Thursday, November 5, 2015

መንግስት በመምህር ግርማ ላይ ከግድያ ወንጀል ጋር በተያየዘ ተጨማሪ ክስ ሊመሠርት መሆኑ ተሰማ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48005#sthash.2WxJr11Z.dpuf

girma wendimu

(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂው አጥማዊ መምህር ግርማ ወንድሙ በማታለል ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው ወህኒ ከወረዱ በኋላ አቃቤ ሕግ የጠየቀባቸው 7 ቀን ዛሬ በማለቁ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ በዘ-ሐበሻ መዘገቡ አይዘነጋም:: ከአዲስ አበባ የመጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ፖሊስ በማታለል ወንጀል ያቀረበባቸው ክስ ዋስትና ሊያስፈቅድ የሚችል በመሆኑ ከግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ክስ ለመመስረት አሁንም የጊዜ ቀጥሮ ሊጠይቅባቸው እንደሚችል ነው:: ፖሊስ የመምህር ግርማ ቤትን ከታሰሩ በኋላ እርሳቸው በሌሉበት መበርበሩ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ብርበራ አሁን ሊመሰረትባቸው ከታቀደው የነብስ ግድያ ጋር ከተያያዘ ክስ ጋር ተያያዥነት ይኑረው አይኑረው የታወቀ ነገር የለም ሲሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል:: በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ በታዋቂው አጥማቂ መምህር ግርማ ወንድሙ ላይ የመታሰራቸው ዜና ሲነበብ በርካታ ተከታዮቻቸው መታሰራቸው ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ሴራ ነው በሚል ሲቃወሙ ሰንብተዋል:: ከፍርድ ቤት ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን እናቀርባለን:: - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48005#sthash.2WxJr11Z.dpuf

No comments:

Post a Comment