Tuesday, May 17, 2016

ኔልሰን ማንዴላን በነጮቹ መንግስት ያሲያዛቸው የአሜሪካው የስለላ ድርጅት CIA ነው ተባለ (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች | 
  • 175
     
    Share
#ለድርቅና ለረሃብ የተሰበሰበው ገንዘብ ከሚያስፈልገው 54 ከመቶ ብቻ ነው ተባለ
#ኔልሰን ማንዴላን በነጮቹ መንግስት ያሲያዛቸው የአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲ አይ ኤ ነው ተባለ
#የአምስቱ አገሮች ጥምር ኃይል አምስት የቦኮ ሃራም መሪዎችን ያዝኩ፣ በርከት ያሉ ዜጎችንም አስለቀቅኩ አለ
#የኮንጎ ወታደሮች እና ፖሊሶች በሰሜን ኮሪያ ወታደሮች እየሰለጠኑ መሆናቸውና የሰሜን ኮሪያ ሽጉጦችን መታጠቃቸው ተገለጸ
#የግብጽ ፍርድ ቤቶች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉ ዜጎች ላይ የእስራት ቅጣት በየኑ
በተፈጥሮ የአየር መዛባት፣ በዝናም እጥረትና ወያኔ በሚከተለው ዘረኛና የተበላሸ ፖሊሲ ምክንያት በኢትዮጵያ በ50 ዓመት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ድርቅና ረሃብ ከተከሰተ ወዲህ ዓለም አቀፍ ድድየዕርዳታ ድርጅቶች በድርቁ ለተጎዳው ወገን የእርዳታ እጃቸውን ዘርግተው የተማጽኖ ድምፅ ቢያሰሙም ከተጠየቀው 1.4 ቢሊሆን ዶላር ውስጥ እስከ አሁን የተገኘው 54 ከመቶ ብቻ መሆኑ ተገልጿል። ከዚህ ገንዘብ ውስጥ አሜሪካ 705 ሚሊዮን ዶላር መርዳቷ ሲታወቅ በሶሪያ ባለው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉትና ወደ አውሮፓ ለሚፈልሱት ስደተኞች የሚደረገው እርዳታ ለኢትዮጵያ ድርቅና ረሃብ ጉዳተኞች ሊሰጥ በሚችለው አጠቃላይ የዕርዳታ መጠን ላይ ተጽእኖ መፍጠሩ ተጠቅሷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጎርፉ አደጋ በኢትዮጵያ የዕለት ተዕለት ክስተት እየሆነ መምጣቱና ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ በጎርፉ አደጋና በመሬት መደርመስ ከ 100 በላይ ሰዎች መገዳልቸውና በሽህ የሚቆጠሩ የቤት እንስሳት ማለቃቸው እንዲሁም በሚሊዮን የሚቆጠር ብረት መውደሙ አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ሲሆን የዝናቡ መጠን በዚህ ከቀጠለ መጭው ክረምት ከመጠናቀቁ በፊት 500 ሺ ሲዎች ከቀያቸው ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተሰግቷል።
mandela3.jpg
 የደቡብ አፍሪካ እውቁ ታጋይና የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ሚስተር ኔልሰን ማንዴላ የዛሬ 54 ዓመት በዘረኛው የደቡብ አፍሪካ የነጮች መንግስት ሊያዙ የቻሉት በአሜሪካ የስለላ ተቋም በሲ አይ አባል ጥቆማ እንደሆነ ተጋለጠ። ሚስጥሩ ሊጋለጥ የቻለው ጥቆማውን ያካሄዱት በወቅቱ በደቡብ አፍሪካ ዲፕሎማት የነበሩት የሲ አይ ኤ አባል ዶናልድ ሪካርድ ከመሞታቸው በፊት “ የማንዴላ ጠመንጃ” ( “Mandela’s Gun”) በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ፊልም ዳይሬክተር
ላደረጉላቸው ቃለ ምልልስ በሰጡት መልስ መሆኑን ሰንደይ ታይምስ የተባለው የእንግሊዝ ጋዜጣ እሁድ ግንቦት 7 ቀን ባወጣው እትሙ ገልጿል። ከዚህ በፊት የሲ አይ ኤው ድርጅት ሚስተር ማንዴላን ከመያዛቸው በፊት ሲከተታል የነበረ መሆኑና በመጨረሻም እንዲያዙ የጠቆመው የዚሁ ድርጅት አባል ነው የሚለው ወሬ በሰፊው ሲሰራጭ የኖረ ቢሆንም የሲ አይ ኤ ባለስልጣኖች በተለያዩ ጊዜያት ሲክዱ የቆዩ መሆናቸው ይታወሳል። ማንዴላ ለረጅም ጊዜ በልዩ ልዩ መንገድ
ከደቡብ አፍሪካ የጸጥታ ኃይሎች ሲያመልጡ ከቆዩ በኋላ ተይዘውና ተፈርዶባቸው ለ27 ዓመታት ያህል በእስር ቤት አሳልፈዋል። ማንዴላ ሲመሩት የቆየቱ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግሬስ በሬገን ዘመነ መንግስት በአሜሪካ ሽብረተኛ ድርጅት ሊስት ውስጥ ተመዝግቦ የቆየ ሲሆን ሽብረተኛ የሚለው ስም የተነሳለት በ2000 ዓም መሆኑ ይታወቃል።

