Wednesday, May 18, 2016

ኖርዌይ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከታዘብኩት – ከተማ ዋቅጅራ

Filed under: News Feature,ነፃ አስተያየቶች | 
  • 200
     
    Share
በ10.05.2016 ላይ ከመላው የኖርዌይ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች የኖርዌይ መንግስ በህገ ወጥ መንገድ 800 ኢትዮጵውያንን በሃይል ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በራሳቸው ባለስልጣን እና በራሳቸው ሚዲያ ካስነገሩ በኋላ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያሳዘነ ብሎም ያስቆጣ ነበር። ያሳዘነበት ምክንያት ኖርዌይ የራሷን ዜጎች ከአንድም ሶስት ግዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ችግር ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ ስታስጠነቅቅ በዚው ግዜ ውስጥ ከ800 በላይ 60 ህጻናትን ጨምሮ  ጸጥታዋ ወደተናጋው አገር እንመልሳለን በማለታቸው በአለም የሰባዊ መብት ከሚከበርባቸው ግንባር ቀደም እንደውም በአንደኝነት የምትጠቀሰው አገር በኢትዮጵያውያኖች ላይ የሰባዊ መብት ጥሰት መደረጉ አሳዝኖናል። ያስቆጣን ደግሞ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎች መብታችን ተገፎ ያለ አግባብ ለረጅም አመታት በካንፕ ማስቀመጣቸው ሳያንሳቸው በግፍ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ አሳልፈው ለአንባ ገነን መንግስት  ሊሰጡን መሆኑን በሚዲያቸው መስማታችን ከዚህ ቀደም ተደርጎ የማይታወቅ ጠንከር ያለ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ቁጣችንን ለመግለጽ የችግሩ ተጠቂዎች ከያሉበት ተሰባስበው በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ በመገኘት ችግራችንን በቁጣ  ለኖርዌይ ማህበረሰብ ብሎም ለአለም ህብረተሰብ እንድናሰማ አዘጋጅቶን ነበር።
Norway Ethiopians
ከዋናው ከተማ ኦስሎ ራቅ ካለ ቦታ የመጣን ስለነበረ ሌሊቱን ተጉዘን ጠዋት ነበር የደረስነው። ኦስሎ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያኖችም ተቀብለውን ወደተዘጋጀው ማረፊያ ቦታ በመውሰድ የሰልፉ ሰዓት እስከሚደርስ ድረስ ከ18 ያላነስን ሰዎች ከሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ እና ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ኮሚቴዎች ጋር ስለ ሰላማዊ ሰልፉ እና ጠንከራ ተቃውሞ ሰልፍ ስለማድረጉ ጉዳይ ላይ የተለያዩ  ሃሳቦችን በማንሸራሸር ከተወያየን በኋላ በኖርዌይ ህግ መሰረት ጠንካራ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ከ25 ሰው በላይ መሆን አለበት ስለሚል ጠንካራ ሰልፉን ለመውሰድ ከ25 ሰው በላይ ሰው ካለ ተስማምተን ነበር። ከዚህ ስብሰባ የታዘብኩት ሁለት ነገርን ነው። የመጀመሪያው በመስማማት የተስማሙ እና  ሁለተኛው ደግሞ በመስማማት ያልተስማሙ ናቸው። እነዚህ ሁለት ሃሳቦች ተይዘው ወደ ሰልፉ መነሻ ቦታ ሄድን። ሰልፉ መነሻ ቦታ ላይ የጠበቁን ሰዎች በዛ ያሉ ነበሩ በግምት በመቶ የሚቆጠሩ ነበሩ። የዚን ግዜ በልቤ ውስጥ ከዚህ በፊት ተደርጎ የማይታወቀው ጠንካራው ሰላማዊ ሰልፍ ከበቂ በላይ ስለሆንን በኢትዮጵያ ያለውን ችግር እና የኛንም ችግር ለኖርዌይ ህዝብም ለአለምም ህብረተሰብ የምናሳውቅበት ግዜ በመሆኑ ልቤን ደስታ ሞልቶት ነበረ።
ሰልፉ ተጀመረ በተለያዩ  ወንድሞች እና እህቶች ማይክሮፎኑን በመያዝ የተቃውሞ መፈክሮችን እያሰማን በከተማው መሃል መንገድ ጀመርን ። የተቃውሞ ድምጻችንን እያሰማን ጥቂት የማይባል ጉዞ ከተጓዝን በኋላ የኖርዌጃን ሚዲያ TV2 የሚባለው መስራቤት ደረስን እዚህ ጋር ሁላችንንም እንድንቆም በማስደረግ ብዙ አመት ኖርዌይ የኖረ ኢትዮጵያዊ ወንድማችን ለግዜው ስሙን መግለጽ አይጠበቅብኝም የድምጽ ማጉያውን በመያዝ የሁሉንም ሰልፈኛ ስሜት በሚነካ መልኩ የኖርዌጃንን ሚዲያ መውቀስ ጀመረ ።《የኢትዮጵያን እውነተኛ ገጽታ ታውቃላችሁ በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰውን ግፍና በደል ታውቃላችሁ በኢትዮጵያን ላይ የሚደርሰውን እስራትና ሞታ ታውቃላችሁ ነገር ግን ይሄንን እያወቃችሁ እውነታውን ህዝባችሁ እንዲያውቀው አላደረጋችሁም TV2 በናንተ አፈርን》 በማለት በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰልፈኛ ልቦናውስጥ ያለውን ሃሳብ ስሜት በሚነካ መልኩ ኢትዮጵያውስ ያለውን ችግር ዘርዝሮ በመንገር የኖርዌጃን ጋዜጠኞች ግን እውነታውን እያወቁ ለህዝባቸው በመደበቃቸው ከፍተኛ ትችት እና ወቀሳ በማስተላለፍ ሰልፈኛው ድምጻችን እስከሚዘጋ ድረስ ያስጮሀ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ብየዋለው። ይሄንን ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ ሳላደንቀው እና ሳላመሰግነው ማለፍ አልፈልግም በእውነት ላይ የቆምህ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ልጅ ምስጋናዬ ይድረስህ ብያለው።
ሰልፉ ወደፊት መጓዝ ጀመረ  ሁለት ፈረስ ላይ የተቀመጡ ፖሊሶች ከፊታችን ሰልፉን ይመሩታል ሁለት የፖሊስ መኪና ከፈረሶቹ ፊት አሉ የፖሊስ ልብስ ያለበሱ ፖሊሶች በርቀት ይከተሉናል። ጠንካራ ሰልፍ እንደሚደረግ መረጃው የደረሳቸው ይመስሉ ነበር ሁኔታቸውን ለተመለከተ…  እኛ ውስጣችን ተናዷል ኖርዌይ በኢትዮጵያ ስደተኛ ላይ ያላት አመለካከት ጤናማ አይደለምና። ሰልፉ ቀጥሏል የሰልፉ መጨረሻ ፍትህ ሚንስቴር በር ላይ ነበረ።
Norway
ከተማውን በተቃውሞ ድምጽ እያናወጠነው ወደ ፍትህ ሚንስቴር ህንጻ አመራን እዛም እንደደረስን ያ ጀግና ወንድማችን በድጋሚ ማይክራፎኑን ያዘው የኖርዌይ መንግስ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለ አግባብ በመደገፋቸው ህዝባችን ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል የኖርዌይ መንግስ በሚያደርገው የገንዘብ ድጋፍ እንደሆነ ይነግራቸው ጀመር። የቃላት አመራረጡ የድምጽ አወጣጡ ሰልፈኛውን ብቻ ሳይሆን የፍትህ ሚንስቴር በር የሚጠብቁትን ፖሊሶች እና አጅበውን የመጡትን ፖሊሶች ጭምር ቀልብ የገዛ ነበር። እውነት ለመናገር ሁሉም ኢትዮጵያ ቆርጦ ቢታገል  ትግሉ ትልቅ ደረጃ ላይ አድርሶ በአንድ ማስተሳሰር በተቻለ ነበር። በመጨረሻም ከፍትህ ሚንስተር መስሪያ ቤት በመውጣት ሰልፈኞችን አነጋግራለች። ስለ ሰልፋችን አላማ ከሚንስተር መስራቤት ለመጡት ገለጻ ከተደረገላት በኋላ ስለ ሰልፉ አላማ የሚነግር ደብዳቤ ከተሰጣት በኋላ እሷም ደብዳቤውን ከተቀበለች በኋላ ለሰልፈኞቹ ንግግር አድርጋለች።
ከሚንስተር መስራቤት የመጡት ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ ሰልፈኞቹ ወደ ተባለው ጠንካራ ሰልፍ ለመሄድ እየተነጋገርን እያለ ድንገት አንድ ሰው አዲስ ሃሳብ ይዞ ብቅ አለ የሰልፉን አዘጋጆችን በመለየት ጠንካራ ሰልፍ የተባለውን ማድረግ እንደሌለባቸው ይነግራቸው ጀመር። በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ትልቅ የፖለቲካ ስራ ከኖርዌጃን ባለስልጣናት ጋር እየተሰራ እንደሆነ እና ጥሩ ደረጃ ላይ እንዳለ በማሳወቅ ዛሬ ጠንካራ ሰልፍ ቢደረግ እና ከፖሊሶች ጋር ብትጋጩ የተጀመረው ስራ እንደሚበላሽባቸው  በመግለጽ የታሰበው እና ከሁለት ወር በላይ የተዘጋጀንበት ሃሳብ በማስለወጥ ሊወሰድ የታሰበውን ጠንካራ ሰልፉን አስቀርቶታል። ሲጠቀልለው ከኖርዌይ ባለስልጣን ጋር የተጀመረው ውይይት ካልተሳካ ግን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በድጋሚ በመቀስቀስ ጠንካራ ሰልፉን እንደሚወሰድ አሳውቋል። ለዚህም አላፊነቱን እንደሚወስድ በመናገር የሰልፉን ድምዳሜ ነግሮ ሰልፉ ተጠናቋል።
እኛም ውሳኔውን በመጠባበቅ ላይ ነን ያለውን ሁኔታም እየተከታተልኩኝ ለሚዲያ ለማቅረብ እሞክራለው።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሚሰራው ስራ ሃላፊነትን በመውሰድ ተጠያቂነት እንዲኖርበት ያስፈልጋል። መልካም የሰራ ክብር ልንሰጠው እንደሚገባ ሁሉ ስህተት የሰራም ስህተቱ በአደባባይ ሊነገረው ይገባል እላለው። ለጊዜው አበቃው።

Tuesday, May 17, 2016

ኔልሰን ማንዴላን በነጮቹ መንግስት ያሲያዛቸው የአሜሪካው የስለላ ድርጅት CIA ነው ተባለ (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች | 
  • 175
     
