ባለፈውጵያ የሆነው የወያኔ ቡድን በሥልጣን ኮርቻ ላይ ከተቆናጠጠ ጀምሮ የኢትዮጵያን አንጡራ ሀብት ዘርፎና ለቡድኑ መጠቀሚያ አድርጎ በወሰን አካባቢ ያሉ ለም መሬቶችን ተቃዋሚዎችን ለሚቆጣጠርለትና መስል አጽፋዊ ስጦታ ለሚያደርግለት ለሱዳን አስረክቦ፤ ሰፋፊ ለም የእርሻ ቦታዎችን ለውጭ አገር ከበርቴዎች በሊዝ ሸጦ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ትውልድ ይቅር የማይለው ከፍተኛ በደል ፈጽሟል። ይህን ግፍና በደል ለማስቀረትና የሕዝቡን መብትና ጥቅም ለማስከበር ከቡድኑ ጥቅም በላይ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደንታ የሌለውን ዘረኛና አምባገነን ቡድን በሕዝባዊ ኃይል ከማውረድ በስተቀር ሌላ አማራጭ የሌለ በመሆኑ ዛሬም ትግላችንን በሕብረት አጠናክረን ወደፊት እንግፋ የሚለው ጥሪ ወቅታዊ ሆኖ የሚገኝ ነው። ሕዝባዊ ትግሉን በኀብረት እናጠናክር !! ፀረ ኢትዮጵያ የሆነው የወያኔ አገዛዝ ይወገዳል ሳምንት የወያኔ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያዎች በመታጀብ ጎንደር
አርማጭሆ ውስጥ ሶረቃ በሚባለው አካባቢው አርሶ አደሮችን በኃይልና በማን አለብኝነት
አስነስተው ቦታውን ወደ ትግራይ ክልል ለማጠቃለል ያደረጉት ጥረት ሕዝቡ ከዳር እስከዳር
በመንቀሳቀስና ውጊያ በመግጠም ያከሸፈው መሆኑ ታውቋል። በተደረገው ግጭትም ከሁለቱም
በኩል ጉዳት የደረሰ መሆኑ ከሥፍራው የሚገኙ ዜናዎች ያስረዳሉ። ሁኔታው እስካሁን ያልበረደ
ሲሆን ሕዝቡም ከዳር እስከ ዳር ተጠራርቶ መብቱን ለማስከበርና ንብረቱን ለማስጠበቅ
ባንድነት ለመታገል ወስኗል።
የወያኔ አገዛዝ ሥልጣን ላይ ለመቆየት አገሪቱን በጎሳና በቋንቋ እንዲሁም በሃይማኖት በመከፋፈል
በሕዝብና በሀገር ላይ ከፍተኛ በደል ከመፈጸሙ በተጨማሪ ለዓመታት በጎንደርና በወሎ
ክፍለሀገራት የነበሩትን ሰፊ አካባቢዎች ያለ ሕዝቡ ፈቃድና ስምምነት ቀምቶ በትእቢትና
በማናለብኝነት በትግራይ ክልል ውስጥ እንዲጠቃለሉ ያደረገ መሆኑ ይታወሳል። የወያኔ እኩይ
ተግባር ሕዝቡን ከፍተኛ ብሶት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። ይህ አልበቃ ብሏቸው የወያኔ ሆዳም
ባለሥልጣኖች ደኻውን ገበሬ ከእርሻ ቦታው ላይ አፈናቅለው መሬቱን ለመቀራመት የወሰዱት
እርምጃ በጽኑ የሚወገዝ ነው።
ጸረ ኢትዮ!!
No comments:
Post a Comment