እህት ፈቲሐ ነገ ወደ ሐገር ቤት ትገባለች !
=================
* ለወራት በህክምና ላይ የነበረችው እህት ፈቲሐ በወገኖቿ አይዞሽ ባይነት ከትናንት ዛሬ ተሽሏታል
* ያ የተቃጠለ የሚመስለው መልኳ ዛሬ ወዝ ይታይበታል
* እህት ፈቲሐ ነገ ወደ ሐገር ቤት እንድትገባ ትልቅ ድጋፍ ያደረጉላት አረብ አሰሪዎቿ ናቸው
* አረብ አሰሪዎቿ የመውጫ ቪዛ አስጨርሰው በራሳቸው ገንዘብ ትኬት ቆርጠውላታል
* አረብ አሰሪዎቿ መራመድ የማይችለውን እህት ፈቲሐን ሐገር ቤት ደግፎ የሚያደርስ የጤና ረዳት ቀጥረውላታል
* ፈቲሐ ነገ አርብ በሳውዲ አየር መንገድ ከምሽቱ 10:30 ላይ የሀገሯን ምድር ትረግጣለች
* ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቲሐን ምስል ተመልክቶ በእንባ የታጠበው አንጀተ ርህሩህ ወዳጃችን ሳሙኤል ማስረሻ ለእህት ፈቲሐን በመንግስት ሐኪም ቤቶች ግብታ ህክምና እንድታገኝ እንደሚሞክር ቃል ገብቶልኛል
* የተመላሽ ስደተኞች አባት የምንለው ወዳጃችን ሳሙኤል ማስረሻ ቀይ መስቀልን አምቡላንስ ጠይቆ ተፈቅዶለታል
* እዚህም እዚያም ዝግጅቱ ተጠናቅቋል
* እህት ፈቲሐ በጤና እያለች ሰርታ ካገኘችውና በአደራ በጅዳ ቆንሰል ያስቀመጠችውን 4800 የሳውዲ ሪያል ገንዘቧን ዛሬ እንደምትረከብ ትናንት አጫውታኛለች
በእህት ፈቲሐ ለወራት በንጉስ ፉአድ ሆስፒታል ታክማ አሁን ከበፊቱ ተሽሏታል ። በጅዳና አካባቢው ያሉ ለነፍሳቸው ያደሩ በርካታ ኢትዮጵያውን ዘር ሐይማኖት ሳይለዩ ላለፉት ወራት ፈቲሐን እየጎበኙ ተስፋ ሰጥተዋታል ፣ ደግፈዋታል !
” የመንግስት ተወካዮች እርባና ያለው ድጋፍ በማያደርጉበት ሰአት ዜጎች እርስ በርሳችን እንዲህ ሲተባበሩ ማየት ደስ ይላል ! ” ያለኝ ፈቲሐን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እየደገፈ ያለው ወንድም ነው !
እህት ፈቲሐ ለደገፋት ለሁሉም ምስጋና አቅርብልኝ ብላኛለች ፣ ምስጋናዋ ይድረሳችሁ !
ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 22 ቀን 2008 ዓም
No comments:
Post a Comment