 ቦኮ ሃራምን ለማዳከም የተቋቋመው የአምስት አገሮች ጥምር ኃይል ባካሄዳቸው ተከታታይ አሰሳዎች አምስት የቡድኑን ከፍተኛ መሪዎች የያዘ መሆኑና በቡድኑ ታግተው የነበሩ በርካታ ሴቶችንና ህጻናትን ያስፈታ መሆኑን የካሜሩን መንግስት ቃል አቀባይ ገልጿል። አሰሳዎቹ የተካሄዱት ማዳዋ በሚባለው ጫካ ውስጥ መሆኑ ሲገለጽ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ናይጄሪያ ውስጥ ያላቸው የጦር ስፈር ሲደመስስ የተጠቀሰውን ጫካ የጦር ሰፈር ማድረጋቸው ተደርሶበታል። ይህ ዜና የተሰጠው
የምዕራብ አፍሪካ አገሮች መሪዎች የፍረንሳዩ ፕሬዚዳንት ሆላንድ በተገኙበት የቦኮ ሃራምን እንቅስቃሴ ለመግታት አቡጃ ላይ ከፍተኛ ስብሰባ ባደረጉበት ወቅት ነው።

 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤክስፐርት ቡድን የሴሜን ኮሪያ ወታደራዊ ተቋም አባላት ለኮንጎ ወታደሮችና ፖሊሶች ስልጠና እየሰጡ መሆናቸውንና የኮንጎ ፖሊሶች ሰሜን ኮሪያ የተሰሩ ሽጉጦች መታጠቃቸውን ያረጋገጠ መሆኑን ገልጿል። ቡድኑ ተመሳሳይ ሽጉጦች በአገሪቱ ዋና ከተማ ኪንሻሳ ውስጥም በጥቁር ገበያ እንደሚሸጡ መረጃ የደረሰው መሆኑን ጠቁሟል። ሰሜን ኮሪያ ማንኛቸውንም ዓይነት መሳራሪያ በዓለም ገበያ እንዳትሸጥና ወታደራዊ ስልጠና እንዳትሰጥ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የታገደች በመሆኑ ኮንጎ ውስጥ በማስልጠን ስራና በመሳሪያ ሽያጭ ንግድ መሰማራቷ በሁለቱም አገሮች በኩል ህግን መተላለፍ ነው በሚል የኤክስፐርቱ ቡድን ገልጿል።
 ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የግብጽ ፍርድ ቤቶች ያልተፈቀደ ሰላማዊ ስልፍ አድርገዋል የተባሉ 152 ሰዎችን ከ2 እስከ አምስት አመት በሚደርስ እስራት የበየኑባቸው ታውቋል። የተፈረደባቸው የግብጽ ዜጎች ብዙዎቹ በቅርቡ የሲሲ መንግስት በቀይ ባህር ላይ የሚገኙ ሁለት የግብጽ ዴሴቶችን ለሳኡዲ አረበያ መስጠቱን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉ ናቸው። የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተንከባካቢ ድርጅቶች ሲሲ ስልጣን ከያዙ በኋላ ተቃውሞን ለማስተናገድ የማይፈልጉ ፍጹም አምባገነን መሆናቸውን አውግዘው ሁኔታው በጣም ያሳሰባችው መሆኑን ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment