርጋቸው? ምንም! ስለዚህ እኒህ ተፎካካሪ ድርጅቶች የጥቅም ግጭት ነው በመካከላቸው የተረፈው። እናም አንደኛው ሌላኛውን መወንጀል ይከተላል። ከውስጡ መፈረካከስ ይቀጥላል። በዚህ ላይ፤ ወጣት አባሎቻቸው፤ ፍጹም የየግል ክልላቸውን የበላይነት ለመጠበቅ የሚቆሙ ይሆናሉ። የተማሩት ይሄንኑ ነውና! እናም ጠባብነት ንጉስ ይሆናል። ግጭቱ አይቀሬ ነው። ይሄንን ለማርገብና ጊዜ ለመግዛት፤ አጭር እርምጃ መውሰድ ይቻላል። ነገር ግን፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነባር አባላት፤ ይህ እንዳይሆን፤ የነሱን የበላይነት ለወጣት አባሎቻቸው እያስተማሩ ያሳደጉበት ሀቅ ስላለ፤ ራሳቸው ራሳቸውን አስረውታል። ወደኋላ ቢሉ በራሳቸው ወጣት አባላት የሚመቱት እነሱ ናቸው። እናም ወደፊት መግፋት ብቻ ነው ያላቸው ምርጫ። ከዚህ ተነስተው፤ “ሌሎች” ክፍሎች ወታደራዊና የፖሊስ ኃይሎቻቸውን ማቋቁምና የውጭ ግንኙነታቸውን መመሥረት ተከታዩ እድገታቸው ነው። እስከዛሬ ይህ ሁሉ በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ፍላጎትና እምነት የሚካሄድ ነበር። የአማራዎች፣ የኦሮሞዎች፣ የደቡብ ኢትዮጵያዊያን ሆነ የሌሎች አናሳ የተባሉ የፖለቲካ ድርጅቶች መስራች፤ ይሄው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነው። እናም ምን ጊዜም ቢሆን፤ ማንኛውም መዋቅር ሆነ የሂደት ውሳኔ፤ ለዚህ ወገነተኛ ቡድን ፍላጎት ተገዥ ካልሆነ፤ የመጀመሪያው አኩራፊ፤ ይሄው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ይሆናል። በመጀመሪያ ግጭቱን ፈጣሪ፤ ጥቅሜ ቀረብኝ በማለት፤ ይሄው ድርጅት ይሆናል። የመጀመሪያው ተገንጥሎ ለብቻው የሚሮጠውም ይሄው ድርጅት ነው። ለዚህም ከወዲሁ፤ ፌዴራላዊ የሆኑ ውሳኔዎችን፤ ክልሉን እንዲጠቅሙ አዘጋጅቷል። የዓለም አቀፍ አየር ማረፊያውን በትግራይ አዘጋጅቷል። ወታደራዊ ማዕከሎችን በትግራይ አቋቁሟል። በትምህርት የትግራይ ወገኖቹን በበላይነት አሰልፏል። አሁን ደግሞ የባቡር ሐዲድ ለትግራይ እንዲገባ፤ ፌዴራላዊ ወጪውን አስሸፍኗል። የሱዳን በር እንዲኖረው ከአማራው መሬት ጠቅልሎ ወስዷል። የሀገሪቱን ንብረት፤ በኤፈርት በኩል እጠቃሎ ትግራይ አግብቷል። ወሳኝ የፌዴራል መንግሥቱ ቦታዎች በሙሉ በአባላቱ ቁጥጥር ሥር ናቸው። ለስም እንኳ ከ”ሌሎች” ድርጅቶች የተወከሉ ሰዎች በኃላፊነት ላይ ቢቀመጡም፤ የወሳኝነቱን ሚና የሚጫወቱት፤ የዚሁ ድርጅት አባላት ናቸው። ስለዚህም የተስተካከለ የእኩልነት አሰራር በሌለበት ቦታ፤ አይቀሬው ግጭት ብቅ እያለ ነው። ይህ ከውጪ በሚደረግ ግፊት ሳይሆን፤ በራሱ በአደረጃጀቱና ( ማለትም፤ በዋናው በ”እኔ” ባዩ ድርጅትና በ”ሌሎች” ድርጅቶች መካከል ባለ አደረጃጀት ) በሂደቱ ምክንያት አይቀሬ ሆኖ የሚታይ ሀቅ ነው። እንግዲህ በክልሎቹ መካከል የሚነሳው ግጭት ለሀገሪቱ ከፍተኛ አደጋ አለው። ይህ ወደ ሶስተኛው ነጥብ ይወስደናል። ሶስተኛው ገጦ የሚታየው እውነታ፤ አሁን በያዝነው ሂደት፤ ሀገራችን እጅግ ወደ ከፋና ልትወጣበት ወደማትችለው መቀመቅ ውስጥ እየዘቀጠች መሆኗ ነው። የክልሎች መጋጨት፤ የማይሰራ የፌዴራል መዋቅር ከላይ ተቀምጦ፤ ጉልበተኛ የክልል ገዥዎች የፈለጉትን የሚያደርጉበትን ሀቅ ያሳየናል። የኢትዮጵያ መንግሥት የሚባለው በኖ ይጠፋል። እኒህ የየክልል ገዥዎች ደግሞ፤ በምንም መንገድ በስምምነት ጎረቤት እንኳን ሆነው የሚኖሩበት ሁኔታ እንዳይኖር፤ በጠላትነት የሚፋረጁ ስለሚሆን፤ በመካከላቸው የማይበርድ ጦርነት አይቀሬ ነው። የሕዝብ ቁጥር መጨመር፣ የአካባቢ ንብረት መመንመን ወይንም አዲስ ሀብት በአንዱ አካባቢ መገኘት፣ ከውጪ በሚደረግ የጥቅም ድጋፍ አንዱ ከሌላው በልጦ መገኘት፣ በሃይማኖት ምክንያት በጎረቤት ክልሎች መካከል የሚፈጠረው ልዩነት መስፋት፣ ክልሎችን የበለጠ እንዲራራቁና አክርረው እንዲጋጩ ያደርጋል። ይህ ነው የነገዋ የሀገራችን የኢትዮጵያ ጣጣ። “እኔ የበለጠ ላግኝ፤ የለም እኔ የበለጠ ላግኝ!” በሚል የተጣሉ ክልሎች፤ ከተለያዩ በኋላ ፍርሻው የሚያስከትለው መዘዝ፤ የማይጨበጥ እሳት ነው። ይህ ሁሉ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የፖለቲካ ቀመር ውጤት ነው። ውጤቱ ደግሞ አይቀሬ ነው። መዝጊያ፤ ውጤቱ ቢያስፈራንም፤ በሀገራችን ላይ ከላይ የተጠቀሰው አደጋ የመከሰት እድሉ ያየለ ነው። በሂደት የዚህ ድርጅት የፖለቲካ ስሌት ሊስተካከል ሲገባው፤ አክራሪ የሆነው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ በጀመረው ጠባብ ዓላማ አሁንም መግዛት ስለያዘ፤ መገራት አቃተው። እናም ለዚህ አይቀሬ እውነታ ዳርጎናል። በርግጥ ስለማንፈልገው፤ ሊሆን አይችልም ብለን ልንሸመጥጥና ልንክደው እንችላለን። ይሄን ጸሐፊም ማብጣልጣል እንችላለን። ያ ግን፤ ሊሆን አደግድጎ የመጣውን ሀቅ፤ አይለውጠውም። ይልቅስ አሁን በቁጥጥራችን ሥር ያለውንና ማድረግ የምንችለውን መጀመር አለብን። በቁጥጥራችን ሥር ያለውና ማድረግ የምንችለው፤ በመጀመሪያ፣ የትግሉን ምንነት በአንድነት መቀበል ነው። ይህ ትግል የነፃነት ትግል ነው። ይህ ትግል የኢትዮጵያዊያን በሙሉ ትግል ነው። ይህ ትግል የዛሬ ነው። ይህ ትግል ከያንዳንዳችን የሚጠብቀው አስተዋፅዖ አለ። በመሳተፍ እናበርክት። ይህን ትግል በአንድነት የምናደርገው እንጂ፤ እያንዳንዱ ድርጅት ለየራሱ ባፈተተው የሚጋልብበት ሜዳ አይደለም። እናም የትግሉ የመጀመሪያ አጭር ግብ፤ ታጋዮችን በሙሉ ወደ አንድ አሰባስቦ አንድ የትግል ማዕከል መፍጠር ነው። እናም በሀገራዊ ራዕይና ተልዕኮ፣ በጥቂት የመታገያ ዕሴቶች ዙሪያ መደራጀቱ፤ ግዴታ ነው። ይህን ግድ የሚለው፤ ተጨባጩ የሀገራችን የፖለቲካ እውነታ ነው። ዋናዎቹ ታጋዮች ያሉት በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ከፍተኛውን መስዋዕትነት በመክፈል፤ ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ጋር ሌት ተቀን በኑሯቸው እየተገደዱ፣ እየተሰቃዩ፣ በእስር ቤት እየተንገላቱ፣ መታገያ ሰላማዊ ድርጅቶቻቸውን እየተቀሙ፣ ያሉት ሕዝቡና የሕዝቡ ታጋይ ልጆች ናቸው። ትግላቸው መስተካከል አለበት። ሰላማዊውን ትግል አንድ ድርጅት ብቻ ነው ሊመራው የሚገባ። በአንድ ሀገር ሁለትና ሶስት ሰላማዊ ትግል የለም። ግቡ ውስንና የጊዜው ገደብ ያለው የትግል አንድነትና መታገያ ድርጅት ነው ሊኖረን የሚገባ። አንድ ትግልና አንድ መታገያ ድርጅት ብቻ ነው የሚኖረው። አንድ የትግል ማዕከል እስካልተፈጠረ ድረስ ደግሞ፤ በተናጠል የምናደርገው ትግል፤ በተናጠል መመታትን ነው የሚጋብዘው። ትግሉ አንድ ነው። መታገያ ድርጅቱም አንድ መሆን አለበት። ይሄን እስካልተቀበልን ድረስ፤ የገዥውን እድሜ እያራዘምን ነው። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46916#sthash.2D92zAri.dpuf

የቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ዘመቻ ለምን?

ዘመቻው የተጀመረው የዛሬ ሁለት ሳምንት ገደማ ይመስለኛል፡፡ ለመጀመሩ ምክንያት የሆነው ደግሞ “ቢቢሲ ትኩረቱን በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ላይ ያደረገ የስርጭት ፕሮግራም ይጀምራል” የሚል ዜና መነገሩ ነው፡፡ ታዲያ ይህንን ዜና ተከትሎ “የስርጭት ቋንቋዎቹ አማርኛ እና ትግርኛ ናቸው” የሚል ወሬ ተደመጠ፡፡ ነገሩ እስከ አሁን ገፍቶ ባይመጣም በትክክል ተብሎ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም የውጪ ሰዎች እንዲህ ዓይነቱን ነገር ለመወሰን ሲነሱ በቅድሚያ የሚያዩት በየሀገራቱ ውስጥ በኦፊሴል የሚሰራባቸውን ቋንቋዎች ነው፡፡ ትግርኛ በኤርትራ፣ አማርኛም በኢትዮጵያ የኦፊሴል ቋንቋ የመባል ደረጃ ያላቸው በመሆናቸው ቢቢሲ በዚሁ ምክንያት ፕሮግራሙን በሁለቱ ቋንቋዎች ለማስተላለፍ ወስኖ ሊሆን ይችላል፡፡ በየሀገራቱ ውስጥ ያሉት ቋንቋዎች ተናጋሪ ብዛት ሲታይ ግን አፋን ኦሮሞ ከሁሉም ይቀድማል፡፡ እንደሚታወቀው በሬድዮ የሚተላለፍ ፕሮግራም የሚሻው አድማጭ እንጂ አንባቢ አይደለም ፡፡ ስለዚህ በኤርትራና በኢትዮጵያ ላይ የሚያተኩረው አዲሱ የቢቢሲ የስርጭት ፕሮግራም አድማጮችን ታሳቢ ያደረገ መሆን ይገባዋል ተብሎ ነው የሚታመነው፡፡ ለቢቢሲም ሆነ ስርጭቱ በሚያተኩርባቸው ሀገራት በጣም የሚጠቅመው አካሄድ ይኸው ነው፡፡ እናም ይህንን ያዩ ተመልካቾች “ቢቢሲ የቪኦኤን ሞዴል ቢከተል የተሻለ ነው፤ አፋን ብዙ ተናጋሪ ያለው አፋን ኦሮሞ ከሁለቱ ቋንቋዎች ጋር መደመር አለበት” በማለት በኢንተርኔት የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ ጀመሩ፡፡ እኛም ዘመቻው ተገቢ ሆኖ ስላገኘነው ፊርማችንን ሰጠነው፡፡ ሌሎችም እንዲፈርሙ መቀስቀሱንም ተያያዝነው፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46934#sthash.mqNYdCst.dpuf


