Wednesday, March 30, 2016

በኦሮሚያ በአርሲና ኤሊባቡር የተማሪዎች ተቃውሞ አገርሽቷል – በምዕራብ ሐረርጌም ለሁለተኛ ቀን እንደቀጠለ ነው

ዘ-ሐበሻ) ጋብ ያለ መስሎ የነበረው የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ እንደአዲስ በየቦታው እያገረሸ መሆኑ ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የሚደርሰው መረጃ ጠቆሙ::
በኦሮሚያ በተለያዩ አካባቢዎች እንደአዲስ ተቃውሞው ያገረሸባቸው አካባቢዎች ኢሊባቡር; ሐረርጌ እና አርሲ ናቸው:: በምዕራብ ሐረርጌ ፋዴስ ወረዳ የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሁለተኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል የሰፈረው የሕወሓት ልዩ ኃይል በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ተቃውሞውን እንዲያቆሙ እርምጃ ለመውሰድ ቢሞክርም የሕዝቡ ቁጣ ገንፍሎ እንደሚገኝ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ:: የአካባቢው ነዋሪ የወረዳውን አስተዳደር ከስልጣን እንዳባረረውም ጨምሮ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል::
oromo
በኤሊባቡርና አርሲም እንዲሁም ዳግም የሕዝቡ ቁጣ አይሎ ከሕወሓት ልዩ ኃይል ጋር ህዝቡ ተፋጦ እንደሚገኝ ተሰምቷል:: በኤሊባቡርና አርሲ የተለያዩ ከተሞች የተነሳውን የሕዝብ ተቃውሞ እያካሄዱ የሚገኙት ተማሪዎች ናቸው ተብሏል::

በሌላ ዜና በኮፋሌ በተደረገ የህዝብ ተቃውሞ በሕወሓት ልዪ ኃይል ተመቶ ቁስለኛ የነበረው ወጣት አሊ ቡሪ ቀሬሶ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሕይወቱ ማለፉ ተሰማ:: በኮፋሌ ከተማ ሓዊ ሆቴል ውስጥ ሰራተኛ የነበረው ይኸው ወጣት የአጋዚ ወታደሮች ወደ ሆቴል በመምጣት ወጣቱን የግል ቴሌቭዥን ጣቢያዎችን በተለይም ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክን ለሆቴሉ ደንበኞች ታሳያለህ በሚል ክፉኛ ቀጥቅጠው አቁስለውታል:: በዚህም ጉዳት የደረሰበት ወጣት ለሕክምና ወደ አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መጥቶ ዛሬ ሕይወቱ ማለፉ ተሰምቷል::oromo st

No comments:

Post a Comment