Tuesday, October 27, 2015

(ሰበር ዜና) 300 መንገደኞችን ጭኖ ወደ አሜሪካ ሲበር የነበረው ድሪምላይነር የኢትዮጵያ አውሮፕላን አየር ላይ እንዳለ ሞተሩ መሥራት አቆመ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47635#sthash.S9CLQr33.dpuf

(ዘ-ሐበሻ) ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነውና ከአዲስ አበባ ተነስቶ በአየርላንድ በኩል ወደ አሜሪካ ሲበር የነበረው የበረራ ቁጥሩ ET-500 የሆነው 787-8 ድሪምላይነር የኢትዮጵያ አውሮፕላን አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ችግር ስላጋጠመው ተመልሶ ወደ ደብሊን ለማረፍ መገደዱን ዘደይሊ ሜይል ጋዜጣ ዘገበ:: ዛሬ ከጠዋቱ 6:00 አካባቢ 300 የሚሆኑ መንገደኞችን ጭኖ ከአየር ላንድ ደብሊን አውሮፕላን የተነሳው ይኸው ድሪምላይነር አውሮፕላን ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በረራ ላይ እንዳለ የአንደኛው አውሮፕላን ሞተር ሥራ በማቆሙ ተመልሶ ደብሊን ላይ እንዲያርፍ ተደርጓል::: ለአንድ ሰዓታት ያህል በአየርላንድ ቆይታ አድርጎ ጋዝና ሌሎች ምግቦችን ለተሳፋሪዎች የጫነው ይኸው ቦይንግ 787-8 አውሮፕላንድ ለሁለት ሰዓት ተኩል ያህል ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ጉዞ ለማድረግ በአየር ላይ መቆየቱን ዘ-ሐበሻ ከደይሊ ሜይል ያገኘችው መረጃ ያስረዳል:: የአውሮፕላኑ አንድ ክንፍ ሞተር ሥራ በማቆሙ የተነሳ ከ2:30 ዓየር ላይ ቆይታ በኋላ ወደ ደብሊን የተመለሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድሪም ላይነር አውሮፕላንድ ከጠዋቱ 8:30 አካባቢ በሰላም ማረፉም ተዘግቧል:: ይህ አውሮፕላን ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የማይበር ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቀያሪ አውሮፕላን ከፍራንክፈርት ጀርመን በመላክ የበረራ 500 ተጓዦች እንደገና በረራቸውን በ እንግሊዝ ሰዓት አቆጣተር 1 ሰዓት ላይ እንደሚጀመሩ ዘሐበሻ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል;: ድሪምላይነር አውሮፕላኖች እንዲህ ያለው ችግር ሲያጋጥማቸው ይህ የመጀመሪያው አይደለም::   ከዚህ ቀደም:- በ2013 ዓ.ም:- ድሪምላይነር ቦይንግ 787 ግዙፍ አውሮፕላን ገጠመው በተባለው የባትሪ ችግር ምክንያት ከመሬት እንዳይነሳ ለ3 ወራት ያህል በመላው ዓለም ቢታገድም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ድሪም ላይነር አውሮፕላን ማብረሩ ይታወሳል:: አሁንም በዚያው በ2013 ዓ.ም ተሣፋሪ ባልነበረበት አይሮፕላን ላይ ዛሬ የተነሣ እሳት የለንደኑ ሂትሮው አይሮፕላን ማረፍያ እንዲዘጋ አድርጓል። እሳቱ የተነሳው ድሪምላይነር ቦይንግ 787 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን ውስጥ ነበር:: በአይሮፕላኑ ላይ ጢስ በታየበት ጊዜ ሞተሩ እየሠራ እንዳልነበረና ለስምንት ሰዓታት ያህል እዚያው ቆሞ እንደነበረ እንዲሁም ለምሽት በረራ የተዘጋጀ እንደነበረ የአጋጣሚው መንስዔ ምን እንደሆነ እንደማይታወቅ የአየር መንገዱ ሥራ አስፈጻሚ ገልጸው ነበር:: - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47635#sthash.z7lHEuAQ


fdreamliber ethiopiadream linerdream liner 3

No comments:

Post a Comment