bbc affaan oromo


በእስካሁኑ ሂደት የፈረመው ሰው ብዛት ወደ ሳላሣ ሺህ እየተጠጋ ነው፡፡ በኢንተርኔት ላይ ሆነን እንደታዘብነው ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው፡፡ ሁሉም ወገኖች ዘመቻውን በበጎ መልኩ እያዩት ነው፡፡ እነ አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና ዓሊ ቢራን የመሳሰሉ ታላላቅ ሰዎችም የድጋፍ ፊርማቸውን ሰጥተዋል፡፡ ሌሎችም ድጋፋቸውን እንዲሰጡ እየቀሰቀሱም ነው፡፡ ይህ በጣም ጥሩ ነው፡፡ በተለይም የኢንተርኔቱ ዓለም ከሚታወቅበት “ጽንፋዊ” (polarized) አካሄድ ወጥተን ሁላችንም ፊርማችንን ማኖራችን በእጅጉ የሚያስደስት ነገር ነው፡፡ — የድጋፍ ፊርማችንን ያኖርነው በሙሉ በጎን የማሰብ ዓላማ እንጂ ሌላ ተቀጥላ መነሻ የለንም፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ምክንያቶች በደንብ የተብራሩ አይመስለኝም፡፡ በመሆኑም በጉዳዩ ዙሪያ ይህንን ጽሑፍ አሰናድቼአለሁ፡፡ እንደሚታወቀው “አፋን ኦሮሞ” (ኦሮምኛ) በአፍሪቃ ምድር እጅግ ብዙ ተናጋሪዎች ካሉት ቋንቋዎች አንዱ ነው፡፡ 40 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ቋንቋውን በአፍ መፍቻነት ይናገረዋል፡፡ ከስድስት ሚሊዮን የማያንሱ ህዝቦችም ኦሮምኛን በሁለተኛ ደረጃ ይናገራሉ፡፡ ይሁንና ኦሮምኛን ከሚናገረው ህዝብ መካከል ከ3/4 የሚልቀውና በገጠር የሚኖረው ህዝብ ከኦሮምኛ ውጪ ሌላ ቋንቋን አይናገርም፤ አይሰማም (ነገሩን በተነጻጻሪነት ለማወቅ ካሻችሁ የኦሮሚያ ክልል የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤትን ተመልከቱት)፡፡ ስለዚህ የቢቢሲ ስርጭት ኦሮምኛን ከዘነጋ ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ አይሆንም ማለት ነው፡፡ ታዲያ የሚገርመው ደግሞ በሬድዮ የሚሰማውን ፕሮግራም ከማንም በላይ የሚከታተለው የገጠሩ ህዝብ ነው፡፡ የከተማው ህዝብ በዝንባሌው ለቴሊቪዥን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ለኤፍ ኤም ሬድዮ ነው የሚያደላው፡፡ ቢቢሲ በሬድዮ ፕሮግራሙን ሲጀምር ተጨማሪ አማራጭ የሚፈጠርለት በአብዛኛው ለገጠሬው ህዝብ ነው፡፡ ነገር ግን ኦሮምኛ ከአዲሱ ፕሮግራም ውስጥ ከተዘነጋ የገጠሩ የኦሮሞ ህዝብ ሌሎች ቋንቋዎችን ባለመቻሉ እድሉ ሊያመልጠው ነው፡፡ እንግዲህ ቢቢሲ አፋን ኦሮሞን በስርጭት ሽፋኑ ውስጥ እንዲያካትት በድጋፍ ፊርማ መጠየቁ የተፈለገበት አንደኛው ምክንያት ይህ ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ለህዝቡ አማራጭ የመፍጠር ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ከላይ የተገለጹትን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የኦሮምኛ ተናጋሪዎች የሚመለከት ነው፡፡ እንደሚታወቀው በሶስተኛው ዓለም ሀገራት በአጭር ሞገድ የሚተላለፉ ሬድዮዎች በመንግሥታት የተያዙ በመሆናቸው ህዝቦች መረጃን ከነጻ ምንጭ የማግኘቱ ጉዳይ በጣም ይቸግራቸዋል፡፡ በግል፤ በፖለቲካ ፓርቲ እና በኮሚኒቲ እየተቋቋሙ ወደ አፍሪቃ ምድር ስርጭታቸውን የሚያስተላልፉ ሚዲያዎች በበኩላቸው መንግሥታቱን ለማጋለጥ በሚል ነገሮችን ከልክ በላይ እየለጠጡና እያጋነኑ ለአድማጩ ስለሚተርኩ ግራ መጋባትንና መደናገርን ይፈጥራሉ፡፡ ቢቢሲ፣ ቪኦኤ፣ ዶቼ ቬሌ ወዘተ.. የመሳሰሉት ግን ከሁሉም የተሻሉ ነጻ ሚዲያዎች በመሆናቸው በነርሱ የሚተላለፉት ዘገባዎች ለእውነታ የቀረቡ መሆናቸው ይታመናል፡፡ እናም ቢቢሲ በአፋን ኦሮሞ ፕሮግራም ጀመረ ማለት ኦሮምኛን የሚሰማውና የሚናገረው ህዝብ ነጻ መረጃ የሚያገኝበት እድል ጨመረ ማለት ነው፡፡ ሶስተኛው ምክንያት ደግሞ የቢቢሲ በኦሮምኛ ፕሮግራም መጀመር ለአፋን ኦሮሞ እድገት ወሳኝ ሚና የሚጫወት መሆኑ ነው፡፡ ቢቢሲ ሁሉንም አቀፍ እና በቢሊዮን የሚቆጠሩ አድማጮች ያሉት ተቋም ነው፡፡ የጣቢያው ስርጭት በተመራጭነቱ ቀዳሚ እንዲሆን ያስቻለው በየፕሮግራሙ የሚያስተላልፈው ጭብጥና ይዘት ብቻ ሳይሆን ቀዳሚነቱን ለማስቀጠል የሚያከናውናቸው ተያያዥ መርሐ ግብሮች ጭምር ነው፡፡ ከነዚህ መርሐ ግብሮች አንዱ ስርጭቱን የሚያስተላልፍባቸው ቋንቋዎችን ለማዘመን፣ ለማሳደግ እና ለማስተዋወቅ የሚያደርገው ጥረት ነው፡፡ ተቋሙ ፕሮግራሙን ሲያስተላልፍ የዘፈቀደ የቋንቋ አጠቃቀምን አይከተልም፡፡ ቢቢሲ እያንዳንዱን ቋንቋ በማጥናት የቋንቋው አድማጮች ሁሉ ሊረዱት የሚችሉትን አቀራረብ ይወጥንና በዚያ መሰረት ስርጭቱን ያስተላልፋል፡፡ ራሱ የሚገለገልበት BBC-Standard የተባለ የቋንቋ አጠቃቀም ዘይቤም አለው፡፡ በሌላ በኩል ቢቢሲ ስርጭቱን በሚያስተላልፍባቸው ቋንቋዎች ዙሪያ በሚደረጉት ምርምሮችም ተሳትፎ ያደርጋል፡፡ ቋንቋውንም ለማስተማር ልዩ ልዩ ጥረቶችን ያደርጋል (ለምሳሌ የቢቢሲ የዐረብኛው ፕሮግራም Learn BBC Arabic የተባለ ፕሮግራም አለው)፡፡ በቋንቋው የሚሰለጥኑ ተማሪዎችንም ይደግፋል፡፡ በቋንቋው የሚጻፉ የስነ-ጽሑፍ ውጤቶችን ያበረታታል፡፡ በሬድዮ ጣቢያውም ድርሰቶቹን ያስተዋውቃል፡፡ እነዚህ ተያያዥ ተግባራት ለኦሮምኛ ቋንቋ እድገት እጅግ በጣም ይጠቅማሉ፡፡ እንግዲህ “ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ” የተሰኘውን ዘመቻ ለመደገፍና ሌሎችም ድጋፋቸውን እንዲሰጡት ለመቀስቀስ የወሰንኩት እነዚህን ሁሉ መነሻዎች ካጤንኩ በኋላ ነው፡፡ በመሆኑም ለቋንቋው እድገት የሚቆረቆር እና በተለይም በገጠሩ የሚኖረው ህዝባችን አማራጭ ሚዲያ እንዲፈጠርለት የሚሻ ሰው በሙሉ ሊሳተፍበት የሚገባ ታሪካዊ ዘመቻ ነው ብዬ አምናለ
፡ ከዚህ ቀደም “ኦሮምኛን መማር እፈልጋለሁ” ፣ “ኦሮምኛ ከሌሎች ቋንቋዎች ጋር ያለው ተዛምዶ ለማጥናት ወስኛለሁ”፣ “የዓሊ ቢራን ዘፈን ግጥሞች ትርጉም ማወቅና በርሱ ዙሪያ መጻፍ እሻለሁ” ወዘተ… ስትሉኝ ለነበራችሁት ወዳጆቼ ደግሞ ዘመቻው የናንተንም ሆነ ተመሳሳይ ፍላጎትና ዝንባሌ ያላቸው ሌሎችም ሰዎች ምኞታቸውን እውነት ሊያደርጉ የሚችሉበትን ውጤት ለማምጣት የሚረዳ በመሆኑ ተሳትፎአችሁ በእጅጉ ይጠበቃል፡፡ — ይህ ዘመቻ ማንንም የመጉዳት ዓላማ የለውም፡፡ ዘመቻውን የጀመሩት ሰዎችም ሆኑ በሂደት የተቀላቀሉት ሁሉ ይህንን ጉዳይ በይፋ አስታውቀዋል፡፡ እያሳወቁም ነው፡፡ እኔም ደግሜ አስታውቃለሁ፡፡ ለምሳሌ ቢቢሲ የአማርኛውንም ሆነ የትግርኛውን ፕሮግራም እንዲያስቀር በጭራሽ አልተጠየቀም፡፡ ሊጠየቅም አይችልም፡፡ እንዲህ ብሎ መጠየቁ ከመጥፎ ምሳሌነቱ ሌላ ጥያቄው ተቀባይነት እንዳይኖረው ማድረግ ነው፡፡ ጥያቄው የቀረበው ቢቢሲ የቪኦኤን አርአያ በመከተል ስርጭቱን በሶስቱ ቋንቋዎች እንዲጀምር ነው (ስርጭቱን የሚያስተላልፍበትን የጊዜ መጠን የመወሰኑ ስልጣን የጣቢያው ነው፤ ያንን እኛ አንወስንለትም)፡፡ በመሆኑም ይህ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል፡፡ —- ስለዚህ ወዳጆቻችን ሆይ! ይህ ዘመቻ የተቀደሰ ሃሳብ ያለው ነው፡፡ የድጋፍ ፊርማችሁን በማኖር የዘመቻው ደጋፊ እንድትሆኑ በአክብሮት ትጠየቃላችሁ፡፡ ለዚህ ደግሞ ብዙ መሰዋት አያስፈልጋችሁም፡፡ ሶስት ደቂቃ ብቻ ወስዳችሁ ለዚሁ የተዘጋጀውን petition መፈረምንና ወደሚፈለግበት ቦታ send ማድረግን ብቻ ነው የሚጠይቀው፡፡ እናም ቀጥሎ የተመለከተውን ሊንክ ከፍታችሁ ፔቲሽኑን ፈርሙልን!! ዳይ https://www.gopetition.com/…/bbc-consider-afan-oromo-for-ne… —- ማስታወሻ • ፔቲሽኑን መፈረም ማለት ሊንኩን ከፍቶ ፎርሙን መሙላት ነው:: ስለዚህ ሊንኩን ከፍታችሁ ወደ መፈረሚያው ሂዱልን!! ፎርሙ የሚመጣላችሁ sign the petition የሚለውን ቦታ ስትነኩት ነው፡፡ • ፔቲሽኑን ለመፈረም የግዴታ የኢ-ሜይል አድራሻችሁን ማስገባት አለባችሁ፡፡ ከዚያም የቀረቡትን ጥያቄዎች በመከተል ፎርሙን መሙላት ይገባችኋል፡፡ መጨረሻ ላይ የተሞላውን ፎርም send አድርጋችሁ ስታበቁ ፊርማውን ስለመስጠታችሁ ማረጋገጫው በኢ-ሜይል ይላክላችኋል - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46934#sthash.mqNYdCst.dpuf

