(ዘ-ሐበሻ) ለወዳጅነት ጨዋታ ወደ ኡጋንዳ አምርቶ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዩጋንዳ አቻው 3ለ0 ተሸነፈ:: በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ዘመን ከ31 ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ መድረክ ብቅ ብሎ የነበረው ብሔራዊ ቡድናችን ለዓለም ዋንጫ ለማለፍም ትልቅ ትንቅንቅ አድርጎ እንደነበር ይታወሳል::
የውጭ ሃገር አሰልጣኝ በብዙ ሺ ዶላር በመክፈል ብሔራዊ ቡድኑ እንዲሰለጥን ቢደረግም ውጤቱ ግን እንደ ሰውነት ቢሻው ዘመን ሊሆን አለመቻሉን የስፖርት ተንታኞች ለዘ-ሐበሻ ይናገራሉ::
በሌላ በኩል ኢትዮ ኪክ እንደዘገበው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የለምንም ክፍያ በነፃ የዮጋንዳ እግር ኳስ አፍቃሪ በስታዲየም ገብቶ እንዲከታተለው የአገሪቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአገሪቱ የጤና ቢሮ ጋር በትብብር ያዘጋጁት። በዚሁ እለት የነፃ HIV ምርመራ ማድረግ ለሚፈልጉም ተዘጋጅቷል። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ዮጋንዳ ተጉዞ ይህን የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያደርግ ሙሉ ወጪውን የሸፈነው የዮጋንዳ እ.ፌ ነው።
ዎሊያዎቹ ዛሬ ከዮጋንዳ ጋር አድርገውት የገቡት አረንጓዴ ማሊያ በቀይ ቁምጣ ቁጥሩ ወይም ሳይዙ ለወፍራሙም ለቀጭኑም ተጨዋች ለሁለም አንድ አይነት በመሆኑ አብዛኞቹ ተጨዋቾች ማልያው እና ቁምጣው ሰፍቷቸዋል ቦላሌ ሆኖባቸዋል። አንዳንድ ተጨዋቾቹ ከአዲስ አበባ ከመነሳታቸው በፊት ማላያው እና ቁምጣው ቁጥሩ ትልቅ መሆኑን ቢናገሩም የምትመልሱት ስለሆነ ችግር የለውም ለወዳጅነት ጨዋታ የሰፋ ማሊያ የሰፉ ቁምጣ ችግር የለውም በመባላቸውን ሰምተናል። የሰፋ ማሊያ የሰፋ ጎልና ሽንፈት ይዞ መጣልና ሲል ኢትዮ ኪክ ዘገባውን አጠናቋል
No comments:
Post a Comment