ሚያዚያ 24 ቀን 2008 ዓ.ም.
ርዕሰ ዜና
በጋምቤላ ታፍነው ስለተወሰዱት ህጻናት አወዛጋቢ ጉዳዮች እየተነሱ ነው፤
በኬኒያ በተደረመሰው ህንጻ ሳቢያ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ጨመረ
በሶማሊያ ውስጥ የተደረመሰ መስጊድ የሰው ህይወት አጠፋ፤ አልሸባብም አንድ ከተማ ተቆጣጠር ተባለ
በሱዳን ታግዶ የነበረው አልታየር ጋዜጣ መታተም እንዲጀምር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ
በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ ለሚካሄደው ብሔራዊ ምርጭ አንድ 16
ፓርቲዎች አንድ ተወዳዳሪ መደቡ።
ዝርዝር ዜና
ከጋምቤላ በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ታፍነው የተወስዱት ሕጻናት 32 መለቀቃቸውን የደቡብ
ሱዳን ባለስልጣኖች ከገለጹ ወዲህ የተወሰዱትን ህጻናት አስመልክቶ አወዛጋቢ ጉዳዩ እየተነሱ
መሆናቸው ታውቋል። የ32 ህጻናት መለቀቅ የደቡብ ሱዳን የቦማ ግዛት ተጠባባቂ አስተዳዳሪ
ሕናቶቹን አጋቾቹ ጥለዋቸው ሄዱ በሚል ሰበብ ወደ ፒቦር ከተማ የተወሰዱ መሆናቸውንና
ቀጥሎ በጁባ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደሚላኩና ሌሎችም ህጽናት እየተፈለጉ መሆናቸውን
ተናግረዋል። የወያኔ አገዛዝ ህጻናቱን በወታደራዊ ኃይል አስመልሳለሁ፤ ታጋቾቹን እግር በእግር
እየተከታተልኩ ነው ይበል እንጅ ቆይቶ ግን ድርድር ውስጥ መግባቱ ይታወቃ
ባለፈው ሳምንት በኬኒያ ዋና ከተማ በናይሮቢ በዝናም ምክንያት በተደረመሰ የመኖሪያ ህንጻ ሳቢያ
የሞቱት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ታወቀ። እሁድ ሚያዚያ 23 ቀን 2008 ዓም
በባለስልጣኖች 16 ሰዎች ሞተዋል ተብሎ ተነግሮ የነበረ ሲሆን ሰኞ ሚያዚያ 24 ቀን 5 አስከሬኖች
በመገኘታቸው የሞቱትን ሰዎች ቁጥር ወደ 21 ከፍ አድርጎታል። የኬኒያ ቀይ መስቀል በሰጠው
መግለጫ እስካሁን ያልተገኙ ከ60 የሚበልጡ ሰዎች ምናልባት ሊሞቱ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ
ብሏል። የሁለት ዓመት እድሜ ያለው ባለ ስድስት ፎቅ ህንጻ የተሰራው በወንዝ ዳርቻ ላይ ሲሆን
ደረጃውን ባልጠበቀ ሁኔታ ተሰርቷል በሚል እንዲፈርስ ተወስኖበት በተለያዩ ምክንያቶች የቆየ
መሆኑ ተገልጿል። ቅዳሜ ሚያዚያ 22 ቀን 2008 ዓም. የኬኒያው ፕሬዚዳንት የቤቱ ባለቤት
እንዲታሰር መመሪያ ካስተላለፉ በኋላ ባለቤቱ ለፖሊስ እጁን ሰጥቷል ተብሏል።
አርብ ሚያዚያ 21 ቀን በሶማሊያ ውስጥ በመታደስ ላይ ያለ መስጊድ በመደርመሱ ጸሎት ሲያደርጉ
ከነበሩት መካከል 15 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ ሌሎች 40 ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል።
በመስጊድ ውስጥ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች የነበሩ ሲሆን የሞቱን እና በህይወት የተረፉትን ለማወቅ
የተወሰኑ ቀናት ይወስዳል ተብሏል። መስጊዱን እያደሰ ያለው መሀንዲስ ተይዞ በምርመራ ላይ
የሚገኝ መሆኑን ከአካባቢው የመጣው ዜና ያስረዳል። በተያያዘ ዜና እሁድ ሚያዚያ 23 ቀን 2008
ዓ.ም. የአልሸባብ ታጣቂዎች በመሃል ሸበሌ ግዛት ሩኒርጎድ በተባለች ከተማ ላይ ባካሄዱት ጥቃት
11 የመንግስት ወታደሮች ገድለው ከተማ መልሰው የተቆጣጠሩ መሆናቸውን አንድ የሱማሌ
ወታደራዊ መኮንን ገልጿል። የአልሸባብ ታጣቂዎች ከተማዋን ከመውረራቸው በፊት በአጥፍቶ
