- ኩማ በጭንቅላት እጢ (ቲዩመር) በሽታ ምክንያት ለከፍተኛ ህክምና ዲሲ መምጣታቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ የመዳን ተሳፋቸው 90 በመቶ የተመናመነ መሆኑን ከሃኪሞች እንደተገለፀላቸው አስታውቀዋል።
ከባለቤታቸው ጋር የመጡት ኩማ ሆስፒታል ከመግባታቸው በፊት ባለፈው ሳምንት ማርዮት ሆቴል አርፈው እንደነበረ ሲታወቅ ሁለት ኢትዮጵያውያንን በሆቴሉ መተላለፊያ ላይ ሲያገኙ ክፉኛ ደንግጠው እንደነበረ ማወቅ ተችሏል። አሜሪካ -ዲሲ መምጣታቸው እንዳይታወቅባቸው የሚጠነቀቁትና ፍርሃት የሚታይባቸው ኩማ የስጋታቸው ምንጭ እንደሌሎች ባለስልጣናት ተቃውሞ ይገጥመኛል በሚል እንደሆነ ሲታወቅ የማያውቁትን ስልክ እንደማያነሱ ማረጋገጥ ተችሏል።
በተለይ የመዳን ተስፋ እንደሌላቸው ከተነገራቸው በኋላ ከኢትዮጵያ የሚደወልላቸውን ስልክ እንደማያነሱ ታውቋል። ኩማ ደመቅሳ ከ1993ዓ.ም በፊት ሙስና ውስጥ እንዳልገቡና ነገር ግን የአዲስ አበባ ከንቲባ ከሆኑ በኋላ በከፍተኛ ሙስና ከተዘፈቁት ባለስልጣናት ተርታ እንደተመደቡ ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment