ከወልቃይት ጠገዴ ብጌምድር፤ ጎንደር ኢትዮጵያ
በ24 አመታት ውስጥ በተለያዩ የኢትዮጵያ አከባቢ ጥቂት የሚባሉ መልካም ለውጦች ቢኖሩም እንኳ ጀግናው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ አይደለም የመልካሙን ለውጥ ሊያጣጥም እንዲያውም በተቀነባበረ ሁኔታ የዛሬ 24 አመት ከነበረበት የህልውናና ኑሮ ብዙ እጥፍ አሽቆልቁሎ ተምዘግዝጎ ወርዶበታል፤ ወያኔ አሰቃይቶታል፤ ህይወቱና አኗኗሩ አመሰቃቅሎበታል፤ ለብዙ መከራና ስቃይ ሞትና እንግልት መታሰርና ደብዛ መጥፋት መሰደድና መሸማቀቅ ዳርጎታል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከ1972 ጀምሮ የወያኔ መርዝ የተርከፈከፈበት ህዝብ ነው። አሳዛኙ ነገር ወያኔ የፈጠረው ችግር በሁሉም የኢትዮጵያ መርዙን ከመትፋቱ ጋር ተያይዞ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወገኑ የየራሱን ህመም ሲያዳምጥ ስለኖረ ከህመም ሁሉ ህመም፣ ከእልቂት ሁሉ እልቂት ሲፈጸምበት፣ በእስራኤላውያን ላይ በኦሽዊትስ ካምፕ በናዚዎች የተቀነባበረው የዘር ማጥፋት በ21ኛው መ.ክ.ዘ በወያኔዎቹ በግልጽና በድብቅ ሲደገም የሚዲያ ሽፋን ስለማይደርሰው ኢትዮጵያዉያን ወገኖቹ ሊያውቁለትና ሃይ ሊሉት አልቻሉም መከራዉን ከ1972 አ/ም ጀምሮ ወገኖቹ ሳይደርሱለት ብቻውን ሲጎነጭ ኖሯል።

እዚህ ላይ ለማሳሰብ እምፈልገው ዋና ነጥብ በአማራነታችን እየደረሰብን ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ህወሃት በመልካም አስተዳደር ስም ለማስተባበል መሞከር በፍጹም አይቻልም፤ የመልካም አስተዳደር ችግርማ አሜሪካም ውስጥ ቢሆን ይኖር ይሆናል። እኛ አንደላቃችሁ አኑሩን አይደለም እያልን ያለነው። ዋናው ጥያቄያችን የወልቃይት ጠገዴ ህዝብና መሬት አማራ ስለሆነ ወደ እናት አገራችን ወደ ጎንደር ወደ አማራነታችን መልሱን የሚል ነው። ሰላምን ፈልገው ከመለሱን እጅግ ደስ ይለናል ካልሆነ ደግሞ የእነርሱ ፈቃድና ምስክርነት ሳያስፈልገን በራሳችን ራሳችንን አማራነታችንን አስረግጠን እንመልሳለን።በቃ ይሔው ነው!!! ይህ በትግራይ ተስፋፊና ነጻ አውጭ ቡድን፣ በትግራይ ፖሊስ፣ በትግራይ ልዩ ሃይል፣ በአጋዚ ወታደር፣ በትግራይ አስተዳደር አመራሮችና ካድሬዎች ማዳፈን የማይቻል የሚፋጅ ረመጥ ጥያቄ ነው።
የኢትዮጵያ ወገኖቻችን ሆይ ታሪክ የሚመሰክረስው እውነት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብና መሬት የአማራ እንጂ የትግሬ ሆኖ እንደማያውቅ እንድታውቁሉን ነው። የታሪክ መዛግብት ከሚመሰክሩት እውነት በተቃራኒ ታሪኩን በማዛባት እንደማጣቀሻ ከሚያቀርቡ የትግራይን ህዝብ ከማይወክሉ የወያኔ ባንዳ የሆኑ የታሪክ ሙሁር ነን ባዮች ለምሳሌ እንደ ዶክተር ገላውዲዮስ ያሉ የውሸት ታሪክ አጣቃሾች ታሪክ ይፋረዳቸዋል። በነገራችን ላይ ገላውዲዮስ በትግሬኛ የአሜሪካን ድምጽ ሬድዮ ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ያጣቀሱት መጽሓፍ መጽሓፉ ከሚለው በተቃራኒ ስለሆነ ክስ ለመመስረት ዲግሪያቸውን ለማስነጠቅና ሌላም ህጋዊ ቅጣት እንዲወሰድባቸው ሙሁራኖች እየሰሩ ነው። በዉሸት የህዝብን ጥያቄ አዳፍኖ ዘሩን መጨረስ እንደማይቻል ሊማሩ ይገባቸዋል እነዚህ ከንቱና ጠፊ ዘራፊዎች። ሌላው የተማረ ኢትዮጵያዊ ያለ የማይመስላቸው ጠባቦቹና ዘረኞቹ የትግራይን ምስኪን