    Share
#ለድርቅና ለረሃብ የተሰበሰበው ገንዘብ ከሚያስፈልገው 54 ከመቶ ብቻ ነው ተባለ
#ኔልሰን ማንዴላን በነጮቹ መንግስት ያሲያዛቸው የአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲ አይ ኤ ነው ተባለ
#የአምስቱ አገሮች ጥምር ኃይል አምስት የቦኮ ሃራም መሪዎችን ያዝኩ፣ በርከት ያሉ ዜጎችንም አስለቀቅኩ አለ
#የኮንጎ ወታደሮች እና ፖሊሶች በሰሜን ኮሪያ ወታደሮች እየሰለጠኑ መሆናቸውና የሰሜን ኮሪያ ሽጉጦችን መታጠቃቸው ተገለጸ
#የግብጽ ፍርድ ቤቶች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉ ዜጎች ላይ የእስራት ቅጣት በየኑ
በተፈጥሮ የአየር መዛባት፣ በዝናም እጥረትና ወያኔ በሚከተለው ዘረኛና የተበላሸ ፖሊሲ ምክንያት በኢትዮጵያ በ50 ዓመት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ድርቅና ረሃብ ከተከሰተ ወዲህ ዓለም አቀፍ ድድየዕርዳታ ድርጅቶች በድርቁ ለተጎዳው ወገን የእርዳታ እጃቸውን ዘርግተው የተማጽኖ ድምፅ ቢያሰሙም ከተጠየቀው 1.4 ቢሊሆን ዶላር ውስጥ እስከ አሁን የተገኘው 54 ከመቶ ብቻ መሆኑ ተገልጿል። ከዚህ ገንዘብ ውስጥ አሜሪካ 705 ሚሊዮን ዶላር መርዳቷ ሲታወቅ በሶሪያ ባለው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉትና ወደ አውሮፓ ለሚፈልሱት ስደተኞች የሚደረገው እርዳታ ለኢትዮጵያ ድርቅና ረሃብ ጉዳተኞች ሊሰጥ በሚችለው አጠቃላይ የዕርዳታ መጠን ላይ ተጽእኖ መፍጠሩ ተጠቅሷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጎርፉ አደጋ በኢትዮጵያ የዕለት ተዕለት ክስተት እየሆነ መምጣቱና ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ በጎርፉ አደጋና በመሬት መደርመስ ከ 100 በላይ ሰዎች መገዳልቸውና በሽህ የሚቆጠሩ የቤት እንስሳት ማለቃቸው እንዲሁም በሚሊዮን የሚቆጠር ብረት መውደሙ አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ሲሆን የዝናቡ መጠን በዚህ ከቀጠለ መጭው ክረምት ከመጠናቀቁ በፊት 500 ሺ ሲዎች ከቀያቸው ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተሰግቷል።
mandela3.jpg
 የደቡብ አፍሪካ እውቁ ታጋይና የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ሚስተር ኔልሰን ማንዴላ የዛሬ 54 ዓመት በዘረኛው የደቡብ አፍሪካ የነጮች መንግስት ሊያዙ የቻሉት በአሜሪካ የስለላ ተቋም በሲ አይ አባል ጥቆማ እንደሆነ ተጋለጠ። ሚስጥሩ ሊጋለጥ የቻለው ጥቆማውን ያካሄዱት በወቅቱ በደቡብ አፍሪካ ዲፕሎማት የነበሩት የሲ አይ ኤ አባል ዶናልድ ሪካርድ ከመሞታቸው በፊት “ የማንዴላ ጠመንጃ” ( “Mandela’s Gun”) በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ፊልም ዳይሬክተር
ላደረጉላቸው ቃለ ምልልስ በሰጡት መልስ መሆኑን ሰንደይ ታይምስ የተባለው የእንግሊዝ ጋዜጣ እሁድ ግንቦት 7 ቀን ባወጣው እትሙ ገልጿል። ከዚህ በፊት የሲ አይ ኤው ድርጅት ሚስተር ማንዴላን ከመያዛቸው በፊት ሲከተታል የነበረ መሆኑና በመጨረሻም እንዲያዙ የጠቆመው የዚሁ ድርጅት አባል ነው የሚለው ወሬ በሰፊው ሲሰራጭ የኖረ ቢሆንም የሲ አይ ኤ ባለስልጣኖች በተለያዩ ጊዜያት ሲክዱ የቆዩ መሆናቸው ይታወሳል። ማንዴላ ለረጅም ጊዜ በልዩ ልዩ መንገድ
ከደቡብ አፍሪካ የጸጥታ ኃይሎች ሲያመልጡ ከቆዩ በኋላ ተይዘውና ተፈርዶባቸው ለ27 ዓመታት ያህል በእስር ቤት አሳልፈዋል። ማንዴላ ሲመሩት የቆየቱ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግሬስ በሬገን ዘመነ መንግስት በአሜሪካ ሽብረተኛ ድርጅት ሊስት ውስጥ ተመዝግቦ የቆየ ሲሆን ሽብረተኛ የሚለው ስም የተነሳለት በ2000 ዓም መሆኑ ይታወቃል።

 ቦኮ ሃራምን ለማዳከም የተቋቋመው የአምስት አገሮች ጥምር ኃይል ባካሄዳቸው ተከታታይ አሰሳዎች አምስት የቡድኑን ከፍተኛ መሪዎች የያዘ መሆኑና በቡድኑ ታግተው የነበሩ በርካታ ሴቶችንና ህጻናትን ያስፈታ መሆኑን የካሜሩን መንግስት ቃል አቀባይ ገልጿል። አሰሳዎቹ የተካሄዱት ማዳዋ በሚባለው ጫካ ውስጥ መሆኑ ሲገለጽ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ናይጄሪያ ውስጥ ያላቸው የጦር ስፈር ሲደመስስ የተጠቀሰውን ጫካ የጦር ሰፈር ማድረጋቸው ተደርሶበታል። ይህ ዜና የተሰጠው
የምዕራብ አፍሪካ አገሮች መሪዎች የፍረንሳዩ ፕሬዚዳንት ሆላንድ በተገኙበት የቦኮ ሃራምን እንቅስቃሴ ለመግታት አቡጃ ላይ ከፍተኛ ስብሰባ ባደረጉበት ወቅት ነው።

 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤክስፐርት ቡድን የሴሜን ኮሪያ ወታደራዊ ተቋም አባላት ለኮንጎ ወታደሮችና ፖሊሶች ስልጠና እየሰጡ መሆናቸውንና የኮንጎ ፖሊሶች ሰሜን ኮሪያ የተሰሩ ሽጉጦች መታጠቃቸውን ያረጋገጠ መሆኑን ገልጿል። ቡድኑ ተመሳሳይ ሽጉጦች በአገሪቱ ዋና ከተማ ኪንሻሳ ውስጥም በጥቁር ገበያ እንደሚሸጡ መረጃ የደረሰው መሆኑን ጠቁሟል። ሰሜን ኮሪያ ማንኛቸውንም ዓይነት መሳራሪያ በዓለም ገበያ እንዳትሸጥና ወታደራዊ ስልጠና እንዳትሰጥ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የታገደች በመሆኑ ኮንጎ ውስጥ በማስልጠን ስራና በመሳሪያ ሽያጭ ንግድ መሰማራቷ በሁለቱም አገሮች በኩል ህግን መተላለፍ ነው በሚል የኤክስፐርቱ ቡድን ገልጿል።
 ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የግብጽ ፍርድ ቤቶች ያልተፈቀደ ሰላማዊ ስልፍ አድርገዋል የተባሉ 152 ሰዎችን ከ2 እስከ አምስት አመት በሚደርስ እስራት የበየኑባቸው ታውቋል። የተፈረደባቸው የግብጽ ዜጎች ብዙዎቹ በቅርቡ የሲሲ መንግስት በቀይ ባህር ላይ የሚገኙ ሁለት የግብጽ ዴሴቶችን ለሳኡዲ አረበያ መስጠቱን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉ ናቸው። የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተንከባካቢ ድርጅቶች ሲሲ ስልጣን ከያዙ በኋላ ተቃውሞን ለማስተናገድ የማይፈልጉ ፍጹም አምባገነን መሆናቸውን አውግዘው ሁኔታው በጣም ያሳሰባችው መሆኑን ተናግረዋል።

Saturday, May 14, 2016

‹‹ሲደበድቡኝም አንተ አማራ፣ አንተ ትምክተኛ… እያሉ ነው፤ በአማራነቴ ሲደበድቡኝና ሲሰድቡኝ እኔ ለእነርሱ አዝን ነበር›› አቶ ዘመነ ምሕረት

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች | 
  • 0
     
    Share
ጥያቄ፡ መቼና እንዴት ወደፖለቲካ እንደገቡ፤ በፖለቲካ ውስጥ ለስንት ጊዜ እንደቆዩ ቢገልጹልን?
ዘመነ ምሕረት፡ ቀጥታ ወደ ፖለቲካ የገባሁት በ1997 ዓ.ም. በቅንጅት ጊዜ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ግን በቀጥታ ባይሆንም የፖለቲካ ተሳትፎ ነበረኝ፡፡ ከ91 ዓ.ም. ከአገዛዙ ጋር በኢትዮጵያዊነት ላይና ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጋር ተያይዞ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርር ቤት ተማሪ በነበርኩ ጊዜ ያሳድዱኝ ነበር፡፡ ፈጽሞ ተግባብተን አናውቅም፡፡ በ1993 ዓ.ም በነበረው የአዲስ አበባና በሌሎች ዩንቨርሲቲዎች በነበረው የተማሪዎች እንቅስቃሴ እኔ ጎንደር ነበር፤ ሆኖም በቀጥታ እሳተፍ ነበር፡፡ ሆኖም የፖለቲካ ፓርቲ አባል የሆንኩት በ1997 ዓ.ም. የመለው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትን በመቀላቀል ነበር፤ ወዲያው ቅንጅት ሲመሠረት ወደ ቅንጅት አብረን ገባን፡

13241299_1209752182382726_681976981679470613_nየፖለቲካ ፓርቲ አባል እንድሆን የአሳደጉኝ ቤተሰቦች አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ አያቶቼ አርበኞች ነበሩ፡፡ ሕጻን እያለሁ ቤት ውስጥ የሚወራው ሁሉ ስለአርበኞች ነበር፡፡ የምንወረው ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያዊነትና የነገሥታቱን የእነ አጼ ቴዎድሮስን፣ ምኒልክን ብሎም የአርበኞችን ወሬ ነበር፡፡ የታሪክ መምህርም የሆንኩት በዚሁ ምክንያት ነው ማለት ይቻላል፡፡ የአኔ ቤተሰቦች በደርግ ብዙ በደል ደርሶባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ እነርሱ በጊዜው ይሉት የነበረው ‹ከእንግዲህ የሚመጣው መንግሥት (በገጠር ተሓት ነበር የሚሉት) ኢትዮጵያን የሚቆራርስ፣ አገር የሚያፈርስ የትግሬ መንግሥት ነው› እያሉ ይነግሩን ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ከሕጻንነቴ ዘመን አንስቶ ምንም ዓይነት ኢሕአዴጋዊ ባሕሪ የለኝም ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የፖለቲካ ትግልን ተቀላቅያለሁ፡፡
ጥያቄ፡ በፖለቲካ ተሳትፎዎ የገጠመዎ ችግር ምንድነው?
ዘመነ ምሕረት፡
በፖለቲካ ትግል ብዙ ችግሮች ደርሰውብኛል፡፡ ለአብነት ያክል እንኳን ሌሊት ቤቴ የማላውቃቸው ሰዎች መጥተው በ1997 ዓ.ም. በጥይት ተስቻለሁ፤ በሰሜን ጎንደር አለፋ ጣቁሳ ወረዳ ነው በጥይት የተሳትኩት፡፡ ደኅንቶች በተለያየ ጊዜ ያሳድዱኝ ነበር፤ ተደጋጋሚም ተክስሻለሁ፡፡ ከሥራ ሁሉ ታግጄ ነበር፤ ስብሰባ ላይ እንዳልሳተፍ ተክልክያለሁ፡፡ በሙያየ የማደግ መብት ተከልክያለሁ፡፡ ከመምህርነት በግዴታ አስወጥተው የቢሮ ሥራ ላይ መድበውኝም ነበር፡፡ እኔ የተማርኩት ታሪክ ነው፤ ነገር ግን እነርሱ የጂአይ ኤስ ባለሙያ አድርገው መደቡኝ፡፡ እንኳን እኔ በእኔ የተነሳ ብዙ ጓደኞቼና ዘመዶቼ ከሥራ ታግደዋል፡፡ በመምህራን ማኅበር ጊዜ ራሱ ብዙ ሰዎች ነው ከሥራ የተባረሩት ከእኔ ጋር ይገናኛሉ ተብለው፡፡

የሚገርምህ ሰዎቹ የኢሕአዴግ አባል ናቸው፤ ነገር ግን ከዘመነ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ቁረጡ ተብለው ነው የተባረሩት፡፡ ለምሳሌ ሙሌ ፍስሃ የማክሰኝት ርእሰ መምህር፣ አቶ አማው እባቡ የጎንደር ዙሪያ መምህራን ማኅበር ሰብሳቢ፣ ይታየው ገበያው የጎንደር ዙሪያ ሱፐርቫይዘር፣ በለጠ ታከለ የሚባል የማክሰኝት ምክትል ርእሰ መምህርና ሌሎች ብዙ ሰዎችም ከእኔ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው ከሥራ ወይ ይባረራሉ ወይም ደግሞ ደረጃቸው ዝቅ ብሎ እንዲሠሩ ይደረጋል፡፡ ብዙ ሰዎች የኢሕአዴግ ባለሥልጣን ቢሆኑ በራሱ ከመባረር አይድኑም ነበር፡፡ ይህን ሁሉ የሚያደርገው አንድ የብአዴን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ደሳለኝ አስራደ የሚባል ሰው ነው፡፡ አሁንም ድረስ ብዙዎች እየተሳደዱ ነው፡፡
ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው በፍርሃት ነው፡፡ እርሱ ሌሎችን ሰዎች ስለሚያደራጅ እንዲሁም በዙሪያው ሰው እንዳይቀርበው ካደረግን በፍርሃት ወደ እኛ ይመጣል ብለው ስለሚያስቡ ነው፡፡

