(ዘ-ሐበሻ) ከሮሃ ባንድ ጋር ‘እንደገና’ የተሰኘውን የሙዚቃ አልበሙን በቅርቡ የተለቀቀለት ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ በሃገር ቤትም ሆነ በውጭ ሃገር ዘፈኖቹ በከፍተኛ ሁኔታ እየተደመጡለት ይገኛሉ ተባለ::
ላለፉት 30 ዓመታት ከሠራቸው ተወዳጅ ሙዚቃዎች ውስጥ የተወሰኑትን መርጦ በኮሌሽን መልክ በሲዲ ያቀረበው ኤፍሬም ለአልበሙ መጠሪያ “እንደገና” የሚል ስያሜ ሰጥቶታል:: በዚህ የሙዚቃ አልበም የቀድሞው ሮሃ ባንድ እንደና ተሳትፎበታል::
ኤፍሬም ታምሩ ይህንን አልበም በኮሌክሽን መልክ ለማውጣት ረዥም ጊዜ የፈጀበት ሲሆን ከዚህ ቀደም አልበሙን ሰርቶ ሊለቀው ሲል የ እርሱን ድምጽ አስመስሎ የሚዘፍን ሌላ ድምፃዊ ራሱን ዘፈኖች በሲዲ በመልቀቁ ሲዲው ሊዘገይ ችሏል:: በተጨማሪም ባለፈው ዓመት ይኸው ሥራ ይለቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ በድንገት እናቱ በማረፋቸው እንደገና የሲዲው ሥራ ዘግይቷል:: ለዚህም ነው ኤፍሬም “ይህ የሙዚቃ አልበም የትዕግስትን ምንነት አስተምሮኛል” ያለው::
እንደልፋቱም ይህ የሙዚቃ አልበም በከፍተኛ ሁኔታ እየተደመጠ መሆኑ ድምፃዊውን ሊያስደስተው እንደሚችል ይታመናል:: ኤፍሬም ሰሞኑን በአዲስ አበባ ታትሞ ለወጣው ቁምነገር መጽሔት በሰጠው ቃለምልልስ እስካሁን ለኢትዮጵያ ጀግና አትሌቶች መወደሻ የሚሆን ዘፈን አለመሥራቱን እና ወደፊት ግን እግዚአብሄር እንደሚያውቅ ተናግሯል:: ሙሉ ቃለምልልሱ ከቁምነገር መጽሔት እንደደረሰን እናስነብባችኋለን::
No comments:
Post a Comment