Friday, September 25, 2015

በሕዝብ ጫና የሕወሓት መንግስት የአቡነ ጴጥሮስን ሐውልት ወደ ቦታው ሊመልስ ነው

abune_petrosየአቡነ ጴጥሮስን ሐውልት ከስፍራው በልማት ስር አንስቶ ታሪክን ሊያጠፋ ነበር ተብሎ ሲተች የነበረው የሕወሓት አስተዳደር ሕዝቡ በአደባባይ ይህን ታሪክ ሐውልት እንዲመልስ ባደረገው ጫና መሰረት ወደ ቦታው ሊመልስ መሆኑ ተሰማ:: መንግስታዊው ራድዮ ፋና “የአደባባይ ዲዛይን ስራ እየተገባደደ በመሆኑ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት በቅርቡ ወደ ቀድሞ ስፍራው እንደሚመለስ ተገለፀ” በሚል ዜናውን ቢያስነብብም ሕዝቡ አሁንም ሐውልቱ እስኪመለስ ድረስ ተቃውሞውን እንደሚቀጥል ታውቋል:: በተለያዩ ሶሻል ሚድያዎችም ሐውልቱ ቦታው እስኪመለስ እንጮሓለን የሚሉ መል ዕክቶች እየተሰራጩ ነው:: መንግስታዊው ራድዮ ፋና ስለሐውልቱ ወደ ቦታው ሊመለስ መሆኑን እንደሚከተለው ዘግቦታል:: እንደወረደ እነሆ:- አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት የሚያርፍበት አደባባይ ዲዛይን ዝግጅት የመጨረሻ ምእራፍ ላይ የደረሰ በመሆኑ ግንባታ ተካሂዶ ሀውልቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቀድሞ ስፍራው እንደሚመለስ የፌደራል የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ ገለፁ። አቶ ዮናስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ሀውልቱ የሚያርፍበት አደባባይ ገፅታ እና ይዘት ምን መምሰል አለበት ለሚለው የመጨረሻ መልስ ለመስጠት የቀላል ባቡሩ ስራ የሚጀምርበት ጊዜ ሲጠበቅ ቆይቷል። ይህም ያስፈለገው ባቡሩ በሚንቀሳቀስበት ወቅት የሚፈጠረውን ንዝረት አጥንቶ የአደባባዩን ዲዛይን ማጠናቀቅ ስላስፈለገ ነው ብለዋል። አደባባዩ ሊኖር የሚችለውን ንዝረት በተግባር ተፈትሾ መገንባቱ ወደፊት ሀውልቱ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳይደርስበት ያደርጋልም ነው ያሉት። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46910#sthash.QiEq1E2e.dpuf       ታሪካዊው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሲነሳለፈው እሁድ ቀደም ሲል ሀውልቱ የነበረበትን ስፍራ የሚያካልለው የሰሜን-ደቡብ የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር መስመር አገልግሎት በመጀመሩ የንዝረት መጠኑን በተመለከተ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን አቶ ዮናስ አስረድተዋል።
መረጃ የመሰብሰቡ ስራ እንዳበቃም የአደባባይ ዲዛይኑ ተጠናቆ ወደ ግንባታ ይገባል፤ ከዚያም ሀውልቱ በቀድሞ ስፍራው ይተከላል ብለዋል።
ለአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ግንባታ ሲባል 2005 ዓመተ ምህረት ሚያዚያ ወር ላይ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ከቆመበት ተነቅሎ በብሔራዊ ሙዚየም
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46910#sthash.QiEq1E2e.dpuf

የደህነቱ ሀላፊ ጌታቸው አሰፋ ወንድም የመቀሌ ከንቲባ ሆኑ ፣የህወሓት የስልጣን ሽኩቻ የመቀሌው ቡድን መሪ አባይ ወልዱ በአዲሱ ካቢኔ ተመልሰው ፕሬዝዳንት ሆኑ

የህወሓት ባለስልጣናት የስልጣን ሽኩቻ የመቀሌውን ቡድን በመምራት የበላይነታቸውን አስጠብቀው ወጥተዋል የተባሉት አቶ አባይ ወልዱ በአዲሱ ካቢኔ ተመልሰው ክልሉ ፕሬዝዳንት ሆኑ ሲሆን የመቀሌን ከተማ በከንቲባነት ለመምራት ሙሉ በሙሉ በህወሓት ቁጥጥር ስር ያላውን የአገሪቱን ደህነት መ/ቤት የሚመሩትና ስርዓቱ የሚፈጽማቸውን ግድያና ማሰቃየት ተጠያቂው አቶ ጌታቸው አሰፋ ወንድም ዳንኤል አሰፋ በአዲሱ ካቢኔ የመቀሌ ከንቲባ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46912#sthash.X6xaJ4Ng.dpuf


abay weldu 2ክልሉ ም/አስተዳዳሪ ዶ/ር አዲስ ዓለም ባሌማ፣የትዕምት ሀላፊ አቶ በየነ መክሩ ፣በቀድሞው የህወሃት ፕሮፖጋንዳ ሀላፊ ቴዎድሮስ ሀጎስ አቶ አለም ገብረዋህድ በቦታው በአዲሱ ካቢኔ የተመረጡ ሲሆን በአቶ ኤርሚያስ ለገሰ ቱርፋቶች ባለቤት አልባ በካሳንቺሱ መንግስት ውስጥ የተጠቀሰችው ሞንጆሪኖ (ፈትለወርቅ) የህወሃት ህዝብ አደረጃጀት መሆናቸውን ያገኘነው መረጃ ይገልጻል። ህወሓት የአገሪቱን ዋና ዋና ስልጣን በአንድ ብሄር የበላይነት፣ወታደራዊ፣ዋና ዋና ኢኮኖሚ ተቃማቱንና ደህነቱን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ በቤተሰብና በቡድን የተከፋፈሉትን ስልጣን ከፌዴራል እስከ ክልል መቆጣጠራቸውን አንዳንዶች ከህወሃትም በስልጣንና በሀብት የናጠጠው ቡድን ጥቂት ግለሰቦች የሚያሽከረክሩት ነው ይባላል። ቀድሞ የመለስ አዜብ ቡድን፣የስብሃት ቡድን፣የነአርከበ ቡድን ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው። የህወሓት ባለስልጣናት የመቀሌና የአዲስ አበባ በሚል ከህወሃት ጉባዔ በፊት የጀመሩት የስልጣን ሽኩቻ አንዱ የአንዱን ደጋፊ ወደ ማሳደድ እንደዘለቀ አስቀድመን መዘገባችን አይዘነጋም።የመቀሌው ቡድን በአቶ አባይ ወልዱ የሚመራ ሲሆን የአዲስ አበባው በዶ/ር ደብረጽዮን ይመራ እንደነበርና የአቶ አባይ ቡድን በጉባዔው በአነስተኛ ድምጽ ተመርጦ በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ለትልቁ የፓርቲ ስልጣን በርካታ ደጋፊዎቹን ማስመረጡን አምዶም ገ/ስላሴን ጠቅሰን በስፋት መዘገባችን ይታወሳል - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46912#sthash.gn2U7rsu.dpufabay weldu

Tuesday, September 22, 2015

ቢቢሲ ወደ ኢትዮጵያ ሊያስተላልፍ ያቀደው ፕሮግራም እና የቋንቋ ምርጫ

ቢቢሲ ወደ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሚተላለፍ የዜና ፕሮግራም ለመጀመር ፍላጎት እንዳለው ማሳወቁን ተከትሎ አንዳንድ እራሳቸውን “ኦሮሞ ፈርስት” በማለት የሚጠሩ የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች ቢቢሲ ወደ ኢትዮጵያ ለማስተላለፍ ያሰበውን ፕሮግራም በኦሮምኛ ቋንቋ እንዲያደርግ ፔትሽን በማስፈረም ላይ መሆናቸው ታውቋል።BBC world news to Ethiopia
ቢቢሲ ወደ ኢትዮጵያ ሊያስተላልፍ ያሰበው የዜና ፕሮግራም በምን ቋንቋ እንደሆን የገለጸው ነገር የለም።
ቢቢሲ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ፕሮግራሙን ቢያስተላልፍ ተደማጭነቱ እና ተደራሽነቱ እጅግም ይሆናል፣ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ እንግሊዘኛ ቋንቋን ስለማይነጋገር።
ቢቢሲ ወደ ኢትዮጵይ ሊያስተላልፍ ያሰበውን የዜና ፕሮግራም በሃገሬው ቋንቋ እንዲሆን ከወሰነ ግን የአማርኛ ቋንቋን ይጠቀማል ተብሎ ይገመታል። አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ አማርኛ ቋንቋን ከመናገሩም ባሻገር አማርኛ የኢትዮጵያ የስራ ቋንቋ ሆኖ ኖርዋል።
ምናልባት ቢቢሲ ፕሮግራሙን በተለያዩ ሃገራዊ ቋንቋዎች ለማስተላለፍ ከወሰነ ደግሞ ከአማርኛ ቀጥሎ ኦሮምኛ ቋንቋን በቀዳሚነት ሊጠቀም ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
የቢቢሲ ጀነራል ዳይሬክተር ቶኒ ሃል እንዳሉት ከሆነ በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሰሜን ኮሪያ እና ራሺያ “የዲሞክራሲ እጥረት” በመኖሩ ያንን ቀዳዳ ለመሸፈን በማሰብ ነው ቢቢሲ በእነዚህ ሃገራት አዲስ የዜና ፕሮግራሞችን ለማሰራጨት ያሰበው።

በኢትዮጵያ ታሪክ ጉዳይ ላይ ኢሕአዴግን እንዴት ማመን ይቻላል?!

