Tuesday, September 22, 2015

ቢቢሲ ወደ ኢትዮጵያ ሊያስተላልፍ ያቀደው ፕሮግራም እና የቋንቋ ምርጫ

ቢቢሲ ወደ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሚተላለፍ የዜና ፕሮግራም ለመጀመር ፍላጎት እንዳለው ማሳወቁን ተከትሎ አንዳንድ እራሳቸውን “ኦሮሞ ፈርስት” በማለት የሚጠሩ የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች ቢቢሲ ወደ ኢትዮጵያ ለማስተላለፍ ያሰበውን ፕሮግራም በኦሮምኛ ቋንቋ እንዲያደርግ ፔትሽን በማስፈረም ላይ መሆናቸው ታውቋል።BBC world news to Ethiopia
ቢቢሲ ወደ ኢትዮጵያ ሊያስተላልፍ ያሰበው የዜና ፕሮግራም በምን ቋንቋ እንደሆን የገለጸው ነገር የለም።
ቢቢሲ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ፕሮግራሙን ቢያስተላልፍ ተደማጭነቱ እና ተደራሽነቱ እጅግም ይሆናል፣ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ እንግሊዘኛ ቋንቋን ስለማይነጋገር።
ቢቢሲ ወደ ኢትዮጵይ ሊያስተላልፍ ያሰበውን የዜና ፕሮግራም በሃገሬው ቋንቋ እንዲሆን ከወሰነ ግን የአማርኛ ቋንቋን ይጠቀማል ተብሎ ይገመታል። አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ አማርኛ ቋንቋን ከመናገሩም ባሻገር አማርኛ የኢትዮጵያ የስራ ቋንቋ ሆኖ ኖርዋል።
ምናልባት ቢቢሲ ፕሮግራሙን በተለያዩ ሃገራዊ ቋንቋዎች ለማስተላለፍ ከወሰነ ደግሞ ከአማርኛ ቀጥሎ ኦሮምኛ ቋንቋን በቀዳሚነት ሊጠቀም ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
የቢቢሲ ጀነራል ዳይሬክተር ቶኒ ሃል እንዳሉት ከሆነ በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሰሜን ኮሪያ እና ራሺያ “የዲሞክራሲ እጥረት” በመኖሩ ያንን ቀዳዳ ለመሸፈን በማሰብ ነው ቢቢሲ በእነዚህ ሃገራት አዲስ የዜና ፕሮግራሞችን ለማሰራጨት ያሰበው።

No comments:

Post a Comment