Monday, June 15, 2015

በደ/ብሥራት ቅ/ገብርኤል: ሰበካ ጉባኤውን በማዳከም በካህናት እና ምእመናን ላይ ግፍ የፈጸሙት አለቃ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ ተጠየቀ

bisrate-gabriel-church00የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን: በልማት ስም ከጥቅመኛ ግለሰቦች ጋር በመመሳጠር የቤተ ክርስቲያንን ሀብት እና ንብረት ለግሉ በማካበት በሚታወቀው የቀድሞው አለቃ ኃይሌ ኣብርሃ፥ በግንባታ እንዲኹም የባለቤትነት እና የተጠቃሚነት መብቱን አሳልፈው በሚሰጡ የኪራይ ውሎች ከመመዝበሩም በላይየሚልዮኖች የባንክ ባለዕዳ አድርጎት ያለተጠያቂነት ለመሰል ዘረፋ ወደ ሌላ ደብር ተዘዋውሯል፡፡
በእግሩ የተተኩት ግብታዊው እና ዐምባገነኑ መልአከ ብርሃን ዘመንፈስ ቅዱስ (የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ አባት)፥ በቃለ ዐዋዲው ደንቡ መሠረት በሰበካ ጉባኤው ሙሉ ተሳታፊ የኾኑትን እና የወሳኝነት ድርሻ ያላቸውን የማኅበረ ካህናት፣ የማኅበረ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮችን በማሳደድ እና ከልጃቸው ጋር ተማክረው ሥልጣን በሌለው የክፍለ ከተማው የሰው ኃይል አስተዳደር ሓላፊ በኩል ወደ ሌላ አድባራት በማዘዋወር ሀብቱንና ይዞታውን ከሚነጥቁ ቀማኞች ጋር እየሠሩ ነው፡፡
* * *
  • በአለቃው ከሰበካ ጉባኤው የተባረረው የማኅበረ ምእመናን ተወካዩ እና የሰንበት ት/ቤቱ አባሉ ዲ/ን ሰሎሞን የኋላሸት ‹‹ወረቀት በትኗል፤ አድማ አነሣስቷል›› በሚል በአለቃው ጥያቄ ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ በእስር ላይ ነው
  • በጥፋታቸው ስለሚቃወሟቸው፣ በዋና ሥራ አስኪያጁ ልጃቸው ተመክተው በግፍ ያዘዋወሯቸው ካህናት በሳምንት ጊዜ ውስጥ እንዲመለሱ፤ ሰበካ ጉባኤውም እንደ ቃለ ዐዋዲ ደንቡ በተሟሉ ተወካዮች እንዲጠናከር ምእመናኑ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል
  • በደብሩ የጠበልተኞች ማደርያ የኾነው ቦታ እንዲከበር የሚጠይቁትን የጠበል ዕድርተኞች ፊት በመንሳት ለግለሰብተላልፎ እንዲሰጥ እየተባበሩ ነው
  • በሰበካ ጉባኤው የሰንበት ት/ቤቱ ተወካይ በመልቀቁ በሌላ እንዲተካ ሰንበት ት/ቤቱ ለወራት ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም
  • ምክትል አስተዳዳሪ በሚል ተቀምጦ ቀድሞ ደብሩን ለመዘበረው ኃይሌ ኣብርሃ መረጃ የሚያቀብለው ግለሰብ ተጨማሪ ምእመናንን በጥቆማ ለማሳሰር እየሠራ ነው
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44384#sthash.VPi7LCfL.dpuf

No comments:

Post a Comment