Monday, June 15, 2015

የሕወሓት መንግስት የአማራውን ክልል ሕዝብ በዘይትና ስኳር አቅርቦት እየቀጣው ነው

“አማራውን ምንም ብናደርግለት አይደግፈንም:: የአባይን ጉዳይ አንስተን እንኳ ዞር ብሎ አያየንም” በሚል በሕወሓት መንግስት የተፈረጀው አማራ ክልልን መንግስት በዘይትና ስኳር አቅርቦት እየቀጣው መሆኑ ተዘገበ:: በአማራ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች ከፍተኛ የዘይትና የስኳር አቅርቦት ችግር መኖሩን ነዋሪው ህዝብ በተደጋጋሚ አቤቱታ እያቀረበ ምላሽ ሊያገኝ አለመቻሉንም የደህሚት ድምጽ ዘግቧል:: በመረጃው መሰረት በአማራ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች የስኳርና የዘይት አቅርቦት ከፍተኛ የሆነ ችግር ያጋጠመ ሲሆን ነዋሪው ህዝብ በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርብም ምንም ዓይነት ምላሽ ሊያገኝ አለመቻሉን የገለፀው መረጃው በተለይ በክልሉ የፍኖተ ሰላምና የባህርዳር ልዩ ዞን ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም አንዳንድ የዙሪያ ወረዳ ከተሞች ለችግሩ ተጠቂ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ገልፀው ከየከተሞቹ ከንቲባዎችና የሚመለከታቸው አካላት ግን የማይጨበጥ ተስፋ ከመስጠት በስተቀር ምንም አስቸኳይ መፍትሄ ሊያደርጉ አለመቻላቸውን ገልጿል። መረጃው ጨምሮም በሁሉም ዞኖች እንደአማራጭ በሚል በተመሳሳይ የቀረቡ ውስን የዘይትና የስኳር አቅርቦቶች የሚከፋፈሉት ለብአዴን ኢህአዴግ ቅርበት ባላቸው ካቢኔዎች ሱቅ ለድርጂት አባላቶች እንዲከፋፈል በመደረጉ በተቃዋሚነት አይን የሚታዩ በርካታ ዜጎችና ድሃ ወገኖች የችግሩ ተጎጂ መሆናቸውን አብራቷል። እስካሁን ድረስ በመራቤቴ አካባቢም “ምንም ብናደርግለት ሕዝቡ ስርዓቱን አይደግፍም” በሚል የምንም ዓይነት የልማት ተጠቃሚ እንዳልሆነ ይታወቃል:: የአማራው ክልል በእንደዚህ ዓይነት አይን ያወጣ መልካም አስተዳደር እጦት መሰቃየት ሕዝቡ በስር ዓቱ ላይ ያለውን ጥላቻ በየቀኑ እያሳደገው ይገኛል:: - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44217#sthash.zzJ038F1.dpuf

No comments:

Post a Comment