Saturday, June 20, 2015

ኢህአዴግን አልመረጣችሁም በሚል ቤታቸው እንደፈረሰባቸው የለገጣፎ ነዋሪዎች ገለጹ


  • 404
     
    Share
‹‹በምርጫው ምክንያት ሊበቀሉን ነው ቤታችን በክረምት ያፈረሱት›› ነዋሪዎቹ
11220142_727121737413487_3102328378380879005_n
በ2007 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ኢህአዴግን አልመረጣችሁም በሚል ቤታቸው እንደፈረሰባቸው በለገጣፎ አባኪሮስ፣ ገዋሳ አካባቢ ነዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ነዋሪዎቹ በተለያዩ ጊዜያት ፖሊስና ካድሬዎች ቤታቸውን በቀይ ቀለም ከቀቡ በኋላ በተደጋጋሚ ገንዘብ ሲቀበሏቸው እንደቆዩና ከሰኔ 09/2007 ዓ.ም ጀምሮ በምርጫው ሰበብ ቤታቸውን እያፈረሱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአካባቢው ህዝብ ‹‹ቤትክን እናፈርሳለን!›› እየተባለ በደተጋጋሚ በሚከፍለው ሙስና የተማረረው እንደሆነ የገለጹት ነዋሪዎቹ በአካባቢው ኢህአዴግ እንዳልተመረጠ ገልጸዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ኢህአዴግን ያልመረጡ በተለይም ሰማያዊ ፓርቲን መርጠዋል የተባሉ ነዋሪዎች ቤት ቀይ ምልክት ተቀብቶ እንዲፈርስ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ከምርጫው ጋር በተያያዘ ቤታቸው እንዲፈርስ ቀይ ምልክት ከተቀባባቸው መካከል ለፖሊስና ካድሬዎች ጠቀም ያሉ ገንዘብ የከፈሉ ነዋሪዎች እንዳይፈርስባቸው ሲደረግ ገንዘብ መክፈል ያልቻልነው ቤታችን ፈርሶብናል ብለዋል፡፡


10561823_727121734080154_5796908975695142219_n
ነገረ ኢትዮጵያ ቢሮ ድረስ በመምጣት መረጃውን ያቀበሉን ነዋሪዎቹ ‹‹ኢህአዴግን አልመረጣችሁም፣ ሰማያዊ ፓርቲን ነው የመረጣችሁት በሚል ቤታችን ፈርሶ በአሁኑ ወቅት ከእነ ልጆቻችን ጎዳና ላይ ወድቀናል፡፡›› ብለዋል፡፡ ‹‹እስካሁን ቤታችሁን እናፈርስባችኋለን ብለው በማስፈራራት ከፍተኛ ገንዘብ ሲያስከፍሉን ቆይተዋል፡፡ ቆርቆሮ ገንጥለው ለቆርቆሮው እስከ 2 ሺህ ብር አስከፍለው እንደገና ቆርቆሮውን ይመልሱልን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በምርጫው ምክንያት በአካባቢው ህዝብ ቂም ይዘዋል፡፡ በምርጫው ምክንያት ሊበቀሉን ነው ቤታችን በክረምት ያፈረሱት›› ያለው አንድ ወጣት ሙስና ከፍለው ቤታቸው እንዳይፈርስ ካደረጉት ባሻገር እየዞሩ ቤት የሚያፈርሱት ፖሊሶችና ደህንነቶች በአካባቢው በርካታ ቤቶችን ማስገንባታቸውና የእነሱ ቤት እንደማይፈርስባቸው ገልጾአል፡፡ የካድሬዎች፣ የፖሊሶችና ገንዘብ የሚከፍሉት ሲቀር ‹‹ኢህአዴግን አልመረጣችሁም፡፡ የመረጣችሁት ተቃዋሚዎችን በተለይም ሰማያዊ ፓርቲን ነው›› ተብለው ቤታቸው እንደሚፈርስ ተነግሯቸው ሙስና መክፈል ያልቻሉት ነዋሪዎች ቤት ተመርጦ እየፈረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ገዋሳ፣ ጪሚሲና ሚሽን የተባሉ አካባቢዎች ቤቶች እየፈረሱ መሆኑን የገለጹ በለገጣፎ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ ‹‹የነዋሪዎች ቤት እየፈረሰ የሚገኘው በምርጫው ምክንያት ነው፡፡ ለገጣፎ አካባቢ ምርጫው መጭበርበሩን ያጋለጡ ሰዎች ከፍተኛ ጫና ደርሶባቸዋል፡፡ እኔ ጋርም እንዳይገናኙም ወከባ ይፈፀምባቸዋል፡፡ አሁን
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44486#sthash.UcGUMbGl.dpuf

Friday, June 19, 2015

የአሜሪካ እርዳታ አምባገነኖችን ማጠናከሩ ይቁም፣ ግልፅ ደብዳቤ ለአሜሪካ መንግሥት ሃላፊዎችና ለአሜሪካ ሕዝብ

የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነት ከመቶ ዓመታት በላይ ነው። ይኼ ግንኙነት በሁለቱ ሃገሮች መካከል ሊኖር የሚገባውን የእኩልነትና የጋራ ጥቅም መሰረት ያደረገ እንደ ነበረ ታሪክ ያስታውሳል። መንግሥታት ቢለዋወጡም በሁለቱ ሃገሮች መካከል የተመሰረተው የቆየ ግንኙነት አይፈርስም የሚል እምነት አለኝ። የኢትዮጵያ ስደተኞች አሜሪካን የመጀመሪያ መድረሻ አድርገን አሜሪካዊ የሆንንበትና ወደፊትም የምንሆንበት ዋና ምክንያት የአሜሪካ አስኳል እሴቶች–ነጻነት፤ የግለሰብ ክብር፤ ፍትህ-ርትእ፤ የሰብአዊ መብቶች መከበር፤ በሕግ ፊት ማንኛውም ግለሰብ እኩል መሆን፤ የሕግ የበላይነትና ዲሞክራሳዊ አገዛዝ ስለሳቡንና የመስራት እድል በጎሳ ሳይሆን በሞያ የሚወሰን መሆኑን ስላወቅን ነው። ዛሬ ብዙ መቶ ሽህ የኢትዮጵያ ትውልድ በአሜሪካ ይኖራል፤ ድምጽና መብት አለው። በኢትዮጵያ የማናገኘውን በተሰደድንበት አሜሪካ እናገኛለን። ይኼን እድል ተጠቅመን ለተወልድንባት ሃገር ጠበቃ እንሁን።U.S. and the Oppressive Ethiopian Government
በሁለቱ ሃገሮች የተመሰረተው የቆየ ግንኙነት በወታደራዊው፤ ሶሻሊስት አምባገነን መንግሥት ዘመን ተለውጦ አሜሪካኖች አቋማቸውን ለውጠው ተተኪ መንግሥት ይጠባበቁ እንደ ነበር ብዙ ማስራጃዎች አሉ። ደርግን የተካው የጎሳ ልሂቃን ቅንጅት ህወሓት በበላይነት የሚያሽከረክረው የኢህአዴግ መንግሥት ከምእራብ ሃገሮች፤ በተለይ ከአሜሪካ ጋር ያለው የጥቅም ትሥስር እጅግ በጣም የጠነከረ ነው። የኢትዮጵያ እድገት ፈጣን የሆነው በውጭ እርዳታ፤ ስደተኛው በሚልከው ገንዘብ፤ በሃገር ውስጥ ብድርና በቅርቡ በውጭ ኢንቬስተሮች ድጋፍ ነው። ኢኮኖሚው በራሱ ለመንቀሳቀስ አልቻለም፤ ፍትኅ ከሌለ አይችልም። በአሜሪካኖች ስሌት፤ በፈራረሰው፤ እርጋታና ሰላም በሌለበት የአፍሪካ ቀንድና አካባቢ (በሰሜን ኤርትራ፤ በምስራቅ፤ ሶማሊያ፤ በምእራብ ደቡብና ሰሜን ሱዳን፤ በባህር ማዶ በየመን፤ በሶሪያ፤ በኢራክ፤ በሰሜን አፍሪካ በሊብያና በግብፅ) ያለውን የርስ በርስ ግጭት፤ የሃገሮች መፈራረስና የሃብት ውድመት ሲመለከቱ ኢትዮጵያ “የእርጋታና የልማት” ደሴት ናት ወይንም ትሆናለች ብለው ማመናቸው አያስገርምም። ግዙፉ እርዳታ ከዚህ ስሌት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው። ጸረ-ሽብርተኛነት ሰብሳቢ መርህ ሁኗል። አሜሪካኖች ያላስተዋሉት፤ ቢያስተውሉትም የሚመጣውን ችግር ከራሳቸው ጊዚያዊ ጥቅም ባሻገር ያልተገነዘቡት፤ አምባገነኖች ፀረ-ሽብርተኛነትን ምክንያት በማድረግ ራሳቸው ሽብር ፈጣሪዎችና ሽብርተኞች መሆናቸውን ነው። የሰብአዊ መብቶችና የነጻነት መገፈፍ ሁለተኛ ወይንም ሶስተኛ ደረጃ የያዘው ለዚህ ነው። የሕዝብ መብቶች በተከታታይ ሲጎዱ አፍራሽ ኃይሎች፤ ሽብርተኞችን ጨምሮ መግቢያ ቀዳዳ ያገኛሉ፤ ስደተኝነት እየከፋ ይሄዳል።
የአሜሪካ መንግሥት መሪ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ልክ የዛሬ ሁለት ዓመት በደቡብ አፍሪካ እንዲህ ብለው ነበር። “በአፍሪካ ሃገሮች በሙሉ የማንኛውም ግለሰብ ክብር ቢከበር አሜሪካኖችም ነጻ ይሆናሉ። እኔ የማምነው እያንዳንዳችን ነጻ ለመሆን ከተፈለገ የሁሉም ሰብአዊ ቤተሰቦችና ግለሰቦች ከድህነት ወይንም ከበሽታ ወይንም ከጭቆና ነጻ መሆን አለባቸው።” ይኼ እሴት የአሜሪካኖች እሴት ነው፤ የመላው በነጻነት ለመኖር የሚፈልግ ሕዝብ እሴትና ተስፋ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለክብሩ፤ ለፍትህ፤ ለነጻነት፤ ለሕግ የበላይነትና ለዲሞክራሲ ሲታገል ከዓመሳ አመታት በላይ ሁኗል። ኢትዮጵያ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በአንድ አምባ ገነን ፓርቲ ስትገዛ ቆይታ አሁንም በአራት ቀናት በሚካሄድ “የይስሙላ ምርጫ” የተጠበቀ ውጤት ለሚከተሉት አምስት አመታት ትገዛለች። የኢትዮጵያ የመንግሥት ስርዓት ልክ የፈረሰውን የሶቬት ሕብረት አገዛዝ የሚመስል ጋርዲያን የተባለው ጋዜጣ “ኦርዌሊያን” የሚለው፤ ወይንም በእኔ አመለካከት ፍጹም የሆነ በስለላ መረብ የተቆራኘ፤ በአንድ አናሳ ብሄር የበላይነት የመከላከያ፤ የስለላና የኢኮኖሚ የበላይነት የሚተዳደር አገዛዝ ነው።
ይኼ አገዛዝ ያለ ዓለም ትሥስር የገንዘብ የስለላ፤ የመከላከያ፤ የዲፕሎማሲና ሌላ ድጋፍ ህይወት አይኖረውም። የማይካደው ገዢው ፓርቲ ባለፉት ሃያ አራት አመታት ለልማት ድጎማ ብቻ አርባ ቢሊየን ዶላር ተሰጥቷታል። ኢህአዴግ ከሙስናው፤ ከሃገር በገፍ እየተሰረቀ ከሚሸሽውና ከሌላው ውድመት የተረፈውን ተጠቅሞ መሰረተ ልማት አካሂዷል። ከእድገቱ ባሻገር መታየት ያለበት ሃቅ፤ ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ የምግብ እርዳታ ጥገኛ ከሆነችው፤ ወጣቱ ትውልድ በገፍ ከሚሰደድባት ኢትዮጵያ ተሰርቆ የሸሸው ሃብት ግምት አስር ቢሊየን ዶላር ነው። ይኼ ስንት ፋብሪካ ይከፍት ነበር፤ ለስንት ወጣቶች የስራ እድል ያቀርብ ነበር? የተሰረቀው ተሰርቆና ከሃገር ሸሽቶ፤ የተረፈው መንገድ ስርቷል፤ ሃዲድና ግድቦች እየሰራ ነው። ይኼ ግዙፍ እርዳታና መንግሥት ከባንኮች ተበድሮ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች፤ ቪላዎች፤ መንገድና ሌላ ቢሰራ ምኑ ያስደንቃል? የማይካደው ኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ደረጃ ጥገኛ መሆኗ ነው። ኢትዮጵያ ዛሬ በያመቱ የአራት ቢሊየን ዶላር እርዳታ ተቀባይ ሁናለች፤ ከአፍሪካ ከፍተኛው ከሆነ ቆይቷል። በመንግሥት ደረጃ ሲታይ ከሁሉም ሃገሮች ከፍተኛውን እርዳታ የምትለግሰው አሜሪካ ናት። ፈጣን እድገት አለ በሚባልባት አዲስ አበባ ከፎቆቹ ባሻገር ለማየት ለፈለገ ታዛቢ ቢያንስ አንድ መቶ ሽህ ህፃናት በመንገድ ያድራሉ፤ ብዙ መቶ ሽህ ነዋሪዎች ምግብ ከቆሻሻ ማጠራቀሚያ እየለቀሙ ይበላሉ። ከስምንቶ መቶ ሽህ እስከ አንድ ሚሊየን የኢትዮጵያ ስደተኞች በየመን ብቻ ይገኛሉ። በሊቢያ የታጎሩትን ቁጥር አናውቅም። ለጋሶች ይኼን ሁሉ ግፍ አያውቁም ለማለት አልችልም። በተጨማሪ፤ መጭው ምርጫ ለይስሙላ መሆኑን የአሜሪካ መንግሥት ያውቃል። ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የያዘው ስራ ይረጋገጥለታል፤ አሜሪካኖች ይኼን እንደሚደግፉ አልጠራጠርም። ሕዝብ የፈለገውና እውነተኛ ውድድር ያለበት ምርጫ ቢሆን ኑሮ፤ የአሜሪካ ኢምባሲና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች በምርጫው ቀንና ተከታታይ ቀኖች “ብጥብጥ” ይነሳል በሚል ስሌት የተጠንቀቁ መልእክቶች አያወጡም ነበር።
ከላይ የቀረበውን መሰረት በማድረግ አሜሪካኖችን የጠየቅኋቸውና ያሳስብኳቸው የእርዳታውን ጥቅምና ጉዳት ከራሳቸው መብትና ጥቅም አንፃር እንዲያዩት ነው። “እስኪ አስቡት፤ በአሜሪካ በተከታታይ አንድ ፓርቲ በየ አራት አመቱ በሚደረገው ምርጫ ቢያሸንፍ ምን ትላላችሁ? የፖለቲካ ተወዳዳሪዎች መብታቸውን ለማስከበር ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ ፖሊስ ቢደበድባቸው፤ ቢያስራቸው፤ ቢያሳድዳቸው ምን ትላላችሁ? ምርጫው ሰፊ ውድድር ተካሂዶ የፖሊሲ አማራጮች ውይይት ባይደረግባቸው ምን ትላላችሁ? አስቡት፤ ኢትዮጵያ ከአርባ ቢሊየን ዶላር እርዳታ በኋላ ከዓለም ሃገሮች መካከል አሁንም ፍፁም ድሃና በዓመት የነፍስ ወከፍ ገቢዋ ከአፍሪካ ሃገሮች አንድ ሶስተኛ የሆነ፤ ከዓለም ሃገሮች መካከል በሙሰኛነት የተበከለች፤ ከዓለም ሃገሮች መካከል ከፍተኛውን የምግብ ጥገኝነት ቦታ የያዘች፤ በአፍሪካ ጋዤጠኞችን ከሚያስሩ ሃገሮች መካከል ሁለተኛውን ደረጃ የያዘች፤ በዓለም ደረጃ አራተኛውን ደረጃ የያዘች መሆኗን ብታውቁ ምን ትላላችሁ? ይህች የምግብ ጥገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ አብዛኛውን የምግብ እርዳታ የምታገኘው ከአሜሪካ መንግሥት ነው። ከድሃይቱ ኢትዮጵያ በአራት ዓመታት ብቻ አስር ቢሊየን ዶላር ተሰርቆ ሲሸሽ ለሃገር ጥቅም ቢውል ኑሮ ስንት ፋብሪካዎች ለማቋቋም እንደሚያስችልና ለስንት ኢትዮጵያዊያን የስራ እድል እንደሚፈጥር አስቡት?
እኔ ይኼን ሃተታ ለአሜሪካ ሕዝብና መንግሥት በታወቁ ጋዜጦች አማካይነት ለማቅረብ የተገደድኩት በሙስናውና በገንዘቡ መሰረቅ ምክንያት አይደለም። ያሳሰበኝ፤ የኢትዮጵያዊያን ሰብ አዊ መብቶች በተከታታይ መገፈፋቸው፤ የማህበረሰብ ድርጅቶች፤ ነጻ ጋዜጦችና ጋዜጠኞች፤ ተወዳዳሪ ሊሆኑ የሚችሉና የተሻለ አማራጭ ለሕዝብና ለሃገር ለማቅረብ የሚችሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች መደምሰሳቸው፤ መናገር፤ መሰብሰብ፤ መንግሥትን መተቸት ወንጀል መሆኑ ነው። እነዚህን እሴቶች እንደምታከብሩና እንደምትታገሉላቸው አምናለሁ። ታዲያ፤ የአሜሪካ መንግሥት የሚሰጠው እርዳታ እነዚህን እሴቶች ካላጠናከረ ዘላቂ ጥቅሙ ምንድን ነው? የመናገር፤ የመሰብሰብ፤ የመከራከር፤ የመተቸት፤ የመወዳደር ወዘተ መብቶች ፍጹምና አደገኛ በሆነ ደረጃ ታፍነዋል። ሂውማን ራይትስ ወች እንዲህ ሲል አስጠንቅቆ ነበር። “የኢትዮጵያ መንግሥት በአሰቃቂ ደረጃ ከመንግሥት ቁጥጥር ነጻ የሆነውን መገናኛ ብዙሃን አውድሞታል፤ ቢያንስ ሃያ ሁለት ጋዜጠኞች፤ አሳታሚዎችና ብሎገሮችን በወንጀለኛነት ከሶ አስሯል፤ ከሰላሳ በላይ ጋዜጠኞች በፍርሃት ከሃገር እንዲሰደዱ አድርጓል።” ገዢው ፓርቲ ይኼን ሲያደርግ የሚጠቀምባቸው በ2009 ያፀደቃቸው የጸረ-ሽብርተኛና የመንግሥት ያልሆኑ የበጎ አድራጎትና የማህበረሰብ ድርጅቶችን የሚመለከቱ ሕጎችን ነው። ለነጻነት፤ ለፍትህ፤ ለዲሞክራሲና ለሕግ የበላይነት የተሟገተና የቆመ ግለሰብ ሁሉ ሰለባ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው። በስራ እድል በኩል ሲታይ፤ ለገዢው ፓርቲ ወይንም ለጎሳ ጥቅም ታማኝነት ያላሳየ ሁሉ እድል አይኖረውም። አስተዳደሩ በባለሞያዎች ሳይሆን በታማኝነት ይመራል። ይኼን ሁኔታ ስታዩ፤ አፈናው፤ አድልወው፤ ጭካኔው፤ መገለሉ ወዘተ ለሰላም፤ አብሮ ለመኖር፤ ለእርጋታ አደገኛ መሆኑን ትገምታላችሁ። የአገዛዙ አፋኝነትና አግላይነት ለሽብርተኛነት አመች ሁኔታ ፈጥሯል። የአሜሪካ መንግሥት እንደዚህ ያለ አፋኝና አግላይ መንግሥት ሲደግፍ የአሜሪካን የረዢም ጊዜ ጥቅም ይጎዳል ወይንስ አይጎዳም? ብላችሁ የመጠየቅ ሃላፊነት አለባችሁ።
ይኼን አደጋ በተደጋጋሚ የምናቀርበው ኢትዮጵያዊያን ብቻ አይደለንም። በዚህ ዓመት ፍሪደም ሃውስ ስለ ዓለም ሃገሮች ነጻ መሆን አለመሆን ባወጣው ዘገባ ኢትዮጵያ ከአርባ ዘጠኝ ነጻ ካልሆኑ የአፍሪካ ሃገሮች መካከል አርባ ሶስተኛውን ደረጃ ይዛለች፤ ከኢትዮጵያ የባሱ ስድስት ሃገሮች ብቻ አሉ ማለት ነው። በተመሳሳይ፤ ዘ ኮሚቲ ቱ ፕሮቴክት ጆርናሊስትስ የተባለው ተቋም “ጋዜጠኞችን በከፍተኛ ደረጃ ከሚያስሩ ሁለት የአፍሪካ ሃገሮች መካከል አንዷ መሆኗን፤ በዓለም ደረጃ ሲታይ አራተኛ መሆኗን አመልክቷል። እንደዚህ ጨለማ በሆነ ሁኔታ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ሊካሄድ አይችልም። ምርጫውን በሚመለከት በዚህ ወር ሂውማን ራይትስ ወች “ምርጫ–የኢትዮጵያን ፈለግ የተከተለ” በሚል እንዲህ ከሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል። “ካለፈው ምርጫ ወዲህ፤ ገዢው ፓርቲ በባሰ ደረጃ ቁጥጥሩን አጠናክሯል፤ የመናገር፤ የመሰብሰብ፤ የመደራጀት መብቶችን ከልክሏል… ኢትዮጵያዊያን ወደ ምርጫ ሲሄዱ ተቃዋሚዎች በገጠማቸው አፈና የተነሳ ያላቸው እድል በጣም የጠበበና ጨለማ የሆነ ነው።” የኢትዮጵያን ሕዝብ፤ በተለይ ተቃዋሚውን በንቀት መነፅር ያየችው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ምክትል የፖለቲካ ሃላፊ ዌንዲ ሸርማን “ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ናት፤ ምርጫውን በሚመለከት ነጻ፤ ፍትሃዊ፤ ተቀባይነት ያለው፤ ክፍትና ሁሉን አቀፍ የሆነ ምርጫ እንደሚካሄድ እናምናለን” ያለችው ውሸት ብዙ የምእራብ ታዛቢዎችን ቁጣና ትዝብት አምጥቷል። ዋሽንግተን ፖስት የተባለው የታወቀ ጋዜጣ እሷንና የኢትዮጵያን መንግሥት በሚመለከት “የማስመሰል ምርጫ በኢትዮጵያ” በሚል አርእስት እንዲህ ብሏል። “የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያን መንግሥት ማውገዝ እንጅ ማሞገስ የለበትም።” ስለሆነም፤ የአሜሪካን መንግሥትና ሕዝብ አደራ የምለው ሽብርተኛነትን ለመከላከል በሚል ምክንያት ሽብርተኛነትን የሚፈጥርና የሚያጠናክር መንግሥት መደገፉን ያቁም ነው።
ምን አማራጭ አለ?
ጠቃሚውን ተቃውሞ ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነን ግለሰብ ወይንም መንግሥት ለማሳመን አስቸጋሪ ነው። በእኔ ግምት ለኢትዮጵያ ዘላቂነት፤ ለመላው ሕዝቡ የኑሮ መሻሻል፤ ለአሜሪካ ዘላቂ ጥቅም አጋባብ ያለው አማራጭ ያለምንም ማወላወል ለሰብአዊ መብቶች፤ ለነጻነት፤ ለፍትህና ለሕግ የበላይነት መከበርና ለዲሞክራሲ ግንባታ ያለተቆጠበ ድጋፍ መስጠት ነው። ቢያንስ የአሜርካ መንግሥት ለራሱ ዘላቂ ጥቅም ሲል የሚለግሰውን እርዳታ በሙሉ ከሰብ አዊ መብቶች መከበርና ከዲሞክራሲ ግንባታ ጋር ማጣመር አለበት። ነጻ፤ ፍትሃዊ፤ ተቀባይነት ያለው፤ ክፍትና ውድድር ያለበት ምርጫ ለማካሄድ ቅድመ ሁኔታዎች መከበር ነበረባቸው። አለመከበራቸው ውጤቱን አስቀድሞ ወስኖታል። ገዢው ፓርቲ ያሸንፋል።
የአሜሪካን ሕዝብ፤ የምክር ቤት አባላትንና የመንግሥት ሃላፊዎችን በቀጥታ የምጠይቀው ከሕዝብ ተሰብስቦ ለኢትዮጵያ አምባገነን መንግሥት የሚሰጠው እርዳታ ከዲሞክራዊው አገዛዝ ጋር ምን ግንኙነት አለው፤ ከሌለው ለምን ለሰብአዊ መብቶች፤ ለነጻነት፤ ለፍትህ፤ ለእውነተኛ እኩልነትና ለዲሞክራሲ አትቆሙም? የሚል ነው።”
በእኛ በኩል አብሮና ተባብሮ ከመስራት ሌላ አማራጭ የለንም። የአሜሪካ ዜግነት ያለን ኢትዮጵያዊያን በያለንበት ለአሜሪካ ምክር ቤት ተወካዮች ሳንሰለች ድምፃችን ብናሰማ ከፍተኛ አስተዋፆ እንደምናደርግ አምናለሁ፤ እስቲ ያልሞከርነውን እንሞክር እላለሁ።