ጥያቄ፡ በቅርቡ ታስረው ከፍተኛ የሆነ ቶርቸር እንደተፈጸመብዎ ተገልጿል፡፡ ስለተፈጸመብዎ ነገር በዝርዝር ያጫውቱን?
ዘመነ ምሕረት፡
ጥር 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ማክሰኝት የጽዮን ማርያም ታቦትን ወደ ጥምቀተ ባሕር ስናወርድ በኋላየ የማላውቃቸው ሰዎች መጥተው ያዙኝ፡፡ ሲይዙኝ ምንድን ነው ብየ ገጠምኳቸው፡፡ ከያዙኝ ሰዎች ጋር ስንተናነቅ ፌደራል ፖሊስ ወረረኝ፡፡ የፌደራል ፖሊሶች ከስድስት መኪና በላይ ይሆናሉ፡፡ መጥተው ከዚያው ላይ በአፈ ሙዝ ደበደቡኝ፡፡ ዕውነት ለመናገር መጀመሪያ ሲይዙኝ የሆነ ከቤተሰብ ጋር እኔ ሳላውቀው በተፈጠረ ችግር ሊይዙኝ የመጡ ወንበዴዎች ናቸው የመሠሉኝ እንጅ በመንግሥት የተላኩ እንደሆኑ አላወቅኩም ነበር፡፡ የፖሊስ ዩኒፎርም አልለበሱም፤ ሲቪሎች ናቸው፡፡ ወታደሮቹ ከሕዝብ ፊት ደበደቡኝ፡፡ ልጄና ሚስቴ አብረውኝ ነበሩ፡፡ ልጄ ሕጻን ነው እኔን ሲደበድቡኝ እያለቀሰ መጣ፡፡ የሚገርምህ ልጄን በአፈሙዝ ደበደቡት፡፡ የቀበርከውን አምጣ፣ መሣሪያህን አምጣ አሉኝ፡፡ ቤቴን ሲፈትሹ ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ የሰበሰብኩትን የአዲስ ራዕይ መጽሔት አገኙ፡፡ ምክንያቱም በየወሩ የሚሉትን ለማየት ስበስበው ነበር፡፡ በኋላ የደበቅኩት ቦንብ እርሱ ነው አልኳቸው፡፡ የተለያዩ የፖለቲካና የታሪክ መጽሐፍት እንዳገኙ አሁንም ከልጄም ከሚስቴም ፊት ደበደቡኝ፡፡ ሚስቴ ከፊት አትምቱት ብላ እየጮኸች ወጣች፡፡ ጫማዬን አስወልቀው ካሰሩኝ ወደ መኪና ሲወረውሩኝ ሦስት ዓመት የሚሆነው ልጄ መጥቶ ሲይዘኝ መጥቶ ሲይዘኝ በአፈሙዝ መቱት፡፡ ከዚያ ወደ ጉማራ ወንዝ ስንደርስ ዓይኔን ሸፈኑኝ፤ ከዚያ በኋላ የት እንዳስገቡኝ አላውቅም፡፡ አዘዞ ተክለ ሃይማኖት አካባቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡ መጀመሪያ የያዘኝ ሰው አሸናፊ ተስፋው የሚባል ነው፤ ከዚያ በኋላ ግን አላውቃቸውም፤ ትግሬዎች ናቸው፡፡ ትግርኛ ቋንቋ ተናገር፤ አንተ ትምክተኛ፣ ነፍጠኛ፣ የአማራን የበላይነት ለማምጣት የምትጥር፣… ብዙ ብዙ ነገር ነው የሚሰድቡኝ፡፡ የዱላው ነገር ቅጥ የለውም፡፡ ከአውሬም አይጠበቅ እንኳን ከሰው፡፡ እኔን በጣም ደብድበውኛል፤ የኔ ሳይሆን ልጄ ላይ የሠሩት ነው የሚያሳዝነኝ፡፡ እኔማ መቼም አንድ ጊዜ የፖለቲካ ተሳትፎ አድርጌያለሁ፡፡ ወንጀል ባይሆንም ተቃውሚያለሁ፤ አምኜበትም ነው የገባሁ፡፡ ልጄ ግን ምንም ሳይሠራ መደብደቡ ያሳዝነኛል፡፡
ወያኔዎቹ ከአማራው ላይ ያላቸው ጥላቻ በጣም ከፍተኛ ነው ብልህ አልገልጸውም፤ በጣም በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ሕወሓቶች በተቃዋሚ ላይ ሳይሆን በአማራ ላይ ጥላቻ እንዳላቸው ነው የተገነዘብኩት፡፡ ሲደበድቡኝም አንተ አማራ፣ አንተ ትምክተኛ… እያሉ ነው፡፡ ስታያቸው ጥላቻቸው ከፍተኛ በሽታ የሆነባቸው ይመስለኛል፡፡ በአማራነቴ ሲደበድቡኝና ሲሰድቡኝ እኔ ለእነርሱ አዝን ነበር፡፡ የሚናገሩት ቋንቋ ከሰው የማይጠበቅ የአውሬ ልትለው ትችላለህ፡፡ አማራ ሆኖ መወለድ ወንጀል ነው ለእነርሱ፤ አማራ ምን እንዳደረጋቸው አንተ ንገረኝ፣ ሌላም ሰው ካለ ቢያስረዳኝ ደስ ይለኛል፤ የታሪክ መረጃም ባገኝ ደስ ባለኝ፤ ያሳዝናል፡፡ ከሚደበድቡኝ ይልቅ አነጋገራቸው ነው የሚያመኝ ለእኔ፡፡ ዱላቸውማ ማንንም በተለይ አማራ ሁሉ እንደሚደበድቡት ነው የደበደቡኝ፡፡ አነጋገራቸው ከጤነኛ ሰው ሳይሆን አእምሮው ከታወከ ሰው እንኳ የማይጠበቅ ነው፡፡
ጉድጓድ ውስጥ ራቁቴን ከተው ይሸኑብኛል፤ ይተፉብኛል፤ ትግርኛ ቋንቋ ተናገር ይሉኝ ነበር፡፡ ሱሪየን ፓንቴን ሁሉ ጨምሮ አስወልቀውኛል፡፡ ከላየ ላይ ከሸሚዜ ውጭ አልነበረም፡፡ ዓይኔ ተሸፍኖ ስለነበር የሚደበድቡኝን ሰዎች አላውቃቸውም፡፡ የምሰማው ስድባቸውን ብቻ ነው፡፡ ከፈለጉ ደግሞ አንስተው ሰቅለው እያገላበጡ ይደበድቡኛል፡፡ ያሳዝናል፤ ሁሉንም ለመናገር ቃላት የለኝም፤ አልችልምም፡፡ በጠቅላላው ደስ የማይል ነገር ነው፡፡
ወደ አዲስ አበባ ሲያመጡኝ ወዴት እየወሰዱኝ እንደሆነ አላወቅኩም ነበር፡፡ ማርቆስ ስደርስ ዓይኔን ገለጡልኝ፡፡ የመኢአድ አባል የሆነው መለሰ መንገሻን ማሰራቸውን አላወቅኩም ነበር፡፡ በድብደባ ብዛት ሁለታችንም ራሳችን ስተን ነበር፡፡ ዓይናችን ማርቆስ ላይ የተሸፈነውን አንስተውልን ማርቆስ ካለፍን በኋላ ሽንት እንድንሸና ከመኪና ወረድን ወረድን፡፡ ከዚያ መለሰ መንገሻ መሆኑን በዓይኑ ለየሁት እንጅ የሁለታችንም ሰውነት በድብደባ ብዛት ተለዋውጠን ስለነበር ማን ማን መሆናችን ራሱ አይለይም ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ አዲስ አበባ ማዕከላዊ ስንገባ ጨለማ ቤት ውስጥ ቢሆንም ከሰው ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ተጨመርን፡፡

የተያዝንበት ምክንያት ከፓርቲው እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እነርሱ ሲጠይቁኝ የነበረው ለምን ከአቶ አበባው መሐሪ ጋር አብረህ አትሠራም? የመኢአድ አመራር ሆኖ ከአንተ ጋር አብረው የሚሠራውን ሰው ንገረን፡፡ ያደረጀውን ሰው ንገረን፡፡ ለምን አርፈህ አትቀመጥም? የአማራ የበላይነትን ልታመጣነው የምትታገለው የሚሉ ነገሮችን ነው የጠየቁኝ፡፡ ከግንቦት ሰባት ጋር ትገናኛለህ ምናም የሚሉትን ለስሙ ነው የሚጠይቁኝ፡፡ ወዲያውኑ ከአማራ ጋር አያይዘው ነው የሚወርዱብኝ፡፡ ማጠንጠኛቸው ዞረው ዞረው ከአማራ ጋር ነው የሚያይዙት፡፡
በማዕካላዊም በቃሊቲም ከ14 ሕፃናት እስከ 70 ዓመት የሚሆናቸው አዛውንት አማሮች ታስረዋል፡፡ ከእኔ ላይ የደረሰው ድብደባና ማሰቃየት ከሕፃናትም ከሽማግሌዎችም ላይ ደርሷል፡፡ ልዩነት የለውም፡፡ በደረጃ ባስቀምጥልህ በዓይኔ እንዳየሁት እንደ አበበ ካሴ የተጎዳ የለም፡፡ አበበ ካሴ አሁን ሰባት ዓመት ተፈርዶበት ዝዋይ ነው፡፡ እሱን ጓያ የሰበረው አስመስለው ሽባ ሆኖ ነው እየሔደ ያለው፤ አካሉ ስንኩል ሆኗል፡፡ እንደነገረኝ ከሆነ መውለድም ከዚህ በኋላ አይችልም፡፡ አበበ አካሉ የተባለው የመኢአድ አባልም በድደባ እጁ ሽባ ሆኗል፡፡ ሦስተኛ እንደ ጌትነት ደርሶ፣ መቶ አለቃ ጌታቸውና ቢሆን አለነ ዓይነት ድብደባና ቶርቸር የደረሰሰበት ሰው የለም፡፡ የአግበው ሰጠኝ፣ የመለሰና የእኔ ተመሳሳይ ነው፡፡ የእኔን ድብደባና ቶርቸር ከእነርሱ ጋር አላወዳድረውም፡፡ የእነርሱ ፈታኝ ነው፤ ይከብዳል፡፡
በተለይ ሲመረምሩህ ብሔርህ ማን ነው? ሲሉህ አማራ ነው ካሉህ ጥላቻቸው ይበረታል፤ በጣም ይገናል፡፡ ከዱላቸው ፊታቸው ያስፈራል፡፡ በጣም የተለየ ያደርጉታል፡፡ ገምናናው ጨቅሌ የሚባል የ14 ዓመት ልጅ ከቤተሰቦቹ ጋር ተጣልቶ ከአጎቱ ልጅ ጋር የቀን ሥራ ለመሥራት ሲሔድ ዳንሻ ላይ ያዙት፡፡ ታጥቀህ ኹመራን ልታስመልስ ነው ብለው ነው የደበደቡት፡፡ እዚያ አካባቢ አማራዎች ከተያዙ የሚያገናኙት ከወልቃይትና ጠገዴ ድንበር ጋር ነው፤ ከሥልጣናቸው ጋር ነው የሚያገናኙት፡፡
አስበው ሕፃን ነው፤ ከፍተኛ ድብደባ ደብድበውት አእምሮው ተጎድቷል፡፡ ሲተኛ ይቃዥ ነበር፡፡ እኔና በላይነህ ከመካከላችን እየተኛ ‹‹መጡብኝ!›› እያለ ሲባባ እንደግም ነበር፡፡ አስበው ይህ ልጅ ጭልጋ አካባቢ የገበሬ ልጅ ነው፡፡ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ በአእምሮው ገና ልጅ ነው፡፡ የራሳቸውን መሬት ቀምተው እነርሱ ኢንቨስተር ሆነው፤ ከእነርሱ በቀን ሥራ ለመሥራት ሲሔዱ አንተ ኤርትራ ልትሔድ ነው ተብለው ነው የሚደበደቡት፡፡ እትብታቸው በተቀበረበት መሬት ላይ ነው አማሮች ግፍ የሚቀምሱት፡፡

ጥያቄ፡ እንዴት ተፈተ? አሁንስ ሕይወትዎ አስተማማኝ ነው ወይ?
ዘመነ ምሕረት፡
አሁን ካለሁበት በእርግጥ እስሩ ይሻለኝ ነበር፡፡ ምክንያቱም ክትትሉ ቤተሰቦቼም እኔም ላይ በጣም ከባድ ነው፡፡ ሕይወቴ አሁን የበለጠ አደጋ ላይ እንዳለ አምናለሁ፡፡ የተፈታሁት አቃቢ ሕግ አስተማማኝ ማስረጃ ማቅረብ ስላልቻለ ነው፡፡ ስለዚህ ፍርድ ቤቱ ከሽብር አውጥቶ ወደ ወንጀል ክስ ቀየረው፡፡ ስለዚህ በወንጀል ሕጉ መሠረት ነው በዋስትና የወጣሁት፡፡ ገና ዋስትና ተሰጠኝ እንጅ ነጻ ነህ አልተባልኩም፡፡
ከሥራ ታግጃለሁ (ደብዳቤውን እያሳየ)፡፡ ባለቤቴ መምህር ናት በእርሷ ደመወዝ ነው ቤተሰብ የምናስተዳድር፡፡ ከሥራየ ያታገድኩት ደግሞ በሽብር ወንጀል የተከሰስክ በመሆኑ ነው የሚለው፡፡ እና ከሥራ አንቀበልህም ብለው አባረሩኝ፡፡ በካፌ ብቀመጥ፣ ገጠር ብሔድ ከጎኔ የማይከተሉኝ ጊዜ የለም፡፡

