የመላው ኢትዮጵያአንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ፕሬዝደነንት አቶ ማሙሸት አማረ ፍርድ ቤት ከእስር እንዲፈታ ቢወስንም ፓሊስ ሳይፈታው ቀረ ዘሬ ሰኔ 10/10/2007 ዓም በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርቦ በዝግ የታየው ችሎት ማሙሸት አማረ በ5000:00 ዋስ ከእስር ይለቀቅ ቀጣይ ሀምሌ 02/2007 ዓም ይቅረብ ብሎ አዟል እኛም ለዋስትና የተጠየቀውን ገንዘብ ከምሳ በፊት ገንዘቡን አስይዘን የማስፈቻ ወረቀት ብናወጣም ከህግ በላይ የሆነው ፓሊስ ግን ማሙሸትን አለቅም ብሎ ለሁለተኛ ጊዜ የፍርድ ቤት ውሳኔ ሽሮ አስሮታል በዛሬው ችሎት ዋስትና አስይዘው ይዉጡ የተባሉት ሁሉ ሲወጡ ማሙሸት ግን አልወጣም የተጠየቀውን ዋስትና አስይዘን ለምን አይለቀቅም ብለን ላቀረብነው ጥያቄ የተሰጠን መልስ ማሙሸት ይለቀቅ የሚለውን መፈረም የሚችለው ሰው የለም የሱ ጉዳይ የሚመለከታቸ ሠዎች ተመካክረው ነው የሚፈታው የሚል መልስ ሰጥተውናል በትዕዛዙ መሠረት ነገም ተጨማሪ ጥረት እናደርጋለን ፓሊስ እንዳለፈው በእንቢተኝነቱ ከፀና እስከ ሀምሌ 02/2007 ዓም ድረስ በእስር ሊቆይ ይችላል ከዛስ በኋላ ያለው ምን ታውቆ የመላው ኢትዮጵያአንድነትድርጅት ( መኢአድ ) አባላትና ቤተሰቡ ለሁለተና ጊዜ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማመን አቀባበል ለማድረግ የመጣውን ሰው አሳፍረው መልሰውናል ሁኔታው እጅግ አሳዛኝ ነበር ፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44463#sthash.L0cCSJ0k.dpuf
No comments:
Post a Comment