Thursday, June 18, 2015

የእኛ ዝምታ ለወያኔዎች?

እኛ ኢትዮጵያውያን ዝምታ ወርቅ ነው እየተባልን ማደጋችን የጠቀመንን ያክል ጉዳቱም በዛው ልክ ነው። እውነት ነው በዝምታ ውስጥ ትዕግስት ፣ ማስተዋልና አርቆ አሳቢነት ይንጸባረቅበታል። ይህንን የማይረዱ አካላት ግን ፍርሃት ወይም ድንቁርና ይመስላቸውና ሰባዊና ዲሞክራሲያዊ መብታችንን ይገፋሉ፣ ይነጥቃሉ፣ ይጨቁናሉም። ሁልጊዜም በዝምታ ውስጥ እንድንኖር ይመክራሉ፣ ያበረታታሉ፣ ያስፈራራሉም። ዛሬ የመገናኛ ብዙኃን በረቀቀበትና በተስፋፋበት ዘመን ያለውን እውነታ ግን በሚገባ እናውቃለን። ነገር ግን እውነትን በውስጣችን አፍነን መናገር እየቻልን እንዳንናገር፣ መስራት እየቻልን እንዳንሰራ፣ ለውጥ ማምጣት እየቻልን እንዳንለወጥ፣ ነጻነትና ዲሞክራሲን መጎናጸፍ እየቻልን የነጻነት እጦት እያሰቃየን ለዘመናት በአምባገነን ስርዓት ተጉዘናል። ከመቼውም በበለጠ ደግሞ ዛሬ ላይ ችግሩ ገዝፎና እጥፍ ድርብ ሁኖ ለብዙ ወገኖቻችን የስደትና እስራት ምክንያት ሁኗል።Ethiopian Silence
እርግጥ ነው ዝምታን ሰብረው ስለ ነጻነት ብዙ የተናገሩ፣ የጻፉ እና በአደባባይ የመሰከሩ ሰዎች እጣ ፈንታቸው ወደ እስር ቤት ተወርውረው የህሌና እስረኞች ሆነው ወርቃማ የአለግባብ ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ መደረጉ ይታወቃል። ለእነዚህም እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ስቃይና መከራ መብዛት አይነተኛ ምክንያት የእኛ የብዙዎቻችን ዝምታ መጨመሩ ነው። ምንም በደል ሳይገኝባቸው በሀገራቸው አረመኔያዊ ቡድን ሲታሰሩ፣ ሲደበደቡ፣ ሲንገላቱ፣ ውድ ህይወታቸው በከንቱ ሲሰዋ እያየንና እየሰማን “ነግ በእኔ” የሚለውን እረስተን በዝምታ ቁመን እንመለከታለን። ብዙዎቻችንም ችግሩን የግለሰብ ወይም የፖለቲካ ድርጅቶች ወይም ደግሞ የሰባዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ብቻ እናደርገዋለን።
ምስጋና አይድረሳቸውና ወያኔዎች “እኩልነትን” በተግባር የሚያሳዩበት ትልቁ ተቋም እስር ቤት ነው። ማንኛውም ስርዓቱን የሚቃዎምም ሆነ ግላዊ አስተያየት ሰጪ ሴት፣ ወንድ፣ ወጣት፣ ጎልማሳ፣ አዛውንት ሳይባል ሁሉም በእኩልነት ስቃይ፣ መከራና እስራት ይጠብቀዋል።ከመተቸት/ ከመቃወም እራሱን እስካልገታ ድረስ የወያኔ የማሰቃያ ቦታዎች በራችውን ከፍተው ዘወትር ይጠባበቃሉ። ወገኖቻችን ለነጻነት ብለው ሲታገሉ፣ ለዲሞክራሲ ብለው ሲደሙ፣ ለእኩልነት ብለው ህይወታቸውን አሳልፈው ሲሰጡ እኛ በምን አገባኝነት ቁመን እናያለን። ይህን እኩይ ተግባር ለማስቆም ህዝብ እንደ ህዝብ በአንድነት ከመናገር ይልቅ ዝምታን ስለመረጠ ለወያኔዎች ጋሻና መከታ ሆኗቸዋል።
ወያኔዎች ለሥልጣን ማራዘሚያ አይነተኛ መሳርያ አድርገው የሚጠቀሙበት የህዝብን ዝምታ ነው። ጸሎት አይሉት ድሎት ህዝብ በአርምሞ ውስጥ ”ተመሰገን ማለት ነው የባሰ እንዳይመጣ መጸለይ ነው“ እያለ እንዲኖር በተለይ የወያኔ ተላላኪ የሀይማኖት መሪዎች ሳይቀሩ ህዝብን ለዝምታ ይገፋፋሉ። ወያኔወችም ዝምታን ለማስፈን በአጽንኦት ይሰራሉ፤ ተሳክቶላቸዋል ማለትም ይቻላል። ወያኔዎች ለክፋትና ለተንኮል፣ ሀገርን ለማጥፋት ህዝብን ለመበደል ያእቀዱትን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚደርስባቸው የለም። ምክንያቱም ሰውን ለመግደልም ሆነ ለማሰቃየት ምንም አይነት ሰባዊ ርህራሄ የሚባል ነገር በውስጣቸው የለምና።
መቼም በዚህ በአለንበት በሰለጠነው ዘመን የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ይበጃል፣ ይጠቅማል፣ ይመጥናል የሚል ህሊና ያለው እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብሎ መገመት ያዳግታል። ሥርዓቱ ከአምባገነናዊነት ባሻገር ብሄራዊ ቀውስ እና የሀገርርን ሉዓላዊነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ፣ የብዙ ንጹኃንን ደም ያፈሰሰ፣ ብዙዎችን ለስደትና እስራት የዳረገ አረመኔያዊ አገዛዝ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃም ይህ የወያኔ እኩይ ተግባር የተገለጠና የተመሰከረለት ነው። ለዚህም መረጃም ማስረጃም እኛው እራሳችን ነን። በዝምታ ውስጥ የማንኖር እና እንደ ሀገር የምናስብ ከሆነ በቀጥታ ማስፈራርያ፣ ዘለፋ፣ እስራትና እንግልት በወያኔዎችና ተላላኪዎች ደርሶብናል፤ እየደረሰብንም እንገኛለን። ነገር ግን ይህ ገደብ የለሽ ማስፈራርያ ለዝምታችን ምክንያት መሆን የለበትም፤ ይልቁንም ለመብት፣ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ እንድንነሳ ግፊት ያደርጋል እንጂ። እውነት ነው ፍርሃት እስኪመስል ድረስ ዝምታችን በእጅጉ በዝቷል፤ የዝምታችንም ውጤት ለወያኔወች አረመኔያዊ ኃይል እንዲያገኙ እና በወገኖቻችን ላይ ሰይጣናዊ ድርጊት እንዲፈጽሙ፣ ጥጋብንና ማንአለብኝነትን እንዲላበሱ እድል ፈጥሮላቸዋል።
እንደሚታወቀው በየአምስት ዓመቱ የይስሙላና የቅርጫ ምርጫ በደረሰ ጊዜ ለሀገርና ለወገን ዴንታ የሌለውን ጥቅመኛ ቡድን ፍትሃዊ ምርጫ ለማስመሰል መራጭ በማድረግ አብዛኛውን ህብረተሰብ ደግሞ በዝምታ እንዲያሳልፍ ይደረጋል። ይህ ሥርዓት ለሀገር የሚበጅ ሥርዓት አይደለምና ይወገድ ብሎ እንዳይናገር “ብንናገር እናልቃለን” የሚለውን የሞኝ ፈሊጥ እንዲያስተጋባ የዝምታ ካባ ይደረብለታል። ምርጫው እንደሆነ የተበላ እቁብ መሆኑ ዓለም በሙሉ ያውቀዋል። በወያኔ “በጎ ፈቃድ” በምርጫ እንዲሳተፉ የተደረጉት ተቀዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችም ምርጫውን ዲሞክራሲያዊ ለማስመሰል ቅመም ወይም ቅባት እንጂ ወያኔ በስልጣን ላይ እያለ መቀመጫ ወንበር አግኝተው ፓርላማውን እንዲቀላቀሉ አይደለም። ውይይት፣ ትችት፣ ማካፈልና አብሮ መስራት የወያኔ ባህሪ አይደለም። 24 ዓመታት የወያኔን ስርዓት በሚገባ አይተናል፤ ባህሪውንም ተረድተናል። “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” እንዳለች አህያ ህዝብና ሀገር ለማጥፋት በአህያ አስተሳሰባቸው ተግተው እየሰሩ ነው።
የተባበሩት የዓለም መንግስታት፣ የአውሮፓ ህብረት፣ ዲሞክራሲን የሚናፍቁ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ግለሰቦች የኢትዮጵያ ምርጫ የይስሙላና ኢ-ፍትሃዊ እንደሆነ ከአለፉት ምርጫዎች ስላረጋገጡ ከመታዘብ እራሳቸውን አቅበዋል። እውነት ነው ለውጥ ለማይመጣ ነገር ገንዘብ፣ ጉልበትና ጊዜ ማቃጠሉ ከንቱ ነው። እኛም በምርጫ ለውጥ እንደማይመጣ በሚገባ እናውቃለን፤ ግን ዝምታችን እስከ መቼ ይዘልቃል? በዝምታስ ለውጥ ማምጣት ይቻላልን? በዝምታ ለውጥ ያመጣ ሀገር በታሪክ አጋጣሚ ተዘግቦ አላየንም። እውነት እላችኋለው “እውነትን እውነት፡ ሀሰትን ሀሰት” እስካላልን ድረስ ለውጥ ሊመጣ በፍጹም አይችልም። ነጻነትን፣ ፍትህንና ለውጥን እኛ እናመጣዋለን እንጂ እራሱ በር አንኳኩቶ ሊመጣ አይችልም።
ጭቆናው ጨምሯል! ሰው በሰውነቱ፣ በኢትዮጵያውነቱ፣ በተግባሩና በሥራው ሳይሆን በማንነቱ፣ በሚናገረው ቋንቋ፣ በተወለደበት አካባቢ ስም እየወጣለት ለስቃይና ለመከራ ይዳረጋል። የሥጋ ቆጠራ ይመስል የዘር ግንዱ እየተመዘዘ፣ የተጸውዖ ስም ሳይቀር እየታየ አድሎ ይደረግበታል። ወያኔን የሚቃረን የፖለቲካ አመለካከት ማንጸባረቅ እንኳ የማይታሰብ ነው። ወያኔዎች የጸረ ሽብር ህጉን ተፈጻሚ የሚያደርጉት በእንዲህ አይነት ሰዎች ላይ ነው። ይህን እያየንም፣ እያወቅንም ዝምታ!
ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማርያን፣ የሰባዊ መብት ተሟጋቾች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ተማሪዎች፣ ነጋዴዎች፣ አርሶ አደሮችና አያሌ ንጹሃን ዜጎች በግፍ ሲታሰሩ፣ ሲሰደዱና ሲገደሉ በዝምታ ከመመልከት በላይ ምን የከፋ ነገር ይኖራል። ፈሪ የሚል ቅጽል ስም ቢወጣልንም ስህተት ነው የማለት የሞራል ድፍረት አይኖረንም። አዎ ብዙዎች በግፍ ሲታሰሩና ሲሰደዱ በዝምታ ተመልክተናል፤ ዛሬም ሰማያዊ ወይም ምዕራባዊ ኃይል እየጠበቅን ይሆን እንጇ ቁመን እያየን ነው። ለውጥ ለሌለው የይስሙላ ምርጫ ጆሮአችንን ሰጠን የወያኔን ተራ የሀሰት ወሬ በዝምታ ውስጥ ሆነን እየሰማን እንገኛለን።
በአጠቃላይ የእኛ ዝምታ ለወያኔች መከታ፣ ስልጣን ማራዘሚያ፣ ሃብት ማካበቻ፣ ድንቁርና፣ ማንአለብኝነት ማጎልበቻ ሲሆናቸው ለሀገራችን ኢትዮጵያ ድህነት፣ ኋላ ቀርነት፣ ለውጭ ዜጎች ገነት ለልጆቿ ሲዎል እንድትሆን ሲያደርጋት ለእኛ ለህዝቧ ደግሞ እስራት፣ ስደት፣ እንግልት፣ መከራ፣ የነጻነትና ፍትህ እጦት፣ የመብት ጥሰት እና ውርደትን እንድናስተናግድ አድርጎናል። እኛ በሌሎች ሀገሮችም ሳይቀር እንደ ሰው እንዳንታይ እና ክብር እንድናጣ ዝምታችን አሉታዊ አስተዋጾ አድርጓል።
ስለዚህ ዝምታን በመስበር “የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውን እንመሰክራለን” እንዲሉ ለሀገር የማይጠቅም ለህዝብ የማይሆን ይህን አረመኔያዊ የወያኔ አገዛዝ ከስር መሰረቱ ማስወገድ ጊዜ የማይሰጠው የቀን ተቀንና የዕለት ተግባር ማድረግ ይገባናል። ሀገር ለባዕድ ስትሸጥ፣ ህዝብ በድህነት ሲሰቃይ፣ ብዙዎች በግፍ ሲሰደዱ፣ ሲታሰሩና ሲገደሉ እያዩ እንዳላዩ፣ እየሰሙ እንዳልሰሙ መሆን የታሪክ ተወቃሽ ያደርጋልና ዝምታ ይብቃ። ሌባን ሌባ ለማለት እንደምንደፍር ሁሉ ወያኔንም የሌቦች፣ የቀማኞችና የወንበደኞች አለቃ ነውና በቃ ከህዝብ ጫንቃ ላይ ውረድ ማለትን እንድፈር።
ከአለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል እንደሚባለው ዝምታን አስወግደው ለነጻነትና ለፍትህ የሚናገሩ ብዙ ኢትዮጵያውያን በተለያየ ቦታ ዝምታ ይብቃ እያሉን ነው። በእስር ቤት ሆነውም ሀገራዊ መንፈሳቸው ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት! እያለ በአደባባይ ይሰብካል። እውነተኛ ኢትዮጵያዊ አንደበታቸው ወያኔን ያሸብራል። ሰውን ያክል ክቡር ፍጡር በእስር እያሰቃዩ ፍትሃዊ ምርጫ እያሉ ማውራት አግባብ እንዳልሆነ በዝዋይ፣ በቃሊቲ፣ በቂሊንጦ፣ በማዕከላዊ፣ በሽዋ ሮቢት እና በሁሉም የማሰቃያ እስር ቤቶች የሚገኙ ውድ ኢትዮጵያውያን ድምጻቸው ያስተጋባል። ለይስሙላ ምርጫ ከመሰለፍ ይልቅ ለነጻነት ተሰለፉ ይሉናል።
ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ግንባታ በርሃ ወርደው ብረት አንግበው የሚታገሉ ወገኖቻችን ኑ በህብረት ወያኔን እናስወግድ፤ ጉልበት ያለህ በጉልበት፣ እውቀት ያለህ በእውቀት፣ ገንዘብ ያለህ በገንዘብ ተደጋግፈን ለተከበረች ኢትዮጵያ እንድረስላት በማለት ሀገራዊ ጥሪ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። ነገር ግን በያለንበት ወያኔን ማሳደድና ማዋከብ ከቻልን ሁላችንም በርሃ መውረድ ላይጠበቅብን ይችላል። በተለይ እኛ ወጣቶች!ጉልበታችንን፣ ኃይላችንንና አቅማችንን ተጠቅመን ወያኔን የምናስወግድበትን ስልት በመንደፍ ከሁልጊዜ ስቃይና መከራ ለተወሰነ ጊዜ ትግል ማድረጉ በእጅጉ የተሻለ ነውና በህብረትና በአንድነት ሀገር የማዳንን ትግል እንቀላቀል። በሀገር ተከብሮና ተዝናንቶ መኖር ሲቻል ስደትን አማራጭ መንገድ በማድረግ ለባህር ቀለብ፣ ለአሸባሪዎች የትንሳኤ በግ፣ ለአረብ የጥጋብ ማስታገሻ መሆን የለብንም። በአጠቃላይ ዝምታን በማስወገድ ህዝብን በማስተባበር ነጻነትን ለማወጅ ቆርጠን እንነሳ እላለሁ።
ዝምታ ይብቃና የወያኔን የይስሙላ ምርጫ በመቃወም ነጻነታችንን ለመጎናጸፍ አማራጭ መንገዶችን እንጠቀም

ኢትዮጵያን ባሰብኳት ግዜ አለቀስኩኝ!!!



ፍቅር እንደ ሻማ የተላበሰች አገር፤ ጀግነትን እንደ ባህል የያዘች አገር፤ ጥበብን ለልጆቿ ስታስተምር የኖረች አገር፤ ፍልስፍናን ለአለም ስትገልጽ የቆየች አገር ፤ በሁሉ ቀዳሚ የሆነች አገር መሆናን በአፍ ሳይሆን በተግባር ገልፃ ያሳየች እንደሆነች እናውቃለን። ፍደልን ቀርፃ ዘመንን ቀምራ የተገኝች ብችኛዋ አፍሪካዊት አገር ፤ ኢትዮጵያ የዜማና የፍልስፍና አስተምሮ የበቀለባት አገር፤ በቀኝ ያልተገዛች ቅኝ ገዢወችን አሳፍራ ያባረረች የአፍሪካ ፈር ቀዳጅ ውዷ አገራችን ኢትዮጵያ ናት። ይሄንን ለመግቢያ ያክል አልኩኝ እንጂ ዛሬ ግን ይህ ሁሉ ክብርና ዝና ሀይልና መፈራት ፍቅርን እና መዋደድን አንድነት እና መስማማትን ከኢትዮጵያ አገሬ ጠፍታል። ለምን ይሆን? ማን ነው አጥፍው? ተጠያቂውስ ማን ይሆን በዚህ ዙርያ ትንሽ ልበል፦

ኢትዮጵያ የሀዘን ካባዋን ደርባ ነጠላዋን አዘቅዝቃ ሀዘን ከተቀመጠች ድፍን 24 አመታትን አስቆጥራለች። ከ24 አመት በፊት ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ የነበሩት መንግስታቶች በህዝብ ላይ አንባገነን ሆነው ከፍተኛ በደል ቢያደርሱም ቅሉ በኢትዮጵያ ጉዳይ ግን አይደራደሩም ነበር። ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከ24 አመት በፊት የምትፈራ የምትከበር ህዝቡም በፍቅር የሚኖርባት ነበረች። አሁን ላይ ግን በዘመነ ወያኔ ዜጎች በማንነነታቸው ከየት አካባቢ ብሄር የመጣኸው/ሽው? እዚህ ለመኖር፣ ለመስራት፣ ለመሳሰሉት የመኖሪያ ፈቃድ አለህ/ሽ ወይ? በሚል ብሄርን ከፋፍሎ መለያ በመስጠት ተከባብሮ የኖረን ህዝብ በትውልድ ሀገሩ እርስ በርሱ እንዲጋጭ እየተደረገ ነው ።
እትዮጵያ ማለት ከአንባገነንም በላይ አንባገነን የነገሰባት የአንድ ዘር የበላይነት የታወጀባት ሆና እርስ በርሳችን እንደንጠላላ የማድረግ ስራ እየተሰራባት ኢትዮጵያ የምትባል አገር በአለም የተናቀች አድርጎ ሕዝባችንን በሃገሩም የተገፋ በስደትም የተናቀ እንዲሆን ሌት ተቀን እየሰሩ ነው።
ከኢትዮጵያ በፊት ዘሬን ላስቀድም የሚል ትውልድ መፍጠር ለዚህም በዘር ከፋፍሎ ለሁሉም ዘር ባንዲራ መስጠት እና ያንን ባንዲራ በየክልሉ እንዲውለበለብ በማድረግ ልዩነት እንዳለን በማስመሰል የእከሌ ዘር ይህንን ባንዲራ የእከሌ ዘር ያንን ባንዲራ ብሎ ከኢትዮጵያዊነት ዝቅ ብሎ ዘር ተራ አውርዶ ዘሩን እንዲያስብ ማድረግ ወያኔ ያመጣው ሰይጣናዊ አመለካከት ነው።
በመሰረቱ ወያኔንም እስከአሁን በስልጣን ላይ ያቆየው የዘር ፖሊሲው ነው ይህ ቁማር ለጊዜው የሚጠቅመው ለወያኔወች ሊሆን ይችላል በሃላ ግን ለልጅ ልጆቹ የማይፋቅ እዳም እያስቀመጠ ያለውም ወያኔ ነው። ክልል ብሎ በከለለው እንኳን ብንሄድ ድንጋያማዋን ትግራይን ይዞ ቁጭ ብሎ የደም እንባ የሚያነባውና የሚራበው ወያኔ ቆሜለታለው የሚለው የራሱ ሰዎች ናቸው። ሌሎቹን ብንመለከት ግን ሰፊ ለም መሬት ሰፊ የውሃ ሃብት አላቸው ዛሬ ደስ ብሎህ የምትንጫጫ የወያኔ ጉጅሌ ሁላ ነገ እንደ ወንዝ የማያባራ እንባህን ትዘራታለህ ሁሉም የእጁን ነው የሚያገኝው እዚህ ላይ ግን በዚህ አካሄድ ላሰምርበት የምፈልገው ብዙ ያልተረጋጉ ሁኔታወች አመኔታ ያላገኙ የክልል ክለላወች እንዳሉ እሙን ነው። ይሄ ነው የኔ፡ እዚህ ድረስ ነው፡ የኔ የሚል እሰጣ ገባ ውስጥ ከወያኔ ውጪ ሌላው ህብረተስብ መግባት እንደሌለበት ለመናገር እወዳለው። አይ የለም መገባት አለበት የሚባል ከሆነ ግን ተመልሰን እንደጋርዮሽ ስረአት ቀድሞ የኔ ቦታ እዚህ ድረስ ነበርና ማስመለስ አለብኝ የኔ ግዛት ትንሽ አንሳለች እና ማስፋፋት አለብኝ ወደሚለው መሄዳችን ግልጽ ነው። በፍቅርና በአንድነት ስንኖር እንኳን ለኛ ኢትዮጵያን ቀርቶ ለአለም የሚተርፍው አገራችንን በይገባኛል ተራን የማይረባ ነገር አገራችንን ሲኦል እንዳናደርጋት አደራ እላለው ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ኢትዮጵያ ጠፈታለች አንድ ዘር ከአንድ ዘር ጋር በጎን እንዲተያዩ እየተደረገ ነው። አንዱ ሃይማኖት ከሌላው ሃይማኖት ጋር ጥላቻ እያስፈኑ ነው። ክልል ድንበር እያለ በኢትዮጵያ ምድር በነፃነት እንዳንቀሳቀስ እያደረጉን ነው። ይህን ሁሉ የኢትዮጵያ ሰላም ያናጋ የኢትዮጵያን ፍቅር ያጠፋ ወያኔ የተባለ የተደራጀ ዘራፊ ሰይጣናዊ ቡድን ነው። ይህንን ዘራፊ ቡድን ባስቀመጠልን የመከራ ክልል ሳንወናበድ፧ ወያኔ በዘረጋው የዘር ከዘር ልዩነት ሳንከፋፍለን፧ ኢትዮጵያን የማዳኑን ስራ የመስራት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ነው። ከወገኔ አንድ ሰው ቢሞትብኝ አልቅሼ የምቀብረው አገር ሲኖር ነው። አገር ከሞተች ግን እንኳን በደስታ መኖር ይቅርና በክብርም መቀበርያ እናጣለን አገር እየገደለ ያለው ወንበዴ ወያኔን ቀድመን ልንገለው ግድ ይለናል።


ኢትዮጵያን ሁሉ ዘር ሳይለያየን ሃይማኖት ሳይከፋፍለን ከዳር እስከዳር እጅ ለእጅ ተያይዘን በደስታ፧ በነፃነት ፧ በእኩልነት፧ የምንኖርባትን አገር ለመመስረት ኢትዮጵያን እየገደላት ያለውን ወያኔ የተባለውን ገዳያን እንግደልላት ከጸጋዋ ተካፍለን በፍቅራ እንድንጠለል ፍቅር አጥፊውን ወያኔን እናጥፋ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44350#sthash.wR7mMRGO.dpuf

አርበኞች ግንቦት 7 – ለሰማዕታቱ አደራ የምንሰጠው ምላሽ ምንድን ነው?

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy

ኢትዮጵያ አንድ ተጨማሪ ወጣት ልጇን አጣች። ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓም ማታ የደብረ ማርቆሱ የሰማያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ኢሰብዓዊ በሆነ ድብደባ ሕይወቱ አልፏል። ይህ ወጣት በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ በጽናት ታግሏል። ለኢትዮጵያ ይበጃል ብሎ ባመነበት መንገድ ተጉዞ ለትግሉ ሕይወቱን ሰጥቷል። ሳሙኤል በሕይወቱ ላይ ያንዣበበውን አደጋ በትክክል ያውቅ ነበር፤ ለህልፈት የዳረገው አደጋ በመድረሱ በፊት ተደጋጋሚ ጥቃቶች ደርሰውበታል፤ ሆኖም ግን ግንባሩን አላጠፈም። በሕይወቱ ላይ ያንዣንበበውን አደጋ ምን ያህል የከፋ ሊሆን እንደሚችል አስቀድሞ በመገመቱ “ከታሠሩኩም ህሊናዬ አይታሰርም፤ ከገደሉኝም ትግሌን አደራ። በተለይ የኔ ትውልድ አደራ!”የሚል ኗሪውን እረፍት የሚነሳ ተማጽኖ በጽሁፍ አስቀምጦ የመጨረሻውን ከፍተኛ ዋጋ ከፍሏል። ለዚህ የሙት አደራ ምላሻችን ምንድነው?
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በወጣት ሳሙኤል አወቀ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፤ ለቤተሰቦቹም መጽናናትን ይመኛል።
ዛሬን እየኖርን ያለነው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከሀቅ ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠናል። እንዴት ነው የሳሙኤል አወቀ እና ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰማዕታት አደራ መወጣት የምንችለው? እንዴት ነው ይህንን የህወሓት ፋሽስታዊ ዘረኛ ሥርዓት ማስወገድና በምትኩ ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነበት፤ የአገር አንድነት የተረጋገጠበት ሥርዓት መገንባት የምንችለው? እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለዚህ ትግል የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ምንድነው? ማንን ነው የምንጠብቀው?
አርበኞች ግንቦት 7 መፍትሔው ሁለገብ ትግል ነው ብሎ ያምናል። ሁለገብ ትግል ደግሞ ሕዝባዊ አመጽንና ሕዝባዊ እምቢተኝነትን አቀናጅቶና አስማምቶ ማራመድን ይጠይቃል። በሁለገብ ትግል እያንዳንዱ ለውጥ ፈላጊ የሚያበረክተው ነገር አለ። ሁለገብ ትግልን የሆነ አካል የሆነ ቦታ እስኪጀምረው መጠበቅ አይገባም፤ እያንዳንዳንችን እንደሁኔታው በየአካባቢያችን ልንጀምረው የምንችለው የትግል ስትራቴጄ ነው። ሁለገብ ትግል በየአካባቢያችን በምስጢር በመደራጀት “እኔም ኃላፊነት አለብኝ” እንድንል የሚያደርግ አሳታፊ የሆነ የትግል ስትራቴጂ ነው። ሁለገብ ትግል ጥቂቶችን ሳይሆን በርካታ ኢትዮጵያዊያን የሚያሳትፍ ሕዝባዊ ትግል ነው።
በየጊዜው በህወሓት ፋሽስቶች ለሚደርስብን በደል ምላሽ መስጠት የሚኖርብን በየአካባቢያችን በምስጢር በመደራጀት ለአምባገነን አገዛዝ ያለን ጥላቻ ስንገልጽ ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከራሱ ይጀምር፤ ለህወሓት አምባገነን አገዛዝ ላለመንበርከክ ቃል ይግባ፤ ከሚመስለው ጋር ይቧደን፤ የትግሉን አቅም ይገንባ፤ በአቅሙ መጠን አምባገነኑን ሥርዓት ይገዳደር። ትግሉ እሆነ ቦታ እስኪጀመር መጠበቁን ትተን በሁሉም ከተሞችና በሁሉም የገጠር መንደሮች በአቅማችን መጠን ትግሉን እናፋፍም። እያንዳንችን ለነፃነታችን ኃላፊነት አለብን። የሰማዕታት አደራ የእያንዳንዳችን አዕምሮ እረፍት ሊነሳ ይገባል። ይህንን ስናደርግ ነው ለሰማዕታቱ አደራ ምላሽ ሰጠን ማለት የምንችለው።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ESAT Special News Samuel Awoke Jun 16 2015 ESAT


የሳሙኤል አወቀ መገደል የነፃነት ትግሉን አያስቆመውም !!



“ለማንኛውም የምከፍለው ዋጋ ለለሃገሬና ለነፃነት ነው፡፡ በአካል ብታሰርም ህሊናዬ አይታሰርም፡፡ ከገደሉኝም ትግሌን አደራ!!! አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትም! ትግላችን የነፃነት፤ ጉዞአችን ጎርባጣ፤ መድረሻችን ነፃነት፤ ታሪካችን ዘላለማዊ ነው፡፡” ሳሙኤል አወቀ ፊስቡክ ገፅ ላይ የተገኘ ሰኔ 8/2ዐዐ7 ዓ.ም፡፡

ምስራቅ ጎጃም ግንደ ወይን 1978 ዓ/ም ተወልዶ – በህግ የዲፕሎማ እና ዲግሪውን ሰርቷል፡፡ ሣሙኤል አወቀ የሠማያዊ ፓርቲ መስራች አባልና ከዚያም በፊት እንደ ሌሎች ጓደኞቹ ከቅንጅት ጀምሮ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ ሲታገል የቆየ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ ነበር፡፡ ሣሙኤል በሙያው የህግ ባለሙያና በጥብቅና ስራ በግል እየሠራ ጎን ለጎን ደግሞ ለአገሩ ከነበረው ፅኑ ፍቅር የተነሣ በሠላማዊ ትግል በማመን ገና በልጅነቱ ትግሉን ተቀላቅሎ በግፍ እስከተገደለ ድረሥ በንቁ የፖለቲካ አመራር ሲታገል ቆይቷል፡፡ ሣሙኤል የሠማያዊ ፓርቲ ከተመሠረተ ጀምሮ በከፍተኛ ኃላፊነት በንቃትና በተደራጀ መልኩ በተወከለበት ቀጠና በምስራቅ ጎጃም ዞን ሲያደራጅና ሲያስተባብር ነበር፡፡

ሳሙኤል አወቀ በአካባቢው ዘንድ የተከበረ እና ምስጉን ወጣት ነበር፡፡ በቅርቡም በተደረገው ሃገራዊ ምርጫ ፓርቲውን ወክሎ የዞኑ የተወካዬች ም/ቤት ጠንካራ ተወዳዳሪ እንደነበር አስመስክሯል፡፡ ሣሙኤል በምሰራቅ ጎጃም አካባቢ እታች አርሦ አደሩ መንደር በመዝለቅ በንቃት ሲያደራጅና ሲያስተባብር የነበረ በየአካባቢው ይደርስ የነበረውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ አስተዳደራዊ ጭቆናና በደል እየተከታተለ ለሕዝብ መረጃ ሲያቀብል እንደነበረ! በተለይም በፓርቲው ልሣን በነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ላይ አምደኛ በመሆን ተከታታይ መረጃዎችን ሲያቀብል የነበረ ጠንካራ የማይበገር ታጋይ እንደነበር ተገንዝበናል፡፡

በትናትናው ዕለት ማለትም ሰኔ 8 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም የወያኔ ኢህአዴግ የፀጥታ ሃይሎች ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ ከሚኖርበት ቤት አጠገብ ደ/ማርቆስ ከተማ ውስጥ እጅግ አሠቃቂ ድብደባ ተፈጽሞበት በግፍ ለተገደለው የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባል ሣሙኤል አወቀ አለም ሃዘናችን ፅኑ፣ መራርና ፈጽሞ ለአፍታም ያህል የማይረሳ የዘመናችን የነፃነት ትግል አርዓያ ዋና ተምሣሌት፣ እንዲሁም ለኢትዮጵያችን እንደቀደሙት ጀግኖች እንደነ አቡነ ጴጥሮስ የታሪክ ባለአደራ የወቅቱ የትግል ጥሪ ፈር ቀዳጅ ጀግናችን ነው፡፡ ለሣሙኤል አወቀ ቤተሰቦች እግዚአብሔር እንዲያፅናናቸው እየተመኘን ዛሬ ሣሙኤል በአካል ከትግል አጋሮቹ ጋር ባይኖርም የሥራው ተምሣሌት ግን ለነፃነት ትግሉ ጉዞ ህያው ሥንቅ ሆኖ ይቀጥላል፡፡

ሣሙኤልን በጥቅም ሣይደለል በኃይል በማስፈራራት ወይም በአካሉ ላይ ድብደባ በመፈጸም ትግሉን ለማስቆም ያልቻሉት የወያኔ ኢህአዴግ ቅልብ ወንጀለኞች በአካሉ ላይ ያደረሱት ጉዳት አልበቃ ብሏቸው በትናትናው ዕለት በስለት ፊቱንና አካሉን በመቆራረጥ ማንነቱን መለየት እስከማይቻል ድረስ በጭካኔ ገድለው ጥለውታል፡፡ ይህ ዓይነቱ የመንግስታዊ አሸባሪነት የመጀመሪያ ሣይሆን በተደጋጋሚ የታዬና አገዛዙ ጠንካራ ተቃዋሚ አመራሮችን በተመሣሣይ ጥቃት ሲያደርስ እንደቆየ ሕዝቡ ያውቃል፡፡ በኢትዮጵያ ተንሠራፍቶ ያለው ኢሰብአዊ አምባገነን ዘረኛ መንግስት በሕዝቡ ላይ በተለይም በተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና በነፃው ኘሬስ አባላት ላይ ከፍተኛ በደሎች ማለትም እስራት፣ ድብደባ፣ግድያና ሁለገብ የሆነ የስነ ልቦና፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሃይማኖታዊ ወንጀል እየፈጸመ ይገኛል፡፡ የሣሙኤል አወቀ የግፍ ግድያ ከላይ እነደተጠቀሰው አገዛዙ ሕዝቡን የሚያጠቃበት መለያ ባህረው አንድ አካል መሆኑን አስረጅ ሊሆን የሚችልና አገዛዙ ምን ያህል በጥላቻ እንደተጠመደና እጅግ አሣሣቢ ደረጀ ላይ መድረሱን ያሣያል፡፡ የወንድማችን የሣሙኤል የግፍ አገዳደል አልበቃ ብሏቸው የአገዛዙ ቅልብ ነፍሰ ገዳዬች በሣሙኤል ቀብር ላይ የተገኙትን ሌሎች አመራር አባላት ከቀብሩ ስነስርዓት ሲመለሱ አግተው አስረዋቸዋል፡፡

ውድ የኢትየጵያ ሕዝብ ሆይ፦

ይህ አይነቱ እጅግ ዘግናኝ በደል ሃዘናችንንና ቁጭታችንን ያባብሰዋል እንጅ ለነፃነት የተጀመረውን መራር ትግል ለአፍታም አያስቆመውም፡፡ በአገርቤትም በውጭም የምንኖር የሠላማዊ ትግል ደጋፊዎችና አራማጆች እንዲሁም መላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የአገዛዙን ሰይጣናዊ ስራ በአንድ ድምፅ ማውገዝና መቃወም ይገባናል፡፡ ዛሬ በሣሙኤል ሞት ልባችን እንደቆሰለ ነገ በሌሎች ሣሙኤሎች ተመሣሣይ ግፍ እንዳይፈጸም ሁላችንም በአንድ ላይ እንነሣ! አገዛዙን በጋራ ታግለን ማስወገድ ይኖርብናል፡፡



ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

እግዚአብሔር የሣሙኤልን ነፍስ በገነት ያኑርልን!- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44456#sthash.gPWji0wf.dpuf

የመላው ኢትዮጵያአንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ፕሬዝደነንት አቶ ማሙሸት አማረ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት ውሎ -

የመላው ኢትዮጵያአንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ፕሬዝደነንት አቶ ማሙሸት አማረ ፍርድ ቤት ከእስር እንዲፈታ ቢወስንም ፓሊስ ሳይፈታው ቀረ ዘሬ ሰኔ 10/10/2007 ዓም በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርቦ በዝግ የታየው ችሎት ማሙሸት አማረ በ5000:00 ዋስ ከእስር ይለቀቅ ቀጣይ ሀምሌ 02/2007 ዓም ይቅረብ ብሎ አዟል እኛም ለዋስትና የተጠየቀውን ገንዘብ ከምሳ በፊት ገንዘቡን አስይዘን የማስፈቻ ወረቀት ብናወጣም ከህግ በላይ የሆነው ፓሊስ ግን ማሙሸትን አለቅም ብሎ ለሁለተኛ ጊዜ የፍርድ ቤት ውሳኔ ሽሮ አስሮታል በዛሬው ችሎት ዋስትና አስይዘው ይዉጡ የተባሉት ሁሉ ሲወጡ ማሙሸት ግን አልወጣም የተጠየቀውን ዋስትና አስይዘን ለምን አይለቀቅም ብለን ላቀረብነው ጥያቄ የተሰጠን መልስ ማሙሸት ይለቀቅ የሚለውን መፈረም የሚችለው ሰው የለም የሱ ጉዳይ የሚመለከታቸ ሠዎች ተመካክረው ነው የሚፈታው የሚል መልስ ሰጥተውናል በትዕዛዙ መሠረት ነገም ተጨማሪ ጥረት እናደርጋለን ፓሊስ እንዳለፈው በእንቢተኝነቱ ከፀና እስከ ሀምሌ 02/2007 ዓም ድረስ በእስር ሊቆይ ይችላል ከዛስ በኋላ ያለው ምን ታውቆ የመላው ኢትዮጵያአንድነትድርጅት ( መኢአድ ) አባላትና ቤተሰቡ ለሁለተና ጊዜ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማመን አቀባበል ለማድረግ የመጣውን ሰው አሳፍረው መልሰውናል ሁኔታው እጅግ አሳዛኝ ነበር ፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44463#sthash.L0cCSJ0k.dpuf



