Saturday, September 26, 2015

የቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ዘመቻ ለምን?

ዘመቻው የተጀመረው የዛሬ ሁለት ሳምንት ገደማ ይመስለኛል፡፡ ለመጀመሩ ምክንያት የሆነው ደግሞ “ቢቢሲ ትኩረቱን በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ላይ ያደረገ የስርጭት ፕሮግራም ይጀምራል” የሚል ዜና መነገሩ ነው፡፡ ታዲያ ይህንን ዜና ተከትሎ “የስርጭት ቋንቋዎቹ አማርኛ እና ትግርኛ ናቸው” የሚል ወሬ ተደመጠ፡፡ ነገሩ እስከ አሁን ገፍቶ ባይመጣም በትክክል ተብሎ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም የውጪ ሰዎች እንዲህ ዓይነቱን ነገር ለመወሰን ሲነሱ በቅድሚያ የሚያዩት በየሀገራቱ ውስጥ በኦፊሴል የሚሰራባቸውን ቋንቋዎች ነው፡፡ ትግርኛ በኤርትራ፣ አማርኛም በኢትዮጵያ የኦፊሴል ቋንቋ የመባል ደረጃ ያላቸው በመሆናቸው ቢቢሲ በዚሁ ምክንያት ፕሮግራሙን በሁለቱ ቋንቋዎች ለማስተላለፍ ወስኖ ሊሆን ይችላል፡፡ በየሀገራቱ ውስጥ ያሉት ቋንቋዎች ተናጋሪ ብዛት ሲታይ ግን አፋን ኦሮሞ ከሁሉም ይቀድማል፡፡ እንደሚታወቀው በሬድዮ የሚተላለፍ ፕሮግራም የሚሻው አድማጭ እንጂ አንባቢ አይደለም ፡፡ ስለዚህ በኤርትራና በኢትዮጵያ ላይ የሚያተኩረው አዲሱ የቢቢሲ የስርጭት ፕሮግራም አድማጮችን ታሳቢ ያደረገ መሆን ይገባዋል ተብሎ ነው የሚታመነው፡፡ ለቢቢሲም ሆነ ስርጭቱ በሚያተኩርባቸው ሀገራት በጣም የሚጠቅመው አካሄድ ይኸው ነው፡፡ እናም ይህንን ያዩ ተመልካቾች “ቢቢሲ የቪኦኤን ሞዴል ቢከተል የተሻለ ነው፤ አፋን ብዙ ተናጋሪ ያለው አፋን ኦሮሞ ከሁለቱ ቋንቋዎች ጋር መደመር አለበት” በማለት በኢንተርኔት የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ ጀመሩ፡፡ እኛም ዘመቻው ተገቢ ሆኖ ስላገኘነው ፊርማችንን ሰጠነው፡፡ ሌሎችም እንዲፈርሙ መቀስቀሱንም ተያያዝነው፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46934#sthash.mqNYdCst.dpuf


bbc affaan oromo


በእስካሁኑ ሂደት የፈረመው ሰው ብዛት ወደ ሳላሣ ሺህ እየተጠጋ ነው፡፡ በኢንተርኔት ላይ ሆነን እንደታዘብነው ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው፡፡ ሁሉም ወገኖች ዘመቻውን በበጎ መልኩ እያዩት ነው፡፡ እነ አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና ዓሊ ቢራን የመሳሰሉ ታላላቅ ሰዎችም የድጋፍ ፊርማቸውን ሰጥተዋል፡፡ ሌሎችም ድጋፋቸውን እንዲሰጡ እየቀሰቀሱም ነው፡፡ ይህ በጣም ጥሩ ነው፡፡ በተለይም የኢንተርኔቱ ዓለም ከሚታወቅበት “ጽንፋዊ” (polarized) አካሄድ ወጥተን ሁላችንም ፊርማችንን ማኖራችን በእጅጉ የሚያስደስት ነገር ነው፡፡ — የድጋፍ ፊርማችንን ያኖርነው በሙሉ በጎን የማሰብ ዓላማ እንጂ ሌላ ተቀጥላ መነሻ የለንም፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ምክንያቶች በደንብ የተብራሩ አይመስለኝም፡፡ በመሆኑም በጉዳዩ ዙሪያ ይህንን ጽሑፍ አሰናድቼአለሁ፡፡ እንደሚታወቀው “አፋን ኦሮሞ” (ኦሮምኛ) በአፍሪቃ ምድር እጅግ ብዙ ተናጋሪዎች ካሉት ቋንቋዎች አንዱ ነው፡፡ 40 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ቋንቋውን በአፍ መፍቻነት ይናገረዋል፡፡ ከስድስት ሚሊዮን የማያንሱ ህዝቦችም ኦሮምኛን በሁለተኛ ደረጃ ይናገራሉ፡፡ ይሁንና ኦሮምኛን ከሚናገረው ህዝብ መካከል ከ3/4 የሚልቀውና በገጠር የሚኖረው ህዝብ ከኦሮምኛ ውጪ ሌላ ቋንቋን አይናገርም፤ አይሰማም (ነገሩን በተነጻጻሪነት ለማወቅ ካሻችሁ የኦሮሚያ ክልል የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤትን ተመልከቱት)፡፡ ስለዚህ የቢቢሲ ስርጭት ኦሮምኛን ከዘነጋ ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ አይሆንም ማለት ነው፡፡ ታዲያ የሚገርመው ደግሞ በሬድዮ የሚሰማውን ፕሮግራም ከማንም በላይ የሚከታተለው የገጠሩ ህዝብ ነው፡፡ የከተማው ህዝብ በዝንባሌው ለቴሊቪዥን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ለኤፍ ኤም ሬድዮ ነው የሚያደላው፡፡ ቢቢሲ በሬድዮ ፕሮግራሙን ሲጀምር ተጨማሪ አማራጭ የሚፈጠርለት በአብዛኛው ለገጠሬው ህዝብ ነው፡፡ ነገር ግን ኦሮምኛ ከአዲሱ ፕሮግራም ውስጥ ከተዘነጋ የገጠሩ የኦሮሞ ህዝብ ሌሎች ቋንቋዎችን ባለመቻሉ እድሉ ሊያመልጠው ነው፡፡ እንግዲህ ቢቢሲ አፋን ኦሮሞን በስርጭት ሽፋኑ ውስጥ እንዲያካትት በድጋፍ ፊርማ መጠየቁ የተፈለገበት አንደኛው ምክንያት ይህ ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ለህዝቡ አማራጭ የመፍጠር ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ከላይ የተገለጹትን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የኦሮምኛ ተናጋሪዎች የሚመለከት ነው፡፡ እንደሚታወቀው በሶስተኛው ዓለም ሀገራት በአጭር ሞገድ የሚተላለፉ ሬድዮዎች በመንግሥታት የተያዙ በመሆናቸው ህዝቦች መረጃን ከነጻ ምንጭ የማግኘቱ ጉዳይ በጣም ይቸግራቸዋል፡፡ በግል፤ በፖለቲካ ፓርቲ እና በኮሚኒቲ እየተቋቋሙ ወደ አፍሪቃ ምድር ስርጭታቸውን የሚያስተላልፉ ሚዲያዎች በበኩላቸው መንግሥታቱን ለማጋለጥ በሚል ነገሮችን ከልክ በላይ እየለጠጡና እያጋነኑ ለአድማጩ ስለሚተርኩ ግራ መጋባትንና መደናገርን ይፈጥራሉ፡፡ ቢቢሲ፣ ቪኦኤ፣ ዶቼ ቬሌ ወዘተ.. የመሳሰሉት ግን ከሁሉም የተሻሉ ነጻ ሚዲያዎች በመሆናቸው በነርሱ የሚተላለፉት ዘገባዎች ለእውነታ የቀረቡ መሆናቸው ይታመናል፡፡ እናም ቢቢሲ በአፋን ኦሮሞ ፕሮግራም ጀመረ ማለት ኦሮምኛን የሚሰማውና የሚናገረው ህዝብ ነጻ መረጃ የሚያገኝበት እድል ጨመረ ማለት ነው፡፡ ሶስተኛው ምክንያት ደግሞ የቢቢሲ በኦሮምኛ ፕሮግራም መጀመር ለአፋን ኦሮሞ እድገት ወሳኝ ሚና የሚጫወት መሆኑ ነው፡፡ ቢቢሲ ሁሉንም አቀፍ እና በቢሊዮን የሚቆጠሩ አድማጮች ያሉት ተቋም ነው፡፡ የጣቢያው ስርጭት በተመራጭነቱ ቀዳሚ እንዲሆን ያስቻለው በየፕሮግራሙ የሚያስተላልፈው ጭብጥና ይዘት ብቻ ሳይሆን ቀዳሚነቱን ለማስቀጠል የሚያከናውናቸው ተያያዥ መርሐ ግብሮች ጭምር ነው፡፡ ከነዚህ መርሐ ግብሮች አንዱ ስርጭቱን የሚያስተላልፍባቸው ቋንቋዎችን ለማዘመን፣ ለማሳደግ እና ለማስተዋወቅ የሚያደርገው ጥረት ነው፡፡ ተቋሙ ፕሮግራሙን ሲያስተላልፍ የዘፈቀደ የቋንቋ አጠቃቀምን አይከተልም፡፡ ቢቢሲ እያንዳንዱን ቋንቋ በማጥናት የቋንቋው አድማጮች ሁሉ ሊረዱት የሚችሉትን አቀራረብ ይወጥንና በዚያ መሰረት ስርጭቱን ያስተላልፋል፡፡ ራሱ የሚገለገልበት BBC-Standard የተባለ የቋንቋ አጠቃቀም ዘይቤም አለው፡፡ በሌላ በኩል ቢቢሲ ስርጭቱን በሚያስተላልፍባቸው ቋንቋዎች ዙሪያ በሚደረጉት ምርምሮችም ተሳትፎ ያደርጋል፡፡ ቋንቋውንም ለማስተማር ልዩ ልዩ ጥረቶችን ያደርጋል (ለምሳሌ የቢቢሲ የዐረብኛው ፕሮግራም Learn BBC Arabic የተባለ ፕሮግራም አለው)፡፡ በቋንቋው የሚሰለጥኑ ተማሪዎችንም ይደግፋል፡፡ በቋንቋው የሚጻፉ የስነ-ጽሑፍ ውጤቶችን ያበረታታል፡፡ በሬድዮ ጣቢያውም ድርሰቶቹን ያስተዋውቃል፡፡ እነዚህ ተያያዥ ተግባራት ለኦሮምኛ ቋንቋ እድገት እጅግ በጣም ይጠቅማሉ፡፡ እንግዲህ “ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ” የተሰኘውን ዘመቻ ለመደገፍና ሌሎችም ድጋፋቸውን እንዲሰጡት ለመቀስቀስ የወሰንኩት እነዚህን ሁሉ መነሻዎች ካጤንኩ በኋላ ነው፡፡ በመሆኑም ለቋንቋው እድገት የሚቆረቆር እና በተለይም በገጠሩ የሚኖረው ህዝባችን አማራጭ ሚዲያ እንዲፈጠርለት የሚሻ ሰው በሙሉ ሊሳተፍበት የሚገባ ታሪካዊ ዘመቻ ነው ብዬ አምናለ
