ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ እንደዘገበው የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፀኃፊና በ2007 ዓ.ም ምርጫ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው ወጣት ሳሙኤል አወቀ ተገደለ፡፡ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ትናንት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ቤቱ እየገባ በነበረበት ወቅት በሁለት ግለሰቦች ከፍተኛ ድብዳባ ከተፈፀመበት በኋላ ሆስፒታል ውስጥ ነፍሱ አልፋለች፡፡
ወጣት ሳሙኤል ከቀድሞው አንድነት ጀምሮ ሲታገል የቆየ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲ መስራች አባል ነው፡፡ በአካባቢው የሚፈፀሙ በደሎችን ለሚዲያ በማጋለጥ ሲያበርክተው ከነበረው ሚና ባሻገር በፓርቲው በነበረው ጠንካራ እንቅስቃሴ ምክንያት በተደጋጋሚ እስርና ድብደባ ተፈፅሞበታል፡፡
የወጣቱን ግድያ ተከትሎ የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ አዘጋጅ ጌታቸው ሽፈራው በፌስቡክ ገጹ የሚከተለውን አስፍሯል:: እንደወረደ ይኸው:-
ሳሙኤል ይህ አረመኔያዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት ያውቅ ነበር፡፡ ግን ትግል ነውና ወደኋላ አላለም፡፡ ከሳምንታት በፊት እግሩን ሰብረውታል፡፡ ከዛ በፊት በተደጋጋሚ ታስሯል፡፡ ህዝብ በዳኞች ላይ ተማርሮ የጻፈውን የህዝብ አስተያየት አንተ ነህ የጻፍከው ተብሎ ታስሯል፡፡ እንደሚገድሉት ዝተውበታል፡፡ ይህ ሁሉ አልሆንላቸው ሲል ከሀገር እንዲወጣ ወትውተውታል፡፡ እሱ ግን እስከ ትናንትናዋ ማታ ድረስ ፀንቶ ቆይቷል!
ከሁለት ሳምንት በፊት ደግሞ በፌስቡክ ገጹ እኔን ቢገድሉኝም እናነተ ግን ፅኑ ብሎ አደራውን አስተላልፎ ነበር፡፡
ውድ የደብረማርቆስ ከተማ ኗሪዎች!ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ከ25’0000 በላይ መራጮች(ኮረጆውን) እርሱት እና በተጨማሪም በ31 ዩኒቨርስቲ የምትገኙ ከ14,000 በላይ ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ሌሎች ደጋፊዎች እና የኢሕአዴግ አባላትም የማያፍረው ብአዴን / ኢሕአዴግ ድምፅ መቀማቱ ሳያንስ በ21/08/2007 ዓም አፍነው ደብድበው ከሞት መትረፌ ቆጭቷቸው እሰር ቤት ለመወርወር ያለመከሰስ መብቴን እንኳን ተዳፍረው የሀሰት ክሰ እየፈጠሩ ነው!በስልኬ እደተደወለም ያለፍላጎቴ ደሕንነት እያስገደደኝ ይገኛል፡፡ተገደልሁም፣ ታሠርሁም፣ ታፈንኩም ነፃነት አይቀርም እና ለማሰረጃነት የደሕንነቶችን ስም፤ ፎቶግራፍ ፤ እና አድራሻ እንዲሁም በሐሠት ምሰክርነት እና ከሳሽነት የተደራጁ አካላት እና ዋና ተወካዮች የደብረማርቆስ ከተማ 04 ቀበሌ አመራሮች እና ፖሊስ ለታሪክ አሰመዘግባለሁ፡፡ ማንኛውም የምከፍለው ዋጋ ለሀገሬ እና ለነፃነት ነው፡፡ ከታሠርሁም ሕሊናዬ አይታሰርም ከገደሉኝም ትግሌን አደራ በተለይ የኔ ትውልድ አደራ! አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትም! ትግላችን የነፃነት ጉዟችን ጎርባጣ መድረሻችን ነፃነት ታሪካችን ዘላለማዊ ነው!(ከሳሙኤል አወቀ ዓለም –የሰማያዊ ፓርቲ የደብረ ማርቆስ የሕዝብ ተወካዮች እጩ ተወ
No comments:
Post a Comment