በዲ/ን ኒቆዲሞስ ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል የኢትዮጵያችን ልዩ ቅርስ በኾነው የዘመን አቆጣጠራችንን በተመለከተ አንድ ጥያቄ አንስቶአል፡፡ ይኸውም የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር በተመለከተ ‹‹ጠቅላይ ሚ/ሩን እንመን ወይስ አርቲስቶቻችንን?!›› የሚል ጥያቄ አንስቶ አንድ ትዝብትና ማሳሰቢያ አከል ጽሑፍ አስነብቦናል፡፡ እኔ ግን እንዲህ እላለሁ በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠርም ሆነ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ታሪክ ጉዳይ ላይ ኢሕዴግን/ክቡር ጠቅላይ ሚ/ሩን እንዳናምናቸው የሚያደርጉን አንዳንድ የታሪክ ሐቆች እንዳሉ ላንሣ፡፡ እስቲ እነዚህን ሐቆች በጥቂቱ ብቻ ለማየት እንሞከር፡፡ በመሠረቱ የአገሪቱን ታሪክ ወደ መቶ ዓመት አውርዶ ለሚተነትነው፣ ጥንታዊው የሆነው ፊደላችን፣ ሦስት ሺሕ ዘመንን ያስቆጠረውን የሥነ-መንግሥት ታሪክ ‹‹የአቢሲኒያውያን/የነፍጠኞች ቅኝ ገዢዎች ታሪክ›› አድርጎ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ታሪክ በብሔር ብሔረሰቦች ማዕቀፍ ቀንብቦ ዳግም ለመፍጠር ለሚውተረተረው፤ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሚመሩት የኢሕአዴግ መንግሥት በምን ሞራልና ተጠየቅ፡- ‹‹ከአፍሪካ አገራት ሺሕ ዘመናትን ያስቆጠረ የራሳችን ፊደልና የዘመን አቆጣጠር ያለን ኩሩ ሕዝቦች …፡፡›› ተብሎ በአደባባይ ሊነግሩን እንደደፈሩ አይገባኝም፡፡ የታሪክ እውነት/ሐቅ ሲያሻን የምንደርበው እንዲያ ሲል ደግሞ አውልቀንና አሽቀንጥረን የምንጥለው የበረሃ ሽርጥ ኾነ እንዴ ጎበዝ …?! ይሄ በእውነት ያስተዛዝባል፡፡ ወይስ ደግሞ እንደው ሳንሰማ ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያለውን አቋም አስተካክሎ ይሆን እንዴ … እ…እ…እ… አይመስለኝም፡፡ በዚህ ረገድ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትራችን የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊም፣ ‹‹… የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ ዓመት ታሪክ ነው፣ የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑ ነው …?! እንዳላሉን ኹሉ የኢትዮጵያ ሚሊኒየም ሲከበር ባደረጉት ንግግራቸው፣ ‹‹… እኛ ኢትዮጵያውያን የሦስት ሺሕ ዘመን ታሪክና መንግሥት ያለን ነጻና ኩሩ ሕዝቦች …›› ሲሉ ሰምተናቸው መገረማችንን አስታውሳለኹ፡፡ እዚህ ጋራ የኢትዮጵያን ታሪክ ‹‹በአቢሲኒያውያን/በነፍጠኞች ቅኝ ግዛት ወረራ›› የታሪክ መነጽር የሚመለከተው ኢሕአዴግ ሙሉ ድጋፉንና ፈቃዱን በቸረበትና የኤርትራውያን ጥያቄ ‹‹የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው›› በሚል የኤርትራውያን ነጻ እንዲወጡ ባደረገበት ወቅት የኾነውን የታሪክ ቀውስም በጥቂቱ ማየት እንችላለን፡፡ ትናንትና የኢትዮጵያ አካል የነበሩት ኤርትራውያን ወገኖቻችን ነጻነታቸውን ባወጁ ማግሥት የዘመን አቆጣጠራቸውን ወደ ጎርጎርሳውያን የቀየሩት የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ቅኝ ገዢዎቹ አቢሲኒያውያን/ነፍጠኞች እንደ ብርድ ልብስ የደረቡብን የእኛ ያልሆነ- ታሪካችንን፣ ቅርሳችንንና ማንነታችንን የሚያራክስ፣ የሚያጣጥል ነው በሚል አመክንዮ እንደሆነ የምንስተው አይመስለኝም፡፡ የኋላ ኋላ የኾነውን ነገር ኹሉ እናስታውሳለን፤ ባልነበረ የፈጠራ ታሪክ ሺሕዎች ጭዳ የኾኑበትን የጦርነት፣ እልቂት መዘዝ በኀዘን እናስታውሳለን፡፡ አሁንም ድረስ የኹለቱ አገራት ጉዳይ የተዳፈነ እሳት ሆኖ አለ፡፡ በዚሁ የፈጠራ ታሪክ ጦስ የሆነውን ሌላኛው ትዝብቴን ላክል፡፡ ኤርትራዊ ብሔርተኝነትን በአዲስ የታሪክ ሂደትና ትንታኔ ለመፍጠር ሲውተረተር የነበረው የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂና ደጋፊዎቹ/ብሔርተኛ ኤርትራውያን ባለፈው ዓመት ደግሞ፣ ‹‹… ለመሆኑ እንደው የሆነስ ሆነና ኢትዮጵያ ከማን ተሸላ ነው እኛን ሥልጡን፣ የራሳችን የዘመናት ታሪክ፣ ቅርስ፣ ባህልና ሥልጣኔና ያለንን ሕዝቦች ቅኝ ለመግዛት የቻለችው?!›› በሚል ለዓመታት ሲያቀነቅኑ የነበረውን ‹‹ኢትዮጵያ ቅኝ ገዘታናለች›› የሚለውን የታሪክ ምጸት በውስጣቸው የፈጠረውን የበታችነት ስሜትና የማንነት ቀውስ በሌላ ተረት ተረት ላማከምና ኤርትራዊ ብሔርተኝነትን በሁለት እግሩ ለማቆም ደፋ ቀና ሲሉ ታዝበናቸዋል፡፡ በተጨማሪም ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብንም ለዘመናት ሲጠቀምበት የነበረውን ፊደሉን ከግእዝ ፊደል ወደ ላቲን ፊደል እንዲቀይር ያስገደደው ይኸው ኢሕአዴግ በሚያቀነቅነው ‹‹የአቢሲኒያውያን/የነፍጠኞች የቅኝ ገዢዎች ታሪክ›› ትንታኔ መነሻነት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ታዲያ ባለ ሥልጣኖቻችን እንዲህ የሚያጣጥሉትንና የሌሎችና ታሪክና ቅርስ፣ ማንንት ያመከነና የዘረፈ ነው ብለው የሚከራከሩበትን የኢትዮጵያን ታሪክና ቅርስ እንዴት በአደባባይ ሺሕ ዘመናትን ያስቆጠር የፊደል፣ የዘመን አቆጣጠር ያለን የሦስት ሺሕ ዘመናት ታሪክ ባለቤት ሕዝቦች ሊሉን የቻሉበትን ድፍረት የት እንዳገኙት ለመጠየቅ፣ ለመሞገት እንገደዳለን፡፡ እንዲህ እንደ እስስት በመለዋወጥስ የታሪክ ሐቅን መለወጥ ይቻላል እንዴ?! ከኢትዮጵያን ታሪክ አንስቶ እስከ ፊደላችን ድረስ በርካታ ጥያቄዎች አሉብን፡፡ ለአንዳንዶች የኢትዮጵያ የሺሕ ዘመናት ታሪክ የአቢሲኒያውያን/የነፍጠኞች ቅኝ ግዛት ታሪክ እንደሆነ ነው የሚሰማቸው፡፡ ለአንዳንዶች ደግሞ ፊደላቱ ያለ ቅጥ በዝተዋልና ይቀነሡ በሚል ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከራሉ፡፡ ይህን ጥያቄ መዳኘትና መልስ መስጠት የሚገባቸው ከእውነት ጋር የወገኑ የእውቀት ሰዎች-ጠቢባኑ ደግሞ ከመድረክ ተገፍተው ታሪክን እንዳሻቸው የሚተነትኑ አድር ባዮች፣ በአገሪቱ ታሪክ ማኅፀን ሌላ ለከፋፋይ ፖለቲካቸው የሚመቻቸውን ጽንስ እያበጁ እያየንና እየሰማን ይኸው በፍርሃት ተሸብበን አለን፡፡ እነርሱም ያለ ምንም እፍረት ታሪካችንን ለጊዜያዊ ፖለቲካቸው ጥቅም ሲሉ እንዳሻቸው ሲለዋውጡት በአግርሞት እያየናቸውና እየሰማናቸው ነው፡፡ በመጨረሻም ወደ ዘመን አቆጣጠራችን ጉዳይ ስመለስ ዛሬ ዓለም ኹሉ እየተደመመበት ያለውንና ይህ የዘመን አቆጣጠርም ከሥነ ፍጥረት ሕግና ሂደት ጋራ የተስማማ እንደሆነ የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት የካቶሊኩ ፖፕ የነበሩት ጀርመናዊው ፖፕ ቤኔዲክት የአውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር ስህትት እንደሆነና ከአውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር ይልቅ ይኸው የእኛው የኢትዮጵያ ዘመን አቆጠጠር ትክክል እንደሆነ Jesus of Nazareth: The Infancy Narratives በሚል መጽሐፋቸው ለመላው ዓለም አሳውቀዋል፡፡ የኢትዮጵያን ዘመን አቆጣጠርና ደማቅ ክብረ በዓሉን በተመለከተ ደግሞ ዘንድሮ በተለየ ሁኔታ እንደ ለንደኑ ቢ.ቢ.ሲ፣ የአሜሪካው ሲ.ኤን.ኤን፣ የዶሃው አልጀዚራና የኢራኑ ፕሬስ ቴሌቪዥኖች ሽፋን በመስጠት ዘግበውት ነበር፡፡ በተለይ ደግሞ የኩባ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በስፓኒሽ ቋንቋ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኩባውያን ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ሰፊ ሽፋን ሰጥተው ልዩ ዘገባ እንዳቀረቡ ተከታትለናል፡፡ ተወደድም ተጠላ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅርስ የኾነው ይህ የዘመን አቆጣጠራችን ከአፍሪካ አልፎ የዓለም ኹሉ ቅርስ ወደመሆን እየተሸጋገረ እንዳለ እየታዘብን ነው፡፡ ይህን ዓለም ሁሉ አምኖ የተቀበለውንና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ደማቅ አሻራ ያለበትን የአገሪቱን የታሪክ ሐቅ መካድ፣ ማፋለስ፣ መበረዝ፣ … ከራስ ጋራ፣ በፍቅርና በአንድነት የጥበብ ልዩ ሸማ ከተዋበው፣ ዘመናት ካልሻሩት ኢትዮጵያዊ ማንነት፣ ታሪክና ቅርስ ጋራ መጣላት መሆኑን በመግለጽ ልሰናበት፡፡ ሰላም! 

መንግሥት እርዳታ ፈላጊነቱን በይፋ አመነ



Redwan


“መንግሥት እርዳታ ፈላጊነቱን በይፋ አመነ !” መባሉ  ምን አዲስ ነገር አለው ፣ለዛውም የኢትዮጵያ መንግስት በማለት እንዳትሸወዱ ! የህውሓት/ኢህአዲግ ገዥው መንግሰት የምግብ እርዳት እና ድርቅን ለመከላከል ፣ሞቼ ነው በቁሚ የምለምነው ሲል ነበር፡፡ በአገራችን በኢሊኒኖ ምክንያት በተከሰተው ድርቅ፣ በሰው ሕይወት እና በእንስሳት  ላይ እየደረሰ ያላው አደጋ አሳሳቢነት አስመልክቶ ፤የመንግሰት ኮሚኒኪሽን ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሬዲዋን ሁሴን “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን ፣ ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” በማላት የመንግስታቸውን አቋም ነሐሴ ወር 2007 ዓ.ም መግለፃቸው የሚታወስ ነው፡፡ አቶ ሬዲዋን መግለጫውን በሰጡ ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ   ዳያስፓራ ነን ባዩችን በሚሊኒየም አዳራሽ ሰብስበው “አሁን በክረምቱ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ከላይ እስከታች ድርቅ አጋጥሞናል……፣ወዳጆችን በዚህ ሰዓት ተሯሩጠው መጥተው እርዳታ ይሰጡን ነበር ፣አሁን እስኪ እናያቸዋለን በማለት ዳር ነው የቆሙት……. ፣አቅማችን እየጎለበተ ስለመጣ እራሳችን ገዝተን እራሳችን አቅርበን ህዝባችን እንዳይራብ እናደርጋለን ።” በማለት በድፍረት ተናግረዋል፡፡ይህ የድፍረት ንግግራቸው በቀጥታ ስርጭት በኢቲቪ ተላልፏል፡፡ “ጉድ እና ጅራት ….” እንደሚባለው ሆነና አቶ ሬዲዋን ሁሴን ዛሬ ማለትም መስከረም 10 ቀን 2008 ዓ.ም የመንግስታቸውን አቋም ሲገልፁ ፤በኢሊኒኖ ምክንያት በተፈጠረው የዝናብ እጥረት የተጎዱ ዜጎች ቁጥር ቀድሞ ከተገመተው 2ነጥበ9 ሚሊየን ህዝብ በማሻቀብ ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ደርሷል፣ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተጠበቀው ድጋፍ በሚፈለገው መልኩ አልተገኘም፣ይህም በመሆኑ ለልማት ከያዘው በጀት እንጠቀማለን “አሉ”፡፡ ይሄ መንግሥት ነኝ ባይ ህውሓት/ኢህአዲግ በዚህ ደረጃ፣ በአገር እና በህዝብ ላይ መቀልዱ የወደፊት የታሪክ ተጠያቂነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፤አሁን ላይ የሥርዓቱ ውድቀት እየተፋጠነ ለመምጣቱ ከምክንያቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ “የተራበ ህዝብ መሪውን ይበላል” መባሉ ቀርቶ መሆኑ ይመጣ ይሆን ? መልሱን አብረን እንጠብቃለን፡፡ አሁንም ግን በአገራችን በሰሜን ምስራቅ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ መጠኑ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በተለይ በእንስሳት ላይ እየደረሰ ያለው አደጋ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ወገኖቻችን በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ለሞት እየተዳረጉ ነው፡፡የችግሩ አሳሳቢነት ደረጃ ከፍ ማለቱ ገዥው ህውሓት/ኢህአዲግ መንግስት ለመሸሸግ አልቻልም፡፡ በግልፅ ቋንቋ “ከውጭ የሚጠበቀው ድጋፍ ካልተገኘ መንግስት ለልማት የመደበውን ሀብት በማዞር ለዜጎች ምግብና ለእንስሳት የሚሆን መኖ ለማቅረብ እግደዳለው” በማላት በአቶ ሬዲዋን ሁሴን በኩል ገልፆዋል፡፡እንዲህ አይነቱ መንግስታዊ ማስፈራራት ምክንያቱን እና ውጤቱን ለመገመት ቀላል ነው፡፡ ከአንድ ወር በፊት እኔ በግሌ እንዲሁም የተለያዩ ግለሰቦች እና ተቋማት፣ ከመገናኛ ብዙሃን ኢሳት እና የውጪ ሃገር ሚዲያዎች፣ የችግሩን አሳሳቢት በተቻለ አቅም ለመግለፅ ተችሎአል፡፡በተለይ መንግሰት “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን ፣ ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” በማላት በድፍረት ሲናጋር ፣ይሄ ነገር ተገቢ አይደለም ፣የሚመጣው ነገር አይታወቅም ከአጉል ቀረርቶ እና ባዶ ሽለላ መቅረት አለበት፡፡ ስለዚህም ከችግሩ አሳሳቢነት እና ወደፊት ከሚያስከትለው አደጋ አንጻር፣ ለዓለም አቀፍ ማህብረሰብ እንዲሁም ለለጋሽ ድርጅቶች እርዳታ መጠየቅ አለበት፡፡በማለት የችግሩ አሳሳቢነት ለገለፁ ለአገር ወዳድ እና ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊያን የተሰጠው ምልሽ “አቅማችን እየጎለበተ ስለመጣ እራሳችን ገዝተን እራሳችን አቅርበን ህዝባችን እንዳይራብ እናደርጋለን ።” በማለት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በአደባባይ ተዘባበቱ፡፡ ይሄን በተናገሩ ሁለት ወር ሳይሞላ የሚረዳን አጣን፣ለዚህ ጉዳይ የያዝነው ገንዘብ እያለቀ ነው፤ከዚህ በኋላ ለልማት የያዝነውን ገንዘብ ነው የምንጠቀመው፤ሲሉ መስማት ያሳፍራል፡፡ነገ ደግሞ ለልማት የያዝነው ገንዘብ ድርቁን ለመከላከል ያወጣነው ስለሆነ፣ አገር የምናስተዳድርበት ገንዘብ የለንም ይሉ ይሆን ? ያኔ ጊዜ “የተራበ ህዝብ መሪውን ይበላል” መባሉ እርግጥ ይሆናል፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46828#sthash.ceVcAyPq.dpuf

የአንዱዓለም ተፈራ የአገር አንድነት አስተሳሰብ እና የቅማንት ህዝብ መፃኢ ዕጣ-ፈንታ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46802#sthash.yXVnbXkL.dpuf