ህዝብ የማይወክሉ ወረበሎች የኢትዮጵያ ህዝብ በቃችሁ ሊላቸው ይገባል። በዚህ አጋጣሚ የታሪክ እውነተኛ ሙሁር አቻምየለህ ታምሩን ስለሚያደርጉት የውሸተኞች ካድሬ ሙሁሮችን ሴራ ማጋለጥ በእጅጉ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ልባዊ ምስጋና እንዳስተላልፍላቸው ይፈቀድልኝ። እንዲሁም ክቡር ልኡል ራስ መንገሻ ስዩም፣ክቡር አቶ ገብረመድህን አር አያ፣ ክቡር አቶ ያሬድ ጥበቡንና ሌሎች ውድ የኢትዮጵያ አንድነት የሚገዳቸውና አጥብቀው የሚሰሩ እውነተኛ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ አብዛኛው ሙሁር በወልቃይት ጠገዴ ዝምታውን መርጦ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ እንደበግ ለመታረድ ወያኔ የውሸት ታሪክን እንደቅመም እየተጠቀመበት ባለበት ስአት እውነተኛ ቃላቸውን ስለሰጡ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ልዩ ምስጋናየን አቀርባለሁ። ሌሎች ሙሁራን ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሁንም ህዝቡ የግረሱልኝ ጥሪውን በማስተጋባት ላይ ነውና እባካችሁ ድረሱልን።ተሳትፎ ያደርጋችሁ ሙሁራንም ሳይለየን የአገራችን ህግ በወያኔ ምክንያት ካልዳኘን ወደ አለማቀፍ ህግ ጉዳያችን ወስዳችሁ ከሞት እንድትታደጉን እርዳታችሁ እንዳይለየን በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን።
ወያኔ ይህ ሁሉ ስቃይ የሚፈጸምበት ምክንያት ህዝቡ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት የሚታይበት ከዘረግኝነት የጸዳ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ስለሆነ ነው። ይህም ማለትም እስከቅርቡ ድረስ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያየ ብሔር ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በአሁኑ ግዜም ቢሆን ለአፍሪካዉያንም ጭምር ማለትም ሰሜንም ደቡብም ሱዳናዉያን የመሳሰሉ የአፍሪካ ዜጎችም ሰርተው ህይወታቸውን ቀይረውበት በሰላምና በፍቅር ደስ ብሏቸው የሚኖሩበት ከኢትዮጵያዊነቱ በዘለለ በአፍሪካዊነቱም የማይታማ ህዝብና በጣም ለምና በተፈጥሮ ሃብት በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የሆነ አካባቢ በመሆኑ ዘረኞቹ ወያኔዎችና ትግሬዎቹ የተፈጥሮ ሃብቱን ቋመጡት፤ ኢትዮጵያዊ ስሜቱንም አልወደዱትም። የሚገርመው ነገር ህዝቡን አጥፍተው ‘ታላቂቷን ትግራይ’ በመመስረት ከሱዳንና ኤርትራ ጋር እንዋሰናለን አማራም እናጠፋለን ብለው ተነሱ። የሚገርመው ነገር ላለፉት 36 አመታት እነርሱ የሚፈጸሙት ስቃይ አላረካ አልበቃ ብሏቸው በሱዳን ልዩ ሃይሎች ከፍተኛ የአፈናና ግድያ አስፈጸሙበት። የስንቱ የሃገር ጀግናና የአገር አልኝታ ህይወት ቀጠፉት አስቀጠፉት መሰላችሁ። ጀግናው ህዝብም የሚቻለውን ያህል ታገለ ቢሆንም ግን ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ ብሗላ ወታደራዊ ሃይሉን አጠናክሮ በመምጣት ቦታውን ተቆጣጠረ ህዝቡንም በተለይም ወንዶችን ልክ እንደፈርዖን እያደነ ማሰር፣ ማሳደድ፣ ማሰቃየትና መዝረፍ ጀመረ በተለይ ከ1983 አ/ም ጀምሮ።
No comments:
Post a Comment