ጥያቄ፡ በትግሉ ይቀጥላሉ?
ዘመነ ምሕረት፡
አዎ በእርግጠኛነት በትግሉ እቀጥላለሁ፡፡ ምንም ጥርጣሬ አይግባህ፡፡ የትግላችን ሁኔታ በጣም ጠንካራ ጓዶቻችን አሉ እና እነርሱ ጋር ሆነን ውሳኔ ላይ እንደርሳለን፡፡ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክረን እንቀጥላለን፤ በኮረኮሙን ቁጥር ካላማችን የምንሸሽ ሰዎች አይደለንም፡፡ ከእነ አቶ ማሙሸት አማረና አቶ አብርሐም ጌጡ ጋር ተማክረን ወደፊት እንቀጥላለን፡፡ የመንፈስና የጽናት አባታችን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ካስቀመጡልን የትግል መስመር ፈቀቅ አንልም፡፡

ሰቆቃዎ ብሔረ ዐማራ

Filed under: News Feature,ነፃ አስተያየቶች | 
  • 924
     
    Share
ከብሥራት ደረሰ
ይህን ጽሑፍ ከዐማራ ውጪ ማንም ባያነበው ይመረጣል፡፡ ምክንያቱም ዐማራን በተለዬ ሁኔታ የሚወቅስ ጽሑፍ በመሆኑ ለሌሎች ብዙም የሚጠቅም ነገር የለውም፡፡ መወቃቀስ ለዕድገት መሠረት ነው፤ ጉድፍን ለማጥራትና ጠንካራ ጎንን አጠናክሮ ለመቀጠል ሂስና ግለሂስ ጠቃሚ ናቸው፡፡ ተድበስብሶ መጓዝ ግን በግልም ሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ ጠንቅ ነው
Displaced-Amharas-from-West-Shewa-Aremya-province-Dec-2015-1.jpg
ውድ ዐማሮች እንደምን ከረማችሁልኝ? ያለፉትን 40 ዓመታት እንዴት አያችኋቸው? የደርግ መንግሥት አስብቶ ለወያኔው የባንዳዎች ቡድን ለዕርድ አመቻችቷሁ መሄዱን ቀስ እያላችሁ በጊዜ ሂደት ስትነገዘቡ ምን ተሰማችሁ? አሁንስ እንዴት እየሆናችሁ ናችሁ? ስደቱ፣ሞቱ፣ ወያኔ ያወጀባችሁ የዘር ፍጅቱና ዐማራን ከየቦታው ማጽዳቱ፣ እስር-እንግልቱ፣ ከመንግሥት ሥራና ከንግድ – ከቤትና ከመሬት –  ከሕይወትና ከሃይማኖት፣ ከርስትና ከሚስት መፈናቀሉ፣ በጥይት መቆላቱ፣ እንዳትዋለዱና ዘር እንዳትተኩ በትግሬ ዶክተሮች መምከኑ – (አዎና በትግሬ የህክምና ዶክተር! እነፕሮፌሰር አሥራትን የገደለ መርፌ ባላገርን ማምከን ደግሞ ያቅተው እንዴ? ብዙ የሚወራረድ ዕዳ አለባቸው ትግሬ ወያኔዎች!!)፣ በማይድን በሽታ መለከፉ፣ በኑሮ ውድነት መጠበሱ፣ በማይምነት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ መንጠራወዙ፣… እንዴት ይዟችኋል ወንድሞቼና እህቶቼ? የማይለመድ የለምና መቼም ይህን ሁሉ ዘመን አመጣሽ ግፍና በደል ሳትለምዱት እንደማትቀሩ አምናለሁ – ኑሮ ካሉት ፍሪጅስ ማለቴ መቃብርስ ይሞቅ የለም? ደርጎች “የማይለመድ የለም፤ ውስኪውንም ለመድነው “ ብለው ነበር ያኔ ካረቂ መለኪያና ከጠላ ሽክና ወደዊስኪ ብርጭቆ ሲንጠለጠሉ፡፡ እንደምታዘበው በዚህች ምሥኪን ሀገራችን ምድረ ደንቆሮ ከቀበሮ ጉድጓድ ወጥቶም ይሁን ከበረሃ ገስግሶ ሥልጣን የሚይዘውና ለመያዝም የሚቋምጠው መቼም ለዚያ ለፈረደበት ሆድ እንጂ ለመንፈሣዊ እርካታና ለሀገር ባለው ብሔራዊ ስሜት አልሆነም፡፡

Thursday, May 12, 2016

ኖርዌይ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከሃገሯ ለማስወጣት ከኢትዮጵያዊው ጠ/ሚ/ር ጋር ያደረገችውን ስምምነት በመቃወም ሰልፍ ተካሄደ

Norway EthiopiansNorway

ኖርዌይ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በግዳጅ ወደ ሀገራቸው ለመመሰስ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ያደረገችውን ስምምነት የሚቃወም ታላቅ ሰልፍ ተካሄደ::
ኢትዮጵያውያን በስደት ከሚኖሩባቸው የተለያዩ የአውሮፓና ስካንዴኔቪያን ሀገሮች አንዷ የሆነችው ኖርዌይ ስትሆን በኖርዌይ ሃገር ቁጥራቸው አነስተኛ የማይባል ኢትዮጵያውያን የፓለቲካ ስደተኞች ይገኛሉ። እነዚህ ስደተኞች ከሌላው ሀገር ለየት የሚያደርግ ጠንካራ የፓለቲካ አቋም ያላቸው መሆኑም ይታወቃል። ስደተኞቹ በተለያየ ጊዜያት የገዢውን ፓርቲ ብልሹ አስተዳደር የሚያጋልጡ የፓለቲካ ስራዎችን ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወሳል።
ሆኖም ግን የኖርዌይ መንግስት እ.ኤ.አ በ2012 ከቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ ጋር በኖርዌይ የሚኖሩ ጥገኝነት ጠያቂዎችን አስገድዶ ወደ ሃገር ለመመለስ የሚያስችል ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል። ሆኖም ግን ይህ ስምምነት በተለያዩ ምክንያቶች ተግባር ላይ ሳይውል ቀርቷል። ኖርዌይ በድጋሚ አሁን በያዝነው አመት በፌብርዋሪ ወር እንደገና ስደተኞችን አስገድዶ ወደ ሀገር የመመለሱ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ቴዎድሮስ አደሃኖም ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን በኖርዌይ የሚገኙ ታላላቅ የዜና አውታሮች ሲዘግቡ ሰንብተዋል።
ይህንኑ ስምምነት አስመልክቶ በኖርዌይ የሚገኘው የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ማህበር ስምምነቱ ትክክል እንዳልሆነ ተቃውሞውን ለመግለፅ በሜይ 10፣ 2016 ታላቅ ሰልፍ አዘጋጅቷል። ይህ የተቃውሞ ሰልፍ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል። ስደተኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተለይ በቅርቡ በሀገራችን በአደባባይ እየተገደሉ ያሉ ወገኖቻችንን የያዙ ምስሎችንና የኖርዌይ ዜግነት ያላቸውና ከደቡብ ሱዳን ታፍነው በኢትዮጵያ እስር ቤት እየማቀቁ ያሉንትና አሁን ለዘጠኝ አመት የተፈረደባቸው የአቶ ኦኬሎ አኳይ ፎቶግራፍ እንዲሁም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ፎቶግራፎች በመያዝ ስለነሱም አያይዞ ለኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ እየታወቀ ሰዎች በየሰከንዱ እየተገደሉ ባለበት ወቅት ሀገሪቱ በብዙ አቅጣጫ የህዝብ አመፅ ባለበትና ገዢው ፓርቲም ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ሰዎችን እየገደለና እያሰረ ባለበት ሁኔታ ስደተኞችን አስገድዶ ለመመሰል ስምምነት ማድረጉ ለምን እንዳስፈለገ፤ እንዲሁም የኖርዌይ መንግስት ለኖርዌጅያን ዜጎች በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች መዘዋወር አደገኛ መሆኑን መግለጫ እየሰጠ ባለበት ሁኔታ የፓለቲካ ስደተኞችን አሳልፎ መስጠት ሰብአዊነት የጎደለውና የስደተኛ መብት ህግን የሚጥስ መሆኑን ኢትዮጵያውያኑ በሰልፉ ላይ ተናግረዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የስደተኞቹን ጉዳይ የሚከታተሉ የግብረ ሃይሉ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አያሌው ይመር ንግግር ያደረጉ ሲሆን ዝግጅቱም በተያዘለት ሰአት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር በኖርዌይ

Saturday, May 7, 2016

ስንት ትውልድ እስኪጠፋ እንጠብቅ? – ፍርዱ ዘገዬ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች | 