፡ ከዚህ ቀደም “ኦሮምኛን መማር እፈልጋለሁ” ፣ “ኦሮምኛ ከሌሎች ቋንቋዎች ጋር ያለው ተዛምዶ ለማጥናት ወስኛለሁ”፣ “የዓሊ ቢራን ዘፈን ግጥሞች ትርጉም ማወቅና በርሱ ዙሪያ መጻፍ እሻለሁ” ወዘተ… ስትሉኝ ለነበራችሁት ወዳጆቼ ደግሞ ዘመቻው የናንተንም ሆነ ተመሳሳይ ፍላጎትና ዝንባሌ ያላቸው ሌሎችም ሰዎች ምኞታቸውን እውነት ሊያደርጉ የሚችሉበትን ውጤት ለማምጣት የሚረዳ በመሆኑ ተሳትፎአችሁ በእጅጉ ይጠበቃል፡፡ — ይህ ዘመቻ ማንንም የመጉዳት ዓላማ የለውም፡፡ ዘመቻውን የጀመሩት ሰዎችም ሆኑ በሂደት የተቀላቀሉት ሁሉ ይህንን ጉዳይ በይፋ አስታውቀዋል፡፡ እያሳወቁም ነው፡፡ እኔም ደግሜ አስታውቃለሁ፡፡ ለምሳሌ ቢቢሲ የአማርኛውንም ሆነ የትግርኛውን ፕሮግራም እንዲያስቀር በጭራሽ አልተጠየቀም፡፡ ሊጠየቅም አይችልም፡፡ እንዲህ ብሎ መጠየቁ ከመጥፎ ምሳሌነቱ ሌላ ጥያቄው ተቀባይነት እንዳይኖረው ማድረግ ነው፡፡ ጥያቄው የቀረበው ቢቢሲ የቪኦኤን አርአያ በመከተል ስርጭቱን በሶስቱ ቋንቋዎች እንዲጀምር ነው (ስርጭቱን የሚያስተላልፍበትን የጊዜ መጠን የመወሰኑ ስልጣን የጣቢያው ነው፤ ያንን እኛ አንወስንለትም)፡፡ በመሆኑም ይህ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል፡፡ —- ስለዚህ ወዳጆቻችን ሆይ! ይህ ዘመቻ የተቀደሰ ሃሳብ ያለው ነው፡፡ የድጋፍ ፊርማችሁን በማኖር የዘመቻው ደጋፊ እንድትሆኑ በአክብሮት ትጠየቃላችሁ፡፡ ለዚህ ደግሞ ብዙ መሰዋት አያስፈልጋችሁም፡፡ ሶስት ደቂቃ ብቻ ወስዳችሁ ለዚሁ የተዘጋጀውን petition መፈረምንና ወደሚፈለግበት ቦታ send ማድረግን ብቻ ነው የሚጠይቀው፡፡ እናም ቀጥሎ የተመለከተውን ሊንክ ከፍታችሁ ፔቲሽኑን ፈርሙልን!! ዳይ https://www.gopetition.com/…/bbc-consider-afan-oromo-for-ne… —- ማስታወሻ • ፔቲሽኑን መፈረም ማለት ሊንኩን ከፍቶ ፎርሙን መሙላት ነው:: ስለዚህ ሊንኩን ከፍታችሁ ወደ መፈረሚያው ሂዱልን!! ፎርሙ የሚመጣላችሁ sign the petition የሚለውን ቦታ ስትነኩት ነው፡፡ • ፔቲሽኑን ለመፈረም የግዴታ የኢ-ሜይል አድራሻችሁን ማስገባት አለባችሁ፡፡ ከዚያም የቀረቡትን ጥያቄዎች በመከተል ፎርሙን መሙላት ይገባችኋል፡፡ መጨረሻ ላይ የተሞላውን ፎርም send አድርጋችሁ ስታበቁ ፊርማውን ስለመስጠታችሁ ማረጋገጫው በኢ-ሜይል ይላክላችኋል - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46934#sthash.mqNYdCst.dpuf

No comments:

Post a Comment