ለእውነት እንዳንታገል አዚም የሆነብን ምንድር ነው? – ዘጠኙ ምክንያቶችን እንሆ -(በይበልጣል ጋሹ -

ስለ እውነት በተግባር እንጂ በቃል ደረጃ ብዙ ማለት ከባድ ቢሆንም ብዙዎች ብዙ ጽፈዋል ተናግረዋል። እውነት ማለት ያዩትን፣ የሰሙትን፣ የሚያውቁትን፣ የተረዱትን፣ የሆኑትን እና የሚያምኑበትን ነገር ሳይጨምሩ ሳይቀንሱ በግልም ሆነ በአደባባይ በይፋ መናገርና መመስከር መቻል እንደሆነ የዘርፉ ሙህራን ያስረዳሉ። በሌላ መልኩ ደግሞ ያላዩትን፣የማያውቁትን፣ ያልሰሙትን፣ ያልሆነን ነገር ሳያረጋግጡ እና የማያምኑበትን ጉዳይ አለመናገር ማለት እንደሆነም አክለው ያስረዳሉ፡፡ በአጭሩ እውነት የሀሰት ተቃራኒ ነው። እውነት ለመናገር፣ ስለ እውነት ለመመስከር በመጀመርያ ሀሰትን መቃወም ይኖርብናል። ስለ እውነት ለመናገር ያልቆሸሸ ንጹህ ሕሊና ሊኖረን ይገባል። ንጹህ ሕሊና እውነተኛ ዳኛ ነውና። ያልተበረዘ፣ያልቆሸሸ እና ንጽህ ሕሊና ሀሰትን የማስተናገድ ባህሪ የለውም።
Tensaye
ሀቀኝነት፣ ታማኝነት፣ እርግጠኛነት፣ ትክክለኛነት፣ ተጠያቂነትን መቀበል እና ሀላፊነትን መወጣት የእውነት መገለጫ ባህሪያት ናቸው። በሌላ አነጋገር እውነት ማለት ጽድቅን ማድረግ፣ መልካም ሥነ ምግባርን መላበስ እና ለነጻነት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ግንባታ መታገል ማለት ነው። እውነት ማለት ሀገር፣ ታሪክ፣ ባህል እና ማንነት ነው። እውነት አድሎ የማይታይበት፣ ርህራሄና ቸርነት በተሞላበት ለሰው ልጅ ሁሉ መልካም ነገር እንዲያገኝ መመኘትና በጎ ተግባራትን ማከናወን ነው። እውነት የሰው ልጅ ዘላቂ ሰላም እና የተረጋጋ ህይወት እንዲያገኝ ከፍተኛ አስትዋጾ ያደርጋል።

ቀደምት አባቶቻችን ስለእውነት ሲሉ ውድ ህይወታቸውን በሰማዕትነት አሳልፈው ሰጠዋል፤ ብዙ መከራና ስቃይ ተቀብለዋል። ለእውነት ሲሉ ከጊዜያዊ ጥቅም ታቅበዋል። ዛሬም ለእውነት ሲሉ ዋጋ እየከፈሉ የሚገኙ እውነተኛ የእውነት ምስክሮች በብዙ ስቃይና መከራ ውስጥ ይገኛሉ። በብዙ ውጣ ውረድ እውነትን መናገር እጅግ መልካምና ልብን የሚያስደስት ቢሆንም እውነትን የሚወዷትን ያህል የሚፈሯትና ከቻሉም በሀሰት ለውጠው ለማጥፋት የሚመኙ ብዙዎች ናቸው፡፡ በተለይ ጥቅምና ስልጣን ፈላጊዎች እንዲሁም አምባገነን መሪዎች በዋናነት ለእውነት መጥፋት ዋነኛ ተዋናኞች ናቸው፡፡
አምባገነን መሪዎች እውነትን መከተልም ሆነ መስማት አይፈልጉም። መነሻቸውና ግብራቸው ሀሰት ስለሆነ እውነትን ፈጽመው አያውቋትም። እርግጥ ነው እውነት ለእነሱ ጠላት ናት፤ ታጠፋቸዋለች። እነርሱ የሀገር መጥፋት፣ የታሪክ መዛባት፣ የህዝብ ሰላምና ደህንነት አያስጨንቃቸውም። ለሥልጣን ማራዘሚያ ሀገር ይሸጣሉ፣ ህዝብን ይጨቁናሉ፣ ይገድላሉም።
በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ነጻነት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ማውራትና መስበክ ወንጀል ከሆነ ዘመናትን አስቆጥሯል። በዚህ ዙርያም ለምን እና እንዴት ብለው የሚጠይቁ ዜጎች እጣ ፈንታቸው እስር፣ እንግልትና ሞት ሆኗል። በኢትዮጵያም ያለው ይህ እውነትን የሚፈራ እና ከእውነት ፈጽሞ የተጣላ የህወሓት አገዛዝ ለሀቅ፣ ለእውነት የቆሙትንና ሕዝብ እውነትን ያውቅ ዘንድ ያለመታከት እየሰሩ የሚገኙ ጋዜጠኞችን፣ ጦማርያንን፣ የፖለቲካ መሪዎችን እና ንጹሃን ዜጎችን ማሳደድና ማሰር ቀጥሎበታል፡፡ በአጠቃላይ ለነጻነት፣ፍትህና ዲሞክራሲ የሚታገሉ ውድ ኢትዮጵያውያንን ወያኔ ማንኛውንም ዋጋ ከፍሎ ወደ ግዞት እንዲወረወሩ ማድረግ፣ መግደልና ማሰቃየት የሥርዓቱ ተቀዳሚ ተግባር አድርጎታል። ወያኔዎች ሰባዊነት የሚባል በውስጣቸው ቅንጣት ስለሌላቸው በነጻነት ታጋይ ኢትዮጵያውያን ላይ የአካልና የሥነ ልቦና አሰቃቂ እና ኢ_ሰባዊ ድርጊት ካለ ምንም ርህራሄ ይፈጽማሉ፤ ዛሬም በመፈጸም ላይ ይገኛሉ።

የወያኔ ፈላጭ ቆራጭ፣ ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ በህብረተሰቡ ላይ የሚያደርሰው ግፍና ሰቆቃ ከመብዛቱ የተነሳ ለእውነት እንዳንቆም እንቅፋት ሆኖብናል። ብዙዎች እውነት መናገር ቢፈልጉም እንዳይናገሩ የተለያዩ አመክንዮ ይሰጣሉ። ከፊሎችም በወያኔ አምባገነን አገዛዝ ተጠልፈው የሥርዓቱ ከዳሚና ደንገጡር በመሆን ከእውነትና ከእራሳቸው ጋር ተጣልተው የሕሊና እስረኞች ሆነው መኖር ጀምረዋል። አብዛኛው ህዝብ ደግሞ ከእውነት ጋር ለመቆም፣ ለእውነት ለመታገል ጊዜና ወቅት በመጣባበቅ ላይ ይገኛል። ብዙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የወያኔን የውንብድና አገዛዝ ተቋቁመው ለእውነት ሲሉ ሰማዕትነትን እየተቀበሉ ይገኛሉ። እውነት ዘላለማዊ ሰላም የምታጎናጽፍ ከመሆኗም በላይ ድልን የምታቀናጅ አሸናፊ ናትና።
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44426#sthash.8JwkWRYC.dpuf

Wednesday, June 17, 2015

የአቢሲኒያ ባንክ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊ ናቸው ተብሎ በኢሕ አዴግ ባለስልጣናት ተፈረጀ -

የትህዴን ድምጽ እንደዘገበው ባህርዳር ከተማ ውስጥ የሚገኙ የአቢሲኒያ ባንክ ቅርጫፍ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊዎች ናችሁ ተብሎው በኢህአዴግ ባለስልጣናት መነገራቸው ተገለጸ። ለዜና ምንጩ በደረሰው መረጃ መሰረት በባህር ዳር ከተማ የኢህአዴግ ባለስልጣን በሆነው በአዲሱ ለገሰ በተደረገው የስብሰባ መሪነት አብዛኛው የአቢሲያ ባንክ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊዎች ናችሁ፤ ከመንግስት ጋር ያላችሁን ችግር በውይይት እንፋታው ብሎ በከፈተው ስብሰባ ላይ የባንኩ ሰራተኞች እኛን የቀጠረን ባንክ የግል ተቋም ነው። ስለዚህ ላንተ የምንሰጠው መልስ የለንም ብንናገርም የሚመጣ ለውጥ የለም በማለት ያለምንም ፍሬ ነገር ሳይግባቡ ከስብሰባው እንደተበተኑ ለማወቅ ተችሏል። በአሁኑ ሰዓት አብዛኛው የመንግስት ሰራተኛ ምንም ዓይነት ወንጀልና ጥፋት ሳይኖረው ስርዓቱ በውስጡ ካለው ያለመተማመንና መጠራጠር ሁኔታ በመነሳት ንፁሃን ዜጎችን እያንገላታና በቂ ማስረጃ ሳያገኝ እያሰቃያቸው እንደሚገኝ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል። ለዘ-ሐበሻ በደረሰው መረጃ መሰረት ደግሞ አቢሲኒያ ባንክ የአማሮች ባንክ ተብሎ በሕወሓቶች ተፈርጇል:: ሕወሓቶች በአሁኑ ወቅት ወጋገን ባንክን እንደራሳቸው ባንክ የሚቆጥሩ ሲሆን አቢሲኒያ ባንክን ለማክሰም የአማሮች ባንክ በሚል ስያሜ እየሰጡ ሰዎችን እንደሚያሸማቅቁ ታውቋል: - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44420#sthash.gm5zEOAh.dpuf

እርዱን ፍረዱልን አንልም፤ በነፃነት ተጋድሎአችን አይግቡብን! – ከጸጋዬ ገብረመድህን አርአያ -

በመካከለኛዉ ምስራቅ ዝነኛ የሆነዉ ጋዜጠኛ ድንቅ የስነጹሁፍ ሰዉም ነዉ። በኮሎኔል ጋማል አብዱልናስር የቅርብ ሰዉነትነትና አማካሪነትም ይታወቃል። ሖስኒ ሙሃመድ ሃይከል እንደዳቦ የሚገመጡ መጻሕፍትን በመጻፉ፥ ከመካከለኛዉ ምስራቅ ባሻገር የእንግሊዝ አንባቢዎቹ የጹሁፎቹ እስረኞች ናቸዉ። አሁንም በጋርዲያን ጋዜጣና በስፔክቴተር መጽሄት የሚወጡ መጣጥፎቹ እንደጆን ላካሬ ልብወለድ መጻሕፍት የሚያማልሉ ናቸው። በእኛ በኩል ከዚህ ደራሲ-ጋዜጠኛ The Sphinx and the Commissar መጽሃፉ በቀልድም በቁም ነገርም የተጠቀሰ አንድ አጭር ‘ኤፒሶድ’ ለመዋስ እንወዳለን። ሐይከል እንደጻፈው ከሰባቱ ቀን የአረቦችና የእስራኤል (1967) ጦርነት ማብቂያ አካባቢ የግብፁ መከላከያ ሚኒስትር ማርሻል ፋዉዚ ሰፋ ያለ የጦር መሳሪያ ሸመታ ሊስት ይዘዉ ወደ ሞስኮ ይሄዳሉ። በክሬምሊን የተቀበሉአቸው የሶቪየቱ የመከላከያ ሚኒስትር ማርሻል ግሬችኮ ነበሩ። በሰባቱ ቀን የሞስኮ ቆይታቸዉ ወቅት እስራኤል ስላወደመችባቸዉ ታንኮች፥ ኤፒሲዎች፥ አውሮፕላኖች – ስለማረከችባቸዉ ስፍር ቁጥር የሌለው የጦር መሳሪያዎች አንስተው እነዚያን እንዴት መተካት እንደሚቻል ሲነጋገሩ ሰንብተዋል። በዉይይቱ ፍጻሜ ላይ ሁለቱ ማርሻሎች ብቻ ሳይሆኑ በሁለቱም ልዑካን ቡድኖች ዉስጥ አባላት የነበሩ የሁለቱም አገሮች ሹማምንት መለኪያ በማጋጨት “ናዝድራቬ ናዝድራቬ” ሲባባሉ ቆይተዉ የሶቪየቱ የመከላከያ ሚኒስትር የማሳረጊያ ንግግር ያደርጋሉ። የፖለቲካ ባህል ስለሆነ የሶቪየት ኅብረት ቀይ ሰራዊት የጀርመን ናዚዎችን እንዴት እንዳሸነፈ፤ አገሩን ብቻ ሳይሆን መላውን ምስራቅ አዉሮፓን ለድል እንዳበቃና ፒፕልስ ዲሞክራሲዎችን እንዴት እንዳቋቋሙ ደሰኮሩ። ከዚያም ማርሻሉ “አሁንም ከግብፅ ሰራዊት ጎን ተሰልፈን ጽዮናውያንን “እንደመስሳለን! እናሸንፋለን!” ብለው መለኪያ አጋጩ። መፈክር ቀረበ፤ ተፎከረ። (የልዑካን ቡድን አባላት ሆናችሁ ወደሞስኮ የሄዳችሁ ሁሉ የተከታተላችሁት ስነ-ስርዓት ሁሉ ተከናወነ። እንደምታዉቁት በስራ ሰአት በቢሮዎች የሚሾመው ቮድካ፥ ኮኛክ፥ ቪኖ ወዘተ ልክ የለዉም። ትንሽ የአካል ጥንካሬ ከሌለዎ የመጠጡ መጠን አለመኖር ሳይታሰብ ጉድ ያፈላል። ለማንኛዉም ፉከራዋም አለች።) - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44435#sthash.J11rbtRp.dpuf

Tuesday, June 16, 2015

ሰማዕት መንግሥቱ ጋሼ – ከወለጋ እስከ ሊቢያ

በእኔ በኩል በሊቢያ ሰማዕታት ጉዳይ ላይ የምጽፈው ማስታወሻዬ ላይ ሌላ ሰማዕት እስካልተገኘ ድረስ ይህ ታሪክ የመጨረሻዬ ነው ብዬ አስባለሁ ※
” ዘ ሐበሻ እና ድሬ ትዩብ የተባሉ ድረገጾችን ሳላመሰግን አላልፍም ። ምክንያቱም እግር በእግር እየተከታተሉ በፌስቡክ ፔጄ ላይ የምጽፈውን የሰማዕታቱን ታሪክ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ አንባቢዎቻቸው መረጃ በማቅረብ የሰማዕታቱ ቤተሰቦች እንዲረዱ ስላደረጉ ከልብ አመሰግናለሁ” ።
መንግሥቱ ጋሼ ሩቅ አልሞ ቅርብ ያደረው ሰማዕት ።
መንግሥቱ ጋሼ ሩቅ አልሞ ቅርብ ያደረው ሰማዕት ።
” በተለይ በየክፍለ ሀገሩ ለማደርገው ጉዞዬ በስዊዘርላንድ በሚኖረው ወንድሜ ጴጥሮስ አሸናፊ አማካኝነት የተዋወቁኳቸው ኢትዮ ዙሪክ የእግር ኳስ አባላትና ደጋፊዎች ፣ በመጨረሻው ጉዞዬ ወንድሜ ዘማሪ ቀሲስ ወንድወሰን በቀለና የሚኒሶታዎቹ አንድነት የሙዚቃ ባንድ አባላት ሙሉ የሆቴልና የትራንስፖርት ፣ እንዲሁም የስልክ ካርድ መሙያ ይሆንሀል ብላችሁ የላካችሁልኝን በአግባቡ ተጠቅሜበታለሁ እናም ምስጋናዬ ካለሁበት ይድረሳችሁ ” ። ይህ ጉዳይ ያለ እናንተ ተሳትፎ የመሳካቱ ነገር አጠራጣሪነቱ ከፍ ያለም ነበር ። ምክንያቱም አሁን እኔ አሁን ባለሁበት ሆኔታ አቅም ኖሮኝ ሁሉንም እንዲህ በተሟላ መልኩ ማቅረብ እችላለሁ ብዬ ማሰቡ ስለሚከብደኝ ማለት ነው ።
ከዚህ በኋላ የሁሉንም የሰማዕታት ቤተሰቦች የመገኛ አድራሻና የባንክ ሒሳብ ጭምር ፖስት ስላደረግሁ ገንዘብንና ሌሎች ጉዳዮችን ከእኔ ጋር ጭምር በትነካኩ ይመረጣል ። አሁን የሰማዕት መንግሥቱ ጋሼን ታሪክ በእርጋታ እንዲያነቡ ልጋብዝዎት ። መልካም ንባብ ።
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44394#sthash.94HuQ3To.dpuf

ምርጫ ማላገጫ (ሰኔ 2007 ዘሀበሻ) – ይገረም አለሙ

      በቅድሚያ የወያኔን ሕገ ወጥና ሞራለ ቢስ እንዲሁም ወራዳና እኩይ ተግባር ሁሉ ተቋቁመው እዚህ በሀገር ቤት ሰላም በሌለበት ሰላማዊ ብለው የህግ የበላይነት በሌለበት ራሳቸውን ህጋዊ አድርገው ለሚታገሉት ፖለቲከኞች አክብሮትም አድናቆትም ያለኝ መሆኑን እገልጻለሁ፡፡ይህ ስሜት ግን ድክመታቸውን ለማየት ስህተታቸውን ለመተቸት የሚጋርድና የሚከለክል መሆን የለበትም፡፡ የሚወዱትና የሚደግፉት ይበልጥ እንዲጎለብት በግልጽና በድፍረት መተቸት፣ ድክመት ስህተትን ማሳየት ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም፡፡ የሚያሳዝነው ለዚህም አልታደልን፡ ከሚጥመን ውጪ ሌላ ለመቀበል ቀርቶ ለመስማት ፍላጎቱ ብዙም የለንም፡፡ ምርጫ አንድም ሕዝብ በድምጹ ያሻውን መርጦ የሥልጣን ባለቤትነቱን የሚያረጋግጥበት፣ አንድም አምባገነኖች ለሕገ ወጥ ሥልጣናቸው ሕጋዊ ካባ የሚያላብሱበት ክንውን ነው፡፡ ምርጫ አስፈጻሚ ተቋም ተቋቁሞ ተወዳዳሪዎች ተሰይመው መራጭ ተመዝግቦ ካርድ ኮሮጆ ውስጥ መክተቱ ብቻ አይደለም የምርጫን እንዴትነት የሚወስነውና ምንነቱን የሚያሳየው፡፡ ከመነሻው የሥልጣን ባለቤቱ ሕዝብ መሆኑን አምኖ፣ የሥልጣን መያዣው አንድና ትክክለኛ መንገድ ምርጫ መሆኑን ተቀብሎ፣ በሕዝብ ውሳኔ ለመገዛት ራስን አዘጋጅቶ፣ የሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ነጻ ተአማኒና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል እንዲሆን ከማድረግ ነው የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥ ትክክለኛ ምርጫ የሚጀምርው፡፡ ወያኔ ከደደቢት ተነስቶ ለአስራ ሰባት ዓመታት ገድሎና ሞቶ ለምኒልክ ቤተ መንግሥት ከበቃ እነሆ ዘንድሮ አምስተኛውን ምርጫ አካሂዷል፡፡ በ1997 ዓም ከተካሄደው ሶስተኛ ምርጫ በስተቀር ሌሎቹ ለውጥ ሊታይባቸው ቀርቶ በሰው አዕምሮ ውስጥ ጥለውት ያለፉት ትውስታ የለም፡፡ አለ ከተባለ የ2002ቱ 99.6 በመቶ ወያኔ አሸናፊ መሆኑ በአንጻሩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ 20 ዓመት ወደ ኋላ መመለሱ ነው፡፡ እንደ ወያኔ በሁለንተናዊ ተግባሩ የህዝብ ድጋፍ የተለየው ፓርቲ ቀርቶ ከፊል የህዝብ ድጋፍ ያለው ፓርቲ እንኳን ቢሆን በተከታታይ አምስት ምርጫ ሊያሸንፍ አይችልም፡፡ የሰው ልጅ ለውጥ መፈለጉ የተፈጥሮ ህግ ነውና የጎደለው እንዲሟላለት፣ ቅር የተሰኘበት እንዲስተካከልለት አለያም በስልጣን ላይ የቆየው ፓርቲ ተምሮ ለወደፊት የተሻለ ሆኖ እንዲቀርብ ወዘተ ሌላ ይመርጣል፡፡ እናም በዴሞክራሲያዊ ሀገራት ሕዝቡ በሚያዝበት የሥልጣን ወንበር ላይ አንዱን ከአንዱ እያፈራረቀ ያያል ይፈትናል፡፡ በኢትዮጵያ ግን ይህ የለም፤ብሎ ብሎ የዘንድሮው ውጤት መቶ በመቶ ወያኔ አሸናፊ የተባለበት ሆኗል፡የሚገርመው በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የወያኔ ተወዳዳሪ ሙሉ ድምጽ አገኘ ሲባል ለሌሎቹ ተወዳዳሪዎች አገኙት ተብሎ የተገለጸው የእያንዳንዳቸው ውጤት ዜሮ በድፍረት ተጽፎ መገለጹ ነው፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ራሳቸውን አልመረጡም ?ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የላቸውም? ወያኔ ሀፍረት ብሎ ነገር አያወቅም እንጂ ይህ ማስተዋል የሌለበት አሳፋሪ የድንቁርና ስራ ነው፡፡ ሲዋሽ ትንሽ እውነት ይዞ ማጭበርበር ሲፈጽም ትንሽ ትንሽ እያስመሰሉ እንጂ እንዲህ ግልጽ ሆኖ የሚታይ እኩይ ስራ አይሰራም፡፡ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ምርጫ ቦርድን ያመሰገኑት በዚህና ለዚህ ተግባሩ ነው፡፡ እስካሁን የተደረጉትን ምርጫዎች (ምርጫ 97ን ትተን) ብንፈትሽ የምናገኘው ምርጫ ማላጋጫ መሆኑን ነው፡፡ ቅንጅቶች በምርጫ 97 ወያኔ የሚያላግጥበትን ምርጫ የምር ምርጫ ለማድረግ በመቻላቸው ሕዝብ የለውጥ ፍላጎቱን በምርጫ ካርዱ አሳይቶ  ወያኔን ላልተዘጋጀበት አይደለም ፈጽሞ ላላሰበው ሽንፈት ሲዳርጉት ብዙዎቹ የወያኔ ሹማምንት ለጭንቅላት በሽታ እንደተዳረጉ ከራሳቸው ጭምር ሰምተናል፡፡ ምርጫ ቃሉን እንኳን ሲሰሙ ያ በሽታቸው ስለሚነሳባቸው ነው በምርጫ ወቅት የሚያቀበጠብጣቸው፡፡ በዛ ታሪካዊ ምርጫ ወያኔ  በእውር ድንብር ህገ ወጥ ተግባር ጉልበት ከሥርዓት ተጠቅሞ በፈጸመው ድርጊት “ሥልጣን ወይም ሞት፣ በጠመንጃ የተገኘ ስልጣን በምርጫ አይነጠቅም፣ በዮሀንስ ዘመን የተፈጸመው የሥልጣን ንጥቂያ በእኛ ዘመን አይደገምም”ወዘተ የሚልና እሱን ከስልጣን ለማንሳት የሚደረገውም ትግል ከባድ መስዋእትነት የሚያስከፍል መሆኑን አሳይቷል፡፡ በጠመንጃ ኃይል ሽንፈቱን ቀልብሶ አሸናፊዎቹን አስሮ ሥልጣኑን ካረጋገጠ በኋላ   ሽንፈት ብሎ ነገር ከዛ በኋላ ላለማየት ለሽንፈት የበቃበትን ምክንያትና መንገድ መርምሮ ምክንያቶቹን አስወግዷል፣ መንገዶቹንም ዘግቷል፡፡ ይህን የማያውቅ ፖለቲከኛ የለም ሊኖርም አይችልም፡፡ ስለሆነም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ወያኔ የሚያካሂደው ምርጫ ማላጋጫ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ ሊኖረው የሚችለው ተፎካካሪ ፖለቲከኞቹ የተዘጋውን አስከፍተው፣ የጠበበውን አስፍተው፣ የተከላውን መልሰው፣ ለእድሜ ማራዘሚያ የሚያዘጋጀውን ምርጫ ለሥልጣን ዘመኑ ማክተሚያ እንዲሆን ለማስቻል በየግል ጠንክረው በጋራም ተባብረው መቅረብ ሲችሉ ብቻ ነው፡፡ ወያኔ ለአሯሯጭነትና ለአጨብጫቢነት የፈጠራቸውንና ምርጫ ቦርድም ይህን ያህል ፓርቲ ተወዳድሯል ለማለት እንዲያስችለው የፓርቲነት መስፈርት ሳያሟሉ(አቶ በረከት በመጽኃፉ የቤተሰብ ፓርቲ ያላቸው) ፓርቲ እያለ እየደገፈ ያስቀመጣቸውንና ወያኔ እስትንፋስ የሚሰጣቸውን ትተን  ሕዝብ የሚያውቃቸውና እውቅና የሰጣቸውን ፓርቲዎች ብንወስድ በዘንድሮው ምርጫ አንዳቸውም ለሥልጣን የሚያበቃ የዕጩ ተወዳዳሪ ብዛት አላቀረቡም፡፡ይህን ሲያውቁ የአቅማቸውን ውስንነት ሲረዱ ደግሞ ተመካክረውና ተጋግዘው ሊቀርቡ ሲገባ ይህንንም ማድረግ አልቻሉም፡፡ እንደውም በተግባር የሚታየው  እያንዳንዳቸው ከወያኔ ጋር ከሚፎካከሩት በላይ ርስ በርሳቸው የሚፎካከሩ መሆኑ ነው፡፡ የምኒልክን ቤተ መንግሥት ሁሉም ይመኙታል ግን ሁሉም ያጡታል፡፡ ከዚህ አንጻር ካየነውና ከማለባበስ ወጥተን በእውነት ስለ እውነት ከተነጋገርን ምርጫውን ማላገጫ ያደረገው ወያኔ ብቻ ሳይሆን አጅበው ያዘለቁት  ተዋሚዎችም ናቸው ለማለት ያሰደፍራል፡፡ በምርጫ መወዳደር በራሱ ግብ አይደለም፡፡ የምርጫ ሰሞን ብቅ ብሎ ሆይ ሆይ ማለትም በቂ የፖለቲካ ሥራ አይደለም፡፡ የፖለቲካ ስራውም ሆነ የምርጫ ውድድሩ ምርጫን ምርጫ ለማድረግና አሸንፎ የመንግሥትን ሥልጣን ለመረከብ ካልሆነም በቂ ወንበር አግኝቶ ፓርላማውን የአንድ ፓርቲ መፈንጫ ከመሆን ለማላቀቅ የሚያስችል መሆን ይኖርበታል፡፡ 547 መቀመጫ ላለው የተወካዮች ምክር ቤት ቁጥራቸው ከ200 ያልዘለለ ዕጩዎችን ይዞ ምርጫ መግባትና እናሸንፋለን ብሎ መፎከር አለያም የምርጫው ውጤት አስቀድሞ የታወቀ ነው እያሉ ማላዘን  ምርጫን ማላገጫ ማድረግ እንጂ ምን ይባላል፡፡ እንግዲህ ልብ እንበል፣በየግል ተወዳድሮ ለማሸነፍ የሚያስችል አቅም የላቸውም፡፡ይህን ተረድተው ከግል የሥልጣን ጥም ተላቀው ተባብረው ለምርጫ የሚቀርቡ አይደሉም፡፡ የሥልጣን መና ቢወርድላቸው ተስማምተው ይሄ ለአንተ ይሄ ለእኔ ብለው ስልጣን ተጋርተው መንግስት ለመመስረት የሚያስችል ቁመናም ባህርይም አይታይባቸውም፡፡ታዲያ ምን ሊሆኑ ወደ ምርጫ ገቡ? እነርሱም እንደ ወያኔ በምርጫው ሊያላግጡ? የሚያሳዝነው የፖለቲካ መሪዎቹ በሚያላግጡበት ምርጫ ለእስር ለስደት ለሞትና ለእንግልት የሚዳረገው ዜጋ ነው፡፡ ወያኔ በሥልጣን ከሚቀጥል የምንችለውን ሁሉ እናድርግ ብለው ከልብ ወስነው በቁርጠኝነት ቢነሱ ምርጫ የወያኔ ማላገጫ እንዳይሆን ማድረግ በቻሉ ነበር፡፡ እያንዳንዱን የወያኔ ሴራ እያጋለጡና የተንኮል ስራውን እያመከኑ ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማንበርከክ ባይቻላቻው ከማን አለብኝነት አይን አውጣ ስራ ሊያቅቡት በተቻላቸው ነበር፡፡ አንዱ ሲጠቃ ሌላው እልል እያለ፤አንዱ ከጨዋታ ውጪ ሲደረግ ሌላው ሜዳው የሰፋለት ያህል እየቆጠረ፣የአንዱ ዕጩ ሲሰረዝ ሌላው እሰይ እያለ ወዘተ ወያኔ የሚያላግጥበትን ምርጫ የምር ምርጫ ማድረግ አይቻልም፡፡ በሌላ በሌላው መተባበር ቢቀር ምርጫው የወያኔ ማላገጫ እንዳይሆን ለማድረግ  የጋራ እቅድ ነድፎ ተባብሮ መስራት ይጠይቃል ፡፡ ከፖለቲከኞቻችን አድራጎት የምናያውና ከየንግግራቸው የምንረዳው ግን ከእነርሱ ሌላ ተቀዋሚ ከሚያሸንፍ ወያኔ ቢቀጥል የሚመርጡ መሆናቸውን ነው፡፡ ታዲያ እነዚህ ከወያኔ ባልተናነሰ ምርጫን ማላገጫ ያደረጉ ናቸው ቢባል እውነትን ላለመቀበል ማንገራገር ካልሆነ በስተቀር የሚያከራክር ይሆናል? የተቃውሞ ፖለቲካ መሪነት ሥልጣን ሆኖ በውስጣቸው ርስ በርስ ይታመሳሉ፤ፓርቲ ከፓርቲ ይናቆራሉ፤ባይናቆሩም ፍቅር የላቸውም፤አብረው ሲሆኑም ሆነ ተለያይተው በቃላት ሲሸናቆጡ በቂ ምክንያት የላቸውም፡፡ በዚህ አቋምና ቁመናቸው ምርጫ እያሉ ከወያኔ ባልተናነሰ በምርጫ ያላግጣሉ፡፡ምንግዜም የማይረሳውን ምርጫ 97 ብንወስድ አራት ፓርቲዎች ቅንጅት ፈጥረው አንድ ሆነው ለምርጫ ቀረቡ፡፡ እኛ ስንዋደድ እግዜሩም ይረዳልና ያልታሰበ የምርጫ ምልክት ሁለት ጣት ሰጣቸው፤ልጅ አዋቂ ሳይል የቅንጅት መንፈስ ሰረጸበት፡፡ ምርጫ ቦርድ ሰባ ሰማኒያ ፓርቲዎች አሉ ሲል ሕዝብ በድምጹ የሚጠራው በምልክት የሚያሳየው ቅንጅትን ብቻ ሆነ፡፡ከዛ ቀጥሎ በተለይ በኦሮሚያና በደቡብ አንዳንድ ቦታዎች ህብረት፡፡ እነዚህ ሁለቱ ፓርቲዎች ደግሞ የምርጫ ሂደታቸውን አቀናጅተው በጋራ መግለጫ ከመስጠት አድማ እስከ መጥራት ደረሱ፡፡ እናም ምርጫውን ከወያኔ ማላገጫነት ወደ ትክክለኛ ምርጫነት ቀይረው ለአሸናፊነት በቁ፡፡ መጨረሻው አሳዛኝና አሳፋሪ ቢሆንም፡፡ ዛሬ መተባበሩ ቀርቶ የምርጫውን እንከን ለማሳየት እንኳን በጋራ መግለጫ መስጠት የሚችሉ ፓርቲዎች አላየንም፣ አልሰማንም፡፡ ታዲያ በየግል በቂ ዝግጅት አድርገው በበቂ ቁጥር ዕጩ አቅርበው ታዛቢ አዘጋጅተው የወያኔን ማጭበርበሪያ መንገዶች ለመዝጋት ወይንም በአቋራጭ ለማለፍ ስልት ነድፈው ለውድድር ካልቀረቡ፤ወይ ደግሞ አቅማቸውን ገምተው ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሀኒቱ ብለው ተባብረው ካልሰሩ፡ምርጫ ስለተባለ ብቻ ወደ ምርጫ በመግባት የወያኔ አድማቂ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ ከሌላቸው ምርጫውን ከወያኔ ባልተናነሰ ማላገጫ አድርገውታል ከማለት ሌላ ምን ሊባል ይቻላል፡፡ ሕዝቡ በወያኔ አገዛዝ ተማሯል፣እናም ለውጥ ይፈልጋል፣ይህንንም አሳይቷል፡፡ወያኔ በሕግና በሥርዓት አይደለም በጠመንጃም መግዛት የማይችልበት ደረጃ ቢደርስም ምርጫ 97ን እያስታወሰና እየቃዠ የዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንገዶችን ሁሉ ዘግቶ  በስመ ምርጫ   የአገዛዝ ዘመኑን እያደሰ ቀጥሏል፡፡ ተቀዋሚዎች ደግሞ በተናጠል አይጠነክሩ ወይ ተባብረው አይሰሩ የወያኔን የማላገጫ ምርጫ እያደመቁ ለአገዛዝ ዘመኑ መራዘም ቡራኬ ይሰጣሉ፡፡ ከሁለት ያጣ የሆነው ሕዝቡ ነው፤ የሥልጣን ባለቤትነቱን የሚያረጋግጥለት ቀርቶ ሰዋዊ ክብሩን የሚያከብር የሚያስከብርለት መንግሥት አላገኘ፤ወይንም ከአምባገነን አገዛዝ የሚያላቅቀው ታግሎ የሚያታግለው መርቶ ወደ ለድል የሚያበቃው ተቀዋሚ/ተቀዋሚዎች አላገኘ ፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44405#sthash.pkH02yvd.dpuf






election

አስር አለቃ ጫላ ጋዲሳ ራሱን አጠፋ

ትህዴን ባሰራጨው ዘገባ ለሃምሌ ወር 2007 ዓ/ም የቆይታ ጊዜአቸውን ጨርሰው በሚገኙ የሰራዊት አባላት ላይ እየተካሄደ ባለው የከፋ የዘረኝነት ምልመላ ምክንያት አንድ የኦሮሞ ተወላጅ የሆነ የአስር አለቃ ማዓረግ አይገባህም በመባሉ የተነስ እራሱን እንዳጠፋ ተገለፀ። ለትህዴን በደረሰው መረጃ መሰረት- የ23ኛ ክፍለ ጦር የ2ኛ ሬጅመንት በ3ኛ ሃይል ውስጥ የቲም ምክትል አዛዥ የነበረ አስር አለቃ ጫላ ጋዲሳ የተባለው ወታደር በተለያዩ መድረኮች ላይ ተቃራኒ የሆነ ሃሳቦችን ያቀርባል ለህገ መንግስቱ ታማኝ አይደለም መንግስትን ያማርራል የሚሉ ነጥቦችን አስቀምጠው ማዕረግ አይገባህም ተብሎ ከሃይል አመራር በላይ ያሉ አዛዦች ውሳኔውን በማስተላለፋቸው ምክንያት ስሜቱ የተጎዳው ይህ ወታደር ስብሰባው እንዳለቀ ዋርዲያ ነኝ በሎ በመውጣት እራሱን እንዳጠፋ ከእዙ የደረሰን መረጃ አመለከተ። በአሁኑ ጊዜ በኢህአዴግ የሰራዊት አባላት ውስጥ ያለው የከፋ የዘረኝነት አድሎዎ ለማዕረግ እድገትና ለተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ሲባል በሚደረጉ ምልመላዎች ላይ የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች በሰራዊት ውስጥ ኢ- ፍትሃዊ የሆነ አሰራር እየሰሩ መሆናቸውን በተለያዩ የሰራዊት እዞች ውስጥ የሚገኙ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ ያስረዳል ሲል ትህዴን መረጃውን ቋጭቷል:: - 

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የክስ መቃወሚያ አቀረቡ * ብርሃኑ “እንዴት ማረሚያ ቤቱን ትከሳለህ” ተብሎ ወረቀቱን ተነጥቋል -

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር መንግስት የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን ተሻግረው ኤርትራ የሚገኘውንና በተወካዮች ም/ቤት በሽበርተኝነት የተፈረጀውን የግንቦት ሰባት ወታደራዊ ክንፍ ሊቀላቀሉ ሲሉ በጸጥታ ኃይሎች ማይካድራ ላይ በቁጥጥር ስር አውያቸዋለሁ ያላቸው እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያቸውን አስገቡ፡፡ ዛሬ ሰኔ 9/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የቀረቡት በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የክስ መዝገብ የተካተቱት አራት ተከሳሾች ማለትም፣ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማውና ደሴ ካህሳይ በጋራ ያዘጋጁትን የክስ መቃወሚያ አስገብተዋል፡፡ አራቱ ተከሳሾች ጠበቃ ማቆም አንፈልግም በማለታቸው ያለጠበቃ የቀረቡ ሲሆን፣ ተከሳሾቹ በክስ መቃወሚያቸው ላይ ሁለት አብይት ነጥቦችን በመጥቀስ ክሱ ውድቅ ተደርጎ በነጻ እንዲሰናበቱ ጠይቀዋል፡፡ ተከሳሾቹ በክስ መቃወሚያቸው ላይ እንደጠቀሱት አቃቤ ህግ ያቀረበባቸው ክስ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጣረስና (ጸረ-ሽብር አዋጁ ከህገ መንግስቱ ጋር እንደሚጣረስ በመጥቀስ) በወ/መ/ሥ/ሥ/ህጉ መሰረት ያልቀረበ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ እንደ ህጉ ያልቀረበን ክስ ውድቅ በማድረግ በነጻ ያሰናብተን ብለዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች የቀረበው አቤቱታ ላይ አቃቤ ህግ መልስ እንዲሰጥ በሚል ለሰኔ 19/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በሌላ በኩል አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በተደጋጋሚ በእስር ቤት በሚደርስበት በደል ላይ አቤቱታ ማሰማቱን ቀጥሏል፡፡ በዚህም ፍርድ ቤቱ አቶ ብርሃኑ አለኝ የሚለውን አቤቱታ በጽሑፍ እንዲያቀርብ አዝዞ የነበር ቢሆንም አቶ ብርሃኑ የማዘጋጀውን አቤቱታ ‹‹እንዴት ማረሚያ ቤቱን ትከሳለህ›› በሚል ጽሑፉን እየተነጠቀ እንደሆነ በመግለጽ አቤቱታውን በጽሑፍ ማቅረብ እንዳልቻለ አስረድቷል፡፡ ይህን የአቶ ብርሃኑን አቤቱታ በተመለከተ የማረሚያ ቤቱ ተወካይ ችሎት ፊት እንዲቀርቡ ተደርገው ‹‹ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያለውን አቤቱታ እንዲያቀርብ አዝዘናል፤ ስለዚህ እናንተ መልስ ካላችሁ መልሳችሁን እንቀበላለን፣ አሁን ግን ተከሳሹ የሚያዘጋጀውን አቤቱታ እንዲያቀርብ አድርጉ›› በማለት በፍርድ ቤቱ ተነግሯቸዋል፡፡ በመሆኑም አቶ ብርሃኑ በቀጣዩ ቀጠሮ በእስር ቤት አያያዝ ላይ ያለውን አቤቱታ በጽሑፍ ይዞ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44414#sthash.wjF99pVv.dpuf

የሰማያዊ ፓርቲ የፓርላማ እጩ ተወዳዳሪ ሳሙኤል አወቀ ተገደለ

Samuel Aweke
"በመጨረሻም ተገደለ በቅርብ ከማውቃቸው ቆፍጣና: ሀገሩን ከምንም በላይ በማስቀደም የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ሊታገልላት ቆርጦ በመነሳት ምስክርነቴን ከምሰጣቸው ወጣት ታጋዮች አንዱ ነበር:: ለቃለመጠይቅም ሆነ መረጃ ፍለጋ በደወልኩለት ጊዜ ሁሉ በልዩ የሀገር ፍቅር ስሜት ትብብር በማድረግ የስርዓቱን ግፍና ጭካኔ በማጋለጥ ግዴታውን በሚገባ እየተወጣ የነበረ ብረት የሆነ ወጣት:: ደበደቡት: አሰሩት: በአካሉ ላይ የሚችሉትንና የሚፈልጉትን ሁሉ ጉዳት አደረሱበት:: ሳሙኤል ካመነበት ንቅንቅ የሚል አልነበረም:: በመጨረሻም የወጣትነት ህይወቱን አጠፉት:: ታጋይ ይሞታል:: ትግል ግን........ሳሙኤል ነፍስ ይማር!" - ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን
“በመጨረሻም ተገደለ
በቅርብ ከማውቃቸው ቆፍጣና: ሀገሩን ከምንም በላይ በማስቀደም የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ሊታገልላት ቆርጦ በመነሳት ምስክርነቴን ከምሰጣቸው ወጣት ታጋዮች አንዱ ነበር:: ለቃለመጠይቅም ሆነ መረጃ ፍለጋ በደወልኩለት ጊዜ ሁሉ በልዩ የሀገር ፍቅር ስሜት ትብብር በማድረግ የስርዓቱን ግፍና ጭካኔ በማጋለጥ ግዴታውን በሚገባ እየተወጣ የነበረ ብረት የሆነ ወጣት:: ደበደቡት: አሰሩት: በአካሉ ላይ የሚችሉትንና የሚፈልጉትን ሁሉ ጉዳት አደረሱበት:: ሳሙኤል ካመነበት ንቅንቅ የሚል አልነበረም:: በመጨረሻም የወጣትነት ህይወቱን አጠፉት:: ታጋይ ይሞታል:: ትግል ግን……..ሳሙኤል ነፍስ ይማር!” – ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን
  ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ እንደዘገበው የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፀኃፊና በ2007 ዓ.ም ምርጫ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው ወጣት ሳሙኤል አወቀ ተገደለ፡፡ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ትናንት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ቤቱ እየገባ በነበረበት ወቅት በሁለት ግለሰቦች ከፍተኛ ድብዳባ ከተፈፀመበት በኋላ ሆስፒታል ውስጥ ነፍሱ አልፋለች፡፡
 ወጣት ሳሙኤል ከቀድሞው አንድነት ጀምሮ ሲታገል የቆየ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲ መስራች አባል ነው፡፡ በአካባቢው የሚፈፀሙ በደሎችን ለሚዲያ በማጋለጥ ሲያበርክተው ከነበረው ሚና ባሻገር በፓርቲው በነበረው ጠንካራ እንቅስቃሴ ምክንያት በተደጋጋሚ እስርና ድብደባ ተፈፅሞበታል፡፡
የወጣቱን ግድያ ተከትሎ የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ አዘጋጅ ጌታቸው ሽፈራው በፌስቡክ ገጹ የሚከተለውን አስፍሯል:: እንደወረደ ይኸው:-
ሳሙኤል ይህ አረመኔያዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት ያውቅ ነበር፡፡ ግን ትግል ነውና ወደኋላ አላለም፡፡ ከሳምንታት በፊት እግሩን ሰብረውታል፡፡ ከዛ በፊት በተደጋጋሚ ታስሯል፡፡ ህዝብ በዳኞች ላይ ተማርሮ የጻፈውን የህዝብ አስተያየት አንተ ነህ የጻፍከው ተብሎ ታስሯል፡፡ እንደሚገድሉት ዝተውበታል፡፡ ይህ ሁሉ አልሆንላቸው ሲል ከሀገር እንዲወጣ ወትውተውታል፡፡ እሱ ግን እስከ ትናንትናዋ ማታ ድረስ ፀንቶ ቆይቷል!
ከሁለት ሳምንት በፊት ደግሞ በፌስቡክ ገጹ እኔን ቢገድሉኝም እናነተ ግን ፅኑ ብሎ አደራውን አስተላልፎ ነበር፡፡
samuel aweke lem
ውድ የደብረማርቆስ ከተማ ኗሪዎች!
ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ከ25’0000 በላይ መራጮች(ኮረጆውን) እርሱት እና በተጨማሪም በ31 ዩኒቨርስቲ የምትገኙ ከ14,000 በላይ ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ሌሎች ደጋፊዎች እና የኢሕአዴግ አባላትም የማያፍረው ብአዴን / ኢሕአዴግ ድምፅ መቀማቱ ሳያንስ በ21/08/2007 ዓም አፍነው ደብድበው ከሞት መትረፌ ቆጭቷቸው እሰር ቤት ለመወርወር ያለመከሰስ መብቴን እንኳን ተዳፍረው የሀሰት ክሰ እየፈጠሩ ነው!
በስልኬ እደተደወለም ያለፍላጎቴ ደሕንነት እያስገደደኝ ይገኛል፡፡
ተገደልሁም፣ ታሠርሁም፣ ታፈንኩም ነፃነት አይቀርም እና ለማሰረጃነት የደሕንነቶችን ስም፤ ፎቶግራፍ ፤ እና አድራሻ እንዲሁም በሐሠት ምሰክርነት እና ከሳሽነት የተደራጁ አካላት እና ዋና ተወካዮች የደብረማርቆስ ከተማ 04 ቀበሌ አመራሮች እና ፖሊስ ለታሪክ አሰመዘግባለሁ፡፡ ማንኛውም የምከፍለው ዋጋ ለሀገሬ እና ለነፃነት ነው፡፡ ከታሠርሁም ሕሊናዬ አይታሰርም ከገደሉኝም ትግሌን አደራ በተለይ የኔ ትውልድ አደራ! አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትም! ትግላችን የነፃነት ጉዟችን ጎርባጣ መድረሻችን ነፃነት ታሪካችን ዘላለማዊ ነው!
(ከሳሙኤል አወቀ ዓለም –
የሰማያዊ ፓርቲ የደብረ ማርቆስ የሕዝብ ተወካዮች እጩ ተወ

Monday, June 15, 2015

የሕወሓት መንግስት የአማራውን ክልል ሕዝብ በዘይትና ስኳር አቅርቦት እየቀጣው ነው

“አማራውን ምንም ብናደርግለት አይደግፈንም:: የአባይን ጉዳይ አንስተን እንኳ ዞር ብሎ አያየንም” በሚል በሕወሓት መንግስት የተፈረጀው አማራ ክልልን መንግስት በዘይትና ስኳር አቅርቦት እየቀጣው መሆኑ ተዘገበ:: በአማራ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች ከፍተኛ የዘይትና የስኳር አቅርቦት ችግር መኖሩን ነዋሪው ህዝብ በተደጋጋሚ አቤቱታ እያቀረበ ምላሽ ሊያገኝ አለመቻሉንም የደህሚት ድምጽ ዘግቧል:: በመረጃው መሰረት በአማራ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች የስኳርና የዘይት አቅርቦት ከፍተኛ የሆነ ችግር ያጋጠመ ሲሆን ነዋሪው ህዝብ በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርብም ምንም ዓይነት ምላሽ ሊያገኝ አለመቻሉን የገለፀው መረጃው በተለይ በክልሉ የፍኖተ ሰላምና የባህርዳር ልዩ ዞን ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም አንዳንድ የዙሪያ ወረዳ ከተሞች ለችግሩ ተጠቂ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ገልፀው ከየከተሞቹ ከንቲባዎችና የሚመለከታቸው አካላት ግን የማይጨበጥ ተስፋ ከመስጠት በስተቀር ምንም አስቸኳይ መፍትሄ ሊያደርጉ አለመቻላቸውን ገልጿል። መረጃው ጨምሮም በሁሉም ዞኖች እንደአማራጭ በሚል በተመሳሳይ የቀረቡ ውስን የዘይትና የስኳር አቅርቦቶች የሚከፋፈሉት ለብአዴን ኢህአዴግ ቅርበት ባላቸው ካቢኔዎች ሱቅ ለድርጂት አባላቶች እንዲከፋፈል በመደረጉ በተቃዋሚነት አይን የሚታዩ በርካታ ዜጎችና ድሃ ወገኖች የችግሩ ተጎጂ መሆናቸውን አብራቷል። እስካሁን ድረስ በመራቤቴ አካባቢም “ምንም ብናደርግለት ሕዝቡ ስርዓቱን አይደግፍም” በሚል የምንም ዓይነት የልማት ተጠቃሚ እንዳልሆነ ይታወቃል:: የአማራው ክልል በእንደዚህ ዓይነት አይን ያወጣ መልካም አስተዳደር እጦት መሰቃየት ሕዝቡ በስር ዓቱ ላይ ያለውን ጥላቻ በየቀኑ እያሳደገው ይገኛል:: - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44217#sthash.zzJ038F1.dpuf

ኢትዮጵያውያንን የገደለው አይሲኤስን ለማውገዝ ስልፍ በመውጣቱ የታሰረው አቶ ዳዊት አስራደ ለሶስተኛ ጊዜ የዋስትና ገንዘብ ከፍሎ ታሰረ