ዊት በመዝሙሩ – “አቤቱ ጌታ ሆይ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴም ወዳንተ ይድረስ፣ በመከራየም ቀን ፊትህን ከኔ አታዙር” ሲል ፈጣሪውን ተማጽኗል፡፡ እኛስ? ከልበ ድንጋዮቹ ወንድሞቻችን ግፍና በደል የሚታደገንን ሙሤ እንዲልክልን እንደዳዊት እየጮኽን ነው ወይንስ እንደኖኅና እንደሎጥ የቅጣት ዘመናት በአሥረሽ ምቺው የኃጢኣት ባሕር ከተዘፈቁት ጋር አብረን ፈጣሪን ረስተናል?
እግዚአብሔር የኖኅ ዘመን ሰዎችን በውኃ ቀጣ፡፡ ኋላ ላይ ግን ለፍጡራኑ አዘነ፡፡ በዚያ መልክ ዓለምን ዳግም በውኃ ንፍር እንደማይቀጣም ቃል ገባ፡፡ እግዚአብሔር በሎጥ ዘመን ሶዶምንና ገሞራን በድኝ የእሳት ዝናብ ቀጣ፡፡ ሁለተኛውም ከመጀመሪያው ባሰ፡፡ የሰው ልጅ ግን ከሁለቱም አልተማረም፡፡ እናም በጥፋቱ ቀጠለ – እስካሁኒቷ ወያኔያዊት ዘመነ ፍዳ ወፃማ ቅጽበት ድረስ፡፡ ፈጣሪም የቅጣት ዓይነቶችን በመጠንም በዓይነትም በደረጃም እየለዋወጠ ፍጡራኑን – በአባይ ፀሐይ ትዕቢታዊ አገላለጽ “ልክ ማስገባቱን” እንደቀጠለ እስካሁን አለ፡፡ ግን ማን ልክ ገባ? ማንም! ሰውና ፈጣሪ ያልተገባ ፉክክር ውስጥ ገብተውና እልህ ተጋብተው በተለይ በአሁኑ ዘመን የለዬለት የጨበጣ ውጊያ ውስጥ የገቡ ይመስላል
Freedom
ሦስተኛ ዓይነት መለኮታዊ ቅጣት በኢትዮጵያ በግልጽ ከታወጀ እነሆ 25 ዓመታትን ሊደፍን ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡ ከውኃና ከእሳት ቀጥሎ ወደዚህች ዓለም የመጣው የቅጣት ዓይነት በሀገራችን ኢትዮጵያ ብቻ ለሙከራ ያህል በሚመስል አኳኋን ተግባራዊ የሆነ ሲሆን እሱም ትውልድን በትምህርትና በዕውቀት ማደደብና በቋንቋና በጎሣ መከፋፈል ነው፡፡ ይህ በተከታታይ ትውልዶች ላይ የተቃጣ ገሃነማዊ ቅጣት ከቀደሙት የውኃና የእሳት ቅጣቶች በበለጠ የሚያቃጥልና የሚፋጅ ነው፡፡ ሰዎች እንደቀላል ሊመለከቱት ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ቅጣቱ ጥይት ሳያባክን ትውልድን ማምከን የሚችል ከኒዩክሌር ቦምብ የበለጠ እጅግ አውዳሚና በቀላሉ ማንሠራራትም የማይቻልበት ነው፡፡
ዛሬ በአዲስ አበባ ሂልተን አንድ የመጻሕፍት ምረቃ መርሐ ግብር ነበር፡፡ እዚያ ስብሰባ ውስጥ የነበረ አንድ ወዳጄ በአስቸኳይ እንደሚፈልገኝ ነገረኝና ምን ሆኖ ወይም ምን አጋጥሞት ይሆን ብዬ ተጣድፌ ላገኘው ሞከርኩ፡፡ ቀኑ ብሔራዊ የነፃነት ክብረ በዓል የሚከበርበት እንደመሆኑ ሥራ የለኝምና አንድ ቦታ ተገናኝተን ማርፈጃውን ስለታዘበው ነገር በቁጭት እየተንገበገበ ቀጣዩን ነገር አጫወተኝ፡፡
በሰባት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የልጆችና ሕጻናት መጻሕፍት ሜጋ የመጻሕፍት አሣታሚና በቅርብ እንደተመሠረተ የተነገረለት ስፖትላይት የተባለ ድርጅት በጥምረት ዛሬ ጧት አስመረቁ፡፡ በዚህ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ በርካታ የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች እንዲሁም በንባብ ዙሪያ የሚሠሩ መጻሕፍት አሣታሚዎችና አከፋፋዮች ተጋብዘው ብዙዎቹ ተገኝተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሚሠራው ታዋቂው የፎክሎርና የሥነ ጽሑፍ ምሁር ዶክተር ፈቃደ ትዛዙም (አዘዘ?) ተገኝቶ ንባብን በሚመለከት ከሕይወት ተሞክሮው በጥቂቱ የተጨለፈ አጠር ያለ ገለጻና ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ ታዋቂ ደራሲያንና የመድረክ ሰዎችም ተጋባዥ ነበሩ፡፡ በጣም ደስ የሚል ነበር፡፡…
ወዳጄ ይህን ሲነግረኝ ቀዝቀዝ አልኩ፡፡ ነገር ግን ለዚህ ብሎ በጥድፊያ እኔን መፈለጉ አላሳመነኝምና በአስቸኳይ ለምን ሊያገኘኝ እንደፈለገ ጠየቅሁት፡፡ ጓደኛዬ ንዴት እንጂ ንግግር ብዙም አይሆንለትም፡፡ ከፍ ሲል የነገረኝን በእርጋታ ከነገረኝ በኋላ በንዴት እየተንጨረጨረ እኔንም የሚያናድዱ ብዙ ቁም ነገሮችን ዘከዘከልኝ፡፡ የመጣጥፌ መሠረትም ይህ የነገረኝ ነገር ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ከወዳጄ ተሰናበቱ – ከኔ ጋር ጥቂት እንቆይ፡፡
ከጓኛዬ እንደተገነዘብኩት ዐማርኛን ጨምሮ ሰባት የልጆች የንባብ መጻሕፍት ተዘጋጅተው ለምረቃ በቅተዋል፡፡ ይህ በራሱ እሰዬው የሚያስብል ትልቅ መልካም ነገር ነው፡፡ ይሁንና የመጻሕፍቱ ይዘትና ቅርጽ እንዲሁም የመጻፊያ ሆሄያት ምርጫ ብዙ ማነጋገሩ አልቀረም፡፡ በሥፍራው ግን ይህን ነገር ማንም ደፍሮ እንዳላነሳ ወዳጄ ነግሮኛል፡፡
እንዲህ ያለ ነገር ውስጥ መግባት ጣጣው ብዙ መሆኑን ሁሉም ሳይረዳ አልቀረም፡፡ በዚህ ወያኔ በገነነበትና ያሻውን በሚያደርግበት አደገኛ ወቅት ሰዎች ትክክለኛ መስሎ የሚሰማቸውን ነገር በግልጽ ከመናገር ይልቅ (“ሽብርተኛ” ሆኖ ዘብጥያ ላለመውረድ ሲባል) አድምጡና ተመልከቱ የተባሉትን ብቻ አድምጠውና ተመልክተው ወደየመጡበት መሄድ የተለመደ ሆኗል – ጎመን በጤና፡፡
ከዐማርኛና ከትግርኛ በስተቀር በኦሮምኛ፣ በወላይትኛ፣ በሲዳምኛ፣ በሃዲይኛና በሶማሊኛ የተዘጋጁት መጻሕፍት የተጠቀሙት ሆሄያት የላቲኑን ነው፤ ያሳየኝ ብሮሸርም ይህን ይጠቁማል፡፡ ይህ ነገር በርግጥ የየቋንቋዎቹ ተናጋሪ ኅብረተሰብ ምርጫ ቢሆን ችግር ባልነበረው፤ ምርጫው የወያኔ መሆኑን ለመረዳት ደግሞ እነዚህን መሰል መጻሕፍትና በራሳቸው ቋንቋ የራሳቸውን ቋንቋ ተምረው ሲያበቁ መጨረሻ ላይ የሚሰጧቸውን የፈተና ወረቀቶች ከፈተናው አዳራሽ እንደወጡ በመቀዳደድ አካባቢውን ጨረቃ በጨረቃ ማስመሰላቸው አንዱ ምሥክር ነው፤ እንዲያውም “ ልጆቻችን በአንድ የአካባቢ ቋንቋ ብቻ ተወስነው እንዲቀሩ የሚያደርጉት የትም ሄደው ሥራ እንዳይዙና እዚሁ እንደኛው ገበሬ ሆነው እንዲቀሩ ነው” በሚል የየአካባቢው ሕዝብ እንደሚጮህ የታወቀ ነው – ሰሚ የለም እንጂ፡፡ በመሠረቱ አንድ ዜጋ የራሱን አንድ እና ለሁሉም የሚያገለግል ደግሞ አንድ በድምሩ ቢያንስ ሁለት ቋንቋዎችን ቢለምድ ሕዝብና ሀገር ይበልጥ ይጠቀማሉ እንጂ ጉዳት የለውም፡፡ ዜጎች በአንድ ክልል ተኮድኩደው ከአድማስ ወዲያ ሕይወት መኖሩን እንዳያውቁ ሆን ተብሎ በወያኔ የሚሸረበው ተንኮል ወያኔ አወራርዶ ሊጨርሰው የማይችል የታሪክ ዕዳ ተሸካሚ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሣያል፡፡ ሁሉም ሕዝብ የነዚህን እባቦች ተንኮል በእኩል ደረጃ በሚረዳበት ወቅት ሊከሰት የሚችለውን በጣም አደገኛ ሁኔታ ከአሁኑ ሲያስቡት አስጨናቂ ነው፡፡ የሕዝብ መገናኛ ድልድዩ ሁሉ ፈራርሷል፤ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ቋንቋ፣የጋራ ማኅበራዊ ሥነ ልቦና… የመሳሰሉት ዕሤቶች የሕዝብ መገናኛ ድልድዮች ናቸው፡፡ ወያኔዎች እንዚህን ማስተሳሰሪያ ገመዶች በጣጥሰው አንዱ ከሌላው እንዳይገናኝና በምትኩ ሁሉም ፉዞ ሆኖ የነሱ አሽከርና ባሪያ እንዲሆን በከፍተኛ ደረጃ እየሠሩበት ነው – አብዛኛው ሕዝብም የተኛ ይመስላል፡፡ ችግሩ ታዲያ የተኛ የነቃ እንደሆነ ነው፤ የጊዜ ጉዳይ እንጂ መንቃቱም የማይቀር ነውና፡፡
አንድ ማሳሰቢያ ልስጥ፡፡ እኔ በዘሬ ኢትዮጵያዊ ነኝ – ይህን ስል ግን ወያኔና የወያኔን ፍልስፍና የሚከተል ማንኛውም ወገን “ይህ ሰው ዐማራ ነው” ብሎ እንደሚፈርጀኝ እገምታለሁ፡፡ የማነሳው ጉዳይ ግን ከኔ ማንነትና ምንነት በዘለለ ትልቅ ሀገራዊ ውድመት የሚያስከትል መሆኑን ሁሉም ልብ ሊል ይገባዋል፡፡ እናም እኔ አሁን የምለው ከተቻለ ሀገሪቱን ከመፈራረስ የምናድንበትን መንገድ በጋራ እንፈልግ፣ አለበለዚያ ግን ማንም ተጠቃሚ የማይሆንባት ጥቂት ጮሌዎች ብቻ በሀብትና በሥልጣን ሊያውም ለተወሰነ አጭር ጊዜ ተምነሽንሸውባት በቅርብ ለይቶላት የምትጠፋ ሀገር ውስጥ እየኖርን እንደሆነ እንገንዘብ እያልኩ ነው፡፡ ዐማራን ለማዳን ወይ ስለዐማርኛ ተጨንቄ ወይ ወያኔ በ“ካህናትና ጳጳሣት” ካድሬዎቹ ድራሹን ስላጠፋው ሃይማኖት ተጠብቤ… እንዳይመስላችሁ፡፡ እንዲያውም በዐማራ ምክንያት ወያኔና ግብረ አበሮቹ ኢትዮጵያንና ቀሪውን ወደ 70 ሚሊዮን የሚጠጋውን ሕዝብ ከሚያጠፉ በ20 ሚሊዮን ገደማ የሚገመተው ከወያኔ ጭፍጨፋና ዕልቂት የተረፈው የዐማራ ሕዝብ በሌላ ሀገር ውስጥ ባዶ ቦታ ተፈልጎለት እዚያ ሄዶ ቢሠፍር የምመርጥ ሰው ነኝ – ለእሥራኤላውያን ታስቦ እንደነበረው፡፡ እስኪ ሌሎቻችሁ እንኳን ራሳችሁን አድኑ፤ ሁሉም ተያይዞ ሞኝ አይሁን፤ የዚህን ዐውሬ የትግሬዎች ቡድን አንደርባዊ ድግምቱንና ትብታቡን አፍርሱበትና ራሳችሁን ነፃ አውጡ፡፡ ለመሆኑ ማን ነው ከወያኔ የጥፋትና የውድመት አዙሪት ነፃ የሆነ? የትኛው ጎሣ ወይም አካባቢ ነው ከወያኔ ቀረቤታና በወያኔ ችሮታ የተጠቀመ? ኦሮሞ? ሶማሌ.? አፋር? ጋምቤላ? ቤንሻንጉል? ከድንጋያማ የተራቆተ መሬት የመጡ ቀጫጭንና ከሲታ ወንድሞቻችን ዛሬ እኛን እርስ በርስ እያባሉ እንደጉማሬ በልተው እንደዝኆን ሲወፍሩ ባይናችን በብረቱ እየተመለከትን የምንገኝ አንዳንድ ቂሎች በጋራ ጠላቶች መሠሪ የፈጠራ ወሬ እየተነዳን አሁንም የፈረደበት ዐማራ ላይ እንረባረባለን፤ የሞተን ፈረስ መጋለብ – የደረቀን ወንዝ መሻገር የጀግንነት መገለጫ አይሆንም፡፡ ትኋንን በጠበንጃ፣ ቁንጫን ደግሞ በርግጫ መግደልም የሚያስፎክር ጀብድ አይደለም፡፡ እውነትን ከሀሰት አበጥሮ በመለየት ሁነኛ ዘመድን ማወቅ አንዱ የጀግንነት ምልክት ነው፡፡ እንደቦይ ውኃ በነዱት መነዳትና እንደክርስቶስ ዘመን “ስቅሎ፣ ሰቅሎ” ብሎ በንጹሕ ዜጎች ላይ “ሆ!” እያሉ መዝመትም በትንሹ ቂልነት ነው፡፡ ጠላትንና ወዳጅን አለመለየት ለከፋ ችግር ይዳርጋል፡፡