ከብርቱካን ወለቃ አንዱዓለም ተፈራ የሚባሉና የኢህአዴግንና የፌደራል ሥርዓቱን የሚቃወም ጹህፍ በ‹‹እስከመቸ›› የሚባል ድህረ-ገጽ የሚያዘጋጁ ‹‹ፀኃፊ››  በቅማንት ህዝብ ላይ ኢትዮሚዲያ ዶት ኮም (www.ethiomedia.com ) ላይ በተደጋጋሚ የሚለቋቸውን ፁህፎች ለመጀመሪያ ጊዜ ስመለከት እንደሌሎች ሁሉና በተለመደው መንገድ ግላዊ ስሜታቸውን ለማርካት የሞነጫጨሩት ስለመሰለኝ ምንም ነገር ሳልል ረዘም ላለ ጊዜ አልፌው ነበር፡፡ ጉዳዩ እየተደጋገመ ሲመጣ ግን ዝም ስለተባሉ ‹‹እትንን እትን ካላሉት—›› እንደሚባለው የሚሉትን ተግንዝቦ ሀይ የሚላቸው ሰው የሌለና እሳቸው የሚሉት ነገር ብቻ ትክክል የሆነ እንዳይመስላቸው ይህን መልስ ለመስጠት ተገድጃለሁ፡፡ እኝህ ግለሰብ በመጋቢት 21/2007 ‹‹የቅማንትን ክልል መመስረት በሦስት መንገዶች›› በሚል ርዕስና በነሀሴ ወር 2007 በዚሁ ድህረ-ገፅ ላይ ‹‹የማይለቀን የቅማንት ጉዳይ፤ ብለው ብለው ለአቤቱታ ወደእኛ መጡ›› በሚል ርዕስ ፅፈዋል፡፡ በዚህ ጸህፌ በመጀመሪያ በፃፉት ርዕሰ-ጉዳይ ላይ መልስ ይሆን ዘንድ ይህን አጭር ፁህፍ ለመፃፍ ተግድጃለሁ፡፡ እርግጥ ነው ለእንዲህ አይነት የወረደ አስተሳሰብ መልስ መስጠት ጊዜን ማባከንና እንደሳቸው ሀሳብ የወረደ ሊመስል ቢችልም ግለሰቡ ራሳቸውን አዋቂና የፖለቲካ ተንታኝ  አድርገው እንዳይመለከቱ መልስ  ለመጻፍ ተገድጃለሁ፡፡ በእርግጥ ለሁለተኛ ጊዜ በፃፉት መጣጥፍ ላይ እጅግ በሚምር ቋንቋ ተከሽኖ መልስ ተሰጥቷቿል፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እኔም በቀጣይ የግሌን ሀሳብ እጨምራለሁ፡፡ ግለሰቡ ‹‹የቅማንትን ክልል መመስረት በሦስት መንገዶች›› በሚል ርዕስ የፃፉት ፁህፍ ማጠንጠኛው ጊዜ ባለፈበትና በ19ኛው ክ/ዘመን የፖለቲካ ርዮት ዓለም (political ideology: Establishing strong and united nation through putting multiethnic people together) ላይ የተቃኘ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ለእኝህ ግለሰብ የኢትዮጵያ አንድነት የሚረጋገጠው አንድ ህዝብ፣ አንድ ሀይማኖት፣ አንድ  ቋንቋ በሚለው የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ ተገዥነት በ1960ዎቹ አካባቢ ነፃ ሲወጡ በመሬት ላይ የነበረውን ተጨባጭ ሁኔታ ሳይገነዘቡ ያራመዱት የነበረው አገር የመገንባት አስተሳሰብ ቀጥታ ነፀብራቅ ነው ማለት ይቻላል፡፡ እኝህ ግለሰብ አማራ እና ቅማንት የሚባል ህዝብ መኖሩን በራሳቸው አንድበነት ስለአንድ የጭልጋ አካባቢ ግለሰብ ሲያወሩ ‹‹በአባታቸው ከቅማንት በእናታቸው ደግሞ ከአማራ የተወለዱ ግለሰብ እንደሆኑ ይነግሩንና ከዚህ ግለሰብ የተወለዱት ልጆች ደገሞ የቅማንት ዝርያ ቢኖራቸውም የሚያደሉት ለዐማራነታቸው ነው›› ይላሉ፡፡ ይህን ካሉ በኋላ ቀጠል ያደርጉና  እንዲህ ይላሉ‹‹በእርግጥ ለእኔ ቅማንት ከአማራ የሚለየው በምንድነው?›› ብለው ራሳቸውን ይጠይቃሉ፡፡ ይሁን እንጅ አማራ የሚባለው ህዝብ ከቅማንት የሚለይበትን ምክንያት ፈፅመው ማወቅም ሆነ ጠይቆ መረዳትን አይሹም፡፡ ምክንያቱም ለእሳቸው በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም ህዝቦች በተለይ ደግሞ የአገው አካል የሆነው ቅማንት የአማራ ተቀጥላ እንጅ ራሱን የቻለ ህዝብ ነው ብሎ ማሰብ እጅግ ከመክበድም አልፎ የራሳቸውን ዘር ዝቅ ማድረግ መስሎ ይሰማቸዋል፡፡ ለእኝህ ግለሰብ በኢትዮጵያ የሚገኙ ህዝቦች በሙሉ መጤ ሲሆኑ ነገር ግን እራሳቸው ተገኘሁበት የሚሉት ህዝብ ግን ኢትዮጵያ የምትባልን ምድር ጠፍጥፈው የሰሩና በካስማ ወጥረው የዘረጉ ያክል ብቸኛ ባለመበት እንደሆኑ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ ‹‹ኦሮሞ ፣ቅማንት ትገሬ ፣ ሲዳማ፣አፋር ነኝ›› የሚል ህዝብ ካለ ደግመ ወደ ማዳጋስካር ወደ ግብፅ  ወደ የመን እንዲመለሱ ይመክራሉ፡፡ የአማራ ክልል ለምን እንደተቋቋመ ምንም ነገር ሳይተነፈሱ ‹‹የቅማንት ራስን በራስ ማስተዳደር በወያኔ/ኢህአዴግ/ የተጠነሰሰ አማራን የማዳከም ሴራ ነው›› ይሉናል፡፡ ለዚህ ግለሰብ ለእሱ መብት የሆነው ለሌላው ግን ወንጀል እንደሆነ ይነግሩናል፡፡ህወሀት በዚች አገር ከመምጣቱ በፊት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እንዴት ሲኖሩ እንደነበር የኢትዮጵያ ህዝቦች ህያው ምስክር ናቸው፡፡  ቅማንት የሚባል ህዝብ በማንነቱ ምክንያት እንዴት እየተዋረደ፣ እየተሰደበ እንደኖረና በዚህም ምክንያት ቋንቋውንና ማንነቱን ረስቶ በደባል ማንነት ስር ሲርመጠመጥ እንደነበር ሊነግሩን አይመኙም፡፡ለእነሱ ያ በህዝብ ላይ ሲደርስ የነበረ ግፍ ኢትዮጵያ የምትባልን አገር አንድ ለማድረግ ስለነበር የተደረገው ሁሉ ትክክል ነበር፡፡  እነሱ ‹‹የደጉ ዘመን›› ብለው የሚጠሩት ዘመን ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ የመከራ፣ የስቃይ፣ የግፍ ዘመን ነበር፡፡ ቋንቋቸው ከሰው ፊት እንዳይነገር ‹‹የወፍ ቋንቋ›› ሲባልና አማርኛ ለመናገር የሚኮላተፈው ሁሉ ገመድ አፍ፣ ተብታባ ሲባል እንደነበር ለእዚህ ግለሰብ አይገባውም፡፡ ቅማንት የሆነ ግለሰብም ይሁን ሌላ በዘሩ የተነሳ በነበረው ሥርዓት ተፅዕኖ ምክንያት ሆዱ እያወቀ ያለሆነውን ‹‹አማራ ነኝ›› ሲል እንደነበር ለዚህ ሰውየ መናገር ለቀባሪ ማርዳት ይሆናል፡፡ ሁሉም የሰው ልጅ በስላሴ ዓምላክ መፈጠሩ ተዘንግቶ ከእንጨትና ከእሬት የተገኘ ፍጡር በማድረግ ለዘመናት በማንነቱ ሲሸማቀቅ የነበረው ይህችን አገር አንድ ህዝብ አንድ ቋንቋ አንድ ሀይማኖት እያሉ ህዝቡን ረስተው ሲገዙት የነበሩ ገዥዎች እነማን እንደሆኑ ሊነግሩን አይፈልጉም፡፡ ለዚህ ግለሰብ ግን ያ ዘመን ሁሉም ህዝብ ተዋርዶ ገዥዎችና የዚያ ሥርዓት ደጋፊዎች የበላይ እንዲሆኑ የተደረገበት ዘመን  የአንድነትና የመልካም ዘመን ነበር፡፡ ራሳቸው የሚሰድቡትና ኢትዮጵያን ከፋፈለ ብለው የሚጠሩት የፌደራል ሥርዓትና የትግራይ ነፃ አውጭ ብለው የሚኮንኑት የፖለቲካ ድርጅት  ግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት ተከባብረው እንዲኖሩ መፍቀዱ ለእሳቸውና እሳቸው ለተገኙበት ህዝብ ትልቅ ስደብ እና ያን ‹‹ታላቅ›› የሚሉትን ህዝብ ያዋረደ ከሌሎች በእኩል አይን እንዲታይ ያደረገና ለኢትጵያ መፃኢ ዕድልም አደገኛ እንደሆነ ሳያሰልሱ ይነግሩናል፡፡   እኝህ ግለሰብ የቅማንትን የራስ አስተዳደር ህገ-መንግሥታዊ ጥያቄ በሦስት መንገዶች እመለከተዋለሁ ይላሉ፡፡ ይህውም፣ 1ኛ ከህገ-መንግሥቱ አንፃር ‹ኦሮሞ  ነኝ›  ፣ ‹ቅማንት ነኝ› ‹ወላይታ ነኝ› ማለት  ኢትዮጵያዊነትን የሚደመስስ አስተሳሰብ ነው ይሉና አማራ ነኝ ብሎ መቀጠል ግን ኢትዮጵያዊነት የሚያስቀጥል አስተሳሰብ በመሆኑ ተመራጭና ጤነኛ አስተሳሰብ እንደሆነ ሊነግሩን ይሞክራሉ፡፡ በራሱ የነገድ ሥም የሚጠራ ህዝብ ኢትዮጵያዊነቱን እንደካደ ሊያስረዱን ይሞክራሉ፡፡‹‹ቕማንት ቕማንት ነኝ ብሎ ኢትዮጵያዊነቱን ከሚያጣ ይልቅ አማራ ነኝ ብሎ ኢትዮጵያዊ መሆን ይሻለዋል›› ይላሉ (ገጽ 1 ፓራግራፍ 4 መስመስር 4 እና 5)፡፡ ቅማንት ነኝ፣ ኦሮሞ ነኝ፣ ሽናሻ ነኝ ማለት ኢትዮጵያዊነትን ስለሚደፈጥጥ ኢትዮጵያዊ  ብቸኛው የዘር ሀረግ ‹አማራ› ብቻ እንደሆነ በግልፅ ይነግሩናል ለቅማንት ህዝብ ቅማንት ነኝ ማለት.፣ ለኦሮሞው ኦሮሞ ነኝ ማለት ፣ለትግሬው ትግሬ ነኝ ማለት ወዘተ ነውርና ፀረ-አንድነት ሲሆን ለአማራ አማራነ ነኝ ማለት ግን ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠነክር አስተሳሰብ እንደሆነ ሊሰብኩን ይሞክራሉ፡፡ ለእኝህ ሰው ኢትዮጵያ አንድ የምትሆነው ሁሉም ማንነቱን ረስቶ አማራ ነኝ ሲል ብቻ እንደሆነ ይመክሩናል፡፡ ይህን  በተመለከተ መጋቢት 21/2007 ዓ.ም ‹‹የቅማንትን የክልል አስተዳደር በሦስት መንጎዶች›› ባሉበት መጣጥፋቸው ላይ በግልጽ  እንዲህ ይሉናል፡፡ ‹‹—— ለአንድ የቅማንት ተወላጅ ቅማንት ነኝ ማለቱ እንጅ ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለቱ ዋጋ የለውም›› ይላሉ፡፡ ስለዚህ አንድ ቅማንት ኢትዮጵያዊ ለመሆን ከፈለገ ማንነቱን ረስቶ በኢትዮጵያዊነቱ ይጠራ እንደማለት ነው፡፡ እኝህ ግለሰብ ጎንደር ውስጥ ሲያድጉና ወላጆቻው ራሳቸው በፈጠሩት ስለቅማንት ማንነት የተዛባ ተረት ተረት ሲግቷቸው በማደጋቸውና በኢትዮጵያ ስለ አንድ ብሔረሰብ ታላቅነትና የኢትዮጵያ ብቸኛ ባለቤትነት አጣመው ስላሳደጓቸው በምንም መልኩ የቅማንትን ማንነት መቀበል አይፈልጉም፡፡ በተቃራኒው እርሳቸው የተገኙበት ብሔር ሲጠራ በኩራት ደረታቸውን በትቢት ይወጥራሉ፡፡  የቅማንት ህዝብ የራስ አስተዳደር ‹‹ለምን ጠየቀ?›› ብለው በተቆረቆሩበት አስተሳሰብ ስለአማራ የራስ አስተዳደር መመሥረት ምንም ነገር ማለት አይፈልጉም፡፡ ለዚህ ግሰብ ለአማራ ይህ ተፈጥሯዊ መብት ሲመስላቸው ለቅማንት ግን የማይገባ ጉዳይ ነው፡፡ ወረድ ይሉና እርሳቸውን ያናደደቻቸው ሌላው ነገር በአማራ ክልል የሚገኘው ቅማንት አማራ እንዲሆን አለመደረጉ እንጅ በትግራይ ክልል የሚገኙ ኩናማዎች፣ ሳሆች ኢሮቦች በስማቸው መጠራቸውን አይቃወሙም፡፡ እንዲያውም ይህ አለመደረጉ እጅግ እንደሚያማቸው ይገልጣሉ፡፡ እገረ-መንግዳቸውን ግን አማራ እየተባለ የሚጠራው ህዝብ የጋፋት የሽናሻ፣ የወይጦና የሌሎች ህዝቦች ስብስብ መሆኑን ሳይደብቁ በጹህፋቸው በሌላ አስተሳሰብም ቢሆን ነግረውናል፡፡ 2ኛው ትግራይን ከማስፋፋት አንፃር እኝህ ግለሰብ የቅማንት ቅማንት ነኝ ማለት የህዝቡ መብት መሆኑን በመዘንጋት የቅማንት ጥያቄ መነሻውና መድረሻው የትግራይን ግዛት ከማስፋፋት ጋር ለማያያዝ ይሞክራሉ፡፡ ለእኝህ ግለሰብ ቅማንት ቅማንት የመሆን ተፈጥሯዊ መብቱን በግልፅ ይደመስሱታል፡፡ ቅማንት ጥንታዊ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ የቅማንት ህዝብን የውስጥ አስተዳደር ጥያቄ የሚያይዙትና የሚያዩት ከትግራይ የቦታ መስፋፋት ድብቅ ዓላማ ጋር ያቆራኙታል፡፡ ይህ ማለት ቅማንት የሚባል ህዝብ በኢትዮጵያ ያልነበረ ነገር ግን ወያኔ/ኢህአዴግ/ ለግዛት ማስፋፋት ዓላማው ሲል ብቻ ከ20 ዓመት ወዲህ  የፈጠረው ህዝብ እንደሆነ በግልፅ ይነግሩናል፡፡ የዛሬን አያድርገውና እኝህ ግለሰብ ጎንደር ውስጥ ሲያድጉ ቢያንስ በ24 ሠዓት ውስጥ ቅማንትን የሚያንቋሽሽ ፀያፍ ቃል ወይ ራሳቸው ይሉታለ አለያ ከቤተሰቦቻቸው ወይም ከጎረቤታቸው ሲነገር ሲሰሙ እንዳደጉ የሚዘነጉት አይመስለኝም፡፡ አሁን እያራመዱት ላለው ጭፍን የዘር ጥላቻም መሰረቱ ያደጉበት ቤተሰብና ማህበረሰብ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ታዲያ በዚህ መንግድ ያደገ ግለሰብ የቅማንትን ህዝብ የመብት ጥያቄ በተንሸዋረረ አመለካከታቸው ቢያዩት የሚያስገርም አይደለም፡፡የሚገርመው ግን ዛሬም የኢትዮጵያን አንድነት በ1960ዎች በነበረው አስተሳሰብ ለማስቀጠል ታች ላይ ማለታቸው ነው፡፡ ግለሰቡ ማወቅ አይፈልጉም እንጅ ከአሁን በኋላ የኢትዮጵያን አንድነት በአንድ ህዝብ ሥም አስቀጥላለሁ ብሎ ማሰብ ቐዠት ብቻ  ሳይሆን የጤንነት መጓደል ጭምር ነው፡፡ አቶ አንዱዓለም ‹‹ተስፋፊው የትግራይ ገዥ ከተከዜ አልፎ አስከአባይ ድረስ ለመቆጣጠር ያለውን ዓላማ ለማሳካት ቅማንትን አንደመሸጋገሪያ ድልዲይ ለመጠቀም ሲል ከተኙበት ቀስቅሶ የራስ አስተዳደር ጥያቄ እንዲያነሱ አደረጋቸው›› ይሉናል፡፡ ይሁን እንጅ ገዥው የአማራ ክልል መንግሥት የቅማንትን ህዝብ ያለፈቃዱ ‹‹ከዛሬ ቀን ጀምሮ አማራ ሆናችኋል›› ብሎ ከህዝብና ቤት ቆጠራ ሲሰርዛቸው ያ ለዚያ ታላቅ ህዝብ ለሚሉት መስፋፋት አልነበረም ይሆን?፣ ዘር ማጥፋትም አይደለም?፡፡ ይህን ድርጊት ተገቢና ትክክል አደርገው ስለሚያስቡ የአማራ መንግሥትን መክሰስ ፈፅሞ አይፈልጉም፤ በተቃራኒው ተገቢና  በልባቸው ጀግኖች እያሉ የሚያወድሷቸው ይመስለኛል፡፡ እስኪ እርሳቸው የተገኙበት ህዝብ የቅማንት ዕጣ ፈንታ ቢገጥመው ምን ይሰማቸው ይሆን? አማራ የሚባል ህዝብ ተሰርዞ ኦሮሞ ወይም ትግራዋይ ሆነሀል ቢባል አፈሙዝ ከማዞር የሚያግዳቸው ነገር ይኖር ነበር? ይህ ሆኖ አይደለም ሥልጣን የህዝብ በመሆኑ ከውጭ አገር ሆነው እያስነሱ ያሉትን አቧራ እያሸተትን ነው፡፡ ቁም ነገሩ  ግን ከአቧራነት የሚያልፍ አይደለም፡፡ ‹‹የቅማንት ክልል ለማን ይጠቅማል?›› ብለው በጠየቁበት አንድበታቸው የአማራ ክልል መመስረት ‹‹ለማን ይጠቅማል?›› ብለው ለመጠየቅ ድፍረቱን አላገኙም፡፡ ያሉት ምንድነው ‹‹የቅማንት ክልል ከተመሰረት የአማራ ክልል የቱ ሊሆን ነው? ነበር ያሉት፡፡ ቀጠል በማድረግ ‹‹የቅማንት ደካማ ክልል መመስረት ምን ጊዜም የማያባራ ንትርክ ከአማራው ጋር ይፈጠራል›› በማለት ስጋት አስመስለው ጎንደሬ አማራ የቅማንት ክልል ከተመሰረተ ለጦርነት እንደሚዘጋጅ ሊያስፈራሩን ይሞክራሉ፡፡ ከዚህ የአማራ ህዝብ ቁጣ እና ወረራ ለመዳን የቅማንት ህዝብ ትግሬዎችን አድኑኝ ለማለት ይገደዳሉ በማለት ትንቢታቸውንና ስጋታቸውን ይነግሩናል፡፡ ስለዚህ ነገ የራስክን ክልል በመመስረትህ በአማራ ህዝብ ሊደርስብህ ከሚችለው ቁጣ ለመዳን የራስ አስተዳደር ጥያቂያችሁን ቅማንቶች አቁሙ ይላሉ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ከእኛ አንኳ ብታመልጡ በመጨረሻ በትግሬዎች ተደፍጥጣችሁ እስከውዲያኛው  ከምደረ-ገጽ መጥፋታችሁ አይቀርምና እነሱ ከሚያጠፏችሁ እኛ እንደጀመርነው እንጨርሳችሁ ለማት ይዳዳቸዋል፡፡ በክልሉ ለሚኖሩ ሌሎች ህዝቦችም ማለትም ለአገው ለሽናሻ ለወይጦ  ለሻንቅላ ህዝቦች በቅማንት ሊደረስ የሚችለው እንዳይደርሰባችሁና የመምጫችን ቀን ስለማይታወቅ  ከአሁኑ ንስሀ ግቡ በማለት ይመክራል፡፡ የሚያሳዝነው ከወላጆቻው የወረሱት ፀያፍ የህዝብ ስም አጠራር አንኳ አላስተካከሉም፡፡ አሁንም የሌለን ህዝብ ‹‹ሻንቅላ›› እያሉ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ያላቸውን ንቀት ይነግሩናል፡፡ ሻንቅላ ማነው ‹ነብዩ› አንዱዓለም? ‹‹የቅማንት ክልል መመስረት ዋና ምክንያቱ የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር የፖለቲካ ቅማራ ነው፡፡›› ይላሉ፡፡ ግን በነካ ብዕራቸው የአማራ ክልል መመስረት የየትኛው ተፈጥሯዊ ህግ ውጤት እንደሆነ ቢነግሩን? አቶ አንዱዓለም በአግባቡ አልተረዱተም እንጅ  ወያኔ/ኢህአዴግ/ ያልነበረን የአማራ ህዝብ ራሱን የቻለ ብሔረሰብ ነው ብሎ አንድ ደረጃ ከፍ አድርጎታል፡፡  የደርግ ፕረዚዳንት የነበሩት መንግሰቱ ኃ/ማሪያም‹‹ እውን አማራ የሚባል ህዝብ አለ?