እስካሁን 36 ሺህ ብር ከፍሏል የቀድመው አንድነት አመራር አቶ ዳዊት አስራደ ትናንት ግንቦት 3/2007 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ በ5000 ብር ዋስ እንዲፈታ ዋስትና የተፈቀደለት ቢሆንም ገንዘቡን ካስያዘ በኋላ ዋስትናው እንደተነሳ ተነግሮት በእስር ላይ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡ በትናንትናው ችሎት ፖሊስ ተከሳሾቹ ምስክሮችን ያባብሉብኛል በሚል ምስክሮችና መረጃዎችን አሰባስቦ እስኪያቀርብ ጊዜ ድረስ 14 ቀን እንዲሰጠው ጠይቆ የነበር ቢሆንም አቶ ዳዊት አስራደ፣ አቶ አለነ ማህፀንቱና ወይዘሪት ሜሮን አለማየሁ የ5000 ብር ደሞዝ ያለው የሰው ዋስ ወይንም ገንዘብ አስይዘው ከእስር እንዲወጡ ፈቅዶ ነበር፡፡ ይሁንና የአቶ ዳዊት አስራደ ቤተሰቦች መፍቻ ይዘው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) ሲሄዱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) ፖሊስ አቶ ዳዊትን ለቄራ ፖሊስ ጣቢያ ማስረከቡን እንደገለጸላቸው ጠበቃው አቶ ገበየሁ ይርዳው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የቄራ ፖሊስ ጣቢያም ከአሁን ቀደም አቶ ዳዊት አስራደ በተመሳሳይ ክስ ተፈቅዶለት የነበረውን ዋስትና ማንሳቱን በመግለጽ እንዳሰረው ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ በተፈቀደለት ዋስትና መሰረት 5000 ብር ያስያዘውን አቶ አለነ ማህፀንቱን ፖሊስ መጀመሪያ ወደ ማታ እፈታዋለሁ፣ እንዲሁም ከቆይታ በኋላ ይግባኝ እጠይቃለሁ ብሎ እስር ላይ ቢያቆየውም አሁንም ድረስ ይግባኝ ሳይጠይቅ በእስር ላይ እንደሚገኝ ጠበቃው ገልፀዋል፡፡ መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰረው አቶ ዳዊት አስራዳ በተመሳሳይ ክስ ለሶስተኛ ጊዜ የዋስትና ገንዘብ እያስያዘ እንደገና በእስር ላይ የቆየ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ 25 ሺህ፣ በቀጣይነትም 6 ሺህ፣ እንዲሁም በትናንትናው ዕለት 5 ሺህ ብር በአጠቃላይ 36 ሺህ ብር ዋስትና አስይዞ እንደገና ታስሯል፡፡ አቶ ዳዊት አስራደና ወይዘሪት ሜሮን አለማየሁ ሚያዝያ 14 መንግስት ላይ በተነሳው ተቃውሞ ሰበብ በአንድ ጉዳይ ሁለት ክስ ተመስርቶባቸው በሁለት ፍርድ ቤቶች ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል፡፡ በቄራና ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያም በፈረቃ ሲታሰሩ ቆይተዋል፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44246#sthash.qmWJayKo.dpuf

ይድረስ ስለ አንዳርጋቸው – አብዩ በለው ጌታሁን

andargachew Tisge           እነ ጀነራል ተፈራ ማሞ በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተጠርጥረው በህወሃት የማሰቃያ ጉድጓድ ከተጣሉ እነሆ የዳግሚያ ስቅለት 6ኛ አመታቸው አለፈ ፡፡ ታዲያ በዚያን ሰሞን ነበር፡-
1ኛ. ጀነራሎቹ እንዴት በህወሃት የስለላ ወጥመድ ውስጥ ሊወድቁ ቻሉ?
2ኛ. ስህተቱ በማንና ምን ላይ ተሰራ? ከመካከላቸው ለህወሃት ያደረ ይኖር ይሆን? ወዘተ የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ያለማቋረጥ አስተናግድ የነበረው፡፡
እነሆ ዛሬ እነዚህን መሰል ወሳኝና ፈታኝ ጥያቄዎች ለድርጅታዊ ወይም ለግልፅ ህዝባዊ ውይይት ቀርበው ምላሽ ሳያገኙና የእርምት እርምጃ ሳይወሰድባቸው ስድስት የድብት አመታት አለፉና ዛሬም ሌላ ዙር ክሽፈት፣ ሌላ ዙር አስጨናቂ ጥያቄና፣ ሌላ ዙር መራር መርዶ ለማስተናገድ የተገደድን ይመስለኛል፡፡
በአንፃሩ ደግሞ ዛሬ በህወሃት የማሰቃያ ጉድጓድ ውስጥ የተጣለው የግንቦት 7ቱ አቶ አንዳርጋቸው ባይሆን ኖሮ ከላይ የገለፅኳቸውን ተመሳሳይ ጥያቄዎች ከስድስት አመታት በኃላ ወደ ማን ይዥጎደጉዳቸው ነበር? ብዬ መጠየቄ አልቀረም፡፡ ለምን ቢሉ እነሆ ያ! ብርቱ ጠያቂዬ ዛሬ ሊጠየቅለት ተረኛ ሆኗልና ተጠያቂነቱን ለባለተራዎቹ እነሆ በረከት እላለሁ፡፡
ዛሬ ድረስ በህወሃት አረመኔያዊ የማሰቃያ ዘዴዎች ለሚሰቃዩት ለእነ ጀነራል ተፈራ ማሞ እና ጓዶቹ  መታሰቢያ ትሁንልኝ፡፡
መልካም ንባብ
ለነፃነታችን፣ ለፍትህና፣ ለዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ መገንባት ከህወሃት በተፃፃሪ ተሰልፈን ለምንታገል ሁሉ፤ መቼም ቢሆን ፀፀቱ ለማይለቀን ስህተትና ውድቀት ስንዳረግ፣ ህወሃትንና የስለላ ቡድኑን ምትሃታዊ አድርጎ ማቅረብና ውንጀላውንም ሆነ ተጠያቂነቱን ወደ አንድ ጥግ መግፋት የሚያዋጣና ከተጠያቂነት የሚያድን የብልሆች መንገድ አልመስልህ ካለኝና የ“ቀስት” መንገድ ከተኮላሸ እነሆ አስርት አመታት፤ የእነ ጀ/ል አሳምረው ፅጌ ጉዞ ከከሸፈ ደግሞ ድፍን ስድስት አመታት እንደዋዛ ነጎዱ፡፡
ፈላስፋው “ታሪክ እራሱን ደገመ፣ መጀመሪያ አሳዛኝ ቀጥሎ ቧልት በሚመስል መንገድ” እንዳለው ሁሉ የእነ ጀነራል ተፈራ ማሞ በህወሃት ወጥመድ ውስጥ የወደቁበትን አሳዛኝ እውነታ ለማወቅና የጥፋቱን ቋጠሮ ለመፍታት እንዲያ በእልህና በቁጭት ተውጦ የጥያቄ ናዳ ሲያወርድብኝ የነበረው አይታክቴው የፅጌ ልጅ ዛሬ ለህወሃት ቧልት በሚመስል መልኩ በዚያው ወጥመድ ተጠልፎ ሲሰቃይ ማየት በእጅጉ ያማል፡፡
ይህ ብርቱ ፀፀትና ህመም የሚጠግገውና የህወሃትን የጠለፋ ቡድን ከአስማተኛነት ወደ ወጀድ ጠባቂነት ማውረድ የሚቻለው፣ ከአቶ አንዳርጋቸው መጠለፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ውስጣዊና ውጫዊ ጉዳዮች ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው ሁኔታ በመመርመር፣ የተፈፀሙትን ስህተቶች ነቅሶ በማውጣት የማያዳግም የእርምት እርምጃ መውሰድ ሲቻል ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
ለዚህም ይረዳ ዘንድ በተለይም፡-
1ኛ. ድርጅታቸው ግንቦት 7 ለፍትህና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ (የአሁኑ አርበኞች ግንቦት 7) ፣
2ኛ. የህዝብ አይንና ጆሮ የሆናችሁት የእኔው ኢሳት፣ አዲስ ድምፅ ሬዲዮና፣ ሁላችሁም ነፃና የህዝብ ሚዲያዎቻችን በሙሉ፣
3ኛ. የህወሃትን ሸፍጥ በማጋለጥ የምትተጉና ለእውነት ዘብ የቆማችሁ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች፣ በተለይም ጓዴ አበበ ገላው፣
እናንተ ሁላችሁ ኃላፊነትና ተጠያቂነትን አያጣችሁምና ቅድሚያውን በመውሰድ የየበኩላችሁን ጥረትና ምርመራ በማድረግ የደረሳችሁበትን እውነት ወገኖቹን ከወያኔ መንጋጋ ነፃ ለማውጣት ሌት ከቀን ለሚባዝነው ወገናችሁ የማሳወቅና መጭውንም አደጋ ከወዲሁ የመከላከል ታላቅ ኃላፊነትና አደራ አለባችሁ የሚል ፅኑ እምነት ስለአለኝ፤
ይልቁንም አበው “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” እንዲሉ፡-
እግረ-መንገዳችንም ህወሃት መራሹን ዘራፊ ቡድንና የሚዲያ ተቋማቱን ከምንወቅስበት የግልፅነትና የተጠያቂነት በሽታ ይልቁንም “ከልማታዊ ጋዜጠኝነት” እራሳችንን እያፀዳንና ለዚህ ክስረት አስተዋፅኦ ያደረጉና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አካላት የድርሻቸውን በማንሳት ለህዝባቸው ያላቸውን ታማኝነትና ተጠያቂነት ማረጋገጥ ቢችሉ እሰዬው ነው፡፡
1ኛ. አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በህወሃት የስለላ ወጥመድ ውስጥ እንዴት ሊወድቁ ቻሉ?
እርግጠኛ መሆን አይቻል እንደሆን እንጂ ይህ ጥያቄ የሁሉንም ነፃነት ናፋቂና ታጋይ ኢትዮጵያዊ ህሊና በእጅጉ የሚሞግት ይመስለኛል፡፡ በተለይም ለቀጣዩ የትግል ጉዞ ትምህርት ሊሆኑ የሚችሉ፣ የህወሃትን አስማተኛነት የሚያረክስ፣ ሁሉም በህወሃትና አጋሮቹ የስለላ መረቦች ላይ በሩን አጥብቆ እንዲዘጋ የሚረዱ ቅርቃሮች ለማግኘት በሚያግዙ ተጠየቆች ላይ ትኩረት ይሰጣል የሚል ፅኑ እምነት አለኝ፡፡
የአቶ አንዳርጋቸው የየመን ጉዞ የስህተቶች ሁሉ ድምር ውጤት መቋጫ/መዳረሻ ሊሆን ይችል እንደሆን እንጂ ዋናው ስህተትና የመጀመሪያው መጨረሻ ቀደም ብሎ እንደተሰራ መገመት አያዳግትም፡፡ ከዚህም በመነሳት የፅጌን ልጅ ለክፉው አሳልፎ ሊሰጣቸው የቻለው ስህተት የትኛው/ኞቹ ነበር/ሩ?  ብሎ መጠየቅ ተገቢና ወቅታዊ ይመስለኛል፡፡
ይልቁንም አቶ አንዳርጋቸው ከማንም በተሻለ ሁኔታ የህወሃትና የአጋሮቹን የስለላ መዋቅርና አሰራር ጠንቅቀው የሚያውቁና በተለይም የየመንን መንግስትና በወቅቱ የነበረውን የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ ተንትነው የሚያስረዱ እንደሆኑ ለማመሳከር ወደ ኢሳት ማህደር ጎራ ማለቱ ከበቂ በላይ ይመስለኛል፡፡ በተለይም ይህን የህውሃት አፋኝ ቡድን ተግባራት ጠንቅቆ የሚያውቀው የግንቦት 7 “የስለላ ክንፍ” የመሪውን እንቅስቃሴና ደህንነት እንዴት ነበር የሚከታተለው? የድርጅቱ መሪ በባላንጣው የአፈና ወጥመድ እንዴት ሊታፈኑ ቻሉ? ተቀዳሚ ጥያቄዎቼ ናቸው፡፡
2ኛ. ለመታፈናቸው እነማን አስተዋፅኦ አደረጉ? ተጠያቂዎቹስ? (የወደቀችውን የመን አንድ ብያለሁ)
ሁሌም እንደሚባለውና እንደሚታመነው፣ ለህወሃት መራሹ ዘራፊ ቡድን ጡንቻ መፈርጠምና እድሜ መራዘም ከእራሱ ከህወሃትና ከግብረ-አበሮቹ ጥንካሬ ይልቅ ለነፃነት፣ ለአንድነትና፣ ለዲሞክራሲ መከበር የምንታገል ግለሰቦችና ሃይላት ድክመት ትልቁንና ዋናውን ድርሻ እንደሚይዝ ተብሎ ተብሎ ያለቀለት ጉዳይ ነው፡፡
በተለይም ተጠያቂነትንና ግልፅነትንም በተመለከተ ህወሃት ከበርሃ ጀምሮ ለሚፈፅማቸው መራር ግፍና ወንጀሎች እነሆ ዛሬም ይከሰሳል፡፡ ይወቀሳል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ባለፉት 24 ዓመታት ብቻ ለተለያዩ ድርጅቶች፣ ጥምረቶች፣ ህብረቶችና፣ ቅንጅቶች መፍረስ፣ ለታጋዩ መበታተንና፣ ለነፃነት ናፋቂ ወገናችን ቅስም መሰበር አስተዋፅኦ ያደረጉና ሂደቱንም የመሩ ሁሉ ግልፅ በሆነ መንገድ ሂሳባቸውን ሳያወራርዱና ይመሩት ለነበረው ድርጅትና ህዝብ ያላቸውን ተጠያቂነት ሳያረጋግጡ ከአንዱ ወደ ሌላኛው መገለባበጣቸው ምን ያህል ትግሉን እንደጎዳውና ህወሃትን እንዳፈረጠመው በተግባር አሳይቶናል፡፡
ዛሬ ዛሬ በነፃነት ታጋዩ በኩል ለሚፈፀሙ ተመሳሳይ ክህደቶች፣ ወንጀሎችና፣ ጥፋቶች እንደ አይነታቸውና መጠናቸው ተጠያቂው አካል ተለይቶ ሊታወቅ፣ ተገቢውን የእርምት እርምጃም በወቅቱ ሊወሰድና፣ ውጤቱ እንደ አስፈላጊነቱ ለታጋዩና ለሰፊው ህዝብ ሊገለጥ ይገባል የሚለው አስተሳሰብና እምነት ገዥ ሃሳብ እየሆነ የመጣ ይመስለኛል፡፡ የመሻላችን አንዱና ዋነኛው መገለጫ ግልፅነትና ተጠያቂነት ካልሆነ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? ደርግ ክፍል ሶስትን በላያችን ላይ ለማንገስ?
ይልቁንም በሃገርቤት በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የቆረጡትን ንፁሃን ታጋዮች በማን አለብኝነት እያፈነ፣ በውስጡ ሆነው የተቃወሙትንና ለህሊናቸው ለመቆም የተውተረተሩትን መዋጥ ስላልበቃው፤ ይኃው የሞተው እባብ እኛው ባፈረጠምናቸው ክንዶቹ ባህር ተሻግሮና ድንበሮችን አቆራርጦ በሱደንና በኬንያ ስንገረም የመን ደርሷል፡፡
ህወሃት የመን ድረስ ተጉዞ አቶ አንዳርጋቸውን ሲያፍን በወቅቱ የነበረው የየመን ብልሹና የተፍረከረከ አስተዳደር ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚታወቅና ግልፅ ነው፡፡ ነገር ግን ሌሎች አካላት አስተዋፅኦ አላደረጉም ብሎ ማሰብ ግን ለእኔ አልተቻለኝም፡፡ ጥፋቱንም ሁሉ ህወሃትና የመን ላይ የሚጠፈጥፍ ግለሰብም ሆነ ተቋም ካለ፣ እርሱ በቀደመውና ህወሃት በመጣበት ሁሉንም ጥፋት “አማራ”ና “ደርግ” ላይ የመለጠፍ የሸፍጥና የማንአለብኝነት ጎዳና መሄድን የመረጠ ብቻ ይመስለኛል፡፡
ስለዚህም፡-
ለአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በህወሃት የአፈና ቡድን መጠለፍ አስተዋፅኦ ያደረጉ ሁኔታዎች ምንና ምን ናቸው? ተጠያቂ አካላትስ እነማን ናቸው? ድርጅታቸው ግንቦት 7 እና አመራሩስ ምን ያህሉን ድርሻ ይወስዳሉ? የኤርትራው ሰውዬስ አይመለከታቸው ይሆን? ወዘተ  . . . በማለት አቶ አንዳርጋቸውን አክዬ ስለ አቶ አንዳርጋቸው ድምፄን ከፍ አድርጌ ለመጠየቅ እገደዳለሁ፡፡
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44270#sthash.TZXqgkhK.dpuf