ስሜነህ ከሚኒሶታ
15 ሚሊዮን ሕዝብ ተርቧል ሲባል አንዳንድ የስርዓቱ ገጽታ እንዲበላሽ የማይፈልጉ ተላላኪዎች “የተራበም በርሃብ የሞተም የለም” በሚል አይናቸውን ጨፍነው ሲከራከሩ ማየት በጣም ያማል:: በቅርቡ በቢቢሲ ላይ ወጥታ ልጇ በርሃብ የሞተባት ወ/ሮ ብርቱካን እንዴት አድርገው በመሳሪያ ሃይል አስፈራርተው ልጄ በርሃብ አልሞተም እንድትል እንዳደረጓት የቀናት ት ዝታችን ነው:: ዛሬ ከዓመት በፊት በኢትዮጵያ የተለቀቀውን ቪዲዮ ለትውስታ ያቀረብኩላችሁ እነዚሁ የ ስር ዓቱ መልካም ገጽታ ገንቢዎች እንዲያፍሩ በማሰብ ነው:: አሁን ድረስ በአዲስ አበባ ችግር ውስጥ ያሉ ህፃናት ከቆሻሻ መጣያ ምግብ እያነሱ ይመገባሉ:: የ ስር ዓቱ ተላላኪዎች እነዚህንስ ምን ይሏቸው ይሆን?
የሚያሳዝነው የስርዓቱ ደጋፊዎች ይህን እውነታ ለመደበቅ መሞከራቸው ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ይህን ለመለወጥ ሲሰሩና ሲጥሩ አላሰራ ማለታቸው ነው:: በቅርቡ በየሃገራቱ ያሉት የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች ያወጧቸውን መግለጫዎች ይጠቅሷል::
No comments:
Post a Comment