›› ያሉትን ሀቅ ኢህአዴግ ደምሰሶታል፡፡ እውነታው ግን የመንግሥቱ ኃ/ማሪያም ጥያቂያዊ ንግግር ነበር፡፡ 3ኛው ዐማራውን ከማዳከምና ከማጥፋት አንፃር የቅማንተን ክልል መመስረትን ያየበት ሦስተኛው መንገድ ወያኔ አማራን ለማጥፋት ካለው ዓላማ ጋር ያያዙታል፡፡ ይህን በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፡፡ ‹‹የትግሬዎች ነፃ አውጭ ሲቋቋም ከመጀመሪያዎች አራቱ ግቦች አንዱ በአማራው መቃብር ላይ የትግራይን ሪፑብሊክ እንመስርታለን የሚል ነው›› ይላሉ (ገፅ 3 ፓራግራፍ 2)፡፡ ቀጠል በማድረግ ‹‹ይህ የቅማንት ክልል መመስረት የትግሬዎች ነፃ አውጭ ግንባር ትግራይን ለማስፋፋት እንደሆነ ከላይ በተራ ቁጥር 2 አሳይቻለሁ ይላሉ፡፡ ለእኝህ ግለሰብ በኢትዮጵያ የፀደቀው ህገ-መንግሥት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ሲደርሳባቸው ከነበረው ግፍ አውጥቶ በእኩልነትና በመከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነት እንዲያመጣ ታስቦ በህዝቦች ይሁንታ የመጣ ሳይሆን አማራ የሚባልን ታላቅ ህዝብ ለማዳከምና ብሎም ለማጥፋት  በወያኔ የተጠነሰሰ ሴራ ነው ይሉናል፡፡ ምክንያቱም ይላሉ ‹‹ለወያኔ ከደርግ ይልቅ መሰረታዊ ጠላቱ አድርጎ የሚያየው የአማራን ህዝብ ነው›› ይላሉ፡፡  ነገር ግን ሰው በላው ደርግ የወያኔ ጊዚያዊ ጠላት ነበር በማለት ያስቀምጣሉ፡፡ ይህን ዐማራን የማጥፋት  ተልዕኮውን ለማሳካት ‹‹ወያኔ ቅማንትን ጠፍጥፎ ሰራው›› ይላሉ፡፡ በክልሉ የተለያዩ ህዝቦችን በመፍጠር የአማራን ቁጥር አሳነሰ ይላሉ፡፡ ለአቶ አንዱዓለም ትልቁ ጭንቀት የአንድ ብሔረሰብ እንደህዝብ ራሱን አሳውቆ መቀጠልና ራሱን በራሱ ማስተዳደሩ ተፈጥሯዊ የሆነውን መብቱን ረስተው የቅማንት ህዝብ የራስ አስተዳደር መመስረት የአማራን ህዝብ ቁጥር ማሳነሱ ላይ ያንገበግባቸዋል፡፡ የወያኔ የቅማንት ህዝብ የራስ አስተዳደር መፍቀድ አማራን ለማጥቃት ነው ባሉ አንደበታቸው የቅማንትን ዘር ለማጥፋት እየተደረገ ያለውን ግፍ ለምን ማንሳት አልፈለጉም? ለአንድ ህዝብ ብቻ መቆርቆር እውን የኢትዮጵያን እነድነት ያረጋግጣል? ለዚህ ግለሰብ አንድነት ማለት ቦታ እንጅ ሰው አይደለም፡፡ ይህን እውነታ እንዲህ በማለት ራሳቸውን ይጠይቃሉ፡፡ ወያኔ ‹‹ከየትኛው ቦታ አማራ ተባሮ የቅማንት ህዝብ እንዲሰፍር ይደረጋል?›› ብለው ሲጠይቁ አሁን ቅማንት ሰፍሮ የሚገኝበት ቦታ የአማራ ቦታ እንጅ የቅማንት አይደለም ማለታቸው እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ይህም ማለት ቅማንት አገር የሌለው በእነአንዱዓለም በጎ መግባር የተቀመጠ ህዝብ ነው ማለታቸው ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ምክንያቱም እንአንዱዓለምና መሰሎቹ ያደራጇቸው የአማራ ህብረት አባላት (በኢትዮጵያ)  ‹‹ቅማንት አገር ስለሌለው ወደመጣበት ግብፅ እንመልሰዋለን እንዳሉት ማለት ነው፡፡ የቅማንት ጥያቄ የመብት እንጅ የቦታ ማስፋፋት እንዳልሆነ እያወቁ ቅማንት የሚባል ህዝብ በጎንደር ምድር ላይ ፍፁም ቦታ አንደሌው አድርገው ይነግሩናል፡፡ ምን ይደረግ ‹‹በኋላ የበቀለ ቀንድ በፊት የበቀለውን ጆሮ በለጠው›› አይደል ከእነተረቱ፡፡ ምን ይሁን! የቅማንቶች ምድር ጎንደር ለዚህ ግለሰብ ያለፈ ታሪክ ሆነባቸውና ከነአካቴው የቅማንትን በጎንደር ምድር ቦታ የሌለው ህዝብ እንደሆነ ሊነግሩን ሞከሩ፡፡ የዛሬን አያድርገውና እንኳን የጎንደር ምድር ራሳቸውም የተገኙበት ህዝብ መሰረቱ ቅማንት አንደሆነ የሚጠፋቸው አይመስለኝም፡፡ በአንድ ወቅት በተደረገ የሀይማኖትና የፖለቲካ ተፅዕኖ ተገዶ ማንነቱን የቀየሩትን የአቶ አንዱዓለም ዘመዶች ሥርወ-ግንዱ ቅማንት ነበር፡፡ በፁህፋቸው መጨረሻ ‹‹በትግሬዎች ነፃ አውጭ ግንባር የቅማንት ክልል ተፈጥሯል፤ ታዲያ ይህን እንዴት መታገል ይቻላል?›› ብለው ይጠይቁና  የህን አገር አፍራሽ ተግባር መቃወም  የሁሉም ግዴታ እንደሆን መልሱን ራሳቸው ይመልሱታል›፡፡ መፍትሄውም ‹‹የትግሬን ነፃ አውጭ ድርጅት ተባብሮ መደምሰስ ነው›› ይላሉ፡፡ የትገሬ ነፃ አውጭ ከተደመሰሰ የቅማንት ማንነትም አብሮ ይደመሰሳልና ማለታቸው ነው፡፡ በዚህ ፁህፋቸው አቶ አንዱዓለም ሁለት ትልልቅ ስህቶችን ፈፅመዋል፡፡ 1ኛውና የመጀመሪው  ስህተታቸው የቅማንት ህዝብ እንደህዝብ በራሱ የማይነቀሳቀስ በድን አካል አድርገው በማየታቸው የቅማንት ህዝብ ማንም ሲፈልገው በባዳነት የሚጠቀምበት አስመስለው መሳላቸው ነው፡፡ ግን እኝህ ግለሰብ የዘነጉት አብይ ቁም ነገር ቢኖር ራሳቸው አስር ጊዜ የትግራይ ነፃ አውጭና ከፋፋይ ብለው በሚጠሩት ድርጅት ተመሰረተ በሚሉት የፌደራል ሥርዓት ውስጥተሸቀዳድሞ ስልጣን ላይ ፊጥ ያለው እርሳቸው የተገኙበት ህዝብ አካል የሆነው ቡድን እንደሆነ ረስተውት ሳይሆን ‹‹በብቸኝነት ለምን እኛ ብቻ አገሪቱን አልተቆጣጠርንም›› ከሚል ጭፍን የሥልጣን አባዜ ነው፡፡ ዛሬ የአማራን ክልል የሚመራው በመንደርና በጎጥ በተሰባሰቡ ቡድኖች መሆኑን እያወቁ ስለዚህ ጉዳይ ምንም ማለት አይፈልጉም፡፡ ባንዳነት የራስን መብት ማስከበርና በፌደራል ሥርዓቱ መሳተፍ  ከሆነ የመጀመሪያወ ባንዳ ማን እንደሆን ለማወቅ ምንም አይነት የሂሳብ ቀመር አያስፈልገውም፡፡ ለእኝህ ግለሰብ ቁም ነገሩ የህዝብ ቁጥር ብቻ ስለሚመስላቸው የቅማንትን ህዝብ ከአማራው ህዝብ ጋር በማነጣጠር ‹‹የትም አትደረሱም›› ለማለት የሞክራሉ፡፡ ቁም ነገሩ ቁጥር ቢሆን ኑሮ እስራኤል የምትባል አገር እና አስራኤል የሚባል ህዝብ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የአረብ ህዝብ ተከቦ ህልውናውን ባላስከበረ ነበር፡፡ ከፈለጉ እኝህ ግለሰብ የሚናፍቁትን ጦርነት ጊዜ ሳይወስዱ ማወጅ ይችላሉ፡፡ ይህ የሚናፍቁት ጦርነት የቅማንትን ህዝብ ብቻ ለብልቦ የሚቆም መስሏቸው ከሆነ ተሳስተዋል፡፡ በጎንደር ምድር ላይ ወይ አብረንና ተከባብረን እንኖራለን አለያ ደግሞ በግፍ የሚመጣ ጦርነትን መመከት የሚያቅተው ያለ ህዝብ ያለ አይመስለዎት፡፡ 2ኛውና ሌላው ስህተታቸው የዚህ ፁህፍ ማጠንጠኛቸው ህወሀት/ኢህአዴግ/ የአማራን ህልውና ለመፈታተን የተፈጠረ ድርጅት በማስመሰል የሚደስኩሩትና የዚህ ህዝብ ህልውና መደፈር ለኢትዮጵያ አንድነት መደፈር ብቸኛ ምልክት አድርገው የሚያራምዱት የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው፡፡ ‹‹ተደፈረ፣ በወያኔ የጥፋት በትር ሥር ወደቀ›› የሚሉት ህዝብ ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ  20 በመቶ  ሊሆን ቢችል ነው፡፡ ሌላውን በማግለል እንደገንጣይና ከፋፋይ መመለልከት ጊዜው ያለፈበትና ውኃያማይቋጥር አስተሳሰብ መሆኑን የተገነዘቡት አይመስልም፡፡ የእንዲህ አይነት የተቸካይነት (inflexible) አመለካከት ይበልጥ የኢትዮጵያን ህዝብ ይከፋፍል ካልሆነ በስተቀር የአነድነት ስሜትን ማምጣት አይችልም፡፡ ለአንዱዓለምና ለመሰሎቹ የራሳቸውን የተንሸዋረረ አመለካከት አስተካክሎ ወደ አማካኝ ቦታ ከመምጣት ይልቅ ይህ አመለካከት ወያኔነትና የወያኔነት አቀንቀኝነት ሊመስላቸው ይችላል፡፡ ግድ የለኝም፡፡ በኢትዮጵያ ብሔር. ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩልነት የሚያምን ድርጅት ሁሉ ደጋፊ ነኝ፡፡ እኝህ ግለሰብ አልተረዱትም እንጅ ወያኔ/ኢህአዴግ/ የሚሉት ድርጅት ለዐማራ ህዝብ የማንነት እውቅና በመስጠት የቅማንትን ህዝብ ከአማራ መንግሥት ደጅ እንዲጠና እንዳደረገው የተገዘቡ አይመሰልም፡፡ ለሳቸው ጥያቄ የሆነባቸው አማራ ባለመብት መሆኑ ሳይሆን ቅማንት መብቱን መጠየቁ ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ መብት ለእነሱ ተጥሯዊ  መብት ሲሆን ለቅማንት ግን የማይታሰብ እውነታ አድርገው ያዩታልና፡፡ ይህን በዚህ ላብቃና ግለሰቡ ለሁለተኛ ጊዜ ‹‹የማይለቀን የቅማንትጉዳይ፤ ብለው ብለው ብለው ወደእኛ ለአቤቱታ መጡ›› በሚል ርዕስ www.ethiomeida.com ላይ በፃፉት ዙሪያ ሰፊ መልስ ይዠ አስክመለስ ድረስ ቸር ይግጥመን! ከብርቱካን ወለቃ ይህን ፀሁፍ መነሻ አድርጎ መልስ መፃፍ የሚፈልግ ሁሉ በፌስ ቡክ አድራሻየ ወይም birtukanwoleka@gmail.com በሚለው አድራሻ ሊፅፈልኝ ይችላል፡፡