ዐማሮችን መጥላትና ማጥፋትም ይቻላል፤ ቀላልም ነው፡፡ እንግሊዞችን መጥላትና – ቢያንስ በንድፈ-ሃሳብ ደረጃ – ማጥፋትም ይቻላል፤ ይህም ቀላል ነው፡፡ ዐማርኛንና እንግሊዝኛን ግን ማጥፋት ይቅርና ለማጥፋት ማሰብ በራሱ ዕብደትና ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍልም ነው – ኢትዮጵያን በሚመለከት እየታዘብነው እንዳለነው ይህ ዓይነቱ የወፈፌ ሥራ የትውልድን መቃተት ያስከትላል፡፡
ዐማርኛን ማጥፋት ዐማሮችን እንደማጥፋት ቀላል ቢሆን ኖሮ እስካሁን ትግርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ ሆኖ ነበር፡፡ ወያኔዎች ግን የለየላቸው ደንቆሮና ልበ-ሥውራን በመሆናቸው ይህ ታሪካዊ ኹነት እንኳን ሊገባቸው አልቻለም፡፡ የነሱን ልጆች ሸገር ላይ ለምን ዐማርኛና በዐማርኛ ያስተምራሉ? ለምን ወደ ቻይና፣ እንግሊዝና አሜሪካ እየላኩ ለሥልጣኔ ቅርብ ያደርጓቸዋል? ለሌላውስ ድንቁርናን ለምን ይፈርዱበታል?
ከሌሎች ክልሎች በተሻለ ሁኔታስ በትግራይ ክልል ለምን ዐማርኛ ይነገራል? ገዢዎቸ ራሳቸው ለምን ዐማርኛን ይለምዳሉ? አሃ! ተረዱታ! ጀምጀምንና ጃንጀሮን – ኮንሶና ሙርሲን፣ አሪና በርታን  ለማስገበር፣ ሲዳማንና ወላይታን እንደልብ ለማዘዝ፣ ጠምባሮንና ደራሳን ለማሽቆጥቆጥ፣ አኝዋክንና ኑዌርን ለመቦጥቦጥ፣ ቦንጋንና ቤንቺ ማጂን ለመርገጥ፣ ሃዲያንና ሐረሪን ለመንዳት፣ ኦሮሞንና ሶማሌን ለመግዛት፣… ከዐማርኛ የበለጠ መሣሪያ እንደማያገኙ ዐወቋ! ግን ግን የቋንቋው ጥቅም ገብቷቸው ሲያበቃ ለተናጋሪዎቹ ያላቸው ንቀትና ጥላቻ አላፈናፍን ብሏቸው ይሄውና ይህን ቋንቋ ለማጥፋት – የሚበሉበትን ወጪት ሰባብሮ ለመጣል – ያቺ ሞኝ ሴት በተረቱ አደረገች ተብላ እንደምትታማበቱ ያለ አስቂኝ ግን አጓጉል ነገር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ሞኟ ሴት ግን ምን አደረገች በል? እሷማ ባሏን የጎዳች መሰላትና ሰውነቷን በጋሬጣ ዘነጣጠለችዋ፡፡ ጅል ሴትና ደንቆሮ ወያኔ አይግጠማችሁ፡፡
ዐማርኛ የሙጃ ሣር ነው፡፡ ዐማርኛ ሰንሰልና ሸምበቆ ነው፡፡ ዐማርኛ ባማርኛ አንፋር ወይም ነጭሎ ብለን የምንጠራው የተክል ዓይነት ነው፡፡ የትም ቢሄድ አካባቢውን በቀላሉ ይለምዳል፤ ሞኛሞኝ ቢጤ ነው፡፡ ዐማሮች የሚባሉ ወገኖቻችን እንደዐማርኛ ገርና ለማዳ ስለመሆናቸው አታስወሹኝ እምብዛም አላውቅም፡፡ ዐማርኛ ግን ቀደም ሲል በተፈጠረለት ታሪካዊ አጋጣሚ የተነሣ በመላው ኢትዮጵያ ተሠራጭቶ ሕዝቡን አንድ ለማድረግ ከጥንት ጀምሮ እየደከመ ይገኛል፡፡ ትርፉ ድካም ብቻ ሆኖ መቅረቱ ግን ያሣዝናል፡፡ ለዚህ ልፋቱ – ለዚህ ከ80 በላይ ለሚገመቱ ጎሣና ነገዶች የጋራ የመግባቢያ መሣሪያ ሆኖ ማገልገሉ ባለቤቶቹን ሊያስወድስና ሊያሸልም ሲገባ በተገላቢጦሽ ሽልማታቸው ውግዘትና ጥይት መሆኑ ምን ዓይነት የታሪክ ምፀት እንደገጠመን ጠቋሚ ነው፡፡ ወያኔ በጨለማ ውስጥ የሚኖር የድንጋይ ዳቦ ዘመን ፍጡር ሆኖ እንጂ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ንጉሥ – ለሀፄ ዮሓንስ ጮሙሮ –  ትግሬም ይሁን ኦሮሞ ወይ ዐማራና ቅልቅል ሁሉም የተጠቀሙት ዐማርኛን ነው – ዐማርኛ ኮከቡ ሰምሮለት ላገዛዝ ሳያመች የሚቀር አይመስለኝም – ለተናጋሪዎቹ ጠንቅ ሆነ እንጂ፡፡ ሁሉም ነገሥታትና ገዢዎች ዐማርኛን መጠቀሙ ስላመቻቸውና ስላተረፉበት እንጂ ወደውትም ላይሆን እንደሚችል ቢያንስ በጥርጣሬ ደረጃ መጠርጠር ይቻላል፡፡
የቋንቋ ልደት፣ ዕድገትና ሞት የራሱ አካሄድ አለው – እንደወያኔ በዐዋጅና በጦርነት አንድ ቋንቋ አይወለድም ወይም ተወልዶ እንኳን ቢሆን አያድግምና ለተፈለገው ቁም ነገር አይበቃም፤ ለዚህ ነባራዊ እውነት ዋናው ምሥክር ወያኔዎች ራሳቸው ናቸው፡፡ እንደነሱ ፍላትና ምኞት ቢሆን ኖሮ ትግርኛ የአሁኒቷ ኢትዮጵያ የጋራ ቋንቋ ሆኖ ነበር – ግን እባብ ልቡን ዐይቶ … እንደሚባለው በፈለጉት መሣሪያ ቢወጉት ዐማርኛ አልሞት አላቸው – እንደነሱው አፍር ልሶ ከመቃብሩ ይነሣል፤ እንዲያውም ይባስ ብሎ እየገነነ መጣና በዋሽንግቶን ከተማ ሣይቀር የሥራ ቋንቋ እስከመሆን ደረሰ፡፡ እንጂ እንደነሱ ጥረት – እንደነሱ የባህል ወረራ – እንደነሱ መፍጨርጨር አዳሜ በአሁኑ ሰዓት አብዚሎ ቅብዚሎ እያለች ሁሏም በትግርኛ ትግባባ ነበር – በመሠረቱ ትግርኛ ብሔራዊ ቋንቋ መሆን አለመሆኑ አያሳስበኝም፤ የሚያሳስበኝ የመሆኛውና ያለመሆኛው ሥልት ነው፤ እንጂ እንኳንስ ጠንቅቄ የምናገረው የእናቴ ወገኖች ቋንቋ በአግባቡና በደንቡ ከሆነ የዝንጀሮም “ቋንቋ” ብሔራዊ ቀርቶ የዓለምም ቢሆን በደስታ እቀበላለሁ፡፡
የትግርኛን ቋንቋና የትግራይን ባህል በሌላው ላይ በግዴታ ለመጫን የሚያደርጉት ሙከራ ቀላል አይደለም – ይህ ደግሞ በጣም ያናድድሃል፤ የምትወደው ብትሆን እንኳን እንድትጠላው ሊያደርጉህ ይችላሉ – ፈቃዳችሁ ከሆነ እዚች ላይ አንዲት ፈረንጅኛ አባባል ልጥቀስ መሰለኝ – “A man can take a horse to a river, but twenty cannot make it drink.” አዎ፣ ሙዚቃውን ልትከፍት ትችላለህ – ግን ማን ነው በፍቅር የሚያዳምጥልሀ? እንዴ፣ ከዚህ ከጀመርኩላችሁ ከዘፈን አቅም እንኳን ሚዲያው ሁሉ በዐዋጅ የተገደደ ይመስል ብዙውን ጊዜ ካለትግርኛ ሌላ ዘፈን አይከፍትም – ቲቪውም፣ ኤፍ ኤሙም፣ የባዛርና የንግድ ትርዒት ዝግጅቱም፣ ዕድሩም ሰምበቴውም ምኑም ምናምኑም… ኮበለይና ተበራቢረይ ሲል ነው የምታደምጡት – ይቅርታችሁንና ብዙዎቻችን ደግሞ ማሽቃበጥ ስንወድ! እነዚህን የ simple  psychology ተጠቂ ዶንኪሾታዊ ወንድሞቻችንን በቀላል ነገር የመደሰትና በትንሽ ድል የመኮፈስ ተፈጥሮ የምናውቅ አጎብዳጆች እነሱን ለማስደሰት የምናደርገው አንዳንድ ነገር ለትዝብት ሲዳርገን አስተውላለሁ – ያ ዓይነቱ ራስን ያለመሆን ችግር ደግሞ በጣም ያሳዝነኛል – እነሱ ራሳቸውም ሳይታዘቡን የሚቀሩ አይመስለኝም – ነገ ደግሞ በሌላው ቀን በቅጽበት ሌላ እንደምንሆን ግልጽ ነው፡፡… የትምህርት ቤቶች ሚኒ ሚዲያዎች እንኳን ባቅማቸው ካለበት የተጋባበት ሆነው በዕረፍት ሰዓታቸው የሚለቋቸው ዘፈኖች ብዙዎቹ ትግርኛ ናቸው፡፡ ሰው ደግሞ ጥልት! በኃይል የመጫን አሉታዊ ጎኑ እንግዲህ ይህ ነው፡፡ ወደህ ከሆነ ትጨፍርበታለህ፣ ትፎክትበታለህ ማነው ትፎክርበታለህ፣ ታገባበታለህ፣ ትፈታ…. አይ፣ አይ መፍታትስ ይቅር… ብቻ ከልብህ ትወደውና በሙዚቃው እንደልብህ በፍቅር ትመላለስበታለህ፡፡ ስትገደድ ግን ትጠላዋለህ፡፡ ተገድደህ እንድትቀበል ከሚደረግ ነገር የበለጠ የሚጠላ ነገር የለም፡፡ ስለዚህ እንኳንስ ትልቁን የማንነትህን መገለጫ ይቅርና ከረሜላም ቢሆን በፈቃድህ እንጂ ተገድደህ ብላ ብትባል እንደኔ ሆዳም ካልሆንክ በስተቀር ያቅርሃል ወይም ቢያንስ ሊያቅርህ ይገባል፡፡
መጠጥ ቤቶች ካለትግርኛ አያዘፍኑም – ለነገሩ እነሱ እንኳ አብዛኛው ደምበኛቸው ትግሬ በመሆኑ ሊሆን ይችላል፤ እርግጠኛ ነኝ – የዚህ ዘመን የሆቴልና የመዝናኛ ሥፍራዎች ደምበኛ ሲታይ በአነስተኛ ግምት ከ60 በመቶ በላይ ትግሬ ነው፡፡ ጎበዝ መደባበቅ ብሎ ነገር የለም፡፡ እንዲህ የምለው ደግሞ አንዱን በመጥላት ወይም ሌላውን በመውደድ እንዳይመስላችሁ፡፡ ከዘር ሐረግ አንጻር ዐማራ ቢቀቀል አይሸተኝም፡፡ በተቃራኒው አንድን ትግሬ አንድ ሰው – ምናልባትም ዐማራ – አላግባብ ሲበድለው ባይ ያን ዐማራ እኔ ነኝ ቀድሜ የምፋረደው፡፡ እኔ እንዲህ ነኝ፡፡ ሁሉም እንዲህ ይሁን፡፡ ሰውን በሰውነቱ እንጂ በሰው ሰራሽ ነገሮች ፈርጀን በእንስሳዊ ባሕርይ አንነዳ፡፡ ማን ነው በፈቃደኝነት ዐማራ ወይ ትግሬ የሆነ? እኔ በተወለድኩበት ቤተሰብ ውስጥ እንድወለድ ለእግዜር ያስገባሁት ማመልቻ የት ነው የሚገኘው? ምን ዓይነት የሚጎመዝዝ ቀልድ ነው ይሄ ኦሮሞ፣ ዐማራ፣ ጉራጌ፣ ሽናሻ… የሚሉት ፈሊጥ? ማን ይሆን ይህን የሰው ግርድና አመሳሶ የሚለይ ቆሻሻ ነገር ወደዚች ምድር ያመጣብን?
እደግመዋለሁ – ዐማሮች በዐማርኛ ተጎዱ እንጂ አልተጠቀሙም፡፡ ይህ ቋንቋ እንዲያውም ከናካቴው ባይፈጠር ይሻላቸው ነበር፡፡ ለጥፋትና ውድመታቸው፣ ለስደትና መከራቸው ዋና ምክንያት ሆነ እንጂ የጠቀማቸው አንዳችም ነገር የለም – በስማቸው የተጠቀመ የየትኛውም ዘር ሹምባሽና አገረ-ገዢ ሁሉ ጥቁር ጠባሳውን ወደነሱ እያላከከ ጦሱጥምቡሱ ተረፋቸው እንጂ ዐማሮች ባማርኛ አልተጠቀሙም፡፡ ይህ በጣም አሣዛኝ ነገር ነውና ሁላችንም ለዐማሮች እንዘንላቸው፡፡ በዚህ ሩዋንዳዊና አርመናዊ የዕልቂታቸው ዘመን ካለኛ ማን አላቸው?
ቋንቋ በመሠረቱ ከሸሚዝና ከኮት የዘለለ ጥቅምም ሆነ አስፈላጊነት የለውም፡፡ ሁላችንም ከኅሊና መታወር የተነሣ “ያንተ ቋንቋ፣ የኔ ቋንቋ” እንላለን እንጂ የማንም ቋንቋ የሁሉም ነው፤ የሁሉም ቋንቋ ደግሞ የማንም ነው፡፡ ያንተ ሊባል ይችል የነበረው በትውልድ እንደ አንድ ባሕሪያዊ ስጦታ ብታገኘው ነበር – ለምሣሌ በጄኔቲክ ውርስ ከአባትህ ልትወርሰው እንደምትችለው ሸፋፋ አረማመድ ማለቴ ነው፡፡ ቋንቋን ግን ከሚነገርበት አካባቢ ከራቅህ አታገኘውም – ወይም በሕጻንነትህ ወደሌላ ቦታ ብትወሰድ የዚያን አካባቢ ቋንቋ እንጂ የዘመዶችህን ቋንቋ ጆሮህን ቢቆርጡት አትሰማም፤ጭራሹንም ያለ ቋንቋ ቀርተህ እንደሌሎች እንስሳት ጓደኞቻችን ለምሣሌ እንደላም “እምቧ” እያልክ ልትኖርም ትችላለህ – በከብቶች መሀል ከነሱ ጋር ብቻ እንድታድግ ከተደረገ፡፡ ወያኔዎች ግን ይህን እውነት አያውቁም ወይም ሊያውቁ አይፈልጉም፡፡ ስለዚህም ትግርኛ ተናጋሪ (ትግሬ) ሰው ለነሱ እግዚአብሔራቸው ነው – ዘረኝነት የፈጣሪን ቦታ የተካላቸው የአምልኮት ጽላታቸው መሆኑን መርሳት የለብንም፤ ትግሬ ማለት ለነሱ በምንም ነገር የማይደራደሩበት አካላቸው አምሳላቸው ነው – አጠፋ አላጠፋ፣ ንጹሕ ሆነ ወንጀለኛ ያ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ የጠባብነት ወረርሽኝ የሚያሰቃየው ሰው በዘመናዊ ፈሊጥ ከ”ዕውቀት የፀዳ” በመሆኑ ልክ እንደከብት መሰሉን እየፈለገ እንደከብት ይተሻሻል፤ ሌላውን ደግሞ በጠላትነት ፈርጆ ባገኘው ቀንድ ሁሉ እያሳደደ ይወጋዋል፡፡ ለዚህ ነው ወያኔዎች የነሱን ቋንቋ የማይናገርንና ትግሬ ያልሆነን ሰው ፍዳውን እያሣዩ መፈጠሩን እንዲጠላ የሚያደርጉት፡፡ እንምንታዘበው የዕውቀት አድማሳቸውም ከአፍ እስከ አፍንጫቸው እንኳን አይደርስም፡፡ ተማሩ ተብለው ዶክተርና ፕሮፌሰር ሆነዋል የተባሉትም ቢሆኑ ዕውቀታቸው ያን ያህል ነው – እንዳብዛኛው የወያኔ “ምሁር” ድግሪውን በግዢ ካላመጡት ነው ያውም፡፡ ትምህርት ደግሞ የውስጥ ዐይንን – እንደሎብሳንግ ራምፓ አባባል ሦስተኛውን ዐይን – ካልከፈተ ዋጋ የለውም፡፡ ያ ሁሉ በትምህርት ያሣለፈው ጊዜ ልፋትና ጊዜን መግደል ብቻ ነው፡፡ ብዙ ዓመት ተምሮ መደንቆርን ነው ያተረፈው፡፡ ተማረ የተባለ ሰው በትንሹ ዘረኝነትን መፀየፍ ይኖርበታል፤ በሰው ልጆች እኩልነት ማመን ቀዳሚው የመማር ጥቅም ሊሆን ይገባል – አለዚያ ያ ተማርኩ የሚል ሰው ደደበ እንጂ አልተማረም፡፡ ለነገሩ መማር ማለት መደንቆርም እንደሆነ የሚያምኑ ፈላስፎች አሉ፡፡
ጠባብነትና የግንዛቤ ዕጥረት ደግሞ ጓደኛሞች ናቸው፤ ብዙ ነገርም ያሳጡሃል – ለምሣሌ ማኅበራዊ እንስሳነትህን በማስረሳት የሁሉምነትህን ትተህ የጥቂቶች ወገን ብቻ እንድትሆንና ለጥቂቶች ልብህን ለብዙዎች ግን ጥርስህን እንድትሰጥ ያስገድዱሃል፤ ሃይማኖትህን ያስክዱህና በዘረኝነት ልምሻ ኮድኩደው በከረፋ መሬት ላይ የዘውግ አባላትህን ትፈልግ ዘንድ የእንፉቅቅ ያስኬዱሃል፤ ከሌላ ዘውግ ጓደኛና ወዳጅ ቢኖርህ እሱንም ያስክዱህና በጠባቧ የዘውግ ክፍልህ አውርደው የገማ የገለማ የአጥንትና ደም ጭቃ ውስጥ እንድትንቦራጨቅ ያደርጉሃል፡፡ ዘረኝነትን ምናልባት ከሆነልህ በጸሎትና በጸበል እንጂ በትምህርትና በሕይወት ተሞክሮ በቀላሉ አትገላገለውም፡፡ ቀያጅ ነው፤ ባሪያው ካደረገህ እንደ አደንዛዥ ዕፅ ሱስ፣ እንደሀሽሽና ሱረት ፍዳህን ሳያበላህ አትገላገለውም፡፡ ብቻ ጠባብነትና ዘረኝነት መዘዛቸው ብዙ ነው ወንድሜ፡፡ እግዜር ይጠብቅህ እንጂ በተወርዋሪ ኮከብ የብርሃን ብልጭታ በምትመሰል በዚህች ቅጽበታዊ የምድር ሕይወት ውስጥ የዘረኝነትን ደዌ ጨምሮ የማይታይ አበሳ የለም፡፡
በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ጠፋች ማለት ምን ማለት ነው? ብዙ ሰው ላይገባው ይችላል፡፡
በደምቢ ዶሎ ከተማ በእንግሊዝኛ ቋንቋ በቢኤ ዲግሪ የተመረቀ አንድ ኦሮምኛ ተናጋሪ ወጣት በዚሁ በወያኔ ዘመን ለሥራ ፍለጋ አዲስ አበባ ይመጣል፡፡ ማስታወቂያ ያነብና እኔ የማውቀው አንድ ትምህርት ቤት ሄዶ ለእንግሊዝኛ አስተማሪነት ያመለክታል፡፡ የመመረቂያ ውጤቱ ኤ በኤ ስለነበር ለቃለ መጠይቅ ከተመረጡት ውስጥ ስሙ ይካተትና በቀጠሮ ይጠራል፡፡ ፈታኞቹ አንድ ፈረንጅና ሁለት ሀበሾች ናቸው፡፡ (የዘመናችንን የውጤት መግለጫ ካርድ ስናይ “ቢ” “ሲ”ና “ዲ” የት ገቡ ብለን መጠየቃችን አይቀርም፤ በተግባር ግን ዜሮ! በተለይ አንዳንድ የግል የትምህርት ተቋማት ተማሪን ለመሳብ ሲሉ …)
ብቻ የሚያሣዝን ነው፡፡ ጠፍተናል፡፡ ወያኔዎች ድራሻችንን አጥፍተውናል፡፡ ሰው ግን አላወቀም ወይም ጥልቅ የሆነ ክፍለ ዘመናዊ እንቅልፍ ውስጥ ነው፡፡ ያ ልጅ ራሱን እንዲያስተዋውቅ ዕድል ይሰጠዋል – በእንግሊዝኛ፡፡ ምንም ነገር መናገር ያቅተዋል፡፡ ፍርሀት እንዳይመስላችሁ – የችሎታ ማጠር ነው፤ ቋንቋውን ከየት ያምጣው? ዲግሪን እንደጠበል መርጨት እኮ በጣም ቀላል ነው – ደርግ የከፍተኛ መኮንንነትን ማዕረግ በ“ከዚህ መልስ ሻምበል፤ ከዚያ ታች ወዲህ ደግሞ ሻለቃ” እያለ በለብ ለብ ሥልጠናና አለልክ በተጋነነ ባዶ ጀብድ ያድል አልነበር? – አሁን የነወዩ ብሶ ቁጭ አለ እንጂ! ከበረሃ ትግል በቀጥታ ወደ ጄኔራልነት)፡፡ መቶ ዩንቨርስቲ መክፈት እኮ እጅግ ቀላል ነው – ለዚያውም በቢከፍቱ ተልባ የሚታወቁ ዩንቨርስቲዎችን ለታይታና ለዕቅድ ማስፈጸሚያ ብሎ መክፈት – ባገር ሀብትም መቀለድ፡፡ … ልጁ በዐማርኛ ራሱን እንዲገልጽ በአስተርጓሚ ይጠየቃል፤ ዐማርኛውስ ከየት መጥቶ? በምን ይግባቡ? ፈረንጁም አፉን ይዞ ከተደመመ በኋላ እንዲህ ተብሎ እንዲነገረው መከረ፤” አየህ፣ አሁን እኛ ብንቀጥርህ የ4ኛ ክፍል ተማሪዎች እንደመሆናቸው አንተን ያሣቅቁሃል፤ እነሱ ካንተ መቶ በመቶ ይበልጣሉ… ስለዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ካሉት የግል የቋንቋ ት/ቤቶች በአንደኛው ተመዝገብና ራስህን አሻሽል፡፡ ማሻሻልህን እርግጠኛ ስትሆን ለመቀጠር አመልክት፡፡ አሁን ግን እናዝናለን አልተገናኘንም…”፡፡
ዛሬ የተመረቁት መጻሕፍት በላቲን ነው የተጻፉት ተብሏል፡፡ በላቲን ሆሄ እንዲጠቀሙ የተሸረበውን ወያኔያዊ የፖለቲካ ሤራ ለጊዜው እንተወውና ወደ ወጪው እንሂድ፡፡ በዐማርኛ ቢጻፍ በ100 ገጽ ያልቅ የነበረ መጽሐፍ በላቲን ሲሆን በትንሹ 300 እንደሚሆን ታውቃላችሁ? ካላወቃችሁ ዕወቁ፡፡
ምሣሌ ማየት እንችላለን፡- “ወላይትኛ” ሊባል ሲችል  Wolayttotto Doonaa ተባለ ተሠልጥኖ ተሙቶ፡፡ ማየት ማመን ነውና ወላይታዎች የሆናችሁ ራሳችሁ ፍረዱት፡፡ 7 ፊደል በ17 ፊደል ተመነዘረ፡፡ እኔ በመሠረቱ አይደለም በላቲን በዐረብኛና በቻይንኛም ቢጻፍ ግድ የለኝም – ቋንቋውን ዱሮውንም አላውቀውምና፡፡ የወያኔ መሠረታዊ እሳቤ ግን ወላይታውንና ሌላውን ዘውግ ከኢትዮጵያዊነት የማስተሳሰሪያ ገመድ ለመነጠል ነው፡፡ እንጂ ወላይትኛ በዐማርኛ መጻፍ አለመጻፉ ያን ያህል አጨቃጫቂ ሆኖ እንዳይመስላችሁ፡፡ ወያኔ ደግሞ ቅራኔና ግጭትን እንደመፍጠር የሚያስደስተው ነገር የለም፡፡
ሌላውና ከዚሁ የሚያያዘው ነገር ጎሣዎች ሁሉ በየራሳቸው ቋንቋ እንዲማሩ ተደርጎ ዐማርኛን ሲቻል እንዲጠሉትና በመላ አቅማቸው እንዲዋጉት ያ ባይቻል ከዐማርኛ ርቀው እንዲያድጉና ከሌላው ዜጋ ጋር በምንም ዓይነት የጋራ ገመድ እንዳይገናኙ ማድረግ ነው፡፡ ይህ ዕቅድ በሚገባ ተተግብሮ ፍሬ እያፈራላቸው ነው፡፡ አንድ የፌዴራል ተብዬ ሠራተኛ ከአዲስ አበባ በአራቱም አቅጣጫ ሲወጣ የክልሉን ቋንቋ የሚያውቅ ዐማርኛ ተናጋሪ ይዞ መሄድ አለበት፡፡ ሁሉንም ክልል ፀረ-ዐማርኛና ፀረ-አንድነት አድርገውታል፡፡
አብዛኛው የሥራ ዘርፍ በወያኔዎች በተያዘው አዲስ አበባ ውስጥ በየግንባታው ‹ሳይት› ሥራ ለመቀጠር የሚፈልግ ዜጋ ትግሬ ሆኖ መገኘት ይኖርበታል – በተፈጥሮ ወይም በገዢ – ዲቪ ይገዛል – ትግሬነትም ካወቅህበት ይገዛል፡፡ ትግሬ ካልተሆነ በቀላል መቀጠር የለም (የቅንፍ ጨዋታ፡- አንዲት አሮጊት በአንድ ረጂም ሠልፍ ገብተዋል፡፡ ምግብና ልብስ ለመቀበል ነው ሰዎቹ የተሰለፉት፡፡ ሴትዮዋ ግን ሠልፉ ውስጥ ለመገኘት መሥፈርት መኖሩንም ሆነ የመሥፈርቱን ዓይነት አያውቁም፡፡ ተሠላፊዎቹ የኤች አይቪ ተጠቂዎች ናቸው፡፡ ሴትዮዋ ተራቸው ደረሰና ማስረጃቸውን ተጠየቁ፡፡ ምሥጢሩን ካለማወቃቸውም በተጨማሪ ምንም ማስረጃ የላቸውም፡፡ ያኔ “አይ ፈጣሪየ፣ ለምንድነው ይህን በሽታ እንኳን ያልሰጠኸኝ?” በማለት እግዜር በሽታውን ስላልሰጣቸው አማረሩት አሉ – ሆድ መጥፎ ነው፤ ከሰው በታች ያደርጋል- ያዋርዳል፤ እንደምናየው እንኳንስ ትግሬነትን የማይድን በሽታን ያስመኛል፡፡…) ሁሉም እንደውሻ ዘሩን እያነፈነፈ ነው ወዛደርና ኩሊ እንኳን የሚቀጥር፡፡ እናም መንጓለል አለ – አዳሜ የቀባጭ ምሷን እያገኘች ነው፡፡ በዚህ መልክ ሁሏም ዋጋ እየከፈለች ነው፡፡  በቀጣፊዎች ሸር በተፈጠረ ታሪካዊ ስህተት ለተጎዳ ዜጋ መቼም እሰይ አይባልም እንጂ ሁሉም ይህን ችግር መረዳቱ ጥሩ ነው ባንልም ክፉ አይመስለኝም – ትልቅ ዋጋ ከፍለህ የቀሰምከውን ትምህርት በቀላሉ አትረሳውምና፡፡
አዲስ አበባ የምትመጣ የክልል ሰው ፍዳዋን እያየች ነው፡፡ ከትምህርት ትምህርት የላት፤ ከችሎታ ችሎታ የላት፤ ከቋንቋ ቋንቋ የላት… ባዶዋን ትመጣና ዘበኝነትና ግርድና ባቅማቸው በቀላሉ የማይገኙ እየሆኑ ክፉኛ እየተቸገሩ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ቋንቋ ዋና መሣሪያ ነውና፡፡ ዘመናውያኑ ትግሬዎች ቋንቋቸው ከዐማርኛ እምብዝም ስለማይለይና ሥረ-መሠረታቸው አንድ ግንድ በመሆኑ ለመልመድ ብዙም አይቸገሩም፡፡ ከትግራይ ገጠር በመጡ በሁለትና ሦስት ወር ውስጥ ዐማርኛን አቀላጥፈው በመናገር ይሄን የዋህ የመሀል አገር ሰው በአሽከርነትና በግርድና ያንቆራጥጡታል – ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ አይደለም ብረት ይሰብራል፤ በተግባር አየን፡፡
አሁን ምን ይደረግ? እኔ እንጃ፡፡


Wednesday, May 4, 2016

በጋምቤላ ታፍነው ስለተወሰዱት ህጻናት አወዛጋቢ ጉዳዮች እየተነሱ ነው – (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)

ሚያዚያ 24 ቀን 2008 ዓ.ም.
ርዕሰ ዜና
 በጋምቤላ ታፍነው ስለተወሰዱት ህጻናት አወዛጋቢ ጉዳዮች እየተነሱ ነው፤
 በኬኒያ በተደረመሰው ህንጻ ሳቢያ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ጨመረ
 በሶማሊያ ውስጥ የተደረመሰ መስጊድ የሰው ህይወት አጠፋ፤ አልሸባብም አንድ ከተማ ተቆጣጠር ተባለ
 በሱዳን ታግዶ የነበረው አልታየር ጋዜጣ መታተም እንዲጀምር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ
 በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ ለሚካሄደው ብሔራዊ ምርጭ አንድ 16
ፓርቲዎች አንድ ተወዳዳሪ መደቡ።

ዝርዝር ዜና
 ከጋምቤላ በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ታፍነው የተወስዱት ሕጻናት 32 መለቀቃቸውን የደቡብ
ሱዳን ባለስልጣኖች ከገለጹ ወዲህ የተወሰዱትን ህጻናት አስመልክቶ አወዛጋቢ ጉዳዩ እየተነሱ
መሆናቸው ታውቋል። የ32 ህጻናት መለቀቅ የደቡብ ሱዳን የቦማ ግዛት ተጠባባቂ አስተዳዳሪ
ሕናቶቹን አጋቾቹ ጥለዋቸው ሄዱ በሚል ሰበብ ወደ ፒቦር ከተማ የተወሰዱ መሆናቸውንና
ቀጥሎ በጁባ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደሚላኩና ሌሎችም ህጽናት እየተፈለጉ መሆናቸውን
ተናግረዋል። የወያኔ አገዛዝ ህጻናቱን በወታደራዊ ኃይል አስመልሳለሁ፤ ታጋቾቹን እግር በእግር
እየተከታተልኩ ነው ይበል እንጅ ቆይቶ ግን ድርድር ውስጥ መግባቱ ይታወቃ

Gambela
 ባለፈው ሳምንት በኬኒያ ዋና ከተማ በናይሮቢ በዝናም ምክንያት በተደረመሰ የመኖሪያ ህንጻ ሳቢያ
የሞቱት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ታወቀ። እሁድ ሚያዚያ 23 ቀን 2008 ዓም
በባለስልጣኖች 16 ሰዎች ሞተዋል ተብሎ ተነግሮ የነበረ ሲሆን ሰኞ ሚያዚያ 24 ቀን 5 አስከሬኖች
በመገኘታቸው የሞቱትን ሰዎች ቁጥር ወደ 21 ከፍ አድርጎታል። የኬኒያ ቀይ መስቀል በሰጠው
መግለጫ እስካሁን ያልተገኙ ከ60 የሚበልጡ ሰዎች ምናልባት ሊሞቱ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ
ብሏል። የሁለት ዓመት እድሜ ያለው ባለ ስድስት ፎቅ ህንጻ የተሰራው በወንዝ ዳርቻ ላይ ሲሆን
ደረጃውን ባልጠበቀ ሁኔታ ተሰርቷል በሚል እንዲፈርስ ተወስኖበት በተለያዩ ምክንያቶች የቆየ
መሆኑ ተገልጿል። ቅዳሜ ሚያዚያ 22 ቀን 2008 ዓም. የኬኒያው ፕሬዚዳንት የቤቱ ባለቤት
እንዲታሰር መመሪያ ካስተላለፉ በኋላ ባለቤቱ ለፖሊስ እጁን ሰጥቷል ተብሏል።

 አርብ ሚያዚያ 21 ቀን በሶማሊያ ውስጥ በመታደስ ላይ ያለ መስጊድ በመደርመሱ ጸሎት ሲያደርጉ
ከነበሩት መካከል 15 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ ሌሎች 40 ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል።
በመስጊድ ውስጥ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች የነበሩ ሲሆን የሞቱን እና በህይወት የተረፉትን ለማወቅ
የተወሰኑ ቀናት ይወስዳል ተብሏል። መስጊዱን እያደሰ ያለው መሀንዲስ ተይዞ በምርመራ ላይ
የሚገኝ መሆኑን ከአካባቢው የመጣው ዜና ያስረዳል። በተያያዘ ዜና እሁድ ሚያዚያ 23 ቀን 2008
ዓ.ም. የአልሸባብ ታጣቂዎች በመሃል ሸበሌ ግዛት ሩኒርጎድ በተባለች ከተማ ላይ ባካሄዱት ጥቃት
11 የመንግስት ወታደሮች ገድለው ከተማ መልሰው የተቆጣጠሩ መሆናቸውን አንድ የሱማሌ
ወታደራዊ መኮንን ገልጿል። የአልሸባብ ታጣቂዎች ከተማዋን ከመውረራቸው በፊት በአጥፍቶ
ተጠፊዎች የሚሾፈሩና ቦምብ ያጠመዱ መኪናዎችን በማፈንዳት ጥቃት የፈጸሙ ሲሆን
በአካባቢው የነበሩ የመንግስት ወታደሮች ነቅለው በመውጣታቸው ከተማዋን በቀላሉ ሊቆጣጠሩ
ችለዋል። ከሁለቱም በኩል የሞቱትን ሰዎች በእርገጠኛንት ማረጋገጥ ባይችልም አልሸባብ 32
የመንግስት ወታደሮች ገድያለሁ የሚል መግለጫ ሰጥቷል። አልሸባብ ከባድ ወታደራዊ ሽንፈት
ደርሶበት ከብርካታ ቦታዎች እንዲለቅቅ ተደርጓል፤ እንደቡድንም ተዳከሟል፤ የሚል ተደጋጋሚ
መግለጫዎች ከሱማሊያ መንግስትና ከአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ቢሰጡም ቡድኑ
በተለያዩ ጊዜያት ያካሄዳቸው ጥቃቶች አሁንም ጠንካራ መሆኑን ያሳያል ተብሏል።

 በሱዳን መንግስት ባለስልጣኖች ታግዶ የነበረው አልታየር የተባለው ነጻ ጋዜጣ ስራውን
እንዲጀምር ከፍተኛው ፍርድ ቤት የወሰነ መሆኑን ገልጸው ጋዜጣው በቅርቡ ስራውን
እንደሚጀመር የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ መግለጫ ሰጥተዋል። ባለፈው ታህሥሳስ ወር ጋዜጣው
መንግስት በነዳጅ እና በመብራት ወጭ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ ማንሳቱን አስመልክቶ
በአምዱ ላይ የተቃውሞ አስተያየት በመጻፉ በሱዳን ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ያለው የብሔራዊ
ኢንተለጀንስ እና ጸጥታ ቢሮ እንዳይታተም ያገደው መሆኑ ይታወሳል። ከአምስት ወራት እገዳ
በኋላ የሱዳን ከፍተኛው ፍርድ ቤት እገዳው አግባብ እንዳልሆነ ገልጾ ጋዜጣው መልሶ
እንዲታተም ወስኗል።

 በሚቀጥለው ዓመት ህዳር ወር ላይ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ በሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ
የ51 ዓመት እድሜ ያላቸው ሙአሴ ካቱሚ የጋራ ተወካይ በመሆን እጩ ተወዳዳሪ ሆነው
እንዲቀርቡ 16 የሚሆኑ የገዥው ፓርቲ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የወከሏቸው መሆኑ ተነገረ። ካቱሚ
የደቡብ ካታንጋ ግዛት አስተዳዳሪ የነበሩ ሲሆን ከጥቂት ወራት በፊት ከገዥው ፓርቲ አባልነት
በመሰናበት ተቃዋሚዎችን የተቀላቀሉ ናቸው። የአሁኑ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ ወደ
ስልጣን የመጡት በ1993 ዓም አባታቸው ሎሬት ካቢላ ከተገደሉ በኋላ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ
በሕዝብ ምርጫ ፕሬዚዳንት የሆኑት በ1998 ዓም ነው። በአገሪቱ ህግ መንግስት መሰረት አንድ
ሰው ከሁለት የስልጣን እድሜ በላይ ሊወዳድር ስለማይችል የአሁኑ የስልጣን ጊዜ ለጆዜፍ ካቢላ
የመጨረሻ ቢሆንም ህገ መንግስቱ ከሚፈቅደው ውጭ ለሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር አሳብ አላቸው
የሚለው ዜና በሰፊው እየተወራ መሆኑ ታውቋል። ከጥቂት ቀናት በፊት ጆሴፍ ካቢላ
በሚቀጥለው ምርጫ መወዳደራቸውን በመቃወም ከ5000 የበለጡ ዜጎች ያካሄዱትን የተቃውሞ
ስልፍ ፖሊሶች በድብደባና በአስለቃሽ ጋዝ በትነዋል። የንግድ ስራዎችን ሲያካሄዱ የነበሩት እና
የኮንጎ የእግር ኳስ ቡድን መሪ የነበሩት ካቱሜ ፓርቲዎቹ የሰጧቸውን ውክልና መቀበልና
አለመቀበላቸውን ያልገለጹ ሲሆን በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ በመሆናቸው ምርጫውን በቀላሉ
ያሸንፋሉ የሚል ግምት አለ።