Wednesday, June 17, 2015

እርዱን ፍረዱልን አንልም፤ በነፃነት ተጋድሎአችን አይግቡብን! – ከጸጋዬ ገብረመድህን አርአያ -

በመካከለኛዉ ምስራቅ ዝነኛ የሆነዉ ጋዜጠኛ ድንቅ የስነጹሁፍ ሰዉም ነዉ። በኮሎኔል ጋማል አብዱልናስር የቅርብ ሰዉነትነትና አማካሪነትም ይታወቃል። ሖስኒ ሙሃመድ ሃይከል እንደዳቦ የሚገመጡ መጻሕፍትን በመጻፉ፥ ከመካከለኛዉ ምስራቅ ባሻገር የእንግሊዝ አንባቢዎቹ የጹሁፎቹ እስረኞች ናቸዉ። አሁንም በጋርዲያን ጋዜጣና በስፔክቴተር መጽሄት የሚወጡ መጣጥፎቹ እንደጆን ላካሬ ልብወለድ መጻሕፍት የሚያማልሉ ናቸው። በእኛ በኩል ከዚህ ደራሲ-ጋዜጠኛ The Sphinx and the Commissar መጽሃፉ በቀልድም በቁም ነገርም የተጠቀሰ አንድ አጭር ‘ኤፒሶድ’ ለመዋስ እንወዳለን። ሐይከል እንደጻፈው ከሰባቱ ቀን የአረቦችና የእስራኤል (1967) ጦርነት ማብቂያ አካባቢ የግብፁ መከላከያ ሚኒስትር ማርሻል ፋዉዚ ሰፋ ያለ የጦር መሳሪያ ሸመታ ሊስት ይዘዉ ወደ ሞስኮ ይሄዳሉ። በክሬምሊን የተቀበሉአቸው የሶቪየቱ የመከላከያ ሚኒስትር ማርሻል ግሬችኮ ነበሩ። በሰባቱ ቀን የሞስኮ ቆይታቸዉ ወቅት እስራኤል ስላወደመችባቸዉ ታንኮች፥ ኤፒሲዎች፥ አውሮፕላኖች – ስለማረከችባቸዉ ስፍር ቁጥር የሌለው የጦር መሳሪያዎች አንስተው እነዚያን እንዴት መተካት እንደሚቻል ሲነጋገሩ ሰንብተዋል። በዉይይቱ ፍጻሜ ላይ ሁለቱ ማርሻሎች ብቻ ሳይሆኑ በሁለቱም ልዑካን ቡድኖች ዉስጥ አባላት የነበሩ የሁለቱም አገሮች ሹማምንት መለኪያ በማጋጨት “ናዝድራቬ ናዝድራቬ” ሲባባሉ ቆይተዉ የሶቪየቱ የመከላከያ ሚኒስትር የማሳረጊያ ንግግር ያደርጋሉ። የፖለቲካ ባህል ስለሆነ የሶቪየት ኅብረት ቀይ ሰራዊት የጀርመን ናዚዎችን እንዴት እንዳሸነፈ፤ አገሩን ብቻ ሳይሆን መላውን ምስራቅ አዉሮፓን ለድል እንዳበቃና ፒፕልስ ዲሞክራሲዎችን እንዴት እንዳቋቋሙ ደሰኮሩ። ከዚያም ማርሻሉ “አሁንም ከግብፅ ሰራዊት ጎን ተሰልፈን ጽዮናውያንን “እንደመስሳለን! እናሸንፋለን!” ብለው መለኪያ አጋጩ። መፈክር ቀረበ፤ ተፎከረ። (የልዑካን ቡድን አባላት ሆናችሁ ወደሞስኮ የሄዳችሁ ሁሉ የተከታተላችሁት ስነ-ስርዓት ሁሉ ተከናወነ። እንደምታዉቁት በስራ ሰአት በቢሮዎች የሚሾመው ቮድካ፥ ኮኛክ፥ ቪኖ ወዘተ ልክ የለዉም። ትንሽ የአካል ጥንካሬ ከሌለዎ የመጠጡ መጠን አለመኖር ሳይታሰብ ጉድ ያፈላል። ለማንኛዉም ፉከራዋም አለች።) - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44435#sthash.J11rbtRp.dpuf

No comments:

Post a Comment