Monday, September 21, 2015

Professor Birhanu Nega on Mola Asgedom


መግለጫ ወይንስ መጋለጫ (ይገረም አለሙ)

 ከአንድ ሳምንት ወሬ የማይዘለው የሞላ አስግዶም ኩብለላ ብዙ ነገሮችን አያሳየን ነው፡፡ ወያኔ የሞላ ኩብለላ የሱ የሥራ ውጤት እንደሆነ አሳያለሁ ብሎ “በቅሎ ሽንቷን አጠራ ብላ ሀፍረቷን አሳየች” የሚባለውን አይነት ድርጊት ፈጸመ፡፡ ለነገሩ ወያኔ መቼ ሀፍረት ያውቅና፡ አቶ ሞላም የተሰጠው ስልጠና የአጭር ግዜ ሆኖበት ሽክ ብሎ የቀረበበትን ጋዜጣዊ መግለጫ የወያኔና የራሱ መጋለጫ አደረገው፡፡ የወያኔ የመረጃ ስራ በጉልበት አንጂ በእውቀት እንዳልሆነ የምናውቀውንም ይበልጥ አረጋገጠልን፡፡ የቱንም ያህል ቢጩኹ፤የቻሉትን ያህልም ውሸት ቢደራርቱ እውነትን ማሸነፍ እንደማይቻል ወያኔዎች ብዙ ግዜ ሞከራው ከሽፎባቸው ያዩት ቢሆንም አንዴውኑ ከእውነት ጋር ተጣልተዋልና የህይወት መሰሶአቸውም ውሸት ሆኖአልና ከውሸት ሊላቀቁ አልቻሉም፡፡ ዛሬም እየዋሹ ብዙሀኑን ኢትዮጵያዊ በግድ ሊግትቱ ይዳዳቸዋል፡፡ ጥቂት አይናቸውን ለጆሮአቸው ያስገዙ ሰዎቻቸው ደግሞ እንዴት ብሎ መጠየቅ ለምን ብሎ ማመዛዘን የለም ብቻ ውሸቱን እየተቀበሉ ከበሮ ይደልቃሉ፡፡እውነቱ ሲጋለጥም ሌላ ውሸት ይፈበርካሉ እንጂ ለእውነት እጅ አይሰጡም፡፡ አቶ ሞላ በመግለጫው ትህዴን በርካታ የታጠቀ ሰራዊት ቢኖረውም ከመንግሥት ጋር ባለኝ ግንኙነት የሊቀመንበርነቴን ሥልጣን ተጠቅሜ ለአስር አመታት ምንም ጥቃት አንዳይፈጽምና ጉዳት እንዳያደርስ ለማድረግ የቻልኩበት ሁኔታ ነው የነበረው፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ይህን ማድረግ የማልችልበት ሁኔታ ክፍተት እየታየኝ ስለመጣ የጥፋት ተባባሪ ላለመሆን ስል በርካታ ታጋዮችን በመያዝ እጅ ሰጥቻለሁ ቢል በመጠኑም ቢሆን የተሻለ ይሆን ነበር፡፡ ብዙ ከመቀባጠርም ያድነው ነበር፡፡ ሰልጣኙም አሰልጣኙም መሰረታቸው ውሸት ሆነና በጽሁፍ የሰጡትም ሆነ በቃል የተናገሩት መግለጫ ሀራምባና ቆቦ የረገጠ ሆነና የታሰበለትን ዓላማ ማሳካቱ ቀርቶ እነርሱኑ ያጋለጠ ሆነ፡፡ በዚህ ዙሪያ ከተለያየ አቅጣጫ የተጻፈ ስለሆነ እኔ አልደግመውም፡፡ የሞላ ኩብለላና መቀላመድ ድርጅቶች እድሜ ከመቁጠር ውጪ የተግባር እንቅስቃሴ የማይታይባቸው፣ ተባብሮ መስራትም የማይሆንላቸው ለምን እንደሆነ ቀድሞ የሚታወቀውንና በተለያየ ግዜና መንገድ የተገለጸውን አንዱን ምክንያት አረጋግጦልናል፡፡ ትህዴን በሰራዊት ብዛትና በመሳሪያ አይነት የተጠናከረ መሆኑ አነጋጋሪ አይደለም፡፡ እንዲህ አቅም እያለው ተግባራዊ እንቅስቃሴው አለመታየቱ የዘመቻ ወሎው አለመሰማቱ ግን አነጋጋሪ ብቻ ሳይሆን አጠያቂም ነበር፤ እነሆ ዛሬ ግን ምላሽ አገኘ፡፡ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ወታደራዊ በተፈጥሮ የተሰጡ፣ በእውቀትና ልምድ የካበቱ፣ ለሚሰሩት ስራ እምነትና ጽናት ያላቸውንና ከራስ በላይ የሚያስቡ መሪዎችን ይሻል፡፡ ያ ሳይሆን ሲቀር ውጤቱ ኪሳራ ነው፡፡ ብዙዎቹ ድርጅቶች ዕድሜ አንጂ ውጤት የማይታይባቸው እንዲህ ትግሉና መሪው ታጋዩና አታጋዩ አልገጥም ብለው ነው፡፡ ከሰሞኑ “ማጋላጫ” እንደተረዳነው ሞላ አስር አመት ኤርትሪያ የኖረው በድርጅት ስም እያውደለደለ እንጂ እየታገለ እንዳልሆነ ነው፡፡ ሞላ ለወያኔ ፕሮፓጋንዳ እሰራ ብሎ (ታዞ) በማውደልደል እንደኖረ ሀፍረቱን ኩራት አድርጎ ነገረን፡፡ የነገረን ሁሉ የተሟላላት ከሆነ ይህ ሰው ምን ፍለጋ ይታገላል፡ እንደውም ድርጅቱ በተቋቋመበት አላማ መሰረት ይንቀሳቀስ በቂ ሰራዊት አስተማማኝ መሳሪያ ይዘን ጠመንጃ ታቅፎ መቀመጡ በዛ ታጋዩም እየተሰላቸ ነው የሚል ጥያቄ የሚያነሱ ቢገኙ በተለያየ ዘዴና መንገድ ጸጥ ያሰኛል አንጂ የሰራዊቱን ተነሳሽነት አይቶ ጥያቄአቸውንም ተቀብሎ ዘመቻ ሊያስብ አይችልም፡፡ ጥምረቱን በመቃወምም ለግል ድሎት እንጂ ለሀገር ነጻነት የተሰለፈ አለመሆኑን አረጋግጧል፡፡ አሁን ሁኔታው ተለወጠ በአንድ በኩል የተግባር እንቅስቃሴ ተጀመረ፡፡ ከዚሁ ተያይዞ ከሌሎች ጋር በጥምረት መሰራት መጣ፤ ሞላ ይህን ሁሉ አስቀርቶ እየታገለ ሳይሆን እያውደለደለ መኖሩን ለማስቀጠል የተቻለውን ሁሉ ጣረ ተጣጣረ አልተሳካለትም፡፡ አልሆንልህ አለኝ ብሎ የተሰጠውን ተቀብሎ አንዳይቀጥል ሰግሞ ምክትሉ እንደነገሩን በአመራር ድክመት ተገምግሞ፣ አብሮ መስራት ባለመፈለግ ተኮንኖ፣ ድርጅቱን አስር ኣመታት ያለውጤት በማኖሩ ተወንጅሎ ከመሪነቱ ሊነሳ እንደሆነ ተረዳ፡፡ ልብ በሉ ከመሪነት መነሳቱ ተራ ሥልጣን ብቻ አይደለም የሚያሳጣው፡፡ ቤቱ መኪናው መንደላቀቁ ወዘተ ሁሉ ነው አብሮ የሚቀረው፡፡ ከከተማ ከተማ እየዞረ ምግብና መጠጥ ሌላ ሌላውንም ያማርጥ የነበረ ሞላ ጠመንጃ አንግቦ ከታጋዮች ጋር ሊውል ሊያድር ! አረ ምን ሲደረግ፤መኮብለል እያለ፡፡ አመታት ያስቆጠሩ በሀገር ቤትም በውጪም የሚኖሩ፤ ሰላማዊም ይሁን የጠብ መንጃ ትግል ነው የምናካሂደው የሚሉና አንዳችም ውጤት ያላሳዩ ድርጅቶች ቢፈተሹ ችግራቸው ተመሳሳይ ነው፡፡ መሪዎቹ ያጡትም የጎደለባቸውም ነገር የለም ፤ምኒልክ ቤተ መንግሥትን እያለሙ የተቀዋሚ መሪ ተብሎ መኖር በቂያቸው ነው፡፡ እናም ትግሉ የሚጠይቀውን አመራር በመስጠት ወደ ድል ለማቅናት ትግል ይጠይቃል መስዋእትነት ያስከፍላል፡፡ ይህን በማድረግ ሰላማዊዎቹ አባሎቻቸው ባለጠመንጃዎቹ ታጋዮቻቸው የሚከፍሉትን መስዋዕትነት ወደ ራሳቸው ለምን ያመጣሉ በፕሮፓጋንዳ ተኮፍሰው በተግባር ኮስሰው በድሎት መኖር እያለ፡፡ ከሌሎች ጋር ተባብረው መስዋዕትነቱን ተጋርተው ትግሉን አጠንክረው ለማስኬድ ደግሞ የፓርቲ መሪ መባሉን የሳጣናል ብለው ይሰጋሉ፡፡ የቤተ መንግስቱ ቢቀር የፓርቲ መሪነቱን እንዴት ይጡ! በየፓርቲዎቹ ያሉ አባላትና ታጋዮች መሪዎቻቸውን የመጠየቅ ነጻነት አለፍ ሲልም የማስገደድ መብት ኖሮአቸው እንደ ሞላ እጃቸውን እየተጠመዘዙ ድርጅቶቻቸው ከሌሎች ጋር ትብብር ቢፈራረሙ ወይንም ወደ ተግባር አንቅስቃሴ ቢገቡ ወደ ወያኔ ባይኮበልሉም ሲታገሉና ሲያታግሉ ሳይሆን ሲያውደለድሉ የኖሩበትን ድርጅት ጥለው የሚሄዱ አለያም ተገንጥለው ሌላ መታገያ ሳይሆን መኖሪያ ድርጅት እንደሚፈጥሩ በተደጋጋሚ አይተናል፡፡በውጪም በውስጥም ያሉ ፓርቲዎች ቁትራቸው እንዲህ የበዛበት አንዱና ዋናው ምክንያት ይህ ነው፡፡ ድርጅት ህይወታቸው፤ ስመ ትግል መኖሪያቸው ከሆነ ለምን ብለው ወደ ተጨባጭ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ይገባሉ፤ ለምንስ ብለው የድርጅታቸውን ህልውና የሚያከትምና የእነርሱንም መሪነት ሊያሳጣ የሚችል ትብብርና ውህደት ይቀበላሉ፡፡ ወያኔዎችም ሥልጣን ወይንም ሞት ያሉት እንዲሁ ሆኖባቸው ነው፡፡ ሁሉንም ነገር ያገኙት ሥልጣንን መሳሪያ በማድረግ ነውና ሥልጣናቸውን ባጡ ማግሥት ሁሉንም ነገር የሚያጡ መስሎ ይሰማቸዋል፡፡ የትም በማንምና በምንም ሁኔታ የሚደረግ አንቅስቃሴም ሆነ የሚጻፍና የሚነገር ከሥልጣናቸው የሚያስነሳቸው እየመሰለቸው ነው በጥፋት ላይ ጥፋት በክፋት ላይ ክፋት እየፈጸሙ ከሰዋዊ አስተሳሰብ የወጡት፡፡ ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ወያኔዎች ከግንባርነት ወደ አንድ ፓርቲነት ለመሸጋገር ዝግጅታቸውን አጠናቀው አንደነበር አቶ መለስ ሳይቀሩ በ1990ዎቹ አጋማሽ ላይ ነግረውን ነበር፡፡ የውሀ ሽታ ሆኖ የቀረበት ምክንያት ምን ይሆን? እነርሱም የየፓርቲ ሊቀመንበር መባሉ እንዳይቀርባቸው ብለው ይሆን! ወይንስ ጠቅላዩ ህወኃት አናሳ መሆኑን ተገንዝቦ ውህደት ቢፈጠር እዋጣላሁ ብሎ ፈራ? “ሰይጣን ለተንኮሉ ከመጽኃፍ ቅዱስ ይጠቅሳል” እንደሚባለው የሚመሩት ድርጅት ስም ይዞ ከመቀመጥ ወጥቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ አንዳያደርግም ከሌሎች ጋር ተባብሮ እንዳይሰራም የሚፈልጉ የድርጅት መሪዎች ወያኔን ስለማስወገድ፤ ትግሉን ስለማጠናከር፣ ስለመተባበር አስፈላጊነት አልፎም ስለ ውህደት ለማውራት የሚያህላቸው የለም፡፡ እወነተኛ ማንነታቸው የሚጋለጥበት አጋጣሚ እስኪፈጠር ያለነሱ ታጋይ እየተባሉ ውደሳውም ልገሳውም ይጎርፍላቸዋል፡፡ በተለይ በተቃውሞው ጎራ የምንገኝ የሞላን ኩብለላ አስመልክቶ ወያኔ በትግረኛ ሲጨፍር ቅኝቱንም ሆነ ግጥሙን ሳይረዱ ቡጊ ቡጊ ለሚደንሱ ወገኖች በሁኔታቸው እያዘንን በድርጊታቸው እያፈርን መተው እንጂ እሰጥ አገባ መግጠሙ አንካ ሰላንትያ መያያዙ አስፈላጊ አይሆንም፡፡ የሚበጀው ኩብለላው የጥምረቱ ውጤት መሆኑን በማየትና ከዚህ በመማር ሌሎች ተባብረው ለመስራት ፈቃደኛ ያልሆኑበትንና የሚፈለገው የተቃውሞ ጎራ ጥንካሬ እንዳይመጣ ምክንያት የሆኑትን ጉዳዮች መመርመርና መፍትሄ መሻት ላይ ማተኮር ነው፡፡የምንደግፋቸውን ድርጅቶች ዝም ብለን በስሜት ከማድነቅ ወጣ ብለን ምን ሰሩ ምን እየሰሩ ነው ምን ለመስራ እየተዘጋጁ ነው ብለን እንይ፤የሚታይ ነገር ከሌለ ደግሞ ልን ብለን እንጠይቅ፤ በግል ጠንክሮ ላለመታሉም ሆነ ከሌሎች ጋር ህብረትና ውህደት ላለመፍጠሩ ዋናው ችግር ድርጅቶች የአንድ ወይንም የሁለትና ሶስት ሰዎች የግል ንብረት መሆናቸው ነውና ከዚህ ለማላቀቅ እንጣር፡፡ትህዴን የሊቀመንበሩን ጥምረቱን አለመፈለግ በድምጽ ብልጫ ውድቅ ሲያደርግ በግለሰብ ተጠርንፎ ከመኖር ራሱን ነጻ ማድረጉን አሳይቷል፡፡ ሌሎችም እንደዚሁ ለቆሙለት ዓላማ እንጂ ለመሪ ግለሰቦች ፍላጎት የማይገዙ መሆናቸውን የሚያሳዩበት፣ ድርጅቱ ማለት መሪው መሪው ማለት ድርጅቱ ከነበረበት ሁኔታ የሚላቀቁበትን ዘዴ ብንዘይድ ነው የሚጠቅመው፡፡ ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት የሚታገሉ ሳይሆኑ እንደ ሞላ እያውደለሰሉ አመታት የቆጠሩ መሪዎች እዛም እዚህም ነበሩ፡፡ ዛሬም የድርጅት መሪ መባል እንጂ ትግሉንም ድርጅቱንም የማያወቁ ግን በስሙ ኑሮአቸውን አደላድለው የሚኖሩ የድርጅት መሪዎች ይኖራሉ፡፡ እነዚህ በምንም ተአምር ትግሉን ሊያንቀሳቅሱም ሆነ ከሌሎች ጋር ተባብረው ሊሰሩ አይችሉም፡፡ ሌሎች የተግባር እንቅስቃሴ ሲጀምሩም እንቅፋት ከመሆን አይመለሱም፡፡ ስለሆነም በርግጥ ድርጅቶቹ የተቋቋሙትና የሚፈለጉት ለትግል ከሆነ ከግለሰብ ንብረትነት እንዲላቀቁና በተናጠል የተግባር ድርጅት እንዲሆኑ ከሌሎችም ጋር ተባብረው እንዲሰሩ አባሉም ደጋፊውም ጥረት ማድረግ አለበት፡፡ ውግዘትና ጩኸት ወያኔን እያለመለመው ለመቶ በመቶ አሸናፊነት አደረሰው አንጂ ለውጥ አንደማይመጣ ከበቂ በላይ የተረጋገጠ ይመስለኛል፡፡ ስለሆነም ድጋፋችን ድርጅትን እንጂ ግለሰብን አይሁን፣ ርዳታችን በተግባር እየመዘንን አንጂ በምላስ እየተታለልን አይሁን፡፡ ከሞላ ኩብለላ ያታየው ሌላው ነገር ወያኔ በቀደደው የዘር ቦይ የሚፈሱ ወገኖች ጉዳዮን የጎሳ ካባ አልብሰው ድሮም ሞላዎች ሲሉና ከትህዴን ጋር መጣመርን ሲኮንኑ መሰማታቸው ነው፡፡ የሚገርመው ይህን የሚሉት ብዙዎቹ እነርሱ እንደግፋቸዋልን የሚሉት ፖለቲከኞች ርስ በርስ መተማመንና መስማማት ተስኖአቸው በአንድ ስም አምስትና ስድስት ድርጅት የሚመሩ መሆናቸው ነው፡፡ ከስሜት ይልቅ እውነት ሚዛን ቢደፋ፤ እንዲህ ባላተባለ ነበር፡፡ ሌላውን ከመኮነን በፊት ራስን ማየት ጥሩ ነው፡፡ ራሳቸው መተማመን አጥተው በአንድ ስም አምስትና ስድስት ሆነው ተለያይተው እየተናቆሩ ሌላውን የማይታመን ማለት አንዴት ይቻላል? አረ ጎበዝ ስራችንም ሆነ ንግግራችን ብሎም ጽሁፋችን እየተስተዋለ ይሁን፡፡ እነዚህ ወገኖች ነገሮችን ሁሉ በጎሳ መነጽር መመልከት እንደማይበጅ ተገንዝበው ሰከን ብለው ቢያስቡ መልካም ነው፡፡ ወያኔ ነገሮች ሁሉ የጎሳ መልክ እንዲይዙለት መፈለጉና መስራቱ በኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ ስር ዓላማውን ማሳካት እንደማይችል ስለሚያውቅ፣ አንድነት ከጠነከረ በሥልጣኑ እንደማይሰነብት ስለገባው ነው፡፡ ወያኔን የሚያወግዙ የሚኮንኑ በዚሁ በወያኔ መንገድ መሄዳቸው ግን ለምን ይሆን፡፡ ሞላን መሰል ሰዎች ከየድርጅቶቹ ቢነቀሉ አይደለም ትብብር ውህደት በወራት ውይይት ተግባራዊ ይሆናል፡፡ እናም አባልም ደጋፊም የሆንባቸው ድርጅቶች እንዲጠሩ እንስራ፡፡ ብሽሽቁና አንካ ሰላንቲያው የአንድ ሳምት ጉንጭ ከማልፋት በቀር ጥቅም የለውም፣አጋጣሚዎችን ሁሉ ለበጎ ስራ አንጠቀምባቸው ፣ በቸር ያሰንብተን ፤ፍቅር ይስጠን ልቦና ያድለን፣ለስሜት ሳይሆን ለእውነት ለመቆም ያብቃን፣አሜን