(ዘ-ሐበሻ) ረቡዕ ኦክቶበር 28, 2015 ዓ.ም በቤተሰቧ ሰላም ያውልሽ ተብላ ተመርቃ ወደ ትምህርት ቤት ለማምራት ከቤት ወጣች:: ሕሊና ደሪባ:: ነዋሪነቷ በኤተን ካውንቲ ሚቺጋን አሜሪካ ውስጥ ነው::
የ14 ዓመቷ የዋቨርሊ ከፍተኛ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችው ይህችው ልጅ ድንገት የሚበር መኪና መትቷት ሹፌሩም እንደወደቀች መኪናውን ሳያቆም ጥሏት ጠፋ:: ሰዓቱ ገና ከጠዋቱ 7:30 ነበር::
ሕሊና ወዲያውኑ የህክምና እርዳታ ብታገኝም ከሁለት ቀናት በኋላ ሕይወቷ ሊያልፍ ችሏል::
የዓይን እማኞች ጠቆር ያለ ሲዳን መኪና ያሽከረክር የነበረ ሹፌር ገጭቷት እንደሄደ ለፖሊስ ምስክርነታቸውን በሰጡት መሰረት ተከሳሹ ትናንት እዚያው ሚችጋን ተይዞ በኤተን ካውንቲ በሚገኘው ፍርድ ቤት ቀርቦ ክስ እንደተመሰረተ ከወደ ሚችጋን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል::
የ14 ዓመቷን ሕሊና በመኪና ገጭቶ በማምለጥ ወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረው የ68 ዓመቱ ሄክተር አሮዮ እስከ 15 ዓመት የሚደርስ ቅጣት እንደሚጠብቀው ተገልጿል:: ተጠርጣሪው 3 ክስ እንደተከፈተበት ያስረዱት የዘ-ሐበሻ የመረጃ ምንጮች 1ኛው ክስ የታገደ መንጃ ፈቃድ ይዞ በመንዳት 2ኛው ያለ ውዴታ በስህተት ሰው በመኪና በመግጨትና 3ኛው ሰው ከገጨ በኋላ ሳይረዳ በግዴለሽነት መኪናውን አስነስቶ በመሄድና በዚህም የተነሳ ለሞት በመዳረጓ የሚሉ ክሶች ተከሷል::
ተከሳቹ ኖቬምበር 22 ፍርድ ቤት ለቀጣይ ቀጠሮ እንዲቀርብ ታዟል::
የሟች እናት የልጇን አስከሬን ኢትዮጵያ ወስዳ መቅበር እንደምትፈልግ ያስታወቁት የዘ-ሐበሻ ምንጮች በኢንተርኔት የወላጆቿን ወጪ ለመጋራት የገቢ ማሰባሰብ እየተደረገ ነው:: መርዳት ለምትፈልጉ ሊንኩ የሚከተለው
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47899#sthash.Xpn5wT1Y.dpuf
No comments:
Post a Comment