የህወሓት ባለስልጣናት የስልጣን ሽኩቻ የመቀሌውን ቡድን በመምራት የበላይነታቸውን አስጠብቀው ወጥተዋል የተባሉት አቶ አባይ ወልዱ በአዲሱ ካቢኔ ተመልሰው ክልሉ ፕሬዝዳንት ሆኑ ሲሆን የመቀሌን ከተማ በከንቲባነት ለመምራት ሙሉ በሙሉ በህወሓት ቁጥጥር ስር ያላውን የአገሪቱን ደህነት መ/ቤት የሚመሩትና ስርዓቱ የሚፈጽማቸውን ግድያና ማሰቃየት ተጠያቂው አቶ ጌታቸው አሰፋ ወንድም ዳንኤል አሰፋ በአዲሱ ካቢኔ የመቀሌ ከንቲባ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46912#sthash.X6xaJ4Ng.dpuf
የክልሉ ም/አስተዳዳሪ ዶ/ር አዲስ ዓለም ባሌማ፣የትዕምት ሀላፊ አቶ በየነ መክሩ ፣በቀድሞው የህወሃት ፕሮፖጋንዳ ሀላፊ ቴዎድሮስ ሀጎስ አቶ አለም ገብረዋህድ በቦታው በአዲሱ ካቢኔ የተመረጡ ሲሆን በአቶ ኤርሚያስ ለገሰ ቱርፋቶች ባለቤት አልባ በካሳንቺሱ መንግስት ውስጥ የተጠቀሰችው ሞንጆሪኖ (ፈትለወርቅ) የህወሃት ህዝብ አደረጃጀት መሆናቸውን ያገኘነው መረጃ ይገልጻል። ህወሓት የአገሪቱን ዋና ዋና ስልጣን በአንድ ብሄር የበላይነት፣ወታደራዊ፣ዋና ዋና ኢኮኖሚ ተቃማቱንና ደህነቱን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ በቤተሰብና በቡድን የተከፋፈሉትን ስልጣን ከፌዴራል እስከ ክልል መቆጣጠራቸውን አንዳንዶች ከህወሃትም በስልጣንና በሀብት የናጠጠው ቡድን ጥቂት ግለሰቦች የሚያሽከረክሩት ነው ይባላል። ቀድሞ የመለስ አዜብ ቡድን፣የስብሃት ቡድን፣የነአርከበ ቡድን ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው። የህወሓት ባለስልጣናት የመቀሌና የአዲስ አበባ በሚል ከህወሃት ጉባዔ በፊት የጀመሩት የስልጣን ሽኩቻ አንዱ የአንዱን ደጋፊ ወደ ማሳደድ እንደዘለቀ አስቀድመን መዘገባችን አይዘነጋም።የመቀሌው ቡድን በአቶ አባይ ወልዱ የሚመራ ሲሆን የአዲስ አበባው በዶ/ር ደብረጽዮን ይመራ እንደነበርና የአቶ አባይ ቡድን በጉባዔው በአነስተኛ ድምጽ ተመርጦ በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ለትልቁ የፓርቲ ስልጣን በርካታ ደጋፊዎቹን ማስመረጡን አምዶም ገ/ስላሴን ጠቅሰን በስፋት መዘገባችን ይታወሳል - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46912#sthash.gn2U7rsu.dpuf
No comments:
Post a Comment