Saturday, November 29, 2014

የሶስት ወር ህጻን ልጇን አንቃ የገደለችው በ16 ዓመት እስራት ተቀጣች

ህጻን ልጇን በሻሽ አንቃ በመግደል የጣለችው ተከሳሽ ላይ የእስራት ቅጣት የተወሰነባት መሆኑን የኢትዮጵያ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
crimeበአርሲ ዞን የሒጦሳ ወረዳ ፖሊስ እንደገለፀው በተከሳሽ መስታወት ደረጄ ላይ የእስራት ቅጣት ሊወስንባት የቻለው ከወለደችው የሶስት ወር እድሜ ያለውን ልጇን ሐምሌ 14 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ ጎንዴ ፊንጨማ ልዩ ስሙ ሾሪማ ተብሎ ከሚታወቅበት አካባቢ በመውሰድና ከበቆሎ ማሳ ውስጥ በመግባት በያዘችው ሻሽ አንቃ በመግደሏ ነው፡፡ እንደ ሒጦሳ ወረዳ ፖሊስ ገለጻ የተገደለውን ህጻን የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት አስከሬኑ ተነስቶ በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል በተደረገለት የአስከሬን ምርመራ መሠረት ህጻኑ ታንቆ መገደሉ ተረጋግጧል ተብሏል፡፡
ተከሳሿ በቁጥጥር ስር ውላ በሰጠችው የእምነት ቃልም በቡና ቤት አስተናጋጅነት እየሰራች ሳለ ከተዋወቀችው አሽከርካሪ ጋር ፍቅር በመመስረቷና ከወለደችለት በኋላ ሊረዳት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ድርጊቱን ልትፈጽም መነሳሳቷን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ መስታወት ደረጄን በአስራ ስድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኖባታል፡፡

No comments:

Post a Comment