ተጠፊዎች የሚሾፈሩና ቦምብ ያጠመዱ መኪናዎችን በማፈንዳት ጥቃት የፈጸሙ ሲሆን
በአካባቢው የነበሩ የመንግስት ወታደሮች ነቅለው በመውጣታቸው ከተማዋን በቀላሉ ሊቆጣጠሩ
ችለዋል። ከሁለቱም በኩል የሞቱትን ሰዎች በእርገጠኛንት ማረጋገጥ ባይችልም አልሸባብ 32
የመንግስት ወታደሮች ገድያለሁ የሚል መግለጫ ሰጥቷል። አልሸባብ ከባድ ወታደራዊ ሽንፈት
ደርሶበት ከብርካታ ቦታዎች እንዲለቅቅ ተደርጓል፤ እንደቡድንም ተዳከሟል፤ የሚል ተደጋጋሚ
መግለጫዎች ከሱማሊያ መንግስትና ከአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ቢሰጡም ቡድኑ
በተለያዩ ጊዜያት ያካሄዳቸው ጥቃቶች አሁንም ጠንካራ መሆኑን ያሳያል ተብሏል።
በሱዳን መንግስት ባለስልጣኖች ታግዶ የነበረው አልታየር የተባለው ነጻ ጋዜጣ ስራውን
እንዲጀምር ከፍተኛው ፍርድ ቤት የወሰነ መሆኑን ገልጸው ጋዜጣው በቅርቡ ስራውን
እንደሚጀመር የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ መግለጫ ሰጥተዋል። ባለፈው ታህሥሳስ ወር ጋዜጣው
መንግስት በነዳጅ እና በመብራት ወጭ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ ማንሳቱን አስመልክቶ
በአምዱ ላይ የተቃውሞ አስተያየት በመጻፉ በሱዳን ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ያለው የብሔራዊ
ኢንተለጀንስ እና ጸጥታ ቢሮ እንዳይታተም ያገደው መሆኑ ይታወሳል። ከአምስት ወራት እገዳ
በኋላ የሱዳን ከፍተኛው ፍርድ ቤት እገዳው አግባብ እንዳልሆነ ገልጾ ጋዜጣው መልሶ
እንዲታተም ወስኗል።
በሚቀጥለው ዓመት ህዳር ወር ላይ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ በሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ
የ51 ዓመት እድሜ ያላቸው ሙአሴ ካቱሚ የጋራ ተወካይ በመሆን እጩ ተወዳዳሪ ሆነው
እንዲቀርቡ 16 የሚሆኑ የገዥው ፓርቲ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የወከሏቸው መሆኑ ተነገረ። ካቱሚ
የደቡብ ካታንጋ ግዛት አስተዳዳሪ የነበሩ ሲሆን ከጥቂት ወራት በፊት ከገዥው ፓርቲ አባልነት
በመሰናበት ተቃዋሚዎችን የተቀላቀሉ ናቸው። የአሁኑ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ ወደ
ስልጣን የመጡት በ1993 ዓም አባታቸው ሎሬት ካቢላ ከተገደሉ በኋላ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ
በሕዝብ ምርጫ ፕሬዚዳንት የሆኑት በ1998 ዓም ነው። በአገሪቱ ህግ መንግስት መሰረት አንድ
ሰው ከሁለት የስልጣን እድሜ በላይ ሊወዳድር ስለማይችል የአሁኑ የስልጣን ጊዜ ለጆዜፍ ካቢላ
የመጨረሻ ቢሆንም ህገ መንግስቱ ከሚፈቅደው ውጭ ለሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር አሳብ አላቸው
የሚለው ዜና በሰፊው እየተወራ መሆኑ ታውቋል። ከጥቂት ቀናት በፊት ጆሴፍ ካቢላ
በሚቀጥለው ምርጫ መወዳደራቸውን በመቃወም ከ5000 የበለጡ ዜጎች ያካሄዱትን የተቃውሞ
ስልፍ ፖሊሶች በድብደባና በአስለቃሽ ጋዝ በትነዋል። የንግድ ስራዎችን ሲያካሄዱ የነበሩት እና
የኮንጎ የእግር ኳስ ቡድን መሪ የነበሩት ካቱሜ ፓርቲዎቹ የሰጧቸውን ውክልና መቀበልና
አለመቀበላቸውን ያልገለጹ ሲሆን በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ በመሆናቸው ምርጫውን በቀላሉ
ያሸንፋሉ የሚል ግምት አለ።